ምክክር ለዘላቂ ሠላም
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከጥንታዊ ነጻ ሀገረ መንግሥታት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በበርካታ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና እሴቶች የተዋቀረች ኅብረብሔራዊት ሀገር ናት፡፡
ከ130 ሚሊየን በላይ ሕዝብ መኖሪያ የሆነችው ሀገራችን ህልውናዋን አጽንታ ዘመናትን መሻገር የቻለችው በልጆቿ የተባበረ ክንድ ስለመሆኑ ታሪክ ህያው ምስክር ነው።
በእነዚያ ጊዜያት ውስጥ ሰላሟንና ልማቷን ሲፈታተኑ የዘለቁ ቅራኔዎችን በሰላማዊ ውይይት በመፍታት ነገዋን የተሻለ ለማድረግ በሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ትገኛለች፡፡
ዜጎቿ ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጥ የጋራ መግባባት ላይ የሚያደርስ መፍትሄ እንዲያበጁ በገለልተኛ የምክክር ኮሚሽን የሚመራ አሳታፊና አካታች ሀገራዊ መድረክ አበጅታለች፡፡
ይህ አሳታፊነት ምክከሩ በሀገሪቱ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ከታዩ እጅግ ሰፊና ለውጥ አምጪ እንቅስቃሴዎች መካከል አንዱ መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡
ለብዙ ዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ አለመግባባቶች ዛሬም ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚቀሰቀሱ ግጭቶችና የሰላም እጦት በምክንያትነት ሲቀርቡ ይስተዋላል፡፡
ሀገር በቀል እውቀቶችንና ባህላዊ የውይይት እሴቶችን ማዕከል በማድረግ እየተካሄደ የሚገኘው ሀገራዊ ምክክር እነዚህን የቆዩ ቁርሾዎች በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል፡፡
የጋራ ሀገራዊ ራዕይ እውን የሚሆንበት ይህ መድረክ ከጊዜያዊ ፖለቲካዊ ጥቅም በላይ የሀገሪቱን የዘላቂ ሰላም ጉዞ የሚያሳልጥ ታሪካዊ እድል ነው፡፡
የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድምፅ እኩል የሚሰማበት ይህ ሀገራዊ ምክክር የአሸናፊና ተሸናፊ ትርክትን በጋራ መግባባት ላይ በተመሠረተ ባህል የሚተካ ወሳኝ መድረክ ነው።
አንዲት ሀገር ለትናንት ቅራኔዎች ሕዝብን ባሳተፈ መንገድ እውነተኛ መፍትሄ ሳትሰጥ ሰላማዊ ነገን መገንባት አትችልም።
በዚህ መንፈስ በእኩልነት ላይ በተመሰረተ፣ ግልጽ፣ ነጻ እና አሳታፊ ሂደት እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር፥ ሀገሪቱን ወደ ብልጽግና የሚያሸጋግር ድልድይ እንዲሁም ከውርስ ህመሟ የሚፈውስ ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡
ግጭትና የሕዝቦች መለያየት የሀገርን ሀብት የሚያወድሙና ልማትን የሚያደናቅፉ በመሆናቸው፤ የሀገርን ጥቅም ባስቀደመ የጋራ መግባባት የተረጋጋ ፖለቲካዊ ሁኔታን በመፍጠር ብሔራዊ ምክክሩ ለጠንካራ ኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት ይጥላል።
የዜጎችን የጋራ መግባባት ጽኑ መሰረት አድርጋ የምትገነባው ሰላማዊት ኢትዮጵያ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቴክኖሎጂና ሌሎች የመሠረተ ልማት ዘርፎች ያላትን አቅም ሙሉ በሙሉ በመጠቀም የዜጎቿን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ትችላለች፡፡
ኢትዮጵያ የአህጉሪቱ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ማዕከል እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ እንደመሆኗ፤ አለመግባባትን በውይይት ለመፍታት የጀመረችው ጉዞ አፍሪካውያን ችግሮችን በራሳቸው ለመፍታት ለሚያደርጉት ጥረት መልካም አርአያ ነው።
የተዋሃደችና ደህንነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድን በማረጋጋት የቀጣናውን የኢኮኖሚ ትስስር፣ ንግድና የጋራ ደህንነት ማረጋገጥ ይቻላታል፡፡
ምክክሩ የአንድ ጊዜ ሁነት ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ሀገራዊ ተቆርቋሪነት የሚጠይቅ የታሰበበት ረጅም ጉዞ ነው።
አለመግባባቶች የማህበረሰብ ተፈጥሯዊ አካል ቢሆኑም ጠንካራ ሀገር የሚገነባው ግን እነዚህን ልዩነቶች ባስተናገዱበት ጤናማ መንገድ እንደሆነ ይታመናል፡፡
ኢትዮጵያ ከግጭት ይልቅ ውይይትን በማስቀደም እያከናወነች የምትገኘው ሀገራዊ ምክክር አንድነት፣ የተቋማት ጥንካሬና ዘላቂ ሰላም የሚጸናበት አዲስ ምዕራፍ ነው፡፡
ከምንጊዜውም በላይ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ በመጠቀም ለወደፊቱ ትውልድ ምቹ ሀገር ለመገንባት ጊዜው አሁን ነው።
በምሕረት ደምሴ

24 hours ago