23 days ago
ኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን በጀግኖች አቀባበል ወደ ሀገሩ ተመለሰ
#ethiopia | በ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ታሪካዊ ጉዞ በማድረግ የዓለም የእግር ኳስ አፍቃሪዎችን ያስደነቀው የኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን፣ ወደ አገሩ ሲመለስ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች የጀግና አቀባበል አደረጉለት።
የኖርዌይ ባንዲራዎች በየስፍራው ሲውለበለቡ፣ የድጋፍ ዝማሬና ጭብጨባ በመታጀብ ተጫዋቾቹና የአሰልጣኝ ቡድኑ ከሀገራቸው ህዝብ ልዩ ክብር ተቀበለዋል።
በኮከብ ተጫዋች ኤርሊንግ ሃላንድ የተመራው ቡድን በውድድሩ ያሳየው ጠንካራ አቋም፣ አንድነትና ጽናት በኖርዌይ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ እንደከፈተ ተገልጿል።
ይህ አቀባበል የውጤት ብቻ ሳይሆን የብሔራዊ ኩራት፣ የተስፋ እና የአንድነት ምልክት ሆኖ ተከብሯል። ብዙ ደጋፊዎችም ይህ ትውልድ ለኖርዌይ እግር ኳስ ብሩህ የወደፊት ተስፋ እንደሰጠ ገልጸዋል።
እርስዎ ምን ያስባሉ?
የ2026 የኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን በሀገሪቱ የእግር ኳስ ታሪክ ከታላላቅ ቡድኖች መካከል የቱ ይመደባል?
#norway #fifaworldcup2026 #erlinghaaland #football #norwegianfootball #getutemesgen #ethiopia

25 days ago
እንግሊዝ በቤሊንግሃም አስደናቂ ብቃት ለግማሽ ፍጻሜ አለፈች
#ethiopia |የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች በከፍተኛ ትንቅንቅ እየቀጠሉ ይገኛሉ። ዛሬ በተደረገው እጅግ አስደናቂ ጨዋታ እንግሊዝ ኖርዌይን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜው መሸጋገሯን አረጋግጣለች።
የጨዋታው Highlights
የኖርዌይ መሪነት፡ የውድድሩ አስደናቂ ክስተት በመሆን የቀጠለችው ኖርዌይ በሽልድረፕ ግብ መሪነትን ይዛ የነበረ ቢሆንም፣ የሶስት አንበሶቹን አስፈሪ ጥቃት መቋቋም አልቻለችም። በዚህም የኖርዌይ አስደናቂ ጉዞ በሩብ ፍጻሜው ተገቷል።
የቤሊንግሃም ድምቀት፡ 120 ደቂቃ በወሰደው በዚህ አስደናቂ ፍልሚያ የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ጁድ ቤሊንግሃም ሁለቱንም የእንግሊዝን ግቦች በማስቆጠር የቡድኑ ባለውለታ ሆኗል።
ለኮከብ ግብ አስቆጣሪነት የሚደረግ ፉክክር
ቤሊንግሃም በመድረኩ በተከታታይ ሁለት ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፣ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ላይ ያስቆጠረውን አጠቃላይ የግብ ብዛት 6 አድርሷል። ይህም ለውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብር (ወርቃማው ጫማ) በግንባር ቀደምትነት እንዲፎካከር አድርጎታል።
ቀጣይ ተጋጣሚ ማነው?
ወደ ግማሽ ፍጻሜው ያለፈችው እንግሊዝ፣ ቀጣይ ተጋጣሚዋን ለማወቅ ከአርጀንቲና እና ስዊዘርላንድ ጨዋታ አሸናፊ የሚወጣውን ቡድን የምትጠብቅ ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#worldcup2026 #judebellingham #england #norway #footballnews #getutemesgen

1 month ago
ብራዚል ከ23ኛው ዓለም ዋንጫ ተሰናበተች
**************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የ16ቱ ሀገራት ጥሎ ማለፍ መርኃ ግብር ብራዚል በኖርዌይ 2 ለ 1 ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫው ተሰናብታለች። ኖርዌይም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሩብ ፍፃሜ አልፋለች።
የኖርዌይን የማሸነፊያ ግቦች 79ኛው እና 90ኛው ደቂቃ ላይ ኧርሊንግ ሀላንድ ከመረብ አሳርፏል። ለብራዚል ኔይማር ጁኒየር በፍፁም ቅጣት ምት 90+10 ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
በጨዋታው በብራዚል በኩል ብሩኖ ጉማሬሽ 14ኛው ደቂቃ ላይ ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ኖርዌይ በሩብ ፍፃሜው የሜክሲኮ እና እንግሊዝን አሸናፊ የምትገጥም ይሆናል።
በእድሪስ አሕመድ
#worldcup #fifaworldcup #brazil #norway #knockoutstage #football #sports

ብራዚል 0 - 0 ኖርዌይ :- የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤት
***************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ በብራዚል እና በኖርዌይ መካከል እየተደረገ ያለው ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ያለ ምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

ብራዚል ከ ኖርዌይ፦ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ
*******************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ብራዚል ከ ኖርዌይ የሚያደርጉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል።
ሁለቱ ቡድኖች ወደ ሜዳ ይዘው የሚገቡት የመጀመሪያ አሰላለፍ፦
#worldcup2026 #brazil #norway #roundof16 #ebc

Sponsored by
Surafel
1 month ago
የምድብ ዘጠኝ የመጨረሻ ጨዋታዎች፤ ፈረንሳይ ከ ኖርዌይ እና ሴኔጋል ከ ኢራቅ
************************
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የምድብ ዘጠኝ ተጠባቂ የመጨረሻ ጨዋታዎች በተመሳሳይ ዛሬ ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ ሲደረጉ፣ የምድቡን መሪ ለመለየትና የምርጥ ሦስተኛ ደረጃ ዕድልን ለመጠቀም ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የዓለም ዋንጫን ሁለት ጊዜ ማንሳት የቻለችው ፈረንሳይ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኖርዌይን ትገጥማለች፡፡
ፈረንሳይ ካደረገቻቸው ሁለት ጨዋታዎች ሁለቱንም በማሸነፍ፣ 6 ግቦችን አስቆጥራ 1 ብቻ በማስተናገድ በ6 ነጥብ የምድቡ መሪ ነች።
በአንጻሩ ኖርዌይ ካደረገቻቸው ሁለት ጨዋታዎች ሁለቱንም በማሸነፍ፣ 6 ነጥብ ይዛ በግብ ክፍያ በፈረንሳይ ተበልጣ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ኖርዌይ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪኳ በ1998 እስከ ጥሎ ማለፍ ድረስ መጓዝ የቻለችበት ታሪክ ያላት ሲሆን፣ ዛሬ ከፈረንሳይ ጋር በምታደርገው ጨዋታ የምድቡን የበላይነት ለመያዝ ትጫወታለች።
ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች ቀደም ብለው ባከናወኗቸው የምድብ ጨዋታዎች ላይ ባስመዘገቡት ድል ወደ ቀጣይ ዙር ማለፋቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፣ የዛሬውን ጨዋታ ምድቡን በአንደኝነት ለማጠናቀቅ ይጫወታሉ፡፡
በሌላኛው መርኃ ግብር ሴኔጋል ከኢራቅ ጋር በምታደርገው ጨዋታ ምርጥ ሦስተኛ ሆና ወደ ጥሎ ማለፍ ለመግባት ያላት ዕድል ጠባብ ሲሆን፣ ምንም እንኳ በእርሷ ማሸነፍ ብቻ የሚወሰን ባይሆንም ብሎም በምታስመዘግባቸው ግቦች ብዛት ቢመረኮዝም፣ በዚያ ጠባብ ዕድል ለመጠቀም የሚደረግ ወሳኝ ፍልሚያ ነው።
ሴኔጋል ካደረገቻቸው ሁለት ጨዋታዎች በሁለቱም በመሸነፏ ካለምንም ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
በ2002 የኮሪያ እና ጃፓን ዓለም ዋንጫ እስከ ሩብ ፍፃሜ ተጉዛ ታሪክ የጻፈችው ሴኔጋል፣ ዛሬ ኢራቅን በማሸነፍ ምርጥ ሦስተኛ ሆና ለማለፍ ያላትን ጠባብ ዕድል ለመጠቀም ትጫወታለች።
ኢራቅ በበኩሏ ካደረገቻቸው ሁለት ጨዋታዎች በሁለቱም በመሸነፏ፣ ከምድቡ የተሰናበተች ለመርኃ ግብር ማሟያ እና ለታሪክ ጨዋታዋን ታከናውናለች።
በአሁኑ ሰዓት ስዊድን እና ኢኳዶር በ4 ነጥብ ምርጥ ሦስተኛ ሆነው ለማለፍ ያለውን ዝርዝር እየመሩ ሲሆን፣ የዚህ ምድብ ውጤትም በምርጥ ሦስተኛነት በሚያልፉ ሀገራት ዝርዝር ላይ የራሱ ተጽዕኖ ይኖረዋል።
በዘረንቶስ ሰለሞን
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #worldcup #groupi #france #norway #senegal #iraq #football #sport

Comments