(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሱዳን ዘንድሮ ኢኮኖሚዋ በ9 ፐርሰንት እንደሚያድግ ገለፀች፡፡ በሌተና ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልብሩሀን የሚመራው የሱዳን ወታደራዊ መንግስት የአገሪቱ ኢኮኖሚ በ9 ፐርሰንት ያድጋል የሚል እምነት እንዳለው አስታወቀ፡፡ ይህንን ያስታወቀው ትላንት በካርቱም በተካሄደው የሚኒስትሮች ካቢኔ ስብሰባ ላይ በቀረበው ሪፖርት ነው፡፡ የፋይናንስ ሚኒስትሩ ጅብሪል ኢብራሂም ባቀረቡት በዚህ ሪፖርት በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ኢኮኖሚ በማገገም ላይ መሆኑን ገልፀው በዚህም የአገሪቱ አጠቃላይ ምርት በ2026 በ9 ፐርሰንት ያድጋል የሚል ግምት እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡
ባለፈው አመት ይህ እድገት 1.7 ፐርሰንት ብቻ እንደነበርም አውስተዋል፡፡ ጨምረውም በአገሪቱ ውስጥ የነበረው የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ መምጣቱንና ከግብር የሚገኘው ገቢ ደግሞ በመጨመር ላይ መሆኑን ገልፀዋል ሲል ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው ከወራት በፊት የወጣው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት በ2023 የሱዳን አጠቃላይ አገራዊ ምርት በ6.6 ቢሊዮን ዶላር ቀንሶ 32.4 ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ ይገልፃል፡፡ ይህም የ12 ፐርሰንት ቅናሽ መከሰቱን የሚያሳይ መሆኑን የጠቀሰው የተመድ ሪፖርት ከዚያ በኋላ ባሉት አመታትም እየቀነሰ መምጣቱን ማስረዳቱን አስታውቋል፡፡
እንዲሁም ከ2024 እስከ 2043 ባሉት አመታት ውስጥ የሱዳን ኢኮኖሚ በየአመቱ ከ1.2 ፐርሰንት በላይ እንደማያድግ ግምት ማስቀመጡን ዘገባው አውስቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አይኤምኤፍ ባወጣው የ2026 የአለም ኢኮኖሚ ሪፖርት የሱዳን ኢኮኖሚ እንደሚያድግ የተነበየው በ0.7 ፐርሰንት ነው፡፡

10 hours ago