(ዘ-ሐበሻ ዜና) የግብፁ ፕሬዝደንት አልሲሲ ለቅሶ ለመድረስ ኳታር ገቡ፡፡ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትላንት ወደዶሀ ተጉዘው በአሚር ሼክ ሀማድ ቢን ከሊፋ አልታኒ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ ዛሬ ደግሞ የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በስፍራው ተገኝተው ለቅሶ ደርሰዋል፡፡
በዛሬው እለት በርካታ የአለማችን መሪዎች ዶሀ በመግባት በአሚሩ ሞት ሀዘናቸውን የገለፁ ሲሆን ከእነዚህ መካከል የሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ፣ የማልዲቭስ ፕሬዝደንት መሀመድ ሚዩዙ፣ የካዛኪስታን ፕሬዝደንት ካሳይም ጆማርት ቶካይቭ፣ የሞሮኮ ጠቅላይ ሚኒስትር አዚዝ አካኖች፣ የኢራቅ ፕሬዝደንት ናዚር አሚዲ፣ የሊቢያ አንድነት መንግስት ፕሬዝደንት አብዱል ሀሚድ ድቢባህ፣ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላም፣ የሶሪያ ፕሬዝደንት አህመድ አልሻራና የፊፋ ፕሬዝደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ይገኙበታል፡፡

24 days ago