የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች
👉መልእክት ያልደረሳችሁ ወይም
👉መልእክቱ ከሐምሌ 25 በኋላ የደረሳችሁ ያለቅጣት እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም መክፈል ስለምትችሉ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ሲል የአ.አ ገቢዎች ቢሮ አሳስቧል።
ከሐምሌ 25 በፊት መልእክት የደረሳችሁ ግብር ከፋዮች ግን እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በኦንላይን እንድትከፍሉ አሳስቧል።
የ2018 የግብር ዘመን የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች አብዛኞቹ በኦንላይን የክፍያ ስርዓት ግብራቸውን መክፈላቸውና የተቀሩትም እየከፈሉ መሆኑ ተመላክቷል።
በከተማዋ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ 456 ሺህ 433 የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች እንደሚገኙና ከእነዚህ ግብር ከፋዮችም 9 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱም ተገልጿል።
የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች ግብር ከተቀጣሪዎች ያነሰ መሆኑና ይህም የሆነው የከተማ አስተዳደሩ አነስተኛ ነጋዴዎችን ለማበረታታትና ለማሳደግ ባለው ቁርጠኝነት ምክንያት እንደሆነ መግለጫው አመላክቷል።
እስከ ሐምሌ 25 መልእክት የደረሳችሁ ግብር ከፋዮች እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በኦንላይን እንድትከፍሉ፣ መልእክት ያልደረሳችሁ ወይም ከሐምሌ 25 በኋላ የደረሳችሁ ደግሞ ያለቅጣት እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም መክፈል ስለምትችሉ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ሲልም ቢሮው አሳስቧል።
ግብር በዛብኝ የሚል ቅሬታ ላለው ማንኛውም ግብር ከፋይ የቅሬታ አፈታት ስርዓት ተዘርግቶ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑንም ጠቁሟል።
በስልክ የጽሁፍ መልዕክት የተላከው የደረጃ “ለ” ዓመታዊ ግብር፣ ግብር ከፋዮች በቅድመ ታክስ የከፈሉትን ገንዘብ ተቀናሽ አድርጎ የያዘ እንደሆነም ተገልጿል።(ምንጭ፣ የአ.አ ገቢዎች ቢሮ)
Seledadotio

3 days ago