Logo
FastMereja

የየካው ንጉስ የቅዱስ ሚካኤል መልእክት

ጥንታዊው፣ ታሪካዊው፣ በተአምር ሠሪነቱ፣ በፈዋሽነቱ፣ በስእለት ሰሚነቱ ና በልዩ ግርማ ሞገሱ የሚታወቀው የየካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሁለት ቤዝመንት ያለው ባለ 15 ወለል (2 Basement+G+ 12ወለል) ግዙፍ ጠቅላላ ሆስፒታል በማስገንባት ላይ ይገኛል። ይህም ድንቅ ሆስፒታል በጸበሉ ስፍራ እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን «ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል»የሚል ስያሜ ተሰጥቶት የመጀመሪያው ምዕራፍ የመሰረት ቁፋሮና የአፈር ናዳ መከላከያ (ሾሪንግ) ሥራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

ይህ በ1000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈውና ባለ 250 የህሙማን ሕክምና መስጫ አልጋ አቅም የሚኖረው ዘመናዊ ሆስፒታል፤ የተመላላሽ ክሊኒኮችን፣ የፅኑ ሕክምና (ICU)፣ የቀዶ ጥገና ክፍሎችን እንዲሁም ለእናቶችና ሕጻናት ጤና፣ ለልብ ሕክምናና ለተላላፊ በሽታዎች መከላከያ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ማዕከላትን ያካትታል። ተቋሙ የጤና አጠባበቅን እንደ ንግድ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊና መንፈሳዊ አገልግሎት በመመልከት፣ለሁሉም የማህበረሰቡ አባላት በሙሉ ጥራት ያለው፣ ተደራሽና አቅምን ያገናዘበ የሕክምና አገልግሎት ያቀርባል።

በህንፃ ባለሙያዎች ጥናት መሠረት ለህንፃ ግንባታው አጠቃላይ ወጪ ብር 405,040,000 (አራት መቶ አምስትሚሊዮን አርባ ሺህ ብር) እንደሚሆን ተገምቷል።ይህ ወጪ በየጊዜው በሚታየው የዋጋ ንረት ምክንያት ሊጨምር እንደሚችል ይታሰባል፡፡

ይህንን ከፍተኛ ወጪ ለመሸፈንና ቀጣዩን ወሳኝ የግንባታምዕራፍ ለመጀመር ቤተ ክርስቲያኑ በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚኖሩ ምዕመናንን፣ የንግዱን ማህበረሰብና የልማት አጋሮችን ያሳተፈ የሀብት ማሰባሰቢያ ስልት ቀይሷል።

የደብሩ ሰበካ ጉባኤ እና የልማት ኮሚቴው ምዕመናን በሰጦታቸው ከእግዚአብሔር የሚያገኙትን በረከት በማሰብ፦ «ይህ ታላቅ የማህበራዊና የጤና ልማት ፕሮጀክት ፍጻሜ እንዲያገኝ የዓላማው ደጋፊዎች ሁሉ የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉና አሻራቸውን እንዲያኖሩ በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ስም እንማጸናለን» ሲል ጥሪውን ያስተላልፋል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የፊታችን ነሐሴ 8፣ 9 እና 10 ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል። የየካው ቅዱስ ሚካኤል ያሳደጋችሁ፣ ከሩቅም ከቅርብም ሆናችሁ ፍቅሩን ደግነቱን የቀመሳችሁ፣ የታሪካዊው የየካ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ የሆናችሁ፣ ዝናውን ሰምታችሁ ደጁ የሚናፍቃችሁ፣ ጠብቆ አሳድጎ ለክብር ያበቃችሁና ገና ስሙ ሲጠራ ልባችሁ በደስታ የሚሞላ የኃያሉ መልአክ የቅዱስ ሚካኤል ልጆች ሁላችሁ በቀጥታ ሥርጭቱ በመታደም ድጋፍ እንድታደርጉ እንማጸናችኋለን።

ድግፍ ለማድረግ:-

• ወገን ፈንድ 👉 https://www.wegenfund.com/...

• የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብቁጥር፦
1000000764087 እንዲሁም
አጭር ቁጥር 1277

• አባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፦ 1227

• አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር
013521784586601
• ስዊፍት ኮድ AWINETAA

• ስልክ ቁጥር፦
0945881188 እና 0945771188
1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.