Logo
EBC
በቅድመ ውድድር ዘመን ጨዎታዎች ማንቸስተር ሲቲ ድል ሲያስመዘግብ ቼልሲ አቻ ተለያይቷል
***********************************

በማሌዥያ ኢስካንዳር ፑተሪ በሚገኘው ሱልጣን ኢብራሂም ላርኪን ስታዲየም በተደረገ የቅድመ ውድድር ዘመን የወዳጅነት መርሐ-ግብር ቼልሲ ከጆሆር ዳሩል ታዚም ጋር ተጫውቶ 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።

በዚህ ማራኪ ጨዋታ ለቼልሲ ሊያም ዲላፕ ሁለት ግቦችን በፍጹም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር ክሪስቶባል ማርኩዌዝ ደግሞ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥሯል። በጆሆር ዳሩል ታዚም በኩል ደግሞ አይማን፣ ኦስካር አሪባስ እና ቤርግሰን ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል።

በተመሳሳይ በደቡብ ኮሪያ ሴኡል በሚገኘው ሴኡል ወርልድ ካፕ ስታዲየም በተደረገ ሌላ የቅድመ ውድድር ዘመን የወዳጅነት መርሐ-ግብር ማንቸስተር ሲቲ ስፔናዊውን ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድን ገጥሞ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ለማንቸስተር ሲቲ የማሸነፊያዎቹን ግቦች ኦማር ማርሙሽ ሁለት እንዲሁም ሪያን አይት-ኑሪ አንድ ግብ ከመረብ ሲያሳርፉ፣ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ብቸኛዋን ግብ ጆርጅ ዶሚንጌዝ አስቆጥሯል።
#chelsea #manchestercity #atleticomadrid #preseason #friendlymatch

1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.