የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሚያሰራውን ቤተሰሊሆም አጠቃላይ ሆስፒታል ህንፃ ግንባታን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡
ከሁሉ አሰቀድመን እግዚአብሔር አምላካችን ለ2018 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሁላችንንም በሰላም በጤና ስላደረሰን እናመሰግነዋለን፡፡የተከበራችሁ አበው መነኮሳት፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ካህናት እና ዲያቆናት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ ምዕመናን እና ወጣቶች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንዲሁም ይህን መልእክት ለመላው ዓለም ለማስተላለፍ የተገኛችሁ የሚድያ አካላት በሙሉ በእግዚአብሔር ስም የከበረ ሰላምታችንን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከሆነው ከየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እናቀርባለን፡፡
“በኂሩተ ጻድቃን ትረትዕ ሀገር”
“በጻድቃን ልማት ከተማ ደስ ይላታል”
ምሳ 11፥10
እግዚአብሔር በንጉሱ ሰሎሞን ላይ አድሮ የተናገረውን መነሻ በማድረግ ልማት ለቤተከርስቲያን ፣ልማት ለሀገር፣ልማት ለማኅበረ ስብእ አስፈላጊ መሆኑን በማሰብ በአዲስ አበባ ሀገረ ስበከት በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለሚገነባው ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል የህንፃ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት መርሃ ግብር የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡ የእግዚአበሔር ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን፡፡ አሜን።
1. ታሪካዊ ዳራ እና የልማት መነሻ
ከአክሱም ዘመነ መንግሥት (በአባ ሰላማ ዘመን) የጀመረውና ከ1600 ዓመታት በላይ የዘለቀው የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ የኢትዮጵያን ጥንታዊነትና የአዲስ አበባን ከተማ አመሰራረት የሚተርክ ህያው ቅርስ ነው።ይህ ታሪካዊ ደብር በአብርሃ ወአጽብሃ፣ በዳግማዊ አጼ ምኒልክና በንግሥት ጣይቱ፣ እንዲሁም በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በርካታ የታሪክና የፈተና ምዕራፎችን አልፎ ዛሬ ላይ ደርሷል።
ደብሩ ከሃይማኖታዊ አገልግሎቱ ባሻገር፣ የአዲስ አበባ የመጀመሪያው የቀብር ቦታ በመሆን የሊቃውንቱና የካህናቱ እንዲሁም የታላቁ ሐኪም ወርቅነህ እሸቴን፣ የኢትዮጵያ ታላላቅ ጄነራሎችና ፊት አውራሪዎችን ዓጽም በክበር ማረፊያ ሆኗል፡፡ የጸሎትና ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሁም ለአካባቢው አብያተ ክርስቲያናት መመስረት ባደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይታወቃል። ዛሬ ይህ ታሪካዊ ደብር ጥንታዊ ታሪኩንና መንፈሳዊ ታላቅነቱን በዘመናዊ ማህበራዊ ልማት ለመድገም፣አካላዊ ፈውስን በሳይንሳዊ ሕክምና የመንፈሳዊ ፈውስን በፀሎትና በጠበል የሚያዋህድ ታላቅ የልማት ፕሮጀክት ይፋአድርጓል።
2. የሆስፒታሉ ይዘት፣ ራዕይና ሰብዓዊ ተልዕኮ
ቤተክርስቲያኑ ባለ 15 ወለል ማለትም (2 Basement+G+ 12ወለል) የሆነውን «ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል» ህንፃ ግንባታ የጀመረ ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ምዕራፍ የመሰረት ቁፋሮና የአፈር ናዳ መከላከያ (ሾሪንግ) ሥራ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
ይህ በ1000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈውና ባለ 250 የህሙማን ሕክምና መስጫ አልጋ አቅም የሚኖረው ዘመናዊ ሆስፒታል፤ የተመላላሽ ክሊኒኮችን፣ የፅኑ ሕክምና (ICU)፣ የቀዶ ጥገና ክፍሎችን እንዲሁም ለእናቶችና ሕጻናት ጤና፣ ለልብ ሕክምናና ለተላላፊ በሽታዎች መከላከያ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ማዕከላትን ያካትታል። ተቋሙ የጤና አጠባበቅን እንደ ንግድ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊና መንፈሳዊ አገልግሎት በመመልከት፣ለሁሉም የማህበረሰቡ አባላት በሙሉ ጥራት ያለው፣ ተደራሽና አቅምን ያገናዘበ የሕክምና አገልግሎት ያቀርባል።
3. የግንባታ ወጪ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ
በህንፃ ባለሙያዎች ጥናት መሠረት ለህንፃ ግንባታው አጠቃላይ ወጪ ብር 405,040,000 (አራት መቶ አምስትሚሊዮን አርባ ሺህ ብር) እንደሚሆን ተገምቷል።ይህ ወጪ በየጊዜው በሚታየው የዋጋ ንረት ምክንያት ሊጨምር እንደሚችል ይታሰባል፡፡
ይህንን ከፍተኛ ወጪ ለመሸፈንና ቀጣዩን ወሳኝ የግንባታምዕራፍ ለመጀመር ቤተ ክርስቲያኑ በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚኖሩ ምዕመናንን፣ የንግዱን ማህበረሰብና የልማት አጋሮችን ያሳተፈ የሀብት ማሰባሰቢያ ስልት ቀይሷል።
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ እና የልማት ኮሚቴው ምዕመናን በሰጦታቸው ከእግዚአብሔር የሚያገኙትን በረከት በማሰብ፦ «ይህ ታላቅ የማህበራዊና የጤና ልማት ፕሮጀክት ፍጻሜ እንዲያገኝ የዓላማው ደጋፊዎች ሁሉ የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉና አሻራቸውን እንዲያኖሩ በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ስም እንማጸናለን» ሲል ጥሪውን ያስተላልፋል።
የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ዝርዝር፦
• ቀን፦ ነሐሴ 8፣ 9 እና 10 ቀን 2018 ዓ.ም
• ሰዓት፦ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ
የገቢ ማሰባሰቢያ የባንክ አማራጮች፦
• የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብቁጥር፦
1000000764087 እንዲሁም
አጭር ቁጥር 1277
• አባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፦ 1227
• አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር
013521784586601
• ስዊፍት ኮድ AWINETAA
• ወገን ፈንድ 👉 https://www.wegenfund.com/...
ለተጨማሪ መረጃ፦
• ስልክ ቁጥር፦
0945881188 እና 0945771188
• Email፦ Seyoumwgebrielgmail .com
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።

5 hours ago