ኦሮሚያ ባንክ በገላን የልህቀት ማዕከል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ!
#fastmereja I ኦሮሚያ ባንክ በገላን ክፍለ ከተማ በሚገኘው የልህቀት እና ኮንቬንሽን ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ቃል ከ2 ሺህ በላይ ችግኞችን የመትከል መርሀ-ግብር በዛሬዉ እለት አካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የባንኩ የቦርድ አመራር አባላት፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ደንበኞች፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ እና ሕፃናት ተሳትፈዋል።
የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን እንደገለጹት፤ መርሃ ግብሩ በየዓመቱ የሚካሄድ እና ዘላቂነት ያለው የአካባቢ ጥበቃ አካል መሆኑን ገልፀዉ የተተከሉት ችግኞችም ዓመቱን ሙሉ አስፈላጊው እንክብካቤ እየተደረገላቸው ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ እንደሚደረግ አስረድተዋል።
የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለአካባቢ ውበት፣ ለምግብነት የሚውሉ ምርቶችን ለማረት እንዲሁም ሀገሪቱን ከካርበን ልቀት ነፃ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
በተጨማሪም መርሀ-ግብሩ ሕፃናትን ማሳተፉ የተፈጥሮ እና የአካባቢ ጥበቃ ባህልን ለቀጣዩ ትውልድ ለማሸጋገር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል።
በተያያዘም ተሳታፊዎች በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ እየተካሄዱ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ማዕከሉ ደረጃውን የጠበቀ ሁለገብ የኮንቬንሽን ማዕከል፣ የ9 ፎቅ ንግድ ህንፃ፣ የስፖርትና አካል ብቃት ማዕከል እንዲሁም ለባንከሮች እና ለተለያዩ ሴክተሮች የሚሆን የስልጠናና ቦርዲንግ ማዕከልን ያካተተ ፕሮጀክት መሆኑ ተጠቅሷል።
ተቋሙ ባለፉት ዓመታት የተከላቸው ችግኞች ፀድቀው ለውጤት መብቃታቸውን እና ዘንድሮም የተጀመረው ዘመቻ ይህንን አዎንታዊ አሻራ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቋል።
📷 ከበደ መክብብ

7 hours ago