በኦሮሚያ ክልል በሁሉም ዘርፎች ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኦሮሚያ ክልል በሁሉም ዘርፎች ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል አሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኦቢኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄዎች እና ትግሎች፣ የኢትዮጵያ ታሪክ እና የኦሮሞ ሕዝብ አበርክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም በኦሮሚያ ክልል በሁሉም ዘርፎች እየመጣ ያለው ለውጥ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።
በግብርና፣ በገቢ እና በበጀት እድገት ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡንም በአብነት አንስተዋል።
በክልሉ የሚታረሰው መሬት ከ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር ወደ 17 ሚሊየን ሄክታር ማደጉን ገልጸው፤ ባለፈው ዓመት አጠቃላይ ምርታማነትን በማሳደግ 500 ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን አስታውሰዋል።
በግብርና ዘርፍ ካለው አቅም አንጻር ቀሪ ስራ ቢኖርም በርካታ አዎንታዊ ውጤቶች መጥተዋል ብለዋል።
በ2010 ዓ.ም የነበረው የክልሉ ገቢ ከነበረበት 13 ቢሊየን ብር በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ወደ 342 ቢሊየን ብር ማደጉን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ መልኩ በ2010 ዓ.ም 52 ቢሊየን ብር ብቻ የነበረው የክልሉ አጠቃላይ በጀት በዘንድሮው ዓመት 700 ቢሊየን ብር መድረሱን ጠቅሰዋል።

3 days ago