3 months ago
አርሰናል ከሁለ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ይፋለማል
#ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ ከኤቨርተን ጋር ነጥብ መጣሉን ተከትሎ የሊጉን ዋንጫ ከ22 ዓመታት በኋላ የማንሳት አጋጣሚው ሰፊ የሆነለት አርሰናል ዛሬ ደግሞ በታላቁ የአውሮፓ መድረክ ታሪክ ለመስራት ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
መድፈኞቹ በሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ጨዋታ በስፔን 1 ለ 1 ተለያይተው የተመለሱ ሲሆን ዛሬ ምሽት ወሳኝ የሆነውን የመልስ ጨዋታ በገዛ ሜዳቸው ያከናውናሉ፡፡
ሁለቱ ክለቦች በሃንጋሪ ቡዳፔስት ለሚካሄደው የዘንድሮው የሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ፍልሚያ ለማለፍ ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡
አርሰናል በምድብ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፉ ቢታወስም በዛሬው ጨዋታ ግን ከዲዬጎ ሲሚዮኒ ተጫዋቾች ከባድ ፈተና እንደሚገጥመው ይጠበቃል፡፡
መድፈኞቹ በአውሮፓ መድረክ ከስፔን ክለቦች ጋር ባደረጓቸው ያለፉት ስምንት ጨዋታዎች ሽንፈት አልገጠማቸውም፡፡
በሌላ በኩል አትሌቲኮ ማድሪድ ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር ከሜዳው ውጭ ባደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች የስድስቱን ሽንፈት ቀምሷል፡፡
አትሌቲኮ በሲሚዮኒ መሪነት ለሁለት ጊዜያት ለፍጻሜ ደርሶ በሪያል ማድሪድ ዋንጫውን መነጠቁ የሚታወስ ሲሆን ለሦስተኛ ጊዜ ለፍጻሜ ለመድረስ በሚያደርገው ጉዞ በውድድሩ እስካሁን ያልተሸነፈው አርሰናል ከፊቱ ተደቅኗል፡፡
አርሰናል የዛሬውን ጨዋታ አሸንፎ ለፍጻሜ የሚያልፍ ከሆነ በአዲሱ የሻምፒዮንስ ሊግ አወቃቀር አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ ለዋንጫ ጨዋታ በመድረስ የመጀመሪያው ክለብ በመሆን አዲስ ታሪክ ይጽፋል፡፡
የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ እንደተናገሩት ማርቲን ኦዴጋርድ እና ካይ ሃቨርትዝ ከጉዳታቸው በማገገም ለዛሬው ጨዋታ ዝግጁ ሲሆኑ ዩሪየን ቲምበር ግን አሁንም ከቡድኑ ጋር አይሆንም፡፡
በአትሌቲኮ ማድሪድ በኩል መጠነኛ ጉዳት የነበረባቸው ሁሊያን አልቫሬዝ፣ አሌክሳንደር ሶርሎዝ እና ጂሊያኖ ሲሚዮኒ ለጨዋታው ዝግጁ መሆናቸውን አሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሚዮኒ አረጋግጠዋል፡፡
በአርሰናል በኩል በሳምንቱ መጨረሻ በሊጉ ጨዋታ በፉልሃም ላይ ድንቅ ብቃት ያሳየው ወጣቱ ሉዊስ ስኬሊ ማርቲን ዙቢሜንዲን ተክቶ የመጀመር ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡
#arsenal #atleticomadrid #championsleague #football #ucl #gunners #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 months ago
አትሌቲኮና ፒኤስጂ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ተቃረቡ! 🇫🇷🇪🇸
#ethiopia | የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ያልተጠበቁ ውጤቶችን አስተናግደዋል። የ
ሊቨርፑልና የባርሴሎና ደጋፊዎች ምሽቱን በሀዘን ሲያሳልፉ፣ አትሌቲኮና ፒኤስጂ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለመጓዝ ትልቅ በር ከፍተዋል።
🇫🇷 ፒኤስጂ 2-0 ሊቨርፑል
ዲዘር ዱዌ እና ኪቪቻ ካቫርስኬሊያ ባስቆጠሯቸው ግቦች ፒኤስጂ ድል ቀንቶታል።
መርሲሳይዶቹ በጨዋታው አንድም ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ (0 shots on target) ሳያደርጉ ወጥተዋል።
ሊቨርፑል ከሜዳው ውጭ በአራት ተከታታይ ጨዋታዎች ሲሸነፍ ከ14 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኖ ተመዝግቧል።
🇪🇸 ባርሴሎና 0-2 አትሌቲኮ ማድሪድ 🇪🇸
የሲሚዮኒ ታሪክ፦ አሰልጣኝ ዲየጎ ሲሚዮኒ ባርሴሎናን በሜዳው (ካምፕ ኑ) ለመጀመሪያ ጊዜ ማሸነፍ ችሏል።
ባርሴሎና በሜዳው በአትሌቲኮ ማድሪድ የተሸነፈው ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ፓዎ ኩባርሲ በቀይ ካርድ መውጣቱ ለባርሳ ሽንፈት ትልቅ አስተዋጽኦ ሲያደርግ፣ ሁሊያን አልቫሬዝ እና አሌክሳንደር ሶርሎዝ ድሉን አረጋግጠዋል።
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #championsleague #ucl #psg #liverpool #barcelona #atleticomadrid #simeone #footballnews #ethiopia #የአውሮፓሻምፒዮንስሊግ #ስፖርት #ባርሴሎና #ሊቨርፑል

የሻምፒዮንስ ሊግ ምሽት
የፓሪስ ፈተና ለሊቨርፑልና የስፔኖቹ ፍጥጫ በካታላን
#ethiopia | ትላንት አርሰናል ድል ቀንቶት ምሽቱን በደስታ ብናሳልፍም፣ ዛሬ ደግሞ ሌሎች ታላላቅ ክለቦች ለግማሽ ፍጻሜ አልጋ ለመለየት ይፋለማሉ።
. 🇫🇷 ፒኤስጂ ከ ሊቨርፑል 🏴 (ምሽት 4፡00)
በኤፍ ኤ ዋንጫ በማንችስተር ሲቲ የ 4 ለ 0 መራር ሽንፈት የደረሰባቸው አርን ስሎት፣ ዛሬ በፓሪስ ራሳቸውን ማዳን ይኖርባቸዋል።
ለሦስት ወራት በጉዳት ተለይቶ የነበረው ስዊዲናዊው አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳቅ ወደ ስብስብ መመለሱ ለመርሲሳይዱ ክለብ ትልቅ የምስራች ነው።
ፒኤስጂ በቅርብ ጊዜያት ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር ባደረጋቸው 6 ጨዋታዎች ሽንፈት አላስተናገደም። ብራድሊ ባርኮላና ፋቢያን ሩይዝ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፉም።
🇪🇸 ባርሴሎና ከ አትሌቲኮ ማድሪድ 🇪🇸 (ምሽት 4፡00)
ባርሴሎና በሜዳው ባደረጋቸው ያለፉት 25 ጨዋታዎች በአትሌቲኮ ተሸንፎ አያውቅም። ከሦስት ቀን በፊትም በላሊጋው 2 ለ 1 ማሸነፉ ለዛሬው ጨዋታ የሥነ-ልቦና የበላይነት ይሰጠዋል።
አትሌቲኮ ማድሪድ በሻምፒዮንስ ሊግ የስፔን ክለቦችን ከሜዳው ውጪ አሸንፎ የማያውቅበትን ታሪክ ለመቀየር ይፋለማል።
ባርሴሎና ራፊንሀና ዲዮንግን ቢያጣም ሮናልድ አራውሆ ለጨዋታው ደርሶለታል። በአንጻሩ ያን ኦብላክ ለአትሌቲኮ ዝግጁ መሆኑ ተረጋግጧል።
#getu #championsleague #psg #liverpool #barcelona #atleticomadrid #arneslot #alexanderisak #footballnews #uclquarterfinals #ጌጡተመስገን #getutemesgen #ስፖርት #ሻምፒዮንስሊግ

በላሚን ያማል ላይ የተሰነዘረው አስነዋሪ የዘረኝነት ጥቃት
#ethiopia | በትላንትናው ምሽት በባርሴሎና እና በአትሌቲኮ ማድሪድ መካከል በተደረገው ተጠባቂ ጨዋታ፣ የባርሴሎናው ወጣት ኮከብ ላሚን ያማል የአትሌቲኮ ማድሪድ ደጋፊዎች ኢ-ሰብአዊ ለሆነ የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ ሆኗል።
በጨዋታው ወቅት በስታዲየሙ የተገኙ ደጋፊዎች ያማልን "በጣም አስቀያሚ ነህ" በማለት ሲሳደቡ የሚያሳይ ቪዲዮ በስፋት የተሰራጨ ሲሆን፣ ከዚህም ባለፈ የዘር ማንነቱን በመጥቀስ "ወደ ሞሮኮ ተመለስ" የሚሉ የጥላቻ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ተደምጠዋል።
በዚህ ድርጊት ክፉኛ የተበሳጨው ወጣቱ ተጫዋች፣ ጨዋታው ሲጠናቀቅ በከፍተኛ ስሜት ውስጥ ሆኖ ሜዳውን ለቆ መውጣቱ ተስተውሏል። ላሚን ያማል ከዚህ ቀደም በስፔን ደጋፊዎች አማካኝነት በእምነት ላይ የሚሰነዘሩ ትንኮሳዎችን በጽኑ ሲያወግዝ እንደነበር ይታወሳል።
ይህ ተደጋጋሚ እየሆነ የመጣው የዘረኝነት ድርጊት በስፔን እግር ኳስ ላይ ጥቁር ነጥብ እየጣለ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪዎች እየቀረቡ ይገኛሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #lamineyamal #notoracism #fcbarcelona #laliga #footballnews #humanrights #stopracism #barcelona #atleticomadrid

Sponsored by
Surafel
Comments