1 hr. ago
ለጥንቃቄ!!!!
ትናንት ይሁን ከትናንት ወዲያ ይህንን መረጃ የሰይፉ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ቀርቦ ብዙዎች ተምረውበታል። ጉዳዩን ላልሰማችሁ ለጥንቃቄ እነሆ ብሎ ዳዊት እርገጤ እንዲህ ከትቦታል።
የዕድሜ ልክ ጥረቱን የተበላው የፌድራል ፖሊስ አመራሩ ባለቤት ታማ ፀበል ገባች!
በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉት ረዳት ኢንስፔክተር አንድነት ሽመልስ እና ቤተሰቦቻቸው፣ በዘመናዊ የዲጂታል ቀማኞች ወጥመድ ውስጥ ወድቀው ከ1.3 ሚሊየን ብር በላይ ተዘርፈዋል።
ጉዳዩ የተጀመረው "ቤት ቁጭ ብሎ በወር ከ70 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር መሥራት ይቻላል" በሚል ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚወጣ አታላይ ማስታወቂያ ነው።
የቤት እመቤት የሆነችው ባለቤታቸው ነገሩን አምና አፕሊኬሽኑን ስትሞክረው፤ ወደ ቴሌግራም እና ዋትስአፕ ግሩፖች በመግባት "አሊባባ ኦንላይን ንግድ" በሚባል አደገኛ መዋቅር ውስጥ ትገባለች።
አጭበርባሪዎቹ ሰዎችን ለማጥመድ የተካኑ ስለሆኑ፣ እምነት ለማግኘት ሲሉ በመጀመሪያ 800 ብር ልከው 1,500 ብር ይመልሱላቸዋል። ቤተሰቡም "ነገሩ እውነት ነው" ብሎ እንዲያምን ያደርጉታል።ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ትክክለኛው ሰቆቃ የሚጀምረው።
የገንዘቡ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲመጣ፣ የራሳቸውን ቁጠባ ጨምሮ ከውጭ ሀገር ከምትኖር የባለቤታቸው እህት ጭምር 600,000 ብር ተበድረው ገቢ ያደርጋሉ።
አጭበርባሪዎቹ ጨካኝነታቸውን አሳይተው "አንደኛ ደረጃ ነጋዴ ስለሆናችሁ ከፍተኛ ግብር መክፈል አለባችሁ" በማለት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስገቡ አድርገው በድምሩ 1.3 ሚሊየን ብር እንዲዘረፉ አድርገዋቸዋል።
በሐሰተኛው መተግበሪያ ላይ 3 ሚሊየን ብር አትርፈዋል ተብሎ ይታይባቸውም ነበር፤ ነገር ግን ገንዘቡን ማውጣት ሳይችሉ ቀርተው አካውንታቸው ላይ የቀረው 59 ብር ብቻ ነው! ይህ ሁሉ አሰቃቂ ድርጊት ሲፈጸም ረዳት ኢንስፔክተር አንድነት በሥራ ስምሪት (ፊልድ) ላይ ነበሩ።
የገንዘቡን መበላት ስትሰማ የባለቤታቸው ልብ ድንጋጤን መቋቋም አቅቶት ዛሬ ላይ በጽኑ ታማ በጸበል ቦታ መንፈሳዊ ሕክምና እየተደረገላት ይገኛል። የዕድሜ ልክ ድካማቸው በአንድ ቀን ባዕድ ኃይል መናጋቱ ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ከቷቸዋል። Via_ጉርሻ page
Seledadotio

2 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በዳውሮ ዞን ገና ወረዳ ውስጥ ለአርሶ አደሩ የተመደበ የአፈር ማዳበሪያ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ሥር መዋሉ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጣ እና ጥያቄ አስነስቷል። ማዳበሪያ ለገበሬው የሕይወት መሠረትና የምርት ማሳደጊያ ዋነኛ ግብዓት በሆነበት በአሁኑ ወቅት፣ ምርቱን ከተመደበለት ዓላማ ውጪ በሕገ-ወጥ መንገድ ማዘዋወር አርሶ አደሩን ለከፋ ችግር የሚዳርግ እና በሕዝብ ላይ እንደተፈጸመ ከባድ በደል የሚቆጠር ነው።
የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት መጓደል በግብርናው ዘርፍ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ቀላል አይደለም። አርሶ አደሩ በትክክለኛው የትራክተርና የዘር ወቅት ማዳበሪያ ካላገኘ የምርት መቀነስ፣ የኑሮ ጫና መባባስ እና አጠቃላይ የምግብ ዋስትና ቀውስ ሊገጥመው ይችላል። በመሆኑም ይህ የሕዝብና የሀገር ሀብት ለግል ጥቅም ሲባል በሕገ-ወጥ መንገድ ሲመዘበር ጉዳዩን በቸልታ ማለፍ ፈጽሞ ተገቢ እንዳልሆነ ማኅበረሰቡ አበክሮ እያሳሰበ ይገኛል።
ይህንን ድርጊት ተከትሎ፣ በጉዳዩ ላይ ጥብቅና እውነተኛ ምርመራ ተደርጎ በወንጀሉ የተሳተፉ ግለሰቦችም ሆነ የጥቅም ተካፋዮች ማንነት በሕግ አግባብ ተጣርቶ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጠንካራ የሕዝብ ጥያቄ እየቀረበ ነው። ሕግ ለሁሉም እኩል ሊሆን እንደሚገባ እና የሕዝብን ሀብት የሚያባክን ማንኛውም አካል በሕግ ፊት ያለምንም አድልዎ ሊጠየቅ እንደሚገባ ተጠቁሟል። የሕዝብ ሀብት በምንም ዓይነት መስፈርት የግል መጠቀሚያ ሊሆን አይችልም።
ወደፊትም መሰል ማጭበርበሮች እንዳይከሰቱ የማዳበሪያ ስርጭት ሂደቱ ከመነሻው እስከ መድረሻው ድረስ ግልጽነት ያለው እና ጥብቅ የክትትል ሥርዓት የተዘረጋለት መሆን እንዳለበት ተመላክቷል። ለአርሶ አደሩ የተመደበው ሀብት መንገድ ላይ እንዳይመዘበር፣ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ኃላፊነታቸውን በታማኝነትና በቅንነት ሊወጡ ይገባል። የአርሶ አደሩን ተስፋ የሚያጨልም እና የሀገርን አጠቃላይ ልማት ወደ ኋላ የሚጎትት ይህ ዓይነቱ ሕገ-ወጥ ተግባር በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል።

4 hours ago
የጅማ ዞን በበቆሎ ልማት ያስመዘገበው አዲስ የስኬት ምዕራፍ
********************
የጅማ ዞን በአብዛኛው ጥራትና ብዛት ባለው የቡና ምርቱ የሚታወቅ ሲሆን አሁን ላይ በዞኑ በክላስተር የለማው የበቆሎ ሰብል የግብርና ልማት ለሌሎች በምሳሌነት የሚጠቀስ ሆኗል፡፡
የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ፤ ዞኑ ሀገራችን ከቡናው ዘርፍ የውጭ ምንዛሪ እንድታገኝና መልካም ስም እንድትጎናፀፍ ከማድረጉም ባሻገር ዛሬ በተለያዩ የሰብል ምርቶች አዲስ ስኬት በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት ፅሁፍ፤ በተለይም በጊቤ ወንዝ ሸለቆ ዳርቻ በሚገኘው በቦቶር ጦላይ ወረዳ በክላስተር የለማው በቆሎ ሰፊ መሬት በመሸፈን የግብርና ክላስተር ልማት አርአያ ሆኖ ይታያል ብለዋል።
በአጠቃላይ በቦቶር ጦላይ ወረዳ በሚገኙ 16 የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ 9,540 አርሶ አደሮች በ19,778 ሄክታር መሬት ላይ በቆሎን በክላስተር ማልማታቸውን የገለጹት አቶ አዲሱ አረጋ፤ በጅማ ዞን ደረጃ 198,115 ሄክታር መሬት በቆሎ በክላስተር የለማ ሲሆን ከሄክታር በአማካይ 80 ኩንታል ምርታማነት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።
ይህ ሥራ ምርታማነትን በመጨመር፣ የአርሶ አደሮችን ገቢ በማሳደግና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

6 hours ago
በቅድመ ውድድር ዘመን ጨዎታዎች ማንቸስተር ሲቲ ድል ሲያስመዘግብ ቼልሲ አቻ ተለያይቷል
***********************************
በማሌዥያ ኢስካንዳር ፑተሪ በሚገኘው ሱልጣን ኢብራሂም ላርኪን ስታዲየም በተደረገ የቅድመ ውድድር ዘመን የወዳጅነት መርሐ-ግብር ቼልሲ ከጆሆር ዳሩል ታዚም ጋር ተጫውቶ 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
በዚህ ማራኪ ጨዋታ ለቼልሲ ሊያም ዲላፕ ሁለት ግቦችን በፍጹም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር ክሪስቶባል ማርኩዌዝ ደግሞ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥሯል። በጆሆር ዳሩል ታዚም በኩል ደግሞ አይማን፣ ኦስካር አሪባስ እና ቤርግሰን ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል።
በተመሳሳይ በደቡብ ኮሪያ ሴኡል በሚገኘው ሴኡል ወርልድ ካፕ ስታዲየም በተደረገ ሌላ የቅድመ ውድድር ዘመን የወዳጅነት መርሐ-ግብር ማንቸስተር ሲቲ ስፔናዊውን ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድን ገጥሞ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ለማንቸስተር ሲቲ የማሸነፊያዎቹን ግቦች ኦማር ማርሙሽ ሁለት እንዲሁም ሪያን አይት-ኑሪ አንድ ግብ ከመረብ ሲያሳርፉ፣ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ብቸኛዋን ግብ ጆርጅ ዶሚንጌዝ አስቆጥሯል።
#chelsea #manchestercity #atleticomadrid #preseason #friendlymatch

Sponsored by
Surafel
8 hours ago
ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩቱ አንድ ሺህ 898 ተማሪዎችን አስመረቀ
- በስኮላርሺፕ ከደቡብ ሱዳንና ሶማሌላንድ የመጡ ሰልጣኞች ተመርቀዋል
የኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢኒስቲትዩት በተለያዩ ፕሮግራሞችን ሲያሰለጥናቸው የነበሩ አንድ ሺህ 898 ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመረቀ።በተመሳሳይ ''ክህሎት ለዜጋ'' በሚል መርሐግብር በእስኮላርሺፕ ከደቡብ ሱዳንና ሶማሌላንድ የመጡ ሰልጣኞችን አሰመርቋል።
በዚህ የምርቃት መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የስራና ክህሎት ሚኒስትር መፈሪሃት ካሚል በወቅቱ እንደገለጹት፤ ትምህርትና ስልጠና የሀገርን እምቅ አቅም ለማውጣትና ችግርን ለመፍታት ወሳኝ ነውቴክኒክና ሙያ እውቀትን ከክህሎት በማጣመር እንዲሁም ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ በመፍጠር የሀገርን ብልጽግና ማረጋገጥ የሚስችል ዘርፍ መሆኑን አመላክተዋል ።
ትምህርትና ስልጠና ለመጪው ጊዜ የሚያዘጋጁ የስንቅ ማዕዶች ናቸው ያሉ ሲሆን፣ ሰልጣኞች ብቁና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲጨርሱ በትኩረት መሠራቱን ተናግረዋል።
ላለፉት አምስት ዓመታት ስራን ክህሎትን እንዲሁም ኢንዱስትሪን መሠረት ያደረገ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ጠቅሰው፤ ከዚህም የክህሎት ባንክ አንዱ ነው ብለዋል።
ዓለም አቀፍ ብቃት ያላቸውን ሰልጣኞች ማፍራት የሚያስችሉ ተጨማሪ የክህሎት ፓርኮች እና መሠረተ ልማቶች እየለሙ እንደሚገኙም ሚኒስትሯ ጨምረው ጠቅሰዋል።
ተመራቂዎች ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ በመግለጽ፤ በፅናት፣ በዲሲፕሊን፣ በትጋትና በሀገር ወዳድነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም አስገንዝበዋል። በቀጣይም ዓለም አቀፍ እውቅና ያለውና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሀገርን ወደ ሚገባት ከፍታ ለማድረስ ብቁና የሰለጠነ የሰው ኃይል ያስፈልጋታል፣ ይህም እውን ለማድረግ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የማይተካ ሚና አለው ብለዋል።
ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የጋራ ፕሮግራሞችን የማስተሳሰር ሥራ መሠራቱንም ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል።
የልምድ፣ የክህሎት፣ የዕውቀት፣ የቴክኖሎጂ ኢንኩቤሽን እንዲሁም ከታዳጊነት ዕድሜ ጀምሮ የሙያ ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑን አስታውቀዋል።
በተያዘው ዓመትም 11 አዳዲስና 34 ነባር ፕሮግራሞች ላይ የተለያዩ ስልጠናዎች ሲሰጡ የቆዩ ሲሆን፤ በዕለቱ 1583 በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም 315 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ በአጠቃላይ ፤ አንድ ሺህ 898 ተማሪዎችን መመረቃቸው ተገልጿል።

9 hours ago
በአልኮል እና ሲጋራ ምርቶች ላይ ከተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ የተነሳ ህጋዊ የሲጋራ ገበያ ከ2019 ወዲህ በሁለት ሶስተኛ ገደማ ቢቀንስም፣ የሸ his ንበ "ተጠቃሚዎች ቁጥር ግን አለመቀነሱ ተገለጸ
አዲሱ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ የዋጋ ጭማሪው ተጠቃሚዎች ሱሳቸውን እንዲተው ከማድረግ ይልቅ ወደ ህገ-ወጥ ሲጋራዎች (እንደ ሻልማን፣ ጎልድ እና ኦሪስ) እና ከታክስ ነፃ ወደሆኑ ባህላዊ መጠጦች (አረቄ፣ ጠጅ እና ጠላ) እንዲዞሩ አድርጓቸዋል።
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አቤተሰቦች በዋጋ ጭማሪው ምክንያት አጠቃቀማቸውን ቢቀንሱም፣ አሁንም ወደ 2.4 ሚሊዮን የሚጠጉ አዋቂዎች ሲጋራ ማጨሳቸውን ቀጥለዋል።
በዚህ ታክስ መንግስት ከአልኮል 13.6 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ከትንባሆ 1.7 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ቢችልም፣ አምራቾች የግብር ጫናው ከባድ መሆኑን ይናገራሉ።
በሌላ በኩል የምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን የጥናቱን ሽፋንና ማስረጃ ጥያቄ ውስጥ በማስገባት አከራካሪነቱን ጠቁሟል።
አዲስ ፎርቹን

12 hours ago
የቀብር ሥነ-ሥርዓት መርሃ-ግብር
(ሰኞ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም — ቢሾፍቱ)
#ethiopia | ለኢንጂነር ያደሳ እምሩ አጋ ዕረፍት የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን እየገለጽን፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን።
የጸሎት እና የሽኝት ሥነ-ሥርዓት:
ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በደብረ ዘይት መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን
ግብዓተ መሬት:
ከቀኑ 7:30 ሰዓት በቃጂማ መካነ ኢየሱስ መካነ መቃብር
"የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።"
— መዝሙረ ዳዊት 116፥15
እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን በገነት ያኑር፤ ለቤተሰቡና ለወዳጆቹም መፅናናትን ይስጥ።

17 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢራን ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት አሜሪካ "ባህሪዋን እስካላስተካከለች" ድረስ የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ ክፍት እንደማይሆን በማሳወቅ፣ በቀጠናው በሚደረገው የሰላም ድርድር ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስቀመጠ። የኢራን ኃይለኛ የተባለው አብዮታዊ ዘብ አዛዥ እና የምክር ቤቱ ጸሐፊ መሐመድ ባገር ዞልጋድር ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ አሜሪካ ኢራንን ማስፈራራቷን ማቆም፣ ጦርነቱን በቋሚነት ማብቃት፣ በኢራን ወደቦች ላይ የጣለችውን የባህር ላይ እገዳ ማንሳት እና ጦሯን ከቀጠናው ማስወጣት አለባት። በተጨማሪም አሜሪካ ለጦርነቱ ውድመት ሙሉ ካሳ እንድትከፍል፣ ማዕቀቦችን እንድታነሳ እና የታገዱ የኢራን ሀብቶችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንድትለቅ ጠይቀዋል።
እነዚህ ጥያቄዎች ቀደም ሲል አሜሪካ የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር በተመለከተ ለምታደርገው ቋሚ ስምምነት እንደ ቅድመ ሁኔታ ሲቀርቡ የነበሩ ቢሆንም፣ አሁን ግን የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤን መልሶ ለመክፈት ብቻ መቅረባቸው ሁኔታውን አወሳስቦታል። የ60 ቀናት የሽግግር ስምምነት ጊዜ ሊጠናቀቅ አንድ ሳምንት ገደማ በቀረበት በዚህ ወቅት የቀረቡት እነዚህ ግዙፍ ጥያቄዎች፣ አሜሪካ በቀላሉ ልትቀበላቸው ስለማትችል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ወደ ወታደራዊ እርምጃ ሊገፋፏቸው እንደሚችሉ ተንታኞች እየገለጹ ነው። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በበኩላቸው ከኦማን ጋር በባህር ትራንስፖርት መስመር ዙሪያ ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባቸውን ገልጸው፣ የባህረ ሰላጤው መከፈት ግን አሜሪካ በዋና ዋና ቅድመ ሁኔታዎች ላይ በምትወስደው እርምጃ ላይ የተመሰረተ መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በሰጡት መግለጫ፣ ኢራን በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ ላይ በሚያልፉ መርከቦች ላይ ቀረጥ (ክፍያ) የመጣል እቅድ እንደሌላት ለዋሽንግተን ማሳወቋን ገልጸዋል። ሆኖም ቫንስ አሜሪካ የኢራንን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በቅርበት እንደምትከታተል አሳስበው፣ አሁን ላይ ዋነኛው ትኩረት በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ ኢራን የዘረጋቻቸውን ፈንጂዎች በማጽዳት የንግድ መርከቦች በሰላም የሚያልፉበትን መንገድ ማመቻቸት መሆኑን አስታውቀዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቱ አክለውም አሜሪካ የኢራንን የኒውክሌር እና መደበኛ ወታደራዊ አቅም ክፉኛ እንዳዳከመችው በመግለጽ፣ ኢራን የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር የረጅም ጊዜ ለውጦችን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆነች አሜሪካ ጫናዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል አስጠንቅቀዋል።

1 day ago
ኦሮሚያ ባንክ በገላን የልህቀት ማዕከል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ!
#fastmereja I ኦሮሚያ ባንክ በገላን ክፍለ ከተማ በሚገኘው የልህቀት እና ኮንቬንሽን ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ቃል ከ2 ሺህ በላይ ችግኞችን የመትከል መርሀ-ግብር በዛሬዉ እለት አካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የባንኩ የቦርድ አመራር አባላት፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ደንበኞች፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ እና ሕፃናት ተሳትፈዋል።
የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን እንደገለጹት፤ መርሃ ግብሩ በየዓመቱ የሚካሄድ እና ዘላቂነት ያለው የአካባቢ ጥበቃ አካል መሆኑን ገልፀዉ የተተከሉት ችግኞችም ዓመቱን ሙሉ አስፈላጊው እንክብካቤ እየተደረገላቸው ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ እንደሚደረግ አስረድተዋል።
የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለአካባቢ ውበት፣ ለምግብነት የሚውሉ ምርቶችን ለማረት እንዲሁም ሀገሪቱን ከካርበን ልቀት ነፃ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
በተጨማሪም መርሀ-ግብሩ ሕፃናትን ማሳተፉ የተፈጥሮ እና የአካባቢ ጥበቃ ባህልን ለቀጣዩ ትውልድ ለማሸጋገር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል።
በተያያዘም ተሳታፊዎች በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ እየተካሄዱ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ማዕከሉ ደረጃውን የጠበቀ ሁለገብ የኮንቬንሽን ማዕከል፣ የ9 ፎቅ ንግድ ህንፃ፣ የስፖርትና አካል ብቃት ማዕከል እንዲሁም ለባንከሮች እና ለተለያዩ ሴክተሮች የሚሆን የስልጠናና ቦርዲንግ ማዕከልን ያካተተ ፕሮጀክት መሆኑ ተጠቅሷል።
ተቋሙ ባለፉት ዓመታት የተከላቸው ችግኞች ፀድቀው ለውጤት መብቃታቸውን እና ዘንድሮም የተጀመረው ዘመቻ ይህንን አዎንታዊ አሻራ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቋል።
📷 ከበደ መክብብ

የየካው ንጉስ የቅዱስ ሚካኤል መልእክት
ጥንታዊው፣ ታሪካዊው፣ በተአምር ሠሪነቱ፣ በፈዋሽነቱ፣ በስእለት ሰሚነቱ ና በልዩ ግርማ ሞገሱ የሚታወቀው የየካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሁለት ቤዝመንት ያለው ባለ 15 ወለል (2 Basement+G+ 12ወለል) ግዙፍ ጠቅላላ ሆስፒታል በማስገንባት ላይ ይገኛል። ይህም ድንቅ ሆስፒታል በጸበሉ ስፍራ እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን «ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል»የሚል ስያሜ ተሰጥቶት የመጀመሪያው ምዕራፍ የመሰረት ቁፋሮና የአፈር ናዳ መከላከያ (ሾሪንግ) ሥራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
ይህ በ1000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈውና ባለ 250 የህሙማን ሕክምና መስጫ አልጋ አቅም የሚኖረው ዘመናዊ ሆስፒታል፤ የተመላላሽ ክሊኒኮችን፣ የፅኑ ሕክምና (ICU)፣ የቀዶ ጥገና ክፍሎችን እንዲሁም ለእናቶችና ሕጻናት ጤና፣ ለልብ ሕክምናና ለተላላፊ በሽታዎች መከላከያ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ማዕከላትን ያካትታል። ተቋሙ የጤና አጠባበቅን እንደ ንግድ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊና መንፈሳዊ አገልግሎት በመመልከት፣ለሁሉም የማህበረሰቡ አባላት በሙሉ ጥራት ያለው፣ ተደራሽና አቅምን ያገናዘበ የሕክምና አገልግሎት ያቀርባል።
በህንፃ ባለሙያዎች ጥናት መሠረት ለህንፃ ግንባታው አጠቃላይ ወጪ ብር 405,040,000 (አራት መቶ አምስትሚሊዮን አርባ ሺህ ብር) እንደሚሆን ተገምቷል።ይህ ወጪ በየጊዜው በሚታየው የዋጋ ንረት ምክንያት ሊጨምር እንደሚችል ይታሰባል፡፡
ይህንን ከፍተኛ ወጪ ለመሸፈንና ቀጣዩን ወሳኝ የግንባታምዕራፍ ለመጀመር ቤተ ክርስቲያኑ በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚኖሩ ምዕመናንን፣ የንግዱን ማህበረሰብና የልማት አጋሮችን ያሳተፈ የሀብት ማሰባሰቢያ ስልት ቀይሷል።
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ እና የልማት ኮሚቴው ምዕመናን በሰጦታቸው ከእግዚአብሔር የሚያገኙትን በረከት በማሰብ፦ «ይህ ታላቅ የማህበራዊና የጤና ልማት ፕሮጀክት ፍጻሜ እንዲያገኝ የዓላማው ደጋፊዎች ሁሉ የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉና አሻራቸውን እንዲያኖሩ በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ስም እንማጸናለን» ሲል ጥሪውን ያስተላልፋል።
ለዚህም ይረዳ ዘንድ የፊታችን ነሐሴ 8፣ 9 እና 10 ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል። የየካው ቅዱስ ሚካኤል ያሳደጋችሁ፣ ከሩቅም ከቅርብም ሆናችሁ ፍቅሩን ደግነቱን የቀመሳችሁ፣ የታሪካዊው የየካ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ የሆናችሁ፣ ዝናውን ሰምታችሁ ደጁ የሚናፍቃችሁ፣ ጠብቆ አሳድጎ ለክብር ያበቃችሁና ገና ስሙ ሲጠራ ልባችሁ በደስታ የሚሞላ የኃያሉ መልአክ የቅዱስ ሚካኤል ልጆች ሁላችሁ በቀጥታ ሥርጭቱ በመታደም ድጋፍ እንድታደርጉ እንማጸናችኋለን።
ድግፍ ለማድረግ:-
• ወገን ፈንድ 👉 https://www.wegenfund.com/...
• የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብቁጥር፦
1000000764087 እንዲሁም
አጭር ቁጥር 1277
• አባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፦ 1227
• አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር
013521784586601
• ስዊፍት ኮድ AWINETAA
• ስልክ ቁጥር፦
0945881188 እና 0945771188
2 days ago
ኦሮሚያ ከኢትዮጵያ አትገነጠልም፣ ኦሮሚያ እራሷ ኢትዮጵያ ናት!
ኦሮሞ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ይገኛል። ኦሮሚያ ከኢትዮጵያ በላይ ናት።
የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ከሞላ ጎደል ተመልሷ። ለዚህም ኦሮሞ የአእምሮ ነፃነት አጊንቷል ይህ ነፃነት ያገኘው አእምሮ ደግሞ ኦሮሚያን አበልፅጓል፤ በግብርና በትምህርትና በከተሞች ያመጣነውን እድገት ማየት በቂ ነው።
ኦሮሚያ ከ8 አመት በፊት 52 ቢሊዮን ብር አመታዊ በጀት የነበራት ሲሆን አሁን ላይ የኦሮሚያ በጀት ከ700 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከኦቢኤን ቲቪ ጋር በኦሮምኛ ያደረጉት ንግግር

በኦሮሚያ ክልል በሁሉም ዘርፎች ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኦሮሚያ ክልል በሁሉም ዘርፎች ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል አሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኦቢኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄዎች እና ትግሎች፣ የኢትዮጵያ ታሪክ እና የኦሮሞ ሕዝብ አበርክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም በኦሮሚያ ክልል በሁሉም ዘርፎች እየመጣ ያለው ለውጥ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።
በግብርና፣ በገቢ እና በበጀት እድገት ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡንም በአብነት አንስተዋል።
በክልሉ የሚታረሰው መሬት ከ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር ወደ 17 ሚሊየን ሄክታር ማደጉን ገልጸው፤ ባለፈው ዓመት አጠቃላይ ምርታማነትን በማሳደግ 500 ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን አስታውሰዋል።
በግብርና ዘርፍ ካለው አቅም አንጻር ቀሪ ስራ ቢኖርም በርካታ አዎንታዊ ውጤቶች መጥተዋል ብለዋል።
በ2010 ዓ.ም የነበረው የክልሉ ገቢ ከነበረበት 13 ቢሊየን ብር በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ወደ 342 ቢሊየን ብር ማደጉን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ መልኩ በ2010 ዓ.ም 52 ቢሊየን ብር ብቻ የነበረው የክልሉ አጠቃላይ በጀት በዘንድሮው ዓመት 700 ቢሊየን ብር መድረሱን ጠቅሰዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሱዳን ዘንድሮ ኢኮኖሚዋ በ9 ፐርሰንት እንደሚያድግ ገለፀች፡፡ በሌተና ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልብሩሀን የሚመራው የሱዳን ወታደራዊ መንግስት የአገሪቱ ኢኮኖሚ በ9 ፐርሰንት ያድጋል የሚል እምነት እንዳለው አስታወቀ፡፡ ይህንን ያስታወቀው ትላንት በካርቱም በተካሄደው የሚኒስትሮች ካቢኔ ስብሰባ ላይ በቀረበው ሪፖርት ነው፡፡ የፋይናንስ ሚኒስትሩ ጅብሪል ኢብራሂም ባቀረቡት በዚህ ሪፖርት በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ኢኮኖሚ በማገገም ላይ መሆኑን ገልፀው በዚህም የአገሪቱ አጠቃላይ ምርት በ2026 በ9 ፐርሰንት ያድጋል የሚል ግምት እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡
ባለፈው አመት ይህ እድገት 1.7 ፐርሰንት ብቻ እንደነበርም አውስተዋል፡፡ ጨምረውም በአገሪቱ ውስጥ የነበረው የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ መምጣቱንና ከግብር የሚገኘው ገቢ ደግሞ በመጨመር ላይ መሆኑን ገልፀዋል ሲል ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው ከወራት በፊት የወጣው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት በ2023 የሱዳን አጠቃላይ አገራዊ ምርት በ6.6 ቢሊዮን ዶላር ቀንሶ 32.4 ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ ይገልፃል፡፡ ይህም የ12 ፐርሰንት ቅናሽ መከሰቱን የሚያሳይ መሆኑን የጠቀሰው የተመድ ሪፖርት ከዚያ በኋላ ባሉት አመታትም እየቀነሰ መምጣቱን ማስረዳቱን አስታውቋል፡፡
እንዲሁም ከ2024 እስከ 2043 ባሉት አመታት ውስጥ የሱዳን ኢኮኖሚ በየአመቱ ከ1.2 ፐርሰንት በላይ እንደማያድግ ግምት ማስቀመጡን ዘገባው አውስቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አይኤምኤፍ ባወጣው የ2026 የአለም ኢኮኖሚ ሪፖርት የሱዳን ኢኮኖሚ እንደሚያድግ የተነበየው በ0.7 ፐርሰንት ነው፡፡

የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሚያሰራውን ቤተሰሊሆም አጠቃላይ ሆስፒታል ህንፃ ግንባታን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡
ከሁሉ አሰቀድመን እግዚአብሔር አምላካችን ለ2018 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሁላችንንም በሰላም በጤና ስላደረሰን እናመሰግነዋለን፡፡የተከበራችሁ አበው መነኮሳት፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ካህናት እና ዲያቆናት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ ምዕመናን እና ወጣቶች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንዲሁም ይህን መልእክት ለመላው ዓለም ለማስተላለፍ የተገኛችሁ የሚድያ አካላት በሙሉ በእግዚአብሔር ስም የከበረ ሰላምታችንን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከሆነው ከየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እናቀርባለን፡፡
“በኂሩተ ጻድቃን ትረትዕ ሀገር”
“በጻድቃን ልማት ከተማ ደስ ይላታል”
ምሳ 11፥10
እግዚአብሔር በንጉሱ ሰሎሞን ላይ አድሮ የተናገረውን መነሻ በማድረግ ልማት ለቤተከርስቲያን ፣ልማት ለሀገር፣ልማት ለማኅበረ ስብእ አስፈላጊ መሆኑን በማሰብ በአዲስ አበባ ሀገረ ስበከት በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለሚገነባው ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል የህንፃ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት መርሃ ግብር የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡ የእግዚአበሔር ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን፡፡ አሜን።
1. ታሪካዊ ዳራ እና የልማት መነሻ
ከአክሱም ዘመነ መንግሥት (በአባ ሰላማ ዘመን) የጀመረውና ከ1600 ዓመታት በላይ የዘለቀው የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ የኢትዮጵያን ጥንታዊነትና የአዲስ አበባን ከተማ አመሰራረት የሚተርክ ህያው ቅርስ ነው።ይህ ታሪካዊ ደብር በአብርሃ ወአጽብሃ፣ በዳግማዊ አጼ ምኒልክና በንግሥት ጣይቱ፣ እንዲሁም በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በርካታ የታሪክና የፈተና ምዕራፎችን አልፎ ዛሬ ላይ ደርሷል።
ደብሩ ከሃይማኖታዊ አገልግሎቱ ባሻገር፣ የአዲስ አበባ የመጀመሪያው የቀብር ቦታ በመሆን የሊቃውንቱና የካህናቱ እንዲሁም የታላቁ ሐኪም ወርቅነህ እሸቴን፣ የኢትዮጵያ ታላላቅ ጄነራሎችና ፊት አውራሪዎችን ዓጽም በክበር ማረፊያ ሆኗል፡፡ የጸሎትና ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሁም ለአካባቢው አብያተ ክርስቲያናት መመስረት ባደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይታወቃል። ዛሬ ይህ ታሪካዊ ደብር ጥንታዊ ታሪኩንና መንፈሳዊ ታላቅነቱን በዘመናዊ ማህበራዊ ልማት ለመድገም፣አካላዊ ፈውስን በሳይንሳዊ ሕክምና የመንፈሳዊ ፈውስን በፀሎትና በጠበል የሚያዋህድ ታላቅ የልማት ፕሮጀክት ይፋአድርጓል።
2. የሆስፒታሉ ይዘት፣ ራዕይና ሰብዓዊ ተልዕኮ
ቤተክርስቲያኑ ባለ 15 ወለል ማለትም (2 Basement+G+ 12ወለል) የሆነውን «ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል» ህንፃ ግንባታ የጀመረ ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ምዕራፍ የመሰረት ቁፋሮና የአፈር ናዳ መከላከያ (ሾሪንግ) ሥራ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
ይህ በ1000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈውና ባለ 250 የህሙማን ሕክምና መስጫ አልጋ አቅም የሚኖረው ዘመናዊ ሆስፒታል፤ የተመላላሽ ክሊኒኮችን፣ የፅኑ ሕክምና (ICU)፣ የቀዶ ጥገና ክፍሎችን እንዲሁም ለእናቶችና ሕጻናት ጤና፣ ለልብ ሕክምናና ለተላላፊ በሽታዎች መከላከያ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ማዕከላትን ያካትታል። ተቋሙ የጤና አጠባበቅን እንደ ንግድ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊና መንፈሳዊ አገልግሎት በመመልከት፣ለሁሉም የማህበረሰቡ አባላት በሙሉ ጥራት ያለው፣ ተደራሽና አቅምን ያገናዘበ የሕክምና አገልግሎት ያቀርባል።
3. የግንባታ ወጪ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ
በህንፃ ባለሙያዎች ጥናት መሠረት ለህንፃ ግንባታው አጠቃላይ ወጪ ብር 405,040,000 (አራት መቶ አምስትሚሊዮን አርባ ሺህ ብር) እንደሚሆን ተገምቷል።ይህ ወጪ በየጊዜው በሚታየው የዋጋ ንረት ምክንያት ሊጨምር እንደሚችል ይታሰባል፡፡
ይህንን ከፍተኛ ወጪ ለመሸፈንና ቀጣዩን ወሳኝ የግንባታምዕራፍ ለመጀመር ቤተ ክርስቲያኑ በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚኖሩ ምዕመናንን፣ የንግዱን ማህበረሰብና የልማት አጋሮችን ያሳተፈ የሀብት ማሰባሰቢያ ስልት ቀይሷል።
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ እና የልማት ኮሚቴው ምዕመናን በሰጦታቸው ከእግዚአብሔር የሚያገኙትን በረከት በማሰብ፦ «ይህ ታላቅ የማህበራዊና የጤና ልማት ፕሮጀክት ፍጻሜ እንዲያገኝ የዓላማው ደጋፊዎች ሁሉ የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉና አሻራቸውን እንዲያኖሩ በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ስም እንማጸናለን» ሲል ጥሪውን ያስተላልፋል።
የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ዝርዝር፦
• ቀን፦ ነሐሴ 8፣ 9 እና 10 ቀን 2018 ዓ.ም
• ሰዓት፦ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ
የገቢ ማሰባሰቢያ የባንክ አማራጮች፦
• የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብቁጥር፦
1000000764087 እንዲሁም
አጭር ቁጥር 1277
• አባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፦ 1227
• አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር
013521784586601
• ስዊፍት ኮድ AWINETAA
• ወገን ፈንድ 👉 ሊንክ ኮመንት ላይ አለ
ለተጨማሪ መረጃ፦
• ስልክ ቁጥር፦
0945881188 እና 0945771188
• Email፦ Seyoumwgebrielgmail .com
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።

2ኛው የአዲስ አበባ ሆስፒታሊቲ እና ቱሪዝም እውቅናና ሽልማት ሊካሄድ ነው!
#fastmereja :-የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበር (AAHTPA) የ2ኛውን የከተማዋን የሆስፒታሊቲ እና ቱሪዝም እውቅናና ሽልማት መርሃ-ግብር የፊታችን ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል እና ስፓ እንደሚያካሂድ በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
ማኅበሩ ይፋ ባደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ይህ የእውቅና መርሃ-ግብር ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት ሦስት ዓመታት በዘርፉ የታዩ አበይት አፈጻጸሞችን ለማበረታታት፣ የአገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ እና የላቀ ሙያዊ ብቃትን ለማጠናከርአልሞ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
በእውቅና መርሃ-ግብሩ ላይ በመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአካዳሚክ ተመራማሪዎች፣ የዘርፉ ባለሃብቶችና ባለሙያዎች በተገኙበት በ4 ዋና ዋና ዘርፎች ከ25 በላይ ሽልማቶች እንደሚሰጡ ተገልጿል።
ሽልማቶቹም የግል ሙያዊ ብቃትን፣ የድርጅቶችንና የሆቴሎችን አርአያነት፣ የማኅበረሰብና የአካባቢ ጥበቃ ተጽዕኖን እንዲሁም ለዘርፉ ዕድገት የሕይወት ዘመን አስተዋፅኦ ያበረከቱ አካላትን የሚዘክሩ ናቸው።
የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህNC (AAHTPA) ፕሬዝዳንት አቶ አሸናፊ ሙሉጌታ እንደገለፁት የምርጫ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ በገለልተኝነትና በግልጽነት የተከናወነ ሲሆን፤ የአገልግሎት ጥራት፣ የደንበኞች እርካታ፣ የሥራ አካባቢ ምችት፣ የሙያ ሥነ-ምግባርና ሀገራዊ አስተዋፅኦ በዋና መመዘኛነት መያዛቸዉም ነዉ የተገለፀዉ።
ከእውቅና አሰጣጡ በተጨማሪ «የሆስፒታሊቲ ዘርፍ ለታላላቅ ኩነቶች፦ የኢትዮጵያን ቱሪዝም መፃኢ ዕድል መቅረጽ» በሚል ርዕስ ከፍተኛ የፓናል ውይይት የሚካሄድ ሲሆን ውይይቱ ሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ታላላቅ ኩነቶችን (Mega-Events) በብቃት ለማስተናገድ የሚያስችላትን የተቀናጀ አሠራር በመንግሥት ፖሊሲ፣ በትምህርት ተቋማትና በሆቴሎች መካከል ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበር ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የባለሙያዎችን አቅም በመገንባት፣ የሥራ ዕድል ትስስር በመፍጠር፣ የአሠሪና ሠራተኛ ውዝግቦችን በመፍታትና የሀገርን የበጎ ገጽታ በማስተዋወቅ ረገድ በርካታ አዎንታዊ እርምጃዎችን ሲወስድ መቆየቱ ይታወሳል።

ከኩርሙክ ወርቅ እስከ ዳንጎቴ ማዳበሪያ በማዕድን እና በግብርና የሚመራው የኢትዮጵያ አዲሱ የኢኮኖሚ ሽግግር
********************
ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መዋቅሯን ለማዘመን እና የገቢ ምንጮቿን ለማስፋፋት የምታደርገው ጥረት በአሁኑ ወቅት አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።
ኢትዮጵያ የምድር ውስጥ ሀብቷን በስፋት ማልማት ላይ ትኩረት ማድረጓን ተከትሎ፣ የማዕድን ዘርፉ ለኢኮኖሚ እድገቷ አዲስ የብርሃን ጭላንጭል እየሆነ መጥቷል።
በተለይም እንደ ኩርሙክ ያሉ ግዙፍ የማዕድን ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ መግባታቸው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት መንገድ ከፍቷል።
በዚህም መሰረት ወርቅ በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከሚላኩ ዋና ዋና የወጪ ንግድ ምርቶች አንዱ በመሆን፣ ከዚህ ቀደም ሙሉ በሙሉ በግብርና ምርቶች ላይ ተንጠልጥሎ የነበረውን የንግድ ሚዛን ማስተካከል አስችሏል።
በሌላ በኩል መንግሥት የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል። ግብርና የሀገራችን ኢኮኖሚ ዋነኛ አከርካሪ እንደመሆኑ መጠን ሀገራችን በምግብ አቅርቦት በራስ እንድትተማመን ለማድረግ የታለሙ የካፒታል ኢንቨስትመንቶች እየተከናወኑ ነው።
በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገነባው ግዙፍ የማዳበሪያ ፋብሪካ የዚሁ ጥረት አካል እንደሆነ ይጠቀሳል። ይህ የአፍሪካው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ የ2.5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት 3 ሚሊዮን ቶን የዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም ይኖረዋል።
ይህ ታሪካዊ እንቅስቃሴ ሀገራችን ለግብርና ግብአት ከውጭ ለማስገባት የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት በእጅጉ ይረዳል።
ይህ እንቅስቃሴ የሀገራችንን የእርሻ ምርታማነት ከመጨመሩ ባሻገር፣ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተቀመጠ ትልቅ እቅድ ነው።
በኢንቲሃድ አብራር
#ethiopia #ebc #economicgrowth #miningindustry #agriculture #investment
********************
ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መዋቅሯን ለማዘመን እና የገቢ ምንጮቿን ለማስፋፋት የምታደርገው ጥረት በአሁኑ ወቅት አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።
ኢትዮጵያ የምድር ውስጥ ሀብቷን በስፋት ማልማት ላይ ትኩረት ማድረጓን ተከትሎ፣ የማዕድን ዘርፉ ለኢኮኖሚ እድገቷ አዲስ የብርሃን ጭላንጭል እየሆነ መጥቷል።
በተለይም እንደ ኩርሙክ ያሉ ግዙፍ የማዕድን ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ መግባታቸው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት መንገድ ከፍቷል።
በዚህም መሰረት ወርቅ በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከሚላኩ ዋና ዋና የወጪ ንግድ ምርቶች አንዱ በመሆን፣ ከዚህ ቀደም ሙሉ በሙሉ በግብርና ምርቶች ላይ ተንጠልጥሎ የነበረውን የንግድ ሚዛን ማስተካከል አስችሏል።
በሌላ በኩል መንግሥት የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል። ግብርና የሀገራችን ኢኮኖሚ ዋነኛ አከርካሪ እንደመሆኑ መጠን ሀገራችን በምግብ አቅርቦት በራስ እንድትተማመን ለማድረግ የታለሙ የካፒታል ኢንቨስትመንቶች እየተከናወኑ ነው።
በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገነባው ግዙፍ የማዳበሪያ ፋብሪካ የዚሁ ጥረት አካል እንደሆነ ይጠቀሳል። ይህ የአፍሪካው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ የ2.5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት 3 ሚሊዮን ቶን የዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም ይኖረዋል።
ይህ ታሪካዊ እንቅስቃሴ ሀገራችን ለግብርና ግብአት ከውጭ ለማስገባት የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት በእጅጉ ይረዳል።
ይህ እንቅስቃሴ የሀገራችንን የእርሻ ምርታማነት ከመጨመሩ ባሻገር፣ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተቀመጠ ትልቅ እቅድ ነው።
በኢንቲሃድ አብራር
#ethiopia #ebc #economicgrowth #miningindustry #agriculture #investment
2 days ago
የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሚያሰራውን ቤተሰሊሆም አጠቃላይ ሆስፒታል ህንፃ ግንባታን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡
ከሁሉ አሰቀድመን እግዚአብሔር አምላካችን ለ2018 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሁላችንንም በሰላም በጤና ስላደረሰን እናመሰግነዋለን፡፡የተከበራችሁ አበው መነኮሳት፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ካህናት እና ዲያቆናት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ ምዕመናን እና ወጣቶች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንዲሁም ይህን መልእክት ለመላው ዓለም ለማስተላለፍ የተገኛችሁ የሚድያ አካላት በሙሉ በእግዚአብሔር ስም የከበረ ሰላምታችንን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከሆነው ከየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እናቀርባለን፡፡
“በኂሩተ ጻድቃን ትረትዕ ሀገር”
“በጻድቃን ልማት ከተማ ደስ ይላታል”
ምሳ 11፥10
እግዚአብሔር በንጉሱ ሰሎሞን ላይ አድሮ የተናገረውን መነሻ በማድረግ ልማት ለቤተከርስቲያን ፣ልማት ለሀገር፣ልማት ለማኅበረ ስብእ አስፈላጊ መሆኑን በማሰብ በአዲስ አበባ ሀገረ ስበከት በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለሚገነባው ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል የህንፃ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት መርሃ ግብር የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡ የእግዚአበሔር ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን፡፡ አሜን።
1. ታሪካዊ ዳራ እና የልማት መነሻ
ከአክሱም ዘመነ መንግሥት (በአባ ሰላማ ዘመን) የጀመረውና ከ1600 ዓመታት በላይ የዘለቀው የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ የኢትዮጵያን ጥንታዊነትና የአዲስ አበባን ከተማ አመሰራረት የሚተርክ ህያው ቅርስ ነው።ይህ ታሪካዊ ደብር በአብርሃ ወአጽብሃ፣ በዳግማዊ አጼ ምኒልክና በንግሥት ጣይቱ፣ እንዲሁም በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በርካታ የታሪክና የፈተና ምዕራፎችን አልፎ ዛሬ ላይ ደርሷል።
ደብሩ ከሃይማኖታዊ አገልግሎቱ ባሻገር፣ የአዲስ አበባ የመጀመሪያው የቀብር ቦታ በመሆን የሊቃውንቱና የካህናቱ እንዲሁም የታላቁ ሐኪም ወርቅነህ እሸቴን፣ የኢትዮጵያ ታላላቅ ጄነራሎችና ፊት አውራሪዎችን ዓጽም በክበር ማረፊያ ሆኗል፡፡ የጸሎትና ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሁም ለአካባቢው አብያተ ክርስቲያናት መመስረት ባደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይታወቃል። ዛሬ ይህ ታሪካዊ ደብር ጥንታዊ ታሪኩንና መንፈሳዊ ታላቅነቱን በዘመናዊ ማህበራዊ ልማት ለመድገም፣አካላዊ ፈውስን በሳይንሳዊ ሕክምና የመንፈሳዊ ፈውስን በፀሎትና በጠበል የሚያዋህድ ታላቅ የልማት ፕሮጀክት ይፋአድርጓል።
2. የሆስፒታሉ ይዘት፣ ራዕይና ሰብዓዊ ተልዕኮ
ቤተክርስቲያኑ ባለ 15 ወለል ማለትም (2 Basement+G+ 12ወለል) የሆነውን «ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል» ህንፃ ግንባታ የጀመረ ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ምዕራፍ የመሰረት ቁፋሮና የአፈር ናዳ መከላከያ (ሾሪንግ) ሥራ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
ይህ በ1000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈውና ባለ 250 የህሙማን ሕክምና መስጫ አልጋ አቅም የሚኖረው ዘመናዊ ሆስፒታል፤ የተመላላሽ ክሊኒኮችን፣ የፅኑ ሕክምና (ICU)፣ የቀዶ ጥገና ክፍሎችን እንዲሁም ለእናቶችና ሕጻናት ጤና፣ ለልብ ሕክምናና ለተላላፊ በሽታዎች መከላከያ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ማዕከላትን ያካትታል። ተቋሙ የጤና አጠባበቅን እንደ ንግድ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊና መንፈሳዊ አገልግሎት በመመልከት፣ለሁሉም የማህበረሰቡ አባላት በሙሉ ጥራት ያለው፣ ተደራሽና አቅምን ያገናዘበ የሕክምና አገልግሎት ያቀርባል።
3. የግንባታ ወጪ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ
በህንፃ ባለሙያዎች ጥናት መሠረት ለህንፃ ግንባታው አጠቃላይ ወጪ ብር 405,040,000 (አራት መቶ አምስትሚሊዮን አርባ ሺህ ብር) እንደሚሆን ተገምቷል።ይህ ወጪ በየጊዜው በሚታየው የዋጋ ንረት ምክንያት ሊጨምር እንደሚችል ይታሰባል፡፡
ይህንን ከፍተኛ ወጪ ለመሸፈንና ቀጣዩን ወሳኝ የግንባታምዕራፍ ለመጀመር ቤተ ክርስቲያኑ በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚኖሩ ምዕመናንን፣ የንግዱን ማህበረሰብና የልማት አጋሮችን ያሳተፈ የሀብት ማሰባሰቢያ ስልት ቀይሷል።
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ እና የልማት ኮሚቴው ምዕመናን በሰጦታቸው ከእግዚአብሔር የሚያገኙትን በረከት በማሰብ፦ «ይህ ታላቅ የማህበራዊና የጤና ልማት ፕሮጀክት ፍጻሜ እንዲያገኝ የዓላማው ደጋፊዎች ሁሉ የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉና አሻራቸውን እንዲያኖሩ በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ስም እንማጸናለን» ሲል ጥሪውን ያስተላልፋል።
የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ዝርዝር፦
• ቀን፦ ነሐሴ 8፣ 9 እና 10 ቀን 2018 ዓ.ም
• ሰዓት፦ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ
የገቢ ማሰባሰቢያ የባንክ አማራጮች፦
• የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብቁጥር፦
1000000764087 እንዲሁም
አጭር ቁጥር 1277
• አባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፦ 1227
• አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር
013521784586601
• ስዊፍት ኮድ AWINETAA
• ወገን ፈንድ 👉 https://www.wegenfund.com/...
ለተጨማሪ መረጃ፦
• ስልክ ቁጥር፦
0945881188 እና 0945771188
• Email፦ Seyoumwgebrielgmail .com
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።
ከሁሉ አሰቀድመን እግዚአብሔር አምላካችን ለ2018 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሁላችንንም በሰላም በጤና ስላደረሰን እናመሰግነዋለን፡፡የተከበራችሁ አበው መነኮሳት፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ካህናት እና ዲያቆናት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ ምዕመናን እና ወጣቶች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንዲሁም ይህን መልእክት ለመላው ዓለም ለማስተላለፍ የተገኛችሁ የሚድያ አካላት በሙሉ በእግዚአብሔር ስም የከበረ ሰላምታችንን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከሆነው ከየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እናቀርባለን፡፡
“በኂሩተ ጻድቃን ትረትዕ ሀገር”
“በጻድቃን ልማት ከተማ ደስ ይላታል”
ምሳ 11፥10
እግዚአብሔር በንጉሱ ሰሎሞን ላይ አድሮ የተናገረውን መነሻ በማድረግ ልማት ለቤተከርስቲያን ፣ልማት ለሀገር፣ልማት ለማኅበረ ስብእ አስፈላጊ መሆኑን በማሰብ በአዲስ አበባ ሀገረ ስበከት በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለሚገነባው ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል የህንፃ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት መርሃ ግብር የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡ የእግዚአበሔር ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን፡፡ አሜን።
1. ታሪካዊ ዳራ እና የልማት መነሻ
ከአክሱም ዘመነ መንግሥት (በአባ ሰላማ ዘመን) የጀመረውና ከ1600 ዓመታት በላይ የዘለቀው የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ የኢትዮጵያን ጥንታዊነትና የአዲስ አበባን ከተማ አመሰራረት የሚተርክ ህያው ቅርስ ነው።ይህ ታሪካዊ ደብር በአብርሃ ወአጽብሃ፣ በዳግማዊ አጼ ምኒልክና በንግሥት ጣይቱ፣ እንዲሁም በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በርካታ የታሪክና የፈተና ምዕራፎችን አልፎ ዛሬ ላይ ደርሷል።
ደብሩ ከሃይማኖታዊ አገልግሎቱ ባሻገር፣ የአዲስ አበባ የመጀመሪያው የቀብር ቦታ በመሆን የሊቃውንቱና የካህናቱ እንዲሁም የታላቁ ሐኪም ወርቅነህ እሸቴን፣ የኢትዮጵያ ታላላቅ ጄነራሎችና ፊት አውራሪዎችን ዓጽም በክበር ማረፊያ ሆኗል፡፡ የጸሎትና ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሁም ለአካባቢው አብያተ ክርስቲያናት መመስረት ባደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይታወቃል። ዛሬ ይህ ታሪካዊ ደብር ጥንታዊ ታሪኩንና መንፈሳዊ ታላቅነቱን በዘመናዊ ማህበራዊ ልማት ለመድገም፣አካላዊ ፈውስን በሳይንሳዊ ሕክምና የመንፈሳዊ ፈውስን በፀሎትና በጠበል የሚያዋህድ ታላቅ የልማት ፕሮጀክት ይፋአድርጓል።
2. የሆስፒታሉ ይዘት፣ ራዕይና ሰብዓዊ ተልዕኮ
ቤተክርስቲያኑ ባለ 15 ወለል ማለትም (2 Basement+G+ 12ወለል) የሆነውን «ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል» ህንፃ ግንባታ የጀመረ ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ምዕራፍ የመሰረት ቁፋሮና የአፈር ናዳ መከላከያ (ሾሪንግ) ሥራ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
ይህ በ1000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈውና ባለ 250 የህሙማን ሕክምና መስጫ አልጋ አቅም የሚኖረው ዘመናዊ ሆስፒታል፤ የተመላላሽ ክሊኒኮችን፣ የፅኑ ሕክምና (ICU)፣ የቀዶ ጥገና ክፍሎችን እንዲሁም ለእናቶችና ሕጻናት ጤና፣ ለልብ ሕክምናና ለተላላፊ በሽታዎች መከላከያ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ማዕከላትን ያካትታል። ተቋሙ የጤና አጠባበቅን እንደ ንግድ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊና መንፈሳዊ አገልግሎት በመመልከት፣ለሁሉም የማህበረሰቡ አባላት በሙሉ ጥራት ያለው፣ ተደራሽና አቅምን ያገናዘበ የሕክምና አገልግሎት ያቀርባል።
3. የግንባታ ወጪ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ
በህንፃ ባለሙያዎች ጥናት መሠረት ለህንፃ ግንባታው አጠቃላይ ወጪ ብር 405,040,000 (አራት መቶ አምስትሚሊዮን አርባ ሺህ ብር) እንደሚሆን ተገምቷል።ይህ ወጪ በየጊዜው በሚታየው የዋጋ ንረት ምክንያት ሊጨምር እንደሚችል ይታሰባል፡፡
ይህንን ከፍተኛ ወጪ ለመሸፈንና ቀጣዩን ወሳኝ የግንባታምዕራፍ ለመጀመር ቤተ ክርስቲያኑ በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚኖሩ ምዕመናንን፣ የንግዱን ማህበረሰብና የልማት አጋሮችን ያሳተፈ የሀብት ማሰባሰቢያ ስልት ቀይሷል።
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ እና የልማት ኮሚቴው ምዕመናን በሰጦታቸው ከእግዚአብሔር የሚያገኙትን በረከት በማሰብ፦ «ይህ ታላቅ የማህበራዊና የጤና ልማት ፕሮጀክት ፍጻሜ እንዲያገኝ የዓላማው ደጋፊዎች ሁሉ የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉና አሻራቸውን እንዲያኖሩ በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ስም እንማጸናለን» ሲል ጥሪውን ያስተላልፋል።
የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ዝርዝር፦
• ቀን፦ ነሐሴ 8፣ 9 እና 10 ቀን 2018 ዓ.ም
• ሰዓት፦ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ
የገቢ ማሰባሰቢያ የባንክ አማራጮች፦
• የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብቁጥር፦
1000000764087 እንዲሁም
አጭር ቁጥር 1277
• አባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፦ 1227
• አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር
013521784586601
• ስዊፍት ኮድ AWINETAA
• ወገን ፈንድ 👉 https://www.wegenfund.com/...
ለተጨማሪ መረጃ፦
• ስልክ ቁጥር፦
0945881188 እና 0945771188
• Email፦ Seyoumwgebrielgmail .com
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።
2 days ago
ሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ኩባንያዎቹ ምን እየሰሩ ነው?
👉የብረት ፋብሪካው በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ከአካባቢ ብከላ ነጻ የሆነ የምርት ሂደት መጀመሩ ተነግሯል፡፡
በሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኙት ስቲሊ አር ኤም አይ እና አስመን ኃ/የተ/ግ/ማ እንደ አገር በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተቀመጠውን የኢንደስትሪ ቅጥር ግቢ ሁለት በመቶ ከባቢ በአረንገዴ የመሸፈን ሃላፊነት ተወጥተው ኢንደስትሪዎቹ በሚገኙበት አቅራቢያ የማህበረሰብ አቀፍ የአካባቢ ልማት ላይ በጉልህ መሳተፍ እንደቀጠሉ ተገለጠ፡፡
ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ኢንደስትሪዎቹ በሚገኙበት የቢሾፍቱ ከተማ ቅጥር ግቢ እና አካባቢው በሚገኙ የተራቆቱ ስፍራዎቸን በአረንጓዴ የመሸፈን ስራ አጠናክረው የቀጠለ መሆኑ ታውቋል፡፡
በዚህም ዘንድሮው የክረምት ወቅት ከመንግስት ተረክበው መልሶ እንዲያገግም እየተንከባከቡት በሚገኘው ዲባዬ ተራራ በተከታታይ ለ 5ኛ አመት የተከላ መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡
ሀሙስ ሐምሌ 30 ቀን በተከናወነው እና የሁለቱ ኩባንያ ሰራተኞች በተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቢሾፍቱ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፅ/ቤት ኃላፊ ጣይቱ ያሚ የሁለቱ ድርጅቶች የአረንጓዴ ልማት ተግባር በአካባቢው ለሚገኙ በርካታ ኢንደስትሪዎች አርአያ እና ቀዳሚ ነው ብለዋል፡፡
እንደ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከኢንደስትሪ ግቢ 2 በመቶ በአረንጓዴ መሸፈን አለበት የሚለውን ህግ በተገቢው ሁለቱም ድርጅቶች መወጣታቸውን አስታውሰው፡፡
በተጨማሪነት በሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኙት ስቲሊ አር ኤም አይ እና አስመን ከኢንደስትሪ ስፍራዎቻቸው ባለፈ በአዋሳኝ የመንገድ አካባቢዎች እንዲሁም የተራቆቱ ቦታዎችን ወደ ጫካ የመለወጥ ስራን እንዲወጡ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጣቸውን ቦታዎች በዛፍ የመሸፈን ስራ ለአመታት በከፍተኛ ሃላፊነት ሲሰሩ እንደቆዩ ነው የተናገሩት፡፡
ከተማ አሰስተዳደሩ በአረንጓዴ ልማት ሆነ ሌሎች ማህበራዊ ሃላፊነት ስራዎች ጥሪ ባደረገ ጊዜ ቀድመው የሚገኙ መሆናቸውን ያስታወሱት የከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ጣይቱ ይህን መልካም ተግባር ሌሎች በተሞክሮ እንዲወስዱት ነው ያሳሰቡት፡፡
በተከላው ወቅት የግዙፉ ብረት አምራች ስቲሊ አር ኤም አይ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ሰለሞን ደስታ እንደገለፁት ድርጅታቸው ስቲሊ በመርህ ደረጃ የተያዘውን የማህበራዊ ሃላፊነት የመወጣት ተግባር በህብረተሰብ ድጋፍ ላይ ብቻ ያተኮረ አለመሆኑን አስታውሰው፡፡
በአካባቢ ጠበቃ የሚሰራው ስራ የኩባንያው አይነተኛ መርህ መሆኑን እንደ ተጨማሪ የማህበራዊ ሃላፊነት ስራ ተግባር ለአብነት አንስተዋል፡፡
በዚህም ስቲሊ አር ኤም አይ ማምረት ከጀመረበት ያለፉት ሁለት አስርት አመታት ወደ ስራ ካስገባቸው እንደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት እንዲሁም የውሃ አቅርቦት አይነት ጉልህ ማህበራዊ ሃላፊነት ባልተናነሰ በአረንጓዴ ልማት ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡
በግቢያችን በመንግስት ከተቀመጠው የሁለት በመቶ አረንጓዴ ሽፋን አልፈናል ያሉት ኢ/ር ሰለሞን ለምግብነት የሚያገለግሉ ዛፎችን የመትከል ግቡም ውጤታማ እየሆነልን ነው ሲሉ ነው ያከሉት።
ዋና ስራ አስኪያጁ በተጨማሪነት በአካበቢው በሚገኙ ተራራማ ቦታዎች ችግኝ በመትከል እና በቋሚነት ባለሞያ ቀጥሮ በመንከባከብ ከፍተኛ ውጤት ማስገኘት መቻሉንም እንደ ከፍተኛ ተጠቃሽ ውጤት አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም ኩባያው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በማድረግ ዘመናዊ የምርት ሂደትን ያስተዋወቀ መሆኑን ጠቅሰው። ይህም የአካባቢ ጥበቃ አካል ነው ሲሉ በአገር ደረጃ በዘመናዊነት ቀዳሚ የሆነው የብረት ፋብሪካ የስራ ሂደት ጠቅሰዋል፡፡
በተመሳሳይ ከፍተኛ ተኪ የብረት ምርት እና የግንባታ ግብአቶችን በማምረት ላለፉት ሩብ ክፍለ ዘመናት መቆየት የቻለው የአስመን ስራ አስኪያጅ አቶ ኑሩ እሸቱ የአረንጓዴ አሻራ ስራ የኩባንያቸው ባህል መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ይህ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጠል መሆኑን ነው የገለፁት፡፡
እንደ አስመን ስራ አስኪያጅ ገለፃ የኩባንያውን ሰራተኛና የአካበባቢውን ነዋሪ በማሳተፍ ሲከናወን የቆየው የአካባቢ ጥበቃ ስራ በተለይ አሁን በፋብሪካዎቹ እና የችግኝ ተከላ በሚከናወንበት አቅራቢያ በሚገኘው በአቡሴራ እየተገነባ የሚገኘው የቢሾፍቱ አየር መንገድ ምቹ እና አረንጓዴ ከባቢ በመፍጠር የራሱ ሚና አለው ሲሉ ነው የገለጹት፡፡
የሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የቦርድ ተወካይ አቶ ግርማ አዲስ በበኩላቸው ስቲሊ አር ኤም አይ እና አስመን አረጋውያን የማገዝ፣ ተንከባካቢ የሌላቸው ህጻናትን ከጎናቸው በመሆን አሌንታነት በማረጋገጥ፣ የምገባ ማዕከላትን በማቋቋም፣ በተለያየ ምክንያት እና እንደ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ አይነት አጣዳፊ ሁኔታ ሲያጋጥም ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ የወገን ደራሽ የመሆን ሚናቸውን ከምስረታቸው ጀምሮ እንደተገበሩ ገልፀዋል፡፡
ይህንኑ ተግባር ወደ ፊትም በተቀናጀ መልኩ እንደ ግሩፕ ለማከናወን ፋውንዴሽን መቋቋሙን ነው አክለው የገለጹት፡፡

3 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በህጻናት ክትባት እና በኦቲዝም ዙሪያ አዲስ አስፈጻሚ ትዕዛዝ በቀጣዩ ሳምንት ሊያወጣ እንደሚችል ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ምንጮች አጋለጡ። አስርተ ዓመታትን ያስቆጠሩ ሳይንሳዊ ምርምሮች በክትባት እና በኦቲዝም መካከል ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለ በተደጋጋሚ ቢያረጋግጡም፣ ፕሬዝዳንቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ፍላጎት ማሳየታቸው ተገልጿል።
የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ኩሽ ዴሳይ እንዳሉት፣ "አሜሪካ በዓለም ምርጡን የህጻናት የክትባት መርሐ-ግብር ሊኖራት ይገባል" የሚለው የፕሬዝዳንቱ አቋም ግልጽ ነው። አስተዳደሩም ጥያቄ እና ስጋት ላላቸው በርካታ ወላጆች በሳይንስ ላይ የተመሰረተ ምላሽ ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል። ከዚህ ቀደም ትራምፕ በግንቦት ወር ባወጡት ትዕዛዝ የክትባት መጠኖችን በመቀነስ ከሌሎች ሀገራት ጋር ለማስተካከል የሞከሩ ሲሆን፣ የጤና እና የሰብዓዊ አገልግሎት ጸሐፊው ሮበርት ኤፍ. ኬኔዲ ጁኒየር መደበኛ የክትባት መርሐ-ግብሮችን ለመቀየር ያደረጉት ሙከራ በፍርድ ቤት መታገዱ ይታወሳል።
ባለፈው ሳምንት በካምፕ ዴቪድ በተካሄደ የካቢኔ ስብሰባ ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ ቀደም ሲል የጸረ-ክትባት ቡድንን ሲመሩ ለነበሩት ሮበርት ኤፍ. ኬኔዲ ጁኒየር ስለ ኦቲዝም መንስኤ ምርምር ሂደት በአደባባይ የጠየቋቸው ሲሆን፣ ኬኔዲም "መልስ ይዘን እንመጣለን" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ይህ አዲስ ትዕዛዝ፣ ከመጪው የአጋማሽ ዘመን ምርጫ በፊት አወዛጋቢ ጉዳዮችን ላለማንሳት የጤና ባለስልጣናት ይዘውት የነበረውን ስትራቴጂ የሚቀለብስ እና ርዕሱን ዳግም ወደ አደባባይ የሚያመጣው እንደሚሆን ተገምቷል።

ምክክር ለዘላቂ ሠላም
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከጥንታዊ ነጻ ሀገረ መንግሥታት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በበርካታ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና እሴቶች የተዋቀረች ኅብረብሔራዊት ሀገር ናት፡፡
ከ130 ሚሊየን በላይ ሕዝብ መኖሪያ የሆነችው ሀገራችን ህልውናዋን አጽንታ ዘመናትን መሻገር የቻለችው በልጆቿ የተባበረ ክንድ ስለመሆኑ ታሪክ ህያው ምስክር ነው።
በእነዚያ ጊዜያት ውስጥ ሰላሟንና ልማቷን ሲፈታተኑ የዘለቁ ቅራኔዎችን በሰላማዊ ውይይት በመፍታት ነገዋን የተሻለ ለማድረግ በሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ትገኛለች፡፡
ዜጎቿ ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጥ የጋራ መግባባት ላይ የሚያደርስ መፍትሄ እንዲያበጁ በገለልተኛ የምክክር ኮሚሽን የሚመራ አሳታፊና አካታች ሀገራዊ መድረክ አበጅታለች፡፡
ይህ አሳታፊነት ምክከሩ በሀገሪቱ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ከታዩ እጅግ ሰፊና ለውጥ አምጪ እንቅስቃሴዎች መካከል አንዱ መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡
ለብዙ ዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ አለመግባባቶች ዛሬም ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚቀሰቀሱ ግጭቶችና የሰላም እጦት በምክንያትነት ሲቀርቡ ይስተዋላል፡፡
ሀገር በቀል እውቀቶችንና ባህላዊ የውይይት እሴቶችን ማዕከል በማድረግ እየተካሄደ የሚገኘው ሀገራዊ ምክክር እነዚህን የቆዩ ቁርሾዎች በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል፡፡
የጋራ ሀገራዊ ራዕይ እውን የሚሆንበት ይህ መድረክ ከጊዜያዊ ፖለቲካዊ ጥቅም በላይ የሀገሪቱን የዘላቂ ሰላም ጉዞ የሚያሳልጥ ታሪካዊ እድል ነው፡፡
የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድምፅ እኩል የሚሰማበት ይህ ሀገራዊ ምክክር የአሸናፊና ተሸናፊ ትርክትን በጋራ መግባባት ላይ በተመሠረተ ባህል የሚተካ ወሳኝ መድረክ ነው።
አንዲት ሀገር ለትናንት ቅራኔዎች ሕዝብን ባሳተፈ መንገድ እውነተኛ መፍትሄ ሳትሰጥ ሰላማዊ ነገን መገንባት አትችልም።
በዚህ መንፈስ በእኩልነት ላይ በተመሰረተ፣ ግልጽ፣ ነጻ እና አሳታፊ ሂደት እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር፥ ሀገሪቱን ወደ ብልጽግና የሚያሸጋግር ድልድይ እንዲሁም ከውርስ ህመሟ የሚፈውስ ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡
ግጭትና የሕዝቦች መለያየት የሀገርን ሀብት የሚያወድሙና ልማትን የሚያደናቅፉ በመሆናቸው፤ የሀገርን ጥቅም ባስቀደመ የጋራ መግባባት የተረጋጋ ፖለቲካዊ ሁኔታን በመፍጠር ብሔራዊ ምክክሩ ለጠንካራ ኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት ይጥላል።
የዜጎችን የጋራ መግባባት ጽኑ መሰረት አድርጋ የምትገነባው ሰላማዊት ኢትዮጵያ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቴክኖሎጂና ሌሎች የመሠረተ ልማት ዘርፎች ያላትን አቅም ሙሉ በሙሉ በመጠቀም የዜጎቿን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ትችላለች፡፡
ኢትዮጵያ የአህጉሪቱ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ማዕከል እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ እንደመሆኗ፤ አለመግባባትን በውይይት ለመፍታት የጀመረችው ጉዞ አፍሪካውያን ችግሮችን በራሳቸው ለመፍታት ለሚያደርጉት ጥረት መልካም አርአያ ነው።
የተዋሃደችና ደህንነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድን በማረጋጋት የቀጣናውን የኢኮኖሚ ትስስር፣ ንግድና የጋራ ደህንነት ማረጋገጥ ይቻላታል፡፡
ምክክሩ የአንድ ጊዜ ሁነት ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ሀገራዊ ተቆርቋሪነት የሚጠይቅ የታሰበበት ረጅም ጉዞ ነው።
አለመግባባቶች የማህበረሰብ ተፈጥሯዊ አካል ቢሆኑም ጠንካራ ሀገር የሚገነባው ግን እነዚህን ልዩነቶች ባስተናገዱበት ጤናማ መንገድ እንደሆነ ይታመናል፡፡
ኢትዮጵያ ከግጭት ይልቅ ውይይትን በማስቀደም እያከናወነች የምትገኘው ሀገራዊ ምክክር አንድነት፣ የተቋማት ጥንካሬና ዘላቂ ሰላም የሚጸናበት አዲስ ምዕራፍ ነው፡፡
ከምንጊዜውም በላይ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ በመጠቀም ለወደፊቱ ትውልድ ምቹ ሀገር ለመገንባት ጊዜው አሁን ነው።
በምሕረት ደምሴ

በኮንታ ዞን ሙሉ በሙሉ ተፈጥሯዊነቱን የጠበቀ አዲስ የጫካ ቡና መገኘቱ ተበሰረ!
#fastmereja :-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሚገኘው ታሪካዊው ኮንታ ዞን፣ እስከ ዛሬ በሰው እጅ ያልተነካና ተፈጥሮአዊ ይዘቱን ሙሉ በሙሉ ጠብቆ የቆየ አዲስ የጫካ ቡና (Wild Forest Coffee) ተበሰረ።
ይህ በሰው እጅ ያልተተከለና «ያልተመነዘረ አረንጓዴ ወርቅ» የተባለው አዲስ የቡና ዘር የተገኘው፣ በኮንታ ዞን «ኦሽካ ዴንቻ» ጥቅጥቅ ጫካ ውስጥ በሚገኘው «አሜክ ኤጄቻ» በተሰኘ ልዩ ቦታ ላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን አካባቢው ሰውና የዱር እንስሳት በተስማማ ሁኔታ የሚኖሩበት በመሆኑ፣ የቡናው ተፈጥሯዊ መዓዛና ጣዕም እጅግ ልዩ እንደሆነ ተገልጿል።
ድርጅቱ አዲሱ የቡና ዘር መገኘቱ ለሀገራችን አዲስ ዓለም አቀፍ ብራንድ ይዞ የሚመጣ መሆኑን ጠቁሞ፤ እንደ ጅማ፣ ይርጋጨፌ እና ሐረር ሁሉ «Konta Coffee» በሚል ስም ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ገበያ በመቅረብ፣ የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ብሏል።
በተጨማሪም ያልተነካውን የኮንታ የተፈጥሮ ጫካ እና የቡና መገኛ ቦታዎችን ለዓለም በማስተዋወቅ የኢኮ-ቱሪዝም ዘርፉን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያነቃቃው ገልጿል።
የኮንታ ብሔረሰብ የሙዚቃ አቀንቃኝና የባህል አምባሳደር አርቲስት ወንድወሰን አበበ (ወንዴ ኮንታ) በበኩሉ፣ “«ኑ ቡና ጠጡ» የሚለው ጥሪ የቡና መጠጣት ሥነ-ሥርዓት ብቻ ሳይሆን የሰላም፣ የፍቅር፣ የጽኑ ጉርብትና እና የኢትዮጵያዊነት መስተጋብር ማሳያ ነው” ሲል ተናግሯል።
አርቲስቱ አክሎም ይህንን ውድ ተፈጥሮአዊ ሀብት ጠብቆ ላቆየው ማኅበረሰብ እውቅና መስጠትና ባህሉን ከኪነ-ጥበብ ጋር አዋህዶ ማቅረብ ታሪካዊ ኃላፊነት መሆኑን አብራርቷል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ ለዕይታ ያልበቁና በምስል ያልተቀረፁ የባህል ትውፊቶችን ቅርፃቸውን እንደጠበቁ ለዓለም መድረክ ለማብቃት ሰፊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል።
ይህንን ታሪካዊ ግኝት አስመልክቶ «ቶካ ፊልም መንደር እና ኢኮ ቱሪዝም» (Konta Coffee) በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አዲሱን የጫካ ቡና ይፋ ለማድረግ "ኑ ቡና ጠጡ" የተሰኘ ታላቅ ሀገራዊ ጥሪና የመርሃ ግብር ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።
በዚሁ መሠረት ቶካ ፊልም መንደር ከ«ኪን-ኢትዮጵያ የባህል ቡድን» እና ከ«ቤራ ኢንተርቴይንመንትና ኤቨንትስ» ጋር የጋራ የሥራ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፣ በቅርቡም በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።

"ኑ ቡና ጠጡ" ተብላቹኋል
* በኮንታ ዞን አዲስ የተፈጥሮ የጫካ ቡና መገኘቱን ይፋ ተደረገ
#ethiopia | በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኘው በታሪካዊው ኮንታ ዞን እስከ ዛሬ በሰው እጅ ያልተነካና ተፈጥሮአዊነቱን ፍጹም ጠብቆ የቆየ አዲስ የተፈጥሮ ጫካ ቡና መገኘቱ ተበሰረ።
በኮንታ ዞን ጥቁርና ጥቅጥቅ ባለው «አሜክ ኤጄቻ» ጫካ ውስጥ የተገኘው የቡና ዘር የሀገራችንን የቡና ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የሚያስጀምር መሆኑ ተገልጿል።
ይህንን ታሪካዊ ግኝት አስመልክቶ «ቶካ ፊልም መንደር እና ኢኮ ቱሪዝም» (Konta Coffee) በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አዲሱን የጫካ ቡና ይፋ ለማድረግ "ኑ ቡና ጠጡ" የተሰኘ ታላቅ ሀገራዊ ጥሪና የመርሃ ግብር ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።
ድርጅቱ አዲሱ የቡና ዘር መገኘቱ ለሀገራችን አዲስ ዓለም አቀፍ ብራንድ ይዞ የሚመጣ መሆኑን ገልጿል።
እንደ ጅማ ይርጋጨፌ እና ሐረር ሁሉ «Konta Coffee» በሚል ስም ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ገበያ በመቅረብ የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል።
ያልተነካውን የኮንታ የተፈጥሮ ጫካ እና የቡና መገኛ ቦታዎችን ለዓለም በማስተዋወቅ የዘርፉን ቱሪዝም በከፍተኛ ሁኔታ ያነቃቃዋል ብሏል።
የኮንታ ብሔረሰብ የሙዚቃ አቀንቃኝና የባህል አምባሳደር አርቲስት ወንዴ ኮንታ እንዳለው "ኑ ቡና ጠጡ" የሚለው ጥሪ የቡና መጠጣት ሥነ-ሥርዓት ብቻ ሳይሆን የሰላም የፍቅር የጽኑ ጉርብትና እና የኢትዮጵያዊነት መስተጋብር ማሳያ ነው ።
ይህንን ውድ ተፈጥሮአዊ ሀብት ጠብቆ ላቆየው ማኅበረሰብ እውቅና መስጠትና ባህሉን ከኪነ ጥበብ ጋር አዋህዶ ማቅረብ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው" ሲል ተናግሯል ።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለዕይታ ያልበቁ የባህል ትውፊቶችን ለዓለም ለማስተዋወቅ ቶካ ፊልም መንደር እና ኢኮ ቱሪዝም ከኢትዮጵያ የባህል ቡድን እና ከቤራ ኢንተርቴይንመንት ጋር የጋራ የሥራ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #discoverethiopia #kontacoffee #nubunatetu #ethiopiancoffee #wendekonta

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የሆኑትን አቶ አዘዘው ጫኔን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። ዜናው የሀገሪቱን የፋይናንስ እና የጸጥታ ተቋማት በእጅጉ ያስገረመ ሲሆን፣ ምክትል ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት "ህገ-ወጥ ንግድን እና የኮንትሮባንድ ዝውውርን ይቆጣጠራሉ" ተብሎ በተሰጣቸው ከፍተኛ የኃላፊነት ወንበር ላይ ተቀምጠው፣ በተቃራኒው መንግስትን ለከፍተኛ ኪሳራ የዳረገ የተደራጀ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ነው።
አቶ አዘዘው ጫኔ የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ሀገርን ከኢኮኖሚ አሻጥር ከመጠበቅ ይልቅ አሻጥሩን በዋናነት ሲመሩት እንደነበር ፖሊስ አስታውቋል። ዘ-ሐበሻ የተመለከተው በምክትል ኮሚሽነሩ ላይ ከቀረቡት ዋና ዋና የጥርጣሬ ክሶች መካከል በገቢዎች እና ጉምሩክ አስተዳደር ውስጥ የዘረጉትን ሰፊ መረብ በመጠቀም፣ ትክክለኛ የግብር ምዘናዎችን በማዛባት እና መንግስት ማግኘት የነበረበትን ከፍተኛ ገቢ በማሳጣት የግብር ምዘና ማጭበርበር ወንጀል መፈጸማቸው በዋናነት ይጠቀሳል። ከዚህም በተጨማሪ የሐሰት የክፍያ ደረሰኞችን እና ህገ-ወጥ ሰነዶችን ወደ ተቋሙ ስርዓት በማስገባት እና በማስተናገድ የሰነድ ማጭበርበር እንደፈጸሙ ተገልጿል።
በተያያዘም የመንግሥትን ገቢ ለመቀነስ፣ የፈጸሙትን ወንጀል ዱካ ለማጥፋት እና ምርመራን ለማደናቀፍ ሲባል የተቋሙን ቁልፍ የኮምፒውተር መረጃዎች ሆን ብሎ በመደምሰስ የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎችን በማጥፋት ክስ ቀርቦባቸዋል። ከዚህ ሁሉ ባለፈ፣ አሁን ላይ ሀገሪቱ ተግባራዊ እያደረገች ያለውን የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ለማስተጓጎል በማሰብ፣ ከኮንትሮባንድ አዘዋዋሪዎች እና ከሌሎች ህገ-ወጥ የጥቅም መረቦች ጋር በቀጥታ በመመሳጠር የተደራጀ የኢኮኖሚ አሻጥር መፈጸማቸው በምርመራ መመላከቱን ፖሊስ አብራርቷል።
ይህ ክስተት የህግ የበላይነትን እና የተቋማት ታማኝነትን በተመለከተ ትልቅ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። የህግ ተገዥነትን እንዲያስከብሩ የተሾሙ ከፍተኛ ባለስልጣን፣ የመንግስትን የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎች እስከማጥፋት እና ከኮንትሮባንዲስቶች ጋር እስከመመሳጠር መድረሳቸው በጉምሩክ ኮሚሽኑ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት ላይ ትልቅ የደህንነት ክፍተት መኖሩን ፍንትው አድርጎ ያሳያል።
በተለይም መንግስት የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የውጭ ምንዛሬ እና የገበያ መረጋጋትን ለማምጣት በሚጥርበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ ቁልፍ የተቋሙ አመራሮች ራሳቸው ስርዓቱን ለማፍረስ በሚደረግ አሻጥር ውስጥ መገኘታቸው፣ የጸረ-ሙስና ዘመቻው ከመቼውም ጊዜ በላይ ከራሱ ከመንግስት መዋቅር መጀመር እንዳለበት የሚያመላክት ነው። ፌዴራል ፖሊስ በጉዳዩ ላይ የጀመረውን ጥልቅ ምርመራ አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።

መንግሥት ሌብነትን እና ሕገወጥነትን ለመከላከል ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገለጸ
በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን ሰፊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱ እና የሀገር ሀብት በሚመዘብሩ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታወቀ።
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ፈጣን ልማትና ዕድገት እንድታረጋግጥ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰው፣ በዚህም ሰፋፊና አስደናቂ ሀገራዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህ ሂደት ግን ይህ ውጤት ጉዞው አልጋ በአልጋ እንዳልነበር አመላክተዋል ። ከተለያዩ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች ባሻገር፣ ሕገ-ወጥነት እና የሙስና ተግባራት የልማቱ ዋነኛ ፈተና ሆነው መቆየታቸውንም ክብርት ሚኒስትሯ አብራርተዋል።
እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፣ የሕገ-ወጥነት ችግር በአንድ ወገን ብቻ የሚፈጸም ሳይሆን በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚያጠቃልል መሆኑን ገልጸው ከውስጥም ከውጪም ያሉ በርካታ ኃይሎች በተደራጀ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበር፡፡ በንግዱ ማኅበረሰብ፣ በልማት ድርጅቶች፣ በመንግሥት መዋቅር፣ በግለሰቦች እና በተገልጋዮች ጭምር በተደራጀ መንገድ በስፋት የሚታይ ነው።
እነዚህ አካላት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ከቁጥጥር ውጭ ለማድረግ በፋይናንስ እና በንግድ ሥርዐቱ ውስጥ ሰርገው በመግባት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲፈጽሙ ቆይተዋል" ያሉት ወይዘሮ እናትዓለም፤ ድርጊቱ ሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ፣ የዋጋ ንረትና ኮንትሮባንድ እንዲባባስ እንዲሁም በፍጆታ እቃዎች ላይ ሰው ሠራሽ እጥረት እንዲፈጠር ማድረጉን አስታውቀዋል። ይህንን የተደራጀ አሻጥር ለመግታት መንግሥት እና የሚመለከታቸው የሕግ አካላት ባከናወኑት ሰፊ ኦፕሬሽን አሻጥሩን ማክሸፍ መቻሉ ተገልጿል።
በሌላ በኩል በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ እና አስተዳደር አካላት እንዲሁም የሕዝብ ተቋማት ውስጥ የተሰገሰጉ ሌቦችን በማጽዳት ረገድ መንግሥት ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ያስታወቁት ወ/ሮ እናትዓለም በሕዝብ ሀብት ላይ ከፍተኛ ምዝበራ የፈጸሙ እና ተቋማዊ አሻጥር በሠሩ አመራሮች እና ሌሎች የጥቅም ትስስሮችና ድርጅቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል። በተለይም በሚከተሉት ቁልፍ ዘርፎች ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ሰፊ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት ሰፍኗል ሲሉ ገልጸዋል፡
በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ እና አስተዳደር አካላት፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ የልማት ዘርፎች ውስጥ የተፈጸሙ ዋና ዋና የሙስና እና አሻጥር ወንጀሎችን ለማረም በተወሰዱት ሰፊ ኦፕሬሽኖች እና ሕግ የማስከበር እርምጃዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ማሻሻያውን ለማደናቀፍ በማሰብ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን በማከማቸት እጥረት እንዲፈጠርና ዋጋ እንዲንር ሲያደርጉ የነበሩ 13 አቅራቢ ድርጅቶች ባለቤቶች ላይ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፤ ሕገ-ወጥ ተግባር ሲፈጽሙ በነበሩ ከ7 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶችና መጋዘኖች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል።
በፋይናንስ ተቋማት እና የገንዘብ ዝውውር፡ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሐዋላ እና በጥቁር ገበያ ተሳታፊ የሆኑ 169 ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል። በተደራጀ መንገድ ከንግድ ባንክ ደንበኞች አካውንት ላይ በማጭበርበር ገንዘብ የወሰዱ 36 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የባንክ ሒሳባቸው እንዲታገድ ተደርጓል።
ለሕገ-ወጥ ዝውውር ሽፋን ይሰጡ የነበሩ 7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች በሀገር ውስጥ እንዳይሠሩ ሙሉ በሙሉ ታግደዋል፤ ምርት ልከው የውጭ ምንዛሬ ተመላሽ ያላደረጉ 29 ላኪ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም የህግ ተጠያቂነት ሰፍኗል።
በቤቲንግ እና ፊንቴክ ቢዝነሶች፡ የደንበኞችን መረጃ በመደበቅ መንግሥትን ግብር ያጭበረበሩ፣ ገቢያቸውን የሰወሩ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በፈጸሙ 38 የቤቲንግ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወስዶ ባለቤቶቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ የእነዚህ ሕገ-ወጥ ተቋማት የባንክ ሒሳብ ታግዷል፤
በማዕድን ዘርፍ ሕገ-ወጥ ዝውውር፡ የወርቅ ምርትን ከገበያ ውጭ በኮንትሮባንድ በማስወጣት ወንጀል የተሳተፉ የመንግሥት ኃላፊዎችን፣ የፀጥታ መዋቅር አመራሮችን፣ አምራቾችን እና የውጭ ዜጎችን ጨምሮ 183 ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ ተደርገዋል። በወንጀሉ የተሳተፉ የውጭ ሀገር ዜጎች ከሀገር እንዲወጡ ተደርገዋል፤ ሕገ-ወጥ ወርቅ፣ የወርቅ ሚዛንና ማቅለጫ፣ የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ እንዲሁም የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከነዳጅ አቅርቦት እና ሎጂስቲክስ አንጻር፡ በሕገ-ወጥ መንገድ የሽፋን ደብዳቤዎችን በማዘጋጀት፣ ነዳጅ በመደበቅ እና አየር በአየር በመሸጥ ወንጀል የተሳተፉ 38 የመንግሥት አመራሮች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል። በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድ ላይ የተሰማሩ ከ650 በላይ ግለሰቦች፣ ማደያዎች እና አቅራቢ ኩባንያዎች ላይ የህግ እርምጃ ተወስዷል።
በአፈር ማዳበሪያ ግዢ አሻጥር፡ በተቋሙ የጥቅም ትስስር በመፍጠር ጥራት የጎደለውና ጊዜው ያለፈበት የአፈር ማዳበሪያ ግዢ እንዲፈጸም በማድረግ ሆን ብለው ችግር በፈጠሩ የግብርና ሚኒስቴር አመራሮች ላይ የወንጀል ተጠያቂነት እርምጃ ተወስዷል።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP)፡ ተገቢው መመሪያ በሌለበት ሁኔታ ከ36 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ጋር ሕገ-ወጥ የኃይል ሽያጭ ውል የፈጸሙ 4 ከፍተኛ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል። የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት የፈጸሙ ድርጅቶች እና ግለሰቦችም እንዲሁ በሕግ እንዲጠየቁ ተደርጓል።
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የሰዎች ዝውውር የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ሲስተምን በማዛባት እና ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተሳተፉ 8 ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል። እንዲሁም በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የተሰማሩ 44 ደላሎች እና አዘዋዋሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ ሕገ-ወጥ ፈቃድ የነበራቸው ተቋማት ሙሉ በሙሉ ታሽገዋል።
በገቢዎችና ጉምሩክ ዘርፍ፡ የግብር ውሳኔዎችን በመቀነስ፣ ሐሰተኛ ደረሰኞች በማወራረድ፣ እና በሲስተም መረጃ በማጥፋት የመንግሥት ገቢን ባሳጡ አካላት ላይ ኦፕሬሽን ተካሂዷል። በራሳቸው፣ በዘመድ እና በሹፌሮቻቸው አካውንት በመጠቀም የጥቅም ትስስር የፈጠሩ 109 ተጠርጣሪዎች ተለይተው ከእነዚህ መካከል 91 ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
መንግሥት የልማት እንቅፋት የሆኑትን ሙስና እና ሌብነት እንደማንኛውም ፈተና በጽናት እየተጋፈጣቸው መሆኑን ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል።
መንግሥት ሌብነትን ለማጥፋት ዘመናዊ አሠራሮችን በመዘርጋት እና በዲሲፕሊን የታነጸ አመራር ለመገንባት ቁርጠኛ ነው" ያሉት ወይዘሮ እናትዓለም፤ ሕዝቡ በስፋት የሚያነሣቸውን "ሌብነትን አስቁሙልን" ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመረዉ ጠንካራ እርምጃ ውጤታማ እንዲሆኑ ማኅበረሰቡ ሙስናን በማጋለጥ፣ ሕጋዊ መብቱን በመደለያ ባለመጠየቅ እና ከሕገወጦች ጋር ባለመተባበር ከመንግሥት ጎን በመቆም ሀገርን ከሕገወጥነትና ሙስና የመከላከል ታሪካዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ጤና ልማትና ፀረ‐ወባ ማህበር በአማርኛ የተዘጋጀ የመጀመሪያውን የትምባሆ ቁጥጥር ዲጂታል ዳሽቦርድ ይፋ አደረገ!
#fastmereja :-በኢትዮጵያ በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ ያሉ የተበታተኑ መረጃዎችን በአንድ ማዕከል ለማደራጀትና ተደራሽነታቸውን ለማስፋት ያለመው «የትምባሆ ቁጥጥርዳታ ኢኒሺዬቲቭ» (TCDI Ethiopia) ዳሽቦርድ፣ የአማርኛ ገጾቹን በይዘት በማበልፀግ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመረቀ።
ይህ አገራዊ የዲጂታል ዳሽቦርድ ይፋ የተደረገው የጤና፣ ልማት እና ፀረ-ወባ ማህበር (HDAMA) ከኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን (EFDA) ጋር በመተባበር ባዘጋጁት ልዩ የመክፈቻ መርሃ-ግብር ላይ ነው፡፡
የዳሽቦርዱ በይፋ መከፈት በኢትዮጵያ የትምባሆ ቁጥጥር ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን እና ሕጋዊ ውሳኔዎችን ሙሉ በሙሉ በምርምርና በፅኑ መረጃ (Data-driven decision making) ላይ የተመሰረቱ ለማድረግ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተገልጿል።
ቀደም ሲል በተለያዩ ተቋማት እና ተመራማሪዎች ዘንድ ተበታትነው ይገኙ የነበሩ መረጃዎች በአንድ ቋት መደራጀታቸው፣ ፖሊሲ አውጪዎችና የሕብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች ትክክለኛ አገራዊ ስታቲስቲክሶችን በመጠቀም ፈጣንና ውጤታማ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እንደሚያስችላቸዉ ተገልጿል።
የቋንቋ ተደራሽነትና የባለድርሻ አካላት ምክክር የዳሽቦርዱ ገጾች በአማርኛ ቋንቋ ተበልፅገው መቅረባቸው የመረጃ ተደራሽነትን ከመጨመሩ ባለፈ፣ ለመገናኛ ብዙኃን፣ ለተመራማሪዎችና ለመላው ህብረተሰብ የግንዛቤ ማሳደጊያ ቁልፍ መሳሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል ታውቋል።
በማስጀመርያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የየዘርፉ ባለድርሻ አካላት የዳሽቦርዱን መመረቅ ተከትሎ በስፋት ዉይይት የተካሄደባቸዉ ሲሆን በውይይቱም ዳሽቦርዱ የሚያቀርባቸውን ዳታዎች ለሕግና ፖሊሲ ማሻሻያ አግባብነት ባለው መልኩ ጥቅም ላይ ማዋል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አስተያየቶችን ተለዋውጠዋል።
ይህንን ጠቃሚ ዳሽቦርድ ወደ አማርኛ በመተርጎም፣ በማበልፀግ እና ለዛሬው ማስተዋወቂያ መድረክ የቴክኒክና የመረጃ ማዕከል ድጋፍ ላደረጉት የኢትዮጵያ የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን፣ HDAMA፣ Development Gateway (DG) A Center for the Study of the Economies of Africa (CSEA) እንዲሁም ለሌሎች አጋር አካላት ምስጋና ቀርቧል።

በሙስናና ሕገ-ወጥ አሠራር የተሳተፉ አካላት ላይ የሕግ እርምጃ ተወሰደ
በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን ሰፊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱ እና የሀገር ሀብት በሚመዘብሩ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታወቀ።
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ፈጣን ልማትና ዕድገት እንድታረጋግጥ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰው፣ በዚህም ሰፋፊና አስደናቂ ሀገራዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። በዚህ ሂደት ግን ይህ ውጤት ጉዞው አልጋ በአልጋ እንዳልነበር አመላክተዋል። ከተለያዩ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች ባሻገር፣ ሕገ-ወጥነት እና የሙስና ተግባራት የልማቱ ዋነኛ ፈተና ሆነው መቆየታቸውንም ክብርት ሚኒስትሯ አብራርተዋል።
እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፣ የሕገ-ወጥነት ችግር በአንድ ወገን ብቻ የሚፈጸም ሳይሆን በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚያጠቃልል መሆኑን ገልጸው ከውስጥም ከውጪም ያሉ በርካታ ኃይሎች በተደራጀ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበር። በንግዱ ማኅበረሰብ፣ በልማት ድርጅቶች፣ በመንግሥት መዋቅር፣ በግለሰቦች እና በተገልጋዮች ጭምር በተደራጀ መንገድ በስፋት የሚታይ ነው።
እነዚህ አካላት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ከቁጥጥር ውጭ ለማድረግ በፋይናንስ እና በንግድ ሥርዐቱ ውስጥ ሰርገው በመግባት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲፈጽሙ ቆይተዋል" ያሉት ወይዘሮ እናትዓለም፤ ድርጊቱ ሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ፣ የዋጋ ንረትና ኮንትሮባንድ እንዲባባስ እንዲሁም በፍጆታ እቃዎች ላይ ሰው ሠራሽ እጥረት እንዲፈጠር ማድረጉን አስታውቀዋል። ይህንን የተደራጀ አሻጥር ለመግታት መንግሥት እና የሚመለከታቸው የሕግ አካላት ባከናወኑት ሰፊ ኦፕሬሽን አሻጥሩን ማክሸፍ መቻሉ ተገልጿል።
በሌላ በኩል በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ እና አስተዳደር አካላት እንዲሁም የሕዝብ ተቋማት ውስጥ የተሰገሰጉ ሌቦችን በማጽዳት ረገድ መንግሥት ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ያስታወቁት ወ/ሮ እናትዓለም በሕዝብ ሀብት ላይ ከፍተኛ ምዝበራ የፈጸሙ እና ተቋማዊ አሻጥር በሠሩ አመራሮች እና ሌሎች የጥቅም ትስስሮችና ድርጅቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል። በተለይም በሚከተሉት ቁልፍ ዘርፎች ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ሰፊ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት ሰፍኗል ሲሉ ገልጸዋል።
በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ እና አስተዳደር አካላት፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ የልማት ዘርፎች ውስጥ የተፈጸሙ ዋና ዋና የሙስና እና አሻጥር ወንጀሎችን ለማረም በተወሰዱት ሰፊ ኦፕሬሽኖች እና ሕግ የማስከበር እርምጃዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ማሻሻያውን ለማደናቀፍ በማሰብ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን በማከማቸት እጥረት እንዲፈጠርና ዋጋ እንዲንር ሲያደርጉ የነበሩ 13 አቅራቢ ድርጅቶች ባለቤቶች ላይ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፤ ሕገ-ወጥ ተግባር ሲፈጽሙ በነበሩ ከ7 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶችና መጋዘኖች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል።
በፋይናንስ ተቋማት እና የገንዘብ ዝውውር፡ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሐዋላ እና በጥቁር ገበያ ተሳታፊ የሆኑ 169 ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል። በተደራጀ መንገድ ከንግድ ባንክ ደንበኞች አካውንት ላይ በማጭበርበር ገንዘብ የወሰዱ 36 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የባንክ ሒሳባቸው እንዲታገድ ተደርጓል።
ለሕገ-ወጥ ዝውውር ሽፋን ይሰጡ የነበሩ 7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች በሀገር ውስጥ እንዳይሠሩ ሙሉ በሙሉ ታግደዋል፤ ምርት ልከው የውጭ ምንዛሬ ተመላሽ ያላደረጉ 29 ላኪ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም የህግ ተጠያቂነት ሰፍኗል።
በቤቲንግ እና ፊንቴክ ቢዝነሶች፡ የደንበኞችን መረጃ በመደበቅ መንግሥትን ግብር ያጭበረበሩ፣ ገቢያቸውን የሰወሩ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በፈጸሙ 38 የቤቲንግ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወስዶ ባለቤቶቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ የእነዚህ ሕገ-ወጥ ተቋማት የባንክ ሒሳብ ታግዷል፤
በማዕድን ዘርፍ ሕገ-ወጥ ዝውውር፡ የወርቅ ምርትን ከገበያ ውጭ በኮንትሮባንድ በማስወጣት ወንጀል የተሳተፉ የመንግሥት ኃላፊዎችን፣ የፀጥታ መዋቅር አመራሮችን፣ አምራቾችን እና የውጭ ዜጎችን ጨምሮ 183 ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ ተደርገዋል። በወንጀሉ የተሳተፉ የውጭ ሀገር ዜጎች ከሀገር እንዲወጡ ተደርገዋል፤ ሕገ-ወጥ ወርቅ፣ የወርቅ ሚዛንና ማቅለጫ፣ የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ እንዲሁም የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከነዳጅ አቅርቦት እና ሎጂስቲክስ አንጻር፡ በሕገ-ወጥ መንገድ የሽፋን ደብዳቤዎችን በማዘጋጀት፣ ነዳጅ በመደበቅ እና አየር በአየር በመሸጥ ወንጀል የተሳተፉ 38 የመንግሥት አመራሮች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል። በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድ ላይ የተሰማሩ ከ650 በላይ ግለሰቦች፣ ማደያዎች እና አቅራቢ ኩባንያዎች ላይ የህግ እርምጃ ተወስዷል።
በአፈር ማዳበሪያ ግዢ አሻጥር፡ በተቋሙ የጥቅም ትስስር በመፍጠር ጥራት የጎደለውና ጊዜው ያለፈበት የአፈር ማዳበሪያ ግዢ እንዲፈጸም በማድረግ ሆን ብለው ችግር በፈጠሩ የግብርና ሚኒስቴር አመራሮች ላይ የወንጀል ተጠያቂነት እርምጃ ተወስዷል።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP)፡ ተገቢው መመሪያ በሌለበት ሁኔታ ከ36 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ጋር ሕገ-ወጥ የኃይል ሽያጭ ውል የፈጸሙ 4 ከፍተኛ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል። የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት የፈጸሙ ድርጅቶች እና ግለሰቦችም እንዲሁ በሕግ እንዲጠየቁ ተደርጓል።
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የሰዎች ዝውውር የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ሲስተምን በማዛባት እና ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተሳተፉ 8 ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል። እንዲሁም በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የተሰማሩ 44 ደላሎች እና አዘዋዋሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ ሕገ-ወጥ ፈቃድ የነበራቸው ተቋማት ሙሉ በሙሉ ታሽገዋል።
በገቢዎችና ጉምሩክ ዘርፍ፡ የግብር ውሳኔዎችን በመቀነስ፣ ሐሰተኛ ደረሰኞች በማወራረድ፣ እና በሲስተም መረጃ በማጥፋት የመንግሥት ገቢን ባሳጡ አካላት ላይ ኦፕሬሽን ተካሂዷል።
በራሳቸው፣ በዘመድ እና በሹፌሮቻቸው አካውንት በመጠቀም የጥቅም ትስስር የፈጠሩ 109 ተጠርጣሪዎች ተለይተው ከእነዚህ መካከል 91 ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
መንግሥት የልማት እንቅፋት የሆኑትን ሙስና እና ሌብነት እንደማንኛውም ፈተና በጽናት እየተጋፈጣቸው መሆኑን ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል።
መንግሥት ሌብነትን ለማጥፋት ዘመናዊ አሠራሮችን በመዘርጋት እና በዲሲፕሊን የታነጸ አመራር ለመገንባት ቁርጠኛ ነው" ያሉት ወይዘሮ እናትዓለም፤ ሕዝቡ በስፋት የሚያነሣቸውን "ሌብነትን አስቁሙልን" ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመረዉ ጠንካራ እርምጃ ውጤታማ እንዲሆኑ ማኅበረሰቡ ሙስናን በማጋለጥ፣ ሕጋዊ መብቱን በመደለያ ባለመጠየቅ እና ከሕገወጦች ጋር ባለመተባበር ከመንግሥት ጎን በመቆም ሀገርን ከሕገወጥነትና ሙስና የመከላከል ታሪካዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
Via EBC

ለሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ የባህልና ጥበባት አምባሳደር ሞዴል ሩት ይርጋለም ሸኝት ተደረገላት።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ለምትወክለው ሞዴል ሩት ይርጋለም የእንኳን ደስ አለሽና የሽኝት መርሃ ግብር አደረገ።
ክብርት ሸዊት ሻንካ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ለሞዴሏ መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ ሀገሯን በዓለም አቀፍ መድረክ በማስተዋወቅ በድል እንድትመለስ ተመኝተዋል።
ክብርት ሸዊት በንግግራቸው ሞዴሏ የባህል አምባሳደር ሆና ከተሾመች በኋላ የሀገሪቱን ብዝሃ ባህላዊ ዕሴቶች በቅርበት ለመረዳት በተለያዩ ቦታዎች ጉብኝት ማድረጓን አንስተዋል።
በዚሁ መሠረት በደቡብ ኢትዮጵያ በመገኘት የህዝቡን ባህል፣ በአማራ ክልል ጎንደር በመሄድ የክልሉን ባህላዊ እሴቶች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ባሌ በመገኘት የገዳ ስርዓትንና ድቅ ተፈጥሮአዊ ሀብቶችን በበቂ ሁኔታ ጎብኝታለች ብለዋል።
ይህ በክልሎች ያደረገችው ቆይታ የሀገሪቱን ባህልና ጥበብ ጠልቃ እንድታውቅ የረዳት ሲሆን፣ ከ130 በላይ የዓለም ሀገራት ሞዴሎች በሚሳተፉበት መድረክ ኢትዮጵያን በብቃት ለማስተዋወቅና ገጽታዋን ከፍ ለማድረግ እንደሚያግዛት ገልፀዋል።
የገጠማትን ማንኛውንም ፈተና ተቋቁማ የሀገሯን ባህልና ጥበብ በዓለም አቀፍ አደባባይ ለማሳየት ቆርጣ የተነሳች ጠንካራ ወጣት በመሆኗ ትልቅ አድናቆትና ምስጋና እንደሚገባትም ክብርት ሸዊት ሻንካ አክለዋል።
ክብርት ሸዊት ለመላው ኢትዮጵያውያን ባስተላለፈው መልዕክት በመጪው ውድድር ላይ በሚፈጠረው የማህበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ (Link) አማካኝነት ሁሉም ድጋፉን እንዲሰጥና ለሞዴሏ ስኬት ከጎኗ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
ሞዴል ሩት ይርጋለም በበኩሏ ለተደረገላት የሸኝትና መልካም ምኞት መርሀ ግብር ምስጋና አቅርባለች።
ሞዴሏ ሀገሯን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅና ለማስጠራት ቆርጣ እንደተነሳች በመግለፅ የገጠማት ችግር ወደሗላ እንደማይመልሳት አንስታለች።
ከዓለም አቀፉ ውድድር በሗላም በሀገሯ ያሉ ባህላዊና ጥበባዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅ እደምሰራ ገልፃለች።
በመርሃ ግብሩ ላይ የክልልና የከተማ አስተዳደር የባህልና ስፖርት ሴክተር አመራሮች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች፣ የሙያ ማህበራት አመራሮችና የሞዴሏ ቤተሰቦች ተገኝተው ለሞዴሏ የሀገር አደራ ተሰጥቷል።
Via የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር

የኢትዮጵያና ስሪላንካ ወዳጅነት በኪነ-ጥበብ እና በወጣቶች ትብብር ሊያበብ ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ የስሪላንካ አምባሳደር ኒርማላ ኢንዱማቲ ዲያስ ፓራናቪታና ከኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ እና የትወና ዘርፍ ተወካዮች ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት በባህል ዲፕሎማሲ፣ በወጣቶች አቅም ግንባታ እና በደቡብ-ደቡብ ትብብር ለማጠናከር ያለመ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
አምባሳደሯ ከአምሳ ሦስት በላይ የሰርከስ ትምህርት ቤቶችን ከሚወክለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰርከስ ማህበራት ጥምረት (ENCAC) ፕሬዝዳንት አቶ ተክሉ አሻግሬ (ሄኖክ) ፣ ከ"ቢዮንድ ዳንስ ስቱዲዮ" የደንበኞች አገልግሎት ማኔጀር ሲና አምሳሉ እንዲሁም ከፍካት ሰርከስ አሰልጣኝና ቡድን መሪ አቶ ተመሰገን ግርማ ጋር ተከታታይ ውይይቶችን አድርገዋል።
በውይይቱ ወቅት አምባሳደሯ የስሪላንካን ውብ የባህል ቅርስ በማስተዋወቅ የኢትዮጵያ ወጣት ከዋክብት በባህላዊ ውዝዋዜ፣ በቪዲዮ ትምህርቶች፣ በጉብኝቶች እና በባህል ፌስቲቫሎች የሚሳተፉበትን "ሪትም ኦፍ ላንካ" (Rhythm of Lanka) የተሰኘ መርሃ ግብር አስተዋውቀዋል።
በተጨማሪም በሰርከስና በውዝዋዜ ጥበብ ለተሰማሩ ወጣቶች የጋራ መድረኮችን በመፍጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ አቅማቸውን የሚያሳዩበትና ተሞክሮ የሚለዋወጡበት ዕድል እንደሚመቻች ተገልጿል።
የድርጅቶቹ ተወካዮችም የተጀመረውን የትብብር ጥሪ በበጎ የተቀበሉት ሲሆን መርሃ ግብሩ የወጣቶችን አቅም ከማሳደግ ባለፈ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ተገልጿል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች
👉መልእክት ያልደረሳችሁ ወይም
👉መልእክቱ ከሐምሌ 25 በኋላ የደረሳችሁ ያለቅጣት እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም መክፈል ስለምትችሉ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ሲል የአ.አ ገቢዎች ቢሮ አሳስቧል።
ከሐምሌ 25 በፊት መልእክት የደረሳችሁ ግብር ከፋዮች ግን እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በኦንላይን እንድትከፍሉ አሳስቧል።
የ2018 የግብር ዘመን የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች አብዛኞቹ በኦንላይን የክፍያ ስርዓት ግብራቸውን መክፈላቸውና የተቀሩትም እየከፈሉ መሆኑ ተመላክቷል።
በከተማዋ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ 456 ሺህ 433 የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች እንደሚገኙና ከእነዚህ ግብር ከፋዮችም 9 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱም ተገልጿል።
የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች ግብር ከተቀጣሪዎች ያነሰ መሆኑና ይህም የሆነው የከተማ አስተዳደሩ አነስተኛ ነጋዴዎችን ለማበረታታትና ለማሳደግ ባለው ቁርጠኝነት ምክንያት እንደሆነ መግለጫው አመላክቷል።
እስከ ሐምሌ 25 መልእክት የደረሳችሁ ግብር ከፋዮች እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በኦንላይን እንድትከፍሉ፣ መልእክት ያልደረሳችሁ ወይም ከሐምሌ 25 በኋላ የደረሳችሁ ደግሞ ያለቅጣት እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም መክፈል ስለምትችሉ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ሲልም ቢሮው አሳስቧል።
ግብር በዛብኝ የሚል ቅሬታ ላለው ማንኛውም ግብር ከፋይ የቅሬታ አፈታት ስርዓት ተዘርግቶ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑንም ጠቁሟል።
በስልክ የጽሁፍ መልዕክት የተላከው የደረጃ “ለ” ዓመታዊ ግብር፣ ግብር ከፋዮች በቅድመ ታክስ የከፈሉትን ገንዘብ ተቀናሽ አድርጎ የያዘ እንደሆነም ተገልጿል።(ምንጭ፣ የአ.አ ገቢዎች ቢሮ)

4 days ago
አውሮፓ በእሳት እየተቃጠለች ነው‼
በአውሮፓ የሙቀት መጠኖች አዲስ ሪኮርድ እያሰመዘገቡ ነው፣ ሰደድ እሳቶች እየተስፋፉ ነው፣ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ምርታቸውን እየቀነሱ ነው
እጅግ በጣም ሞቃታማ እና ደረቅ የሆነው የበጋ ወቅት በግብርና ላይ ከባድ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል
አዲስ የሙቀት ሪኮርድ፦ በአውሮፓ የሙቀት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ በኦስትሪያ እስከ 41.2°C ተመዝግቧል።
የኃይል ማመንጫዎች አቅም መቀነስ፦ የዳኑብ እና የሳቫ ወንዞች የውሃ መጠን በመቀነሱ በሃንጋሪ እና በስሎቬንያ የሚገኙ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ምርታቸውን ለመቀነስ ተገደዋል።
የደን እሳት እና መፈናቀል፦ በፈረንሳይ፣ እስፓንያ፣ አልባንያ እና ግሪክ አጥፊ የእሳት አደጋዎች የተከሰቱ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሄክታር መሬቶች ተቃጥለው በርካቶች ተፈናቅለዋል።
የኢኮኖሚና የግብርና ጉዳት፦ በራይን ወንዝ የውሃ ማነስ ምክንያት የመርከብ ትራፊክ ሲስተጓጎል፣ በታላቋ ብሪታንያ ደግሞ እ.ኤ.አ. ከ1984 ወዲህ እጅግ አነስተኛው የእህል ምርት እንደሚመዘገብ ተገምቷል።
የሕይወት እልቂት፦ በሙቀት ማዕበሉ ምክንያት በአህጉሩ ከ1,300 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

Comments