21 hours ago
“ ጩኸት ቢኖርም እኛም በማሸነፍ የራሳችንን ጩኸት እናሰማለን ” ኢንዞ ማሬስካ
የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በድሉ መደሰታቸውን ከጨዋታው በኋላ ተናግረዋል።
ለስካይ ስፖርት ቃላቸውን የሰጡት ኢንዞ ማሬስካ “ በጣም ደስተኛ ነኝ በጨዋታው ነገሮችን አርመን አሸንፈናል "ብለዋል።
በወቅታዊ ሁኔታ “ ከሜዳችን ውጪ ስንጫወት ጫጫታ መሰማቱ ስለማይቀር መላመድ አለብን “ ሲሉ ማሬስካ ተናግረዋል።
አክለውም “ ነገሮችን መላመዱ እንዳለ ሆኖ እኛም የራሳችን ጩኸት መፍጠር አለብን እሱን ለመፍጠር ጨዋታውን ማሸነፍ ነው “ ብለዋል።
“ የቡድኑ እንቅስቃሴ በጣም ጥሩ ነበር
፤ በሶስት ነጥቡ በጣም ደስተኛ ነኝ “ ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
@tikvahethsport kidusyoftahe

23 hours ago
አስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ምን አለ?
#ethiopia | የአሜሪካ ኤምባሲ በአስመራ/ኤርትራ ዛሬ ባወጣው መግለጫ መሠረት በሰሜን ኢትዮጵያ ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ውጊያ መቀጠሉን አስታውቋል።
በኤርትራ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች የጉዞ እገዳዎች፣ የፈንጂ ስጋቶች፣ የዘፈቀደ እስራት ስጋት እና የኤምባሲው የእርዳታ አቅም ውስን መሆን የተነሳ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል።
ኤርትራ የጣምራ ዜግነት ስለማትቀበል ኤርትራ -አሜሪካውያንን እንደ አንድ የኤርትራ ተራ ዜጋ ብቻ እንደምትቆጥራቸው ተገልጿል።
ግለሰቦች ግብር እንዲከፍሉ ሊገደዱ፣ ከሀገር እንዳይወጡ ሊከለከሉ እና በብሔራዊ ግዳጅ ውስጥ እንዲሳተፉ ሊጠየቁ እንደሚችሉና በዚህም የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ጥበቃ ሊያደርግላቸው እንደማይችል ተመላክቷል።
እንዲሁም ከአስመራ ውጭ ባሉ አካባቢዎች የኤምባሲ ሰራተኞች ከአስመራ ከተማ ማዕከል ከ25 ኪሎሜትር በላይ መጓዝ እንደማይችሉ የተገለጸ ሲሆን ከዚህ አካባቢ ውጭ ለሚገኙ ዜጎች ድጋፍ ለመስጠት ያላቸው አቅም ውስን መሆኑ ተነግሯል።
ዜጎች በአሜሪካ መንግሥት እርዳታ ላይ የማይመረኮዝ የለቀቃ እቅድ እንዲያዘጋጁ፣ የጉዞ ሰነዶችን ወቅታዊና በቀላሉ ሊገኙ በሚችሉበት ሁኔታ እንዲይዙ፣ የዩናይትድ ስቴትት ፓስፖርት እና ወቅታዊ የኤርትራ ቪዛን ጨምሮ መታወቂያ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ ተጠይቀዋል።
በተጨማሪም የግል ደህንነት እቅዶችን በመገምገም የአካባቢን ዜናዎች እንዲከታተሉ እና በአስቸኳይ ጊዜ መረጃዎችን ለማግኘት በ Smart Traveler Enrollment Program (STEP) ላይ እንዲመዘገቡ አሳስቧል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

1 day ago
በትግራይ ክልላዊ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ፤ የፌደራል መንግስት “ሙሉ ትግራይን እንደሚያስተዳድር” አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ!
በትግራይ ክልል “ለምርጫ የሚሆን አመቺ ሁኔታ እስኪፈጠር ድረስ” የፌደራል መንግስት “ሙሉ ትግራይን እንደሚያስተዳድር” የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። በክልሉ በፌደራል የሚመራ “ኮማንድ ፖስት” እንደሚቋቋም የገለጹት አቶ ጌታቸው፤ በሁሉም ቦታዎች በሚካሄድ ምርጫ የወረዳ አስተዳዳሪዎች እንደሚሰየሙ አስታውቀዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪነታቸው እንዲቀጥሉ በትላንትናው ዕለት በድጋሚ የተሾሙት አቶ ጌታቸው፤ የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ቲቢኤስ ከተሰኘው የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።
አንድ ሰዓት የሚጠጋ ጊዜ በወሰደው በዚህ ቃለ ምልልስ፤ አቶ ጌታቸው በትግራይ ክልል በቀጣይ የሚከናወኑ ስራዎችን በተመለከተም ጥቆማ ሰጥተዋል።
አቶ ጌታቸው ጥቆማውን የሰጡት ላለፉት ሳምንታት ሲካሄድ ከቆየ ውጊያ በኋላ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በሚመሩ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የነበሩ የትግራይ ክልል በርካታ አካባቢዎች፤ በመከላከያ ሰራዊት እና አጋሮቹ መያዛቸውን ተከትሎ ነው።
የትግራይ ክልል አብዛኞቹ አካባቢዎች በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር መሆናቸውን ያመለከቱት አቶ ጌታቸው፤ በክልሉ ከአሁን በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደማይኖር ይፋ አድርገዋል።
በፌደራል መንግስት እቅድ መሰረት በመጪዎቹ ስድስት ወራት በትግራይ ምርጫ ለማካሄድ እንደታቀደም አቶ ጌታቸው በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው ገልጸዋል።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube FikerAssefa

“ ጫጫታውን እርሱትና ሄደን ሊጉን እናሸንፍ ”
የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ባለፈው ሐሙስ ተጨዋቾቹን አነጋግረው እንደነበር ተገልጿል።
በክለቡ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ የተናገሩት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ለተጨዋቾቹ “ ያለውን ጫጫታ እርሱት ” ሲሉ ማሳሰባቸው ተነግሯል።
“ እዚህ ያለነው ፕሪሚየር ሊጉን ለማሸነፍ ነው ሄደን ሊጉን እናሸንፍ ” ሲሉ አሰልጣኙ ነግረዋቸዋል ተብሏል።
ማንችስተር ሲቲ ዛሬ 12:30 ከሊቨርፑል ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል።

2 days ago
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ መግባት እንዲችሉ በተለያዩ አካባቢዎች የቅበላ ማዕከላት ተዘጋጅተዋል። ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ መግባት እንዲችሉ በተለያዩ አካባቢዎች የቅበላ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ።
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በአሁኑ ወቅት በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መንግስት ወደ አዘጋጀላቸው ማዕከላት ለመግባት ጥሪውን እየተጠባበቁ መሆኑ ታውቋል።
መንግሥት ወደ ሰላም አማራጭ የሚመጣ ማንኛውም አካል በተሃድሶ ሂደትን አልፎ፣ ወደ ማህበረሰቡ በመቀላቀል የተረጋጋ ሕይወት እንዲመራ ያለውን ጽኑ ፍላጎት ገልጸዋል፡፡
መከላከያ ሠራዊትም ወደ ሰላም የሚመጣውን ኃይል በአግባቡ የመቀበል፣ የማስተናገድ እና ወደ ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ማዕከላት የማድረስ ሥራውን በተደራጀ መንገድ እየተገበረ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
ኮሚሽኑ ታጣቂዎቹና አመራሮቻቸው በተሐድሶ ሂደት እንዲያልፉ የመቀበያ ማዕከላትን በዞኖችንና ከተሞችን ማዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡
በዚህም ደቡባዊ ዞን ራያ አካባቢ ማይጨው እና መሆኒ ከተሞች፤ ደቡብ ምስራቅ ዞን መቀሌና አካባቢው በመቀሌ ከተማ በሚገኘው የሰሜን እዝ ጠቅላይ መምሪያ፤ ምስራቃዊ ዞን በአዲግራት እና በውቅሮ ከተሞች የመቀበያ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በተጨማሪም በማዕከላዊ ዞን በአድዋ፣ አክሱም እና አቢዓዲ ከተሞች እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ ዞን በሽሬ ከተማ በሚገኘው የቀድሞው ማዕከላዊ እዝ ጠቅላይ መምሪያ ላይ የመቀበያ ማዕከል መዘጋጀቱን ነው የገለፁት።
የመከላከያ ሠራዊት አባለት ታጣቂዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን አንስተው ታጣቂዎች በእጃቸው የሚገኘውን ትጥቅና ወታደራዊ ቁሳቁስ በማስረከብ ወደ ተዘጋጀላቸው የተሃድሶ ማዕከላት እንደሚገቡ አስታውቀዋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo

3 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ባሳለፉት አዲስ የሹመት ውሳኔ፣ አቶ ፍሰሃ ደሳለኝን በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ አድርገው ሾመዋል። ይህ ሹመት መንግስት በከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ እያደረገ ያለው ሰፋ ያለ ሽግሽግ አካል ነው።
እንደሚታወሰው ዘ-ሐበሻ ከሳምንት በፊት የውስጥ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ፣ አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ በቅርቡ ወደ ከፍተኛ የመንግስት ሹመት እንደሚመጡ ቀድሞ ለተከታታዮቹ አድርሶ ነበር። ተሿሚው ከዚህ ቀደም በመቄት ምርጫ ክልል 1 ለክልል ምክር ቤት በብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ሆነው ቀርበው እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊም::
አዲሱ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪነት የሥራ መደብ፣ የሀገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር የማስፋት፣ የተቋማትን አሰራር የማሻሻል እና የዴሞክራሲ ግንባታ ሒደቶችን በበላይነት የማስተባበር ቁልፍ ኃላፊነት የሚወስድ ይሆናል። አቶ ፍሰሃ በዚህ የኃላፊነት ቦታ ላይ መንግስት የጀመራቸውን የፖለቲካ ሪፎርሞች በቅርበት እንደሚከታተሉ ይጠበቃል።
____
ወቅታዊ እና የተረጋገጡ መረጃዎችን ቀድመው ለማግኘት የዘ-ሐበሻ ገጽን ፎሎው ማድረጋችሁን አትርሱ!

ኤርትራ የጉዞ እገዳ አወጣች በዜጎቿ ላይ
በርካታ ሀገራት ዜጎቻቸው በተለይ በሁሉም የኤርትራ ድንበር 25km ክልል ውስጥ ምንም አይነት ጉዞ እንዳያደርጉ እንዲሁም ወደ ኤርትራ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር እንዳይጓዙ አስጠንቅቀዋል።
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መከላከያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በማንኛውም ሰዓት ወደግጭት ሊያመራ ስለሚችል ወደ ኤርትራ መጓዝም ሆነ መውጣት አስቸጋሪ ስለሚሆን ሀገራት የጥንቃቄ መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛል።
ኤርትራ ለመቆየት የወሰኑ ካሉም የምግብ ፍጆታ እንዲያዘጋጁ መክረዋል።
@Yenetube Fikerassefa

Sponsored by
Surafel
4 days ago
" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " - ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር)
👉 " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም ! "
ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) በደብዳቤ አሳወቀች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር) ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት ደብዳቤ መጻፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በዚህም ደብዳቤ፤ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ለፀጥታው ም/ቤት አባላት በላከችው ደብዳቤ " ኤርትራ በተደጋጋሚ በፈጸመችው ጸብ አጫሪነት እና ድንበር ጥሶ የመግባት እርምጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደጋ መደቀኑን " በመጥቀስ ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቃቸውን አስታውሰዋል።
" ኤርትራ የፀብ አጫሪነት ድርጊቷን በአሁኑ ጊዜ ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግራ ሜካናይዝድ ክፍሎችን ጨምሮ ወታደሮቿን በጥልቀት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት አሰማርታለች " ያሉት ጌዲዮን (ዶ/ር) ፥ " ይህም ሦስት የትግራይ ዞኖችን በማካተት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከ30 አስከ 60 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ርቀት ወደ ውስጥ ገብተዋል " ብለዋል።
ሚኒስትር ጌዲዮን የኤርትራ ድርጊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ውስጥ የሰፈሩትን መሠረታዊ መርሆዎች በግልጽ የሚጥስ ነው በማለት " ይህም ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል ሕጋዊ መብት እንድትጠቀም የሚያስገድድ ነው " ሲሉ ጽፈዋል።
ለፀጥታው ም/ቤት የጻፉት ደብዳቤ የተፈጸመውን ወረራ ለማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ለምትወስደው የመከላከል እርምጃ ድጋፍ ጠይቀዋል።
" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " በማለት ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ የገጠማትን ሁኔታ በመረዳት ድጋፍ እንዲደያርግላት እና ከጎኗ እንዲቆም ጠይቀዋል።
ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በኩል ለረዥም ጊዜ ሲፈጸሙ ለነበሩ ትንኮሳዎች በትዕግሥት እና ራስን በመቆጠብ መቆየቷን አመልክተዋል።
በመሆኑም " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም " ብለዋል።
" ኤርትራ ወራሪ ናት፤ ኢትዮጵያ ደግሞ የወረራ ሰለባ ናት። ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እየጣሰች ነው " ሲሉም አሳውቀዋል።
ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌላትም ገልጸዋል።
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕግን መሠረት በማድረግ ሉዓላዊነቷ እና የግዛት አንድነቷን የመከላከልና የማስጠበቅ ሕጋዊ መብት እንዳላት አሳወቀች። የተባበሩት መንግስታት (UN) ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና ጄን ሙሀመድ አዲስ አበባ ይገኛሉ። ዛሬ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው መክረዋል። ሚኒስትሩ፥ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ እየፈጸመች ስላለው ቀጣይነት ያለው የጠብ አጫሪነት ተግባና…
👉 " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም ! "
ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) በደብዳቤ አሳወቀች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር) ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት ደብዳቤ መጻፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በዚህም ደብዳቤ፤ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ለፀጥታው ም/ቤት አባላት በላከችው ደብዳቤ " ኤርትራ በተደጋጋሚ በፈጸመችው ጸብ አጫሪነት እና ድንበር ጥሶ የመግባት እርምጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደጋ መደቀኑን " በመጥቀስ ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቃቸውን አስታውሰዋል።
" ኤርትራ የፀብ አጫሪነት ድርጊቷን በአሁኑ ጊዜ ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግራ ሜካናይዝድ ክፍሎችን ጨምሮ ወታደሮቿን በጥልቀት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት አሰማርታለች " ያሉት ጌዲዮን (ዶ/ር) ፥ " ይህም ሦስት የትግራይ ዞኖችን በማካተት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከ30 አስከ 60 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ርቀት ወደ ውስጥ ገብተዋል " ብለዋል።
ሚኒስትር ጌዲዮን የኤርትራ ድርጊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ውስጥ የሰፈሩትን መሠረታዊ መርሆዎች በግልጽ የሚጥስ ነው በማለት " ይህም ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል ሕጋዊ መብት እንድትጠቀም የሚያስገድድ ነው " ሲሉ ጽፈዋል።
ለፀጥታው ም/ቤት የጻፉት ደብዳቤ የተፈጸመውን ወረራ ለማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ለምትወስደው የመከላከል እርምጃ ድጋፍ ጠይቀዋል።
" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " በማለት ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ የገጠማትን ሁኔታ በመረዳት ድጋፍ እንዲደያርግላት እና ከጎኗ እንዲቆም ጠይቀዋል።
ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በኩል ለረዥም ጊዜ ሲፈጸሙ ለነበሩ ትንኮሳዎች በትዕግሥት እና ራስን በመቆጠብ መቆየቷን አመልክተዋል።
በመሆኑም " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም " ብለዋል።
" ኤርትራ ወራሪ ናት፤ ኢትዮጵያ ደግሞ የወረራ ሰለባ ናት። ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እየጣሰች ነው " ሲሉም አሳውቀዋል።
ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌላትም ገልጸዋል።
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
4 days ago
የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልም!
*******************
ከጥንታዊቷ እስከ ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ቀይ ባህር የግዛቷ አካል ሆኖ መርከቦቿ ሲጠቀሙበት የኖሩ ሲሆን ጥንታዊት ኢትዮጵያን በአለም ላይ ከነበሩት ታላላቅ ሀይሎች አንዷ እንድትሆን ያደረጓት በወቅቱ ታስተዳድራቸው የነበሩት ወደቦቿ፣ የንግድ ትስስሮቿ እና "ባህረ ነጋሽ" የሚለው የማእረግ መጠሪያ ስያሜ እንደነበሩ ይታወቃል።
ሆኖም ሀገራችን በታሪክ አጋጣሚዎች እና በተደረጉባት እኩይ ሴራዎች ምክንያት ከሶስት አስርት አመታት በላይ የባህር በር አልባ ሆና በመቆየቷ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ የጂኦ ፖለቲካ እና የብሄራዊ ደህንነት ማነቆዎች ተዳርጋ ኖራለች።
በተባበሩት መንግስታት የንግድና ልማት ጉባኤ መረጃ መሰረትም የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከአለም አማካይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ወጪ በላይ ተጨማሪ ክፍያ ለማውጣት የሚገደዱ በመሆኑ ይህ ተፅእኖ በዜጎች እለታዊ የሸመታ አቅም፣ በሀገራችን የኢንቨስትመንት እድሎች እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዲጂታል መረጃ በሚያስተላልፉት ከባህር በታች ያሉ የፋይበር ኦፕቲክስ መስመሮች ተጠቃሚነት ላይ ከፍተኛ ጫና ሲፈጥር ቆይቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግስት ምስረታ ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደገለፁት የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን ሊሆን አይችልም፡፡
በመሆኑም በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት አጥብቀን እንሰራለን ያሉም ሲሆን፤ ይህንን ታሪካዊ ስህተት እና የትውልድ ቁጭት ለመቅረፍ "የመደመር መንግስት" የባህር በር ጥያቄን ከወቅታዊ ፖለቲካ እና ከፓርቲ ወገንተኝነት በላይ በሆነ ትውልድ ተሻጋሪ ብሄራዊ አጀንዳ አድርጎ እንደሚሰራበት ተናግረዋል።
የመደመር መንግስት በያዘዉ ጠንካራ አቋም የኢትዮጵያ ስልጣኔና እድገት ያለ ባህር በር እውን ሊሆን ስለማይችል ሀገራችን በሰጥቶ መቀበል በጋራ ተጠቃሚነት እና በሰላማዊ ዲፕሎማሲ መርህ ወደ አለም የምትወጣበትን መስመር የማረጋገጥ ጉዞዋ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
እውነተኛ ብሄራዊ ደህንነትና ሉአላዊነት የሚረጋገጠው ስትራቴጂካዊ ቁሳቁሶች ያለ ምንም የውጭ ጫና እገዳ ወይም የጎረቤት ሀገራት በጎ ፈቃድ በቀጥታ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ሲችሉ እንደመሆኑ መጠን ቀጥተኛ የባህር በር ማግኘት የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት እድሎችን በመክፈት የወጣቶችን ስራ አጥነት ከመቅረፉ ባሻገር ኢትዮጵያ በቀይ ባህር እና በስትራቴጂካዊ የውሃ አካላት ቀጠናዊ ውሳኔዎች ላይ ያላትን የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ተሰሚነት ከፍ ያደርገዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ አካል እንጂ ከሩቅ የመጣች እንግዳ እንዳልሆነችና በጂኦ ፖለቲካዊ ሴራዎች የባህር በር አልባ እንድትሆን መደረጓን ለአለም እያስረዳች ትገኛለች።
ኢትዮጵያ ቀይ ባህር ላይ እግሯን እንዳትተክል የሚደረጉ የተለያዩ የፖለቲካ የዲፕሎማሲ እና የፕሮፓጋንዳ ሸፍጦች አልቆሙም እነዚህን ሸፍጦች ሲጠነስሱ እንቅልፍ አጥተው የሚያድሩ አካላት መፍጨርጨራቸው ባይገታም ኢትዮጵያን በዘላቂነት ሊያግዷት አይችሉም።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም እና የአካባቢያዊ ትስስር ዋና ምሰሶ እንደመሆኗ የባህር በር ማግኘቷ ለአካባቢው ሀገራትም ቢሆን ትልቅ የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያስገኝ በመሆኑ በቅርብም በሩቅም ያሉ ሀገራት ለኢትዮጵያ ቀና ምላሽ በመስጠት በጋራ መስራትን ተመራጭ ያደርጋሉ።
ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ያለው ኢኮኖሚና ትልቅ ህዝብ ያላት ሀገር መሆኗም ይህን ግስጋሴ የሚያስተናግድ የባህር በር የማግኘት ትልሟን እውን ለማድረግ ትልቅ አቅም ይሆናታል።
በአጠቃላይ የታሪክ እውነታ የህግ መብት እና የህልውና ጥያቄ የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ አይቀሬ ያደርጉታል።
ይህንን አገራዊና ታሪካዊ ሀላፊነት ከግብ ለማድረስ የውስጥ አንድነትን ማፅናትና ደህንነትን ማረጋገጥ የሃሳብ ፖለቲካን ማጠናከር እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር ወሳኝ መፍትሄ ነው።
በአለም አቀፍ የባህር ህግጋት እና በዲፕሎማሲያዊ አማራጮች የታገዘው ይህ ጥረት የመጪውን ትውልድ መብትና እድል የማስከበር የታሪክ ጥሪም ሲሆን ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ገንብቶ ለዘላቂ ብልፅግና የሚያሸጋግር ጨዋታ ቀያሪ ምእራፍ ነው።
ዛሬ ብርቱዋ ኢትዮጵያ ለሶስት አስርት አመታት ካቀረቀረችበት ቀና ብላለች የቀይ ባህር ተጋሪነቷን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ማናቸውም ሸፍጦች ጊዜያዊ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ የህዝቧን የታሪክ እና የተፈጥሮ መብት ሊያጠፉ አይችሉም።
ኢትዮጵያ አትቆምም የጂኦ-ፖለቲካ ሴራዎችን ሁሉ በጣጥሳ ከባህሩ ትደርሳለች ባህር ሀይሏና መርከቦቿም በቀይ ባህር ዳግም ይጓዛሉ።
በብሌን ደምበሎ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #seaaccess #redsea #diplomacy

ዛሬ ሹመታቸውን የተቀበሉት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ ጋር ውይይት አደረጉ
#ethiopia | የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ጄን መሐመድ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸውም በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ የፀጥታ እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት ምክትል ዋና ፀሐፊዋ አሚና ጄን ሙሀመድ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅድሚያ በሚሰጧቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚመክሩ ተመላክቷል፡፡
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#ethiopia | የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ጄን መሐመድ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸውም በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ የፀጥታ እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት ምክትል ዋና ፀሐፊዋ አሚና ጄን ሙሀመድ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅድሚያ በሚሰጧቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚመክሩ ተመላክቷል፡፡
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
4 days ago
“ የሮናልዶ ጥፋት ጄሱስን ምንም ሳይል መውጣቱ ነው ” ሮማሪዮ
የቀድሞ ብራዚላዊ ተጨዋች ሮማሪዮ በወቅታዊ ጉዳይ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ድርጊት ያለውን ድጋፍ አሳይቷል።
“ ጆርጅ ጄሱስ ሮናልዶን በአለም ህዝብ ፊት አዋርዷል ” ያለው ሮማሪዮ “ ሮናልዶ ክብሩ ተጓድሏል ዋጋ እንደሌለው ሲሰማው ሄዷል "ብሏል።
" እኔም ብሆን ተመሳሳይ ነገር አደርጋለሁ ነገርግን አሰልጣኙን ዝም ብዬ አልሄድም " ሲል ተደምጧል።
“ ሮናልዶ የሰራው ስህተት አሰልጣኙን ጥሩ ያልሆነ ቃል ሳይናገር ለቆ መሄዱ ብቻ ነው “ ሲል ሮማሪዮ ተናግሯል።
@tikvahethsport YisakAH

“ በክለቡ አቋም ሙሉ እምነት አለን ” ኢንዞ ማሬስካ
የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በወቅታዊ ሁኔታ በክለቡ አቋም እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ስለ ክለቡ ወቅታዊ ሁኔታ የተጠየቁት ማሬስካ “ ተረጋግቻለሁ ፤ የክለቡ አቋም ግልፅ ነበር በእሱ ሙሉ እምነት አለን “ ብለዋል።
አክለውም “ የእኛ ትኩረት መቆጣጠር በምንችለው ነገር ላይ ብቻ ነው ስፖርቱን ነው መቆጣጠር የምንችለው " ሲሉ ገልጸዋል።
“ የማንችስተር ሲቲ ያለፉት አስራ አምስት አመታት ስኬት ሚስጥር በክለቡ ውስጥ ያለው አንድ አቋም እና ስምምነት ነው ” ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።

ሰበር! "ራሴን ከመከላከል ውጪ አማራጭ የለኝም" ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በደብዳቤ አሳወቀች።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት በጻፉት ደብዳቤ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን ገልጸዋል።
Seledadotio

5 days ago
በዩኒቨርሲቲዎች ስር ለሚተዳደሩ ማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመደበው የሕክምና አገልግሎት በጀት ከመደበኛው የትምህርት በጀት ስሌት ቀመር ውጪ በተናጠል ተጣርቶ የበጀት ድጋፍ እንዲቀርበለት የሚያዘው ደንብ በስራ ላይ ውሏል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከመንግሥት የሚሰጠውን የብሎክ ግራንት የበጀት አፈጻጸም ለመደንገግ ያወጣው ደንብ ቁጥር 594/2018 በስራ ላይ ውሏል።
ደንቡ ተቋማቱ በፋይናንስ ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ በሂደት እየቀነሰ የሚሄድ ዓመታዊ የበጀት ድጋፍ የሚመደብበትን ሥርዓት ያካተተ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታዎቻቸውና ስትራቴጂካዊ ዕቅዶቻቸው በመነሳት በበጀታቸው በነፃነት እንዲጠቀሙና ተልዕኳቸውን በጥራት እንዲወጡ ማስቻልን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ያስረዳል።
ደንቡ ለራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው ዓመታዊ የብሎክ ግራንት እንደ አግባብነቱ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሲባል፣ የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው ነገር ግን የትምህርት ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ተማሪዎች የሚደረግ የበጀት ድጋፍ ሊያካትት እንደሚችል ያስረዳል።
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲዎች በሚያስተዳድሯቸው ማስተማሪያ ሆስፒታሎች አማካኝነት፣ በሕግ አግባብ በነፃ ሊሰጡ ለሚገባቸው የሕክምና አገልግሎቶች እና በነፃ ማግኘት ለሚገባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚውል የበጀት ድጋፍ እንዲያገኙ ለማስቻልም ሊመደብ እንዲሚችል ይገልጻል።
እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች የሚያከናውኗቸውን የምርምርና ጥናት፣ የማኅበረሰብ ጉድኝት አገልግሎት እንዲሁም ብቁ ተቋማዊ አቅምን ለመገንባት የሚያስፈልግ የፋይናንስ ድጋፍ ሊመደብ እንደሚችል ተደንግጓል።
በዚህ ደንብ መሠረት አጠቃላይ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የበጀት ድልድል የግብዓት፣ የውጤትና የፍትሐዊነት መስፍርቶችን መሰረት የሚያደርግ ሲሆን ይህም
• የመማር-ማስተማር ሂደቱን መደበኛ ተማሪዎች ቁጥር፣
• የሳይንሳዊ ምርምር ውጤትና ተፅዕኖን፣
• የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎችን እንዲሁም
• ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን እና የተቋማቱን መልክዓ-ምድራዊ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ታሳቢ ያደርጋል።
ይህ የበጀት ማከፋፈያ ቀመር እንደ አስፈላጊነቱ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር ትብብር የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ለማጣጣም በየሁለት ዓመቱ ክለሳ ይደረግበታል።
በተለየ መልኩ፣ በዩኒቨርሲቲዎች ስር ለሚተዳደሩ ማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመደበው የሕክምና አገልግሎት በጀት ከመደበኛው የትምህርት በጀት ስሌት ቀመር ውጪ በተናጠል ተጣርቶ የበጀት ድጋፍ እንደሚደረግለት ተደንግጓል።
ይህ ድጋፍ ሆስፒታሎቹ በሕግ አግባብ በነፃ ሊሰጡ ለሚገባቸው የሕክምና አገልግሎቶችና ተጠቃሚ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚውል ሲሆን፤ ድልድሉም በሆስፒታሉ አገልግሎት ያገኙ ታካሚዎች ብዛት፣ የህክምና አልጋዎች ቁጥር፣ የአገልግሎቶቹ ውስብስብነት እንዲሁም ለመድኃኒትና ለአላቂ የሕክምና ቁሳቁሶች የሚወጣውን ወጪ መሠረት በማድረግ ይወሰናል።
በዚህም ማንኛውም ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሚያገኘው ዓመታዊ ድጋፍ አጠቃላይ የመማር-ማስተማርና የምርምር በጀቱን እንዲሁም ለማስተማሪያ ሆስፒታሎች በጥናት ላይ ተመስርቶ የሚመደበውን ልዩ በጀት በአንድ ላይ ያካተተ የተቀናጀ የብሎክ ግራንት ሆኖ ይቀርባል።
የበጀት ጥያቄ አቀራረብና አስተዳደርን በተመለከተ፣ ማንኛውም ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የበጀት ጥያቄውን በየዓመቱ እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ ለገንዘብ ሚኒስቴር ማቅረብ እንዳለበት እና የተፈቀደው በጀትም በቀጥታ ወደ ተቋማቱ ፈሰስ እንደሚደረግ ተመላክቷል።
የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማጠናከርም ትምህርት ሚኒስቴር በቁልፍ ውጤት አመላካቾች ላይ የተመሠረተ የአፈጻጸም ውል በመፈራረም በዓመት ሁለት ጊዜ ሁለንተናዊ ግምገማ እንደሚያካሂድ ተደንግጓል።
በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲዎቹ የብሎክ ግራንት ሒሳብ በፌደራል ዋና ኦዲተር እንደሚመረመርና የሒሳብ ሰነዶችም ቢያንስ ለአስር ዓመታት ተጠብቀው እንዲቆዩ በማድረግ ተጠያቂነትና ግልጽነት እንዲሰፍን ይደረጋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም

ኢትዮጵያ ውስጥ የኤርትራ ጦር ድንበር ጥሶ ገብቷል መባሉን ተከትሎ የዜጎች የተቃውሞ ድምፅ እየተሰማ ነው
#fastmereja I የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል በሚል በተስፋፋው መረጃ እና የተከሰተውን ሁኔታ አስመልክቶ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በወቅታዊው ጉዳይ ላይ ስጋታቸውን የገለጹት ዜጎች፣ የሀገሪቱ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በግልጽ እንደተደፈረ በመጥቀስ ጦሩ በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ መሬት እንዲወጣ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።
የተከሰተውን አሳሳቢ ሁኔታ አስመልክቶ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ እየተሰሙ ያሉ ድምጾች እንደሚያሳዩት፣ ዜጎች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መጠበቅ የሁሉንም ዜጋ ቀዳሚ ሃላፊነት መሆኑን በማስታወስ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በአፋጣኝ እጅግ ጥብቅና ግልጽ የሆነ ምላሽ እንዲሰጡበት አጥብቀው እየጠየቁ ይገኛሉ። የድንበር ጥሰቱ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን አንጻራዊ ሰላም ሊያናጋው ይችላል የሚል ስጋትም በህብረተሰቡ ዘንድ ጎልቶ እየታየ ነው።
እስካሁን ባለው ሁኔታ ጉዳዩን አስመልክቶ ከፌዴራል መንግስትም ሆነ ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት በይፋ የተሰጠ አጠቃላይ መግለጫ ያለመኖር ቢታወቅም፣ በሀገር ውስጥ ያለው የህዝብ ቁጣና ስጋት እየጨመረ መምጣቱን ከወጡት መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል።

በኢትዮጵያ የአፍና የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች እጥረት መኖሩ ተገለፀ
በአገሪቱ የአፍና የጥርስ ጤና ችግሮች በስፋት የሚታዩ ቢሆንም በዘርፋ የህክምና ባለሙያዎች እጥረት መኖሩን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ አስታውቋል።
በማህበረሰቡ ዘንድ ከሚስተዋሉ የጥርስ ጤና ችግሮች መካከል በዋናነት የህፃናትና የአዋቂዎች ጥርስ መበስበስ፣ የድድና የጥርስ አቃፊ አጥንት ሕመም፣ የጥርስ መርገፍ እንዲሁም የአፍና የከንፈር ካንሰር ይገኙበታል።
በሆስፒታሉ የጥርስና ማክሲሎፌሻል ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም የፊትና መንጋጋ ቀዶ ጥገና ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አዲስ ካሳሁን ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ጥርስን እስከ ማጣት ሊያደርስ የሚችለው የድድና የጥርስ አቃፊ አጥንት ህመም 18.7 በመቶ ስርጭት ሲኖረው የጥርስ መርገፍ ደግሞ 1.8 በመቶ ስርጭት እንዳለው ተናግረዋል።
የሕክምና ኮሌጁም ከመደበኛው የጥርስ ህክምና በተጨማሪ የአፍ፣ የመንጋጋና የፊት ቀዶ ጥገና ሕክምናን እንደሚሰጥ ገልጿል።ተቋሙም በየቀኑ ከ90 እስከ 140 የሚደርሱ ታካሚዎችን በማስተናገድ ሕክምናን እየሰጠ መሆኑን ዶክተር አዲስ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
በፈረንጆቹ 2022 የታተመውና በ2018 አ/ም የተሰበሰበው መረጃን ያካተተው የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ በኢትዮጵያ የሚገኙት 1 ሺህ 745 የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች ብቻ ናቸው።በዘርፋ የተሰማሩ የባለሙያዎችን ቁጥር አስመልክቶ ወቅታዊና የተጠናቀረ መረጃ ባለመኖሩ በአሁኑ ወቅት ያለው ቁጥር ከዚህ የተለየ ሊሆን እንደሚችልም ዶክተር አዲስ ገልጸዋል።
በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል

#ebola⚠️
በጎረቤት ሃገር ኬንያ የመጀመሪያው ከውጭ የገባ የኢቦላ ቫይረስ ተጠቂ ግለሰብ መሞቱ ሲረጋገጥ በቫይረሱ የተያዘው ሰው ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑን የሃገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አሳውቋል።
• የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ " በወረርሽኞች ዙሪያ ሁሌም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን የተለመዱና የአየር እና የየብስ መግቢያዎቻችን ላይ የሚሰሩ የምርመራ ስራዎች በሙሉ የቀጠሉ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በጎረቤት ሀገር ኬንያ የመጀመሪያው ከውጭ የገባ የኢቦላ (ቡንዲቡግዮ) ቫይረስ በሰው ላይ መገኘቱና የታካሚው ሕይወት ማለፉ የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል።
የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በቫይረሱ ተይዞ ሕይወቱ ያለፈው ግለሰብ ላለፉት ሰባት ዓመታት በኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ (ዲ.አር.ሲ) ይኖር የነበረ የኬንያ ዜጋ ነው።
ግለሰቡ ከዲ.አር.ሲ በየብስ ጉዞ ወደ ዩጋንዳ ካምፓላ ካመራ በኋላ፣ ኦክቶበር 3 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ) በአውሮፕላን ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሱ ተገልጿል።
በሆስፒታል በለይቶ ማቆያ ውስጥ ህክምና ሲከታተል የቆየ ቢሆንም፣ በብሔራዊ የቫይሮሎጂ ሪፈረንስ ላቦራቶሪ (NVRL) እና በኬኤምአርአይ (KEMRI) በተደረገ ምርመራ በቡንዲቡግዮ ኢቦላ ቫይረስ (Bundibugyo Ebola Virus) መያዙ ተረጋግጦ ሕይወቱ አልፏል።
ኬንያ ከሟቹ ጋር ንክኪ የነበራቸውን የቤተሰብ አባላት፣ የጤና ባለሙያዎችና አብረውት የተጓዙ መንገደኞችን የመለየትና በለይቶ ማቆያ የማስገባት ስራ እያከናወነች ትገኛለች ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የቅርብ ጎረቤት የሆነችው ኬንያ ላይ በሽታው መከሰቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ዝግጁነት ምን እንደሚመስል የጤና ሚኒስቴርን ጠይቋል።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በሰጡን ምላሽ በወረርሽኞች ዙሪያ ሁሌም ዝግጁ ነን ያሉ ሲሆን የተለመዱና የአየር እና የየብስ መግቢያዎቻችን ላይ ሁሌም የሚሰሩ የምርመራ ስራዎች አሉ እነዛን በሙሉ እየተሰሩ የቀጠሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ዶ/ር መቅደስ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ማንቂያ ደወል ሲያሰማና ሀገራት በሽታው መግባቱን ይፋ ሲያደርጉ፣ ከእነዚያ ሀገራት በሚገቡ መንገደኞች ላይ ጥብቅ ፍተሻና የክትትል ስራዎች ወዲያውኑ እንደሚተገበሩ አመልክተዋል።
"እኛ ሁልጊዜ ዝግጅት ላይ ነን፤ ስክሪን እንሰራለን፣ በአየርም በየብስም ያለው ይሰራል" ያሉት ሚኒስትሯ "ዘ ሞመንት ደብሊው ኤች ኦ (WHO) አክቲቬት ሲያደርግና አገሮች ዲክሌር ካደረጉበት ሰዓት ጀምሮ ከዛም አገር የሚመጡት ላይ ተመሳሳይ ነገሮችን ኢንፎርስ ይደረጋል፤ የተለመዱ ስራዎች ስላሉን እነዛን በሙሉ አክቲቬት አድርገናል" ብለዋል።
ቫይረሱ ከዚህ ቀደም በዲ.አር.ሲ እና በዩጋንዳ በታየበት ወቅት ጀምሮ የቅድመ ዝግጅት እርምጃዎች ሲወሰዱ መቆየታቸውን ያስታወሱት ዶ/ር መቅደስ፣ አሁን በሽታው ወደ ኬንያ መግባቱ ሲረጋገጥም የዝግጅት ደረጃው ተጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል።
"ገና ዲአርሲ ገባ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ፣ ዩጋንዳም ሲመጣ፣ አሁን ደግሞ እዚህኛውም(ኬንያ) ሲመጣ ደረጃው እያሻሻለ እየጨመረ የሚሰሩ ስራዎች ጀምረናል። ከባለድርሻ አካላት ጋር፣ የድንበር አካባቢ (ክሮስ ቦርደር) ከሚሰሩት ጋር በመረጃ መነባበብ፣ ቅድመ ዝግጅት፣ ቅኝትና ምላሽ እነዚህን በሙሉ አክቲቬት አድርገናል፤ በዛ መልክ ላይ ነው ያለነው" ሲሉ የኢትዮጵያን ወቅታዊ አቋምና ዝግጁነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

6 days ago
" ከኢትዮጵያ ጋር ላለን ጠንካራ ግንኙነት ከፍተኛ ዋጋ እንሰጣለን " - ጌዲዮን ሳር
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ጌድዮን ሳር ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዮስ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸውን ገልጹ።
ሚኒስትሩ ፤ የኢትዮጵያን አንድነትና ጸጥታ አስጠብቆ ማቆየት ለሀገሪቱም ሆነ ለቀጠናው ሰላም ያለው ወሳኝ ሚና ላይ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል።
በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ሁለቱ አገራት የጋራ ፍላጎት እንዳላቸውና ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የረጅም ጊዜ ጠንካራ ወዳጅነት ከፍተኛ ዋጋ የምትሰጥ መሆኑን አፅንዖት በመስጠት፣ የሁለቱን አገራት ሁለገብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን በውይይቱ እንዳረጋገጠች አሳውቀዋል።
ይህ ውይይት የተደረገው የእስራኤል ጎረቤት ግብፅ የቀጠናው ሀገራት የሆኑትን የኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን መሪዎች ሀገሯ ላይ ሰብስባ ስለ ቀይ ባህር፣ ስለ አባይ ወንዝ ፣ እስራኤል የሀገርነት እውቅና ስለሰጠቻት ሶማሌላንድ ስለሚሰጣት እውቅናና ድጋፍ ማውገዝ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መክራ " የጋራ " ያለችውን መግለጫ ካወጣች ከ2 ቀን በኋላ ነው።
እስራኤል፣ ጠንካራ ከሚባሉ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በይፋ ወጥተው ከደገፉ እና ከኢትዮጵያ ጎን ነን ካሉ ሀገራት በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #egypt በግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ጥሪ በግብፅ ኒው ኤል-አለሚን ከተማ የግብፅ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጎረቤታች የሆኑት የሱዳን ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የመሪዎች ስብሰባ ተካሂዶ ነበር። ስብሰባው ላይ የነበሩት ፦ - የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ - የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ (በግብፅ አውሮፕላን ተልኮላቸው ወደ ግብፅ የሄዱ) - የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ…

🚨 አሌሳንድሮ ዴል ፒዬሮ ስለ ወቅታዊው የጣሊያን እግር ኳስ፦
“የጣሊያን እግር ኳስ ከእንግዲህ ያን የቀድሞውን ደስታና ጉጉት አይፈጥርም።"
"በአንድ ወቅት ሴሪኤ የዓለም እግር ኳስ ማዕከል ነበር። ታላላቅ ኮከቦች ከምርጦቹ ጋር ራሳቸውን ለመፈተን ወደዚህ ይመጡ ነበር::"
"ጣሊያን ውስጥ መጫወት ማለት ከፍተኛው ደረጃ ላይ ደርሰሃል ማለት ነበር።"
"ዛሬ ግን ሁለተኛ ምርጫ ወደ መሆን ደርሰናል። ታላላቅ ተሰጥኦዎች ወደ እንግሊዝ፣ ወደ ስፔን እና ወደ ሌሎች ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች ይመለከታሉ።"
"ከእንግዲህ ተጫዋቾች ለመድረስ የሚመኙበት ዋነኛ መዳረሻ አይደለንም፤ ብዙ ጊዜ የአማራጭ ምርጫ ሆነናል።”
[Calciomercato]
@Bisrat_Sport_433et

የእንግሊዝ ኤንባሲ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ውጥረቱ አሳሳቢ ነው አለ
#fastmereja I የብሪታንያ (የዩናይትድ ኪንግደም) ኤንባሲ በአዲስ አበባ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታወቀ። ኤንባሲው በሰጠው መግለጫ፣ ሁሉም ኢትዮጵያውያን አካታች እና ሰላማዊ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዲኖራቸው የአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሽምግልና ጥረት ለሚደረገው ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዩናይትድ ኪንግደም ዝግጁ መሆኗን አረጋግጧል።
በመግለጫው የሰላማዊ ሰዎችን ደህንነት ማስጠበቅ ያለውን ትልቅ ፋይዳ እንደገና አፅንኦት ሰጥቶ የገለጸው ኤንባሲው፤ በተጎዱ አካባቢዎች መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ እና ህይወት አድን ዕርዳታ ለተቸገሩት እንዲደርስ ጥሪ አቅርቧል። በተጨማሪም ሁሉም አካላት ደህንነቱ የተጠበቀና ያልተገደበ የሰብአዊ ድርጅቶች እንቅስቃሴ እንዲፈቅዱ እንዲሁም የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞችን እንዲያከብሩና እንዲጠብቁ አሳስቧል።
በሌላ በኩል፣ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ባለፉት ጊዜያት እየተባባሰ በመጣው ውጥረት የተሰማውን ጥልቅ ስጋት የገለጸው የብሪታንያ ኤንባሲ፤ በክፍለ አህጉሩ የሚገኙ ሀገራት ሁሉ የጎረቤቶቻቸውን ብሔራዊ ሉዓላዊነትና ግዛት አንድነት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል።
ኤንባሲው አያይዞም ግጭቶችን ለማቀዝቀዝ፣ በንግግር ለመፍታት እንዲሁም ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁሉም ተሳታፊ አካላት አስፈላጊውን ጥረት እንዲያደርጉ አበክሮ አሳስቧል።

«ጌታቸው ረዳ ወደ መቐለ ተመለሱ‼️
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ መቐለ ከተማ ከህወሓት ታጣቂዎች ነፃ መውጣቷን ተከትሎ ወደ ከተማዋ መመለሳቸውን ሮይተርስ ዘገበ።
🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦
ወደ መቐለ መመለስ፦ የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ወደ ክልሉ መዲና መቐለ መድረሳቸውን የአለም አቀፉ የዜና ተቋም ሮይተርስ አረጋግጧል።
አካባቢያዊ ሁኔታ፦ አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ ከተማዋ የተመለሱት መቐለ ከህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ነፃ መውጣቷን ተከትሎ መሆኑ ተመላክቷል።
ወቅታዊ ሁኔታ፦ የአካባቢውን ሰላምና ወታደራዊ ሁኔታ በተመለከተ አዳዲስ መረጃዎች እየወጡ እንደሚገኙ ተገልጿል።

«ጌታቸው ረዳ ወደ መቐለ ተመለሱ» — ሮይተርስ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ መቐለ ከተማ ከህወሓት አማፂያን ነፃ መውጣቷን ተከትሎ ወደ ከተማዋ መመለሳቸውን ሮይተርስ ዘገበ።
🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦
ወደ መቐለ መመለስ፦ የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ወደ ክልሉ መዲና መቐለ መድረሳቸውን የአለም አቀፉ የዜና ተቋም ሮይተርስ አረጋግጧል።
አካባቢያዊ ሁኔታ፦ አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ ከተማዋ የተመለሱት መቐለ ከህወሓት አማፂያን ቁጥጥር ነፃ መውጣቷን ተከትሎ መሆኑ ተመላክቷል።

🚨 ሉካ ሞድሪች ስለ ሪያል ማድሪድ ወቅታዊ ሁኔታ፦
“ገና የውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ነው።
በሞውሪንሆ ስር ያለውን ማድሪድ ስመለከት፣ እንደተለመደው ለሁሉም ዋንጫዎች ለመፎካከር ዝግጁ የሆነ ድንቅ ቡድን አያለሁ።
ባርሴሎና በ6 ነጥብ እየመራ ነው ብሎ መጨነቅ ወይም ሁሉም ነገር አብቅቷል ብሎ ማሰብ አያስፈልግም።
ቡድኑ ያንን የነጥብ ልዩነት ሙሉ በሙሉ የማጥበብ እና ዋንጫውን የማሸነፍ አቅም አለው።”

7 days ago
‹‹ብሄራዊ ጥቅሞችን መሠረት ባደረገ መልኩ ከሁሉም ሀገራት ጋር እንሰራለን›› ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ
ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው የመንግስት ምስረታ መርሃ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወቅታዊ የቀጣናዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮችን ባደረጉት ንግግር ላይ አንስተዋል።
የዉጭ ግንኙነታችን የኢትዮጵያን ተፅዕኖ ለአለም በሚያሳይ መልኩ እንዲቃኝ ይደረጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፤ከሁሉም የአለም አካላት ጋር ብሄራዊ ጥቅምን መሠረት ባደረገ መልኩ አብሮ ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉ ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸዉ፤ ጎረቤቶቻችን በተፈጥሮ ያገኘናቸው ወዳጆታችን ናቸዉ ያሉ ሲሆን፤በትብብር የመስራት መርሃችንን እንገፋበታለን ብለዋል።
የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እዉን መሆን አይችልም፤ በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ይሰራል ብለዋል በንግግራቸው።
በቀጣናው ላይ የአየር የበላይነትን ለመፍጠር የሚያስችል አቅም ትገነባለች ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስተሩ አክለዋል።

" ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር (የባህር በር) እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያን ለቀጣይ አምስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመሩ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተሾሙት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል።
በዚህም ንግግራቸው በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል። ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ የባህር በር ጉዳይ ነው።
" ጎረቤቶቻችን በተፈጥሮ ያገኘናቸው ወዳጆቻችን ናቸው " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) " ከሁሉም ጎረቤቶች ጋር በሰላም ፣ በጋራ ጥቅምና በትብብር የመስራት መርሃችንን እንገፋበታለን " ብለዋል።
" ነገር ግን የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን ሊሆን አይችልምና በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን " ሲሉ ተናግረዋል።
ሌላው ያነሱት የመከላከያን ጉዳይ ነው።
" የኢትዮጵያን ታላቅነት፣ የዓለምና የአካባቢያችን ወቅታዊ ሁኔታ ብሎም የወደፊቱን የዓለም አካሄድ ያገናዘበ የመከላከያ ኃይል እንዲኖረን እንሰራለን " ብለዋል።
" በቀጣናችን የአየር የበላይነት ለመፍጠር የሚያስችል አቅም ኢትዮጵያ ትገነባለች። የሚኖረን መከላከያ ዘመናዊ ፣ ፈጣሪ፣ ሁሌም ዝግጁ ብቁና ንቁ በየአውዶቹ የመሰማራት አቅምና ቁመና ያለው ይሆናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ችግሮች ሳይፈጠሩ በፊት አስቀድሞ ማወቅና መግታት ከመጡም መከላከል ከባሰም እንደ አባቶቹ እንደልማዱ ማሸነፍ የሚችል ኃይል ሆኖ ይገነባል " ሲሉ ተናግረዋል።
ሙሉ ንግግር ፦ https://www.youtube.com/li...
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #pm
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾሟል። ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን ለተጨማሪ 5 ዓመት ለመምራት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
ኢትዮጵያን ለቀጣይ አምስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመሩ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተሾሙት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል።
በዚህም ንግግራቸው በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል። ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ የባህር በር ጉዳይ ነው።
" ጎረቤቶቻችን በተፈጥሮ ያገኘናቸው ወዳጆቻችን ናቸው " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) " ከሁሉም ጎረቤቶች ጋር በሰላም ፣ በጋራ ጥቅምና በትብብር የመስራት መርሃችንን እንገፋበታለን " ብለዋል።
" ነገር ግን የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን ሊሆን አይችልምና በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን " ሲሉ ተናግረዋል።
ሌላው ያነሱት የመከላከያን ጉዳይ ነው።
" የኢትዮጵያን ታላቅነት፣ የዓለምና የአካባቢያችን ወቅታዊ ሁኔታ ብሎም የወደፊቱን የዓለም አካሄድ ያገናዘበ የመከላከያ ኃይል እንዲኖረን እንሰራለን " ብለዋል።
" በቀጣናችን የአየር የበላይነት ለመፍጠር የሚያስችል አቅም ኢትዮጵያ ትገነባለች። የሚኖረን መከላከያ ዘመናዊ ፣ ፈጣሪ፣ ሁሌም ዝግጁ ብቁና ንቁ በየአውዶቹ የመሰማራት አቅምና ቁመና ያለው ይሆናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ችግሮች ሳይፈጠሩ በፊት አስቀድሞ ማወቅና መግታት ከመጡም መከላከል ከባሰም እንደ አባቶቹ እንደልማዱ ማሸነፍ የሚችል ኃይል ሆኖ ይገነባል " ሲሉ ተናግረዋል።
ሙሉ ንግግር ፦ https://www.youtube.com/li...
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #pm
7 days ago
ሮናልዶ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ይመለሳል ?
የፖርቹጋል እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፔድሮ ፕሮኣንካ ሮናልዶ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ይመለሳል የሚል ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንቱ በሮናልዶ እና አሰልጣኙ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
“ ሮናልዶ የፖርቹጋል ትልቁ ምልክት ነው ” ያሉት ፕሬዝዳንቱ “ ለእሱ ክብር ሊሰጥ ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።
አክለውም “ እሱ በቡድኑ ያለው ባለው ስፖርታዊ አቅም ምክንያት ነው ይሄ ሊያከራክር አይገባም "ብለዋል።
" የቴክኒክ ብቃቱ እስካለ ድረስ ሁልጊዜ የብሔራዊ ቡድኑ አካል ሆኖ ይቀጥላል እሱ ስሜታችን ይሄ መሆኑን ያውቃል “ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
በቀጣይ ከሮናልዶ ጋር ቁጭ ብለው በመነጋገር መፍትሔ እንደሚፈልጉ ፕሬዝዳንቱ ጨምረው አሳውቀዋል።
@tikvahethsport kidusyoftahe “ ሮናልዶ ስለ ቆይታው በራሱ ይወስናል ” ጆርጅ ጄሱስ “ ለመፍታት ቀላል ነገር ነው የተፈጠረው " የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጆርጅ ጄሱስ ስለ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወቅታዊ ሁኔታ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አሰልጣኙ በሰጡት ቃል “ አሁንም ሁሉም ነገር ክፍት ነው በሩ አልተዘጋም “ ሲሉ መመለስ እንደሚችል ተናግረዋል። “ ሮናልዶ ስለወደፊት ቆይታው በራሱ ይወስናል “ ያሉት አሰልጣኙ “…

የአራቱ ሀገራት መሪዎች በቀይ ባህር ጉዳይ ከቀጣናው ሀገራት ውጭ ማንም አይመለከታቸውም አሉ፤ በዓባይ ወንዝ ላይ ደግሞ የግብፅን አቋም አንፀባረቁ!
ግብፅ፣ ኤርትራ እና ሱዳን በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ጦርነት እጃቸው አለበት በሚል ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ሱዳንን ጨምረው ባካሄዱት ስብሰባ፤ የቀይ ባህር ጉዳይ የሚመለከተው ተዋሳኝ ሀገራትን እንጂ ሌሎችን አይደለም ሲሉ አቋም ያዙ፡፡ በስም አይጥቅሱ እንጂ ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄን ከ2015 ዓ.ም ክረምት አንስቶ እያንጸባረቀች መሆኑ ይታወቃል፡፡
በግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል-ሲሲ አስተናጋጅነት፤ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሃሙድ እና የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄነራል አብዱል ፋታህ አል-ቡርሃን የተሳተፉበት አራትዮሽ የምክክር ጉባኤ ትናንትና መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም በግብጿ አዲስ ከተማ ኤል አላሜይን ከተማ ተካሂዶ የጋራ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል።
መሪዎቹ በጋራ ያወጡት መግለጫ፤ የኤል-አላሜይን ስምምነት በቀጣናዊና ወቅታዊ ጉዳዮች፣ በፖለቲካዊ፣ በንግድ እና በኢኮኖሚ ትብብር እንዲሁም በአካባቢያዊ መረጋጋት ዙሪያ ላይ ያተኮረ መሆኑን ያመላክታል።
መሪዎቹ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በምታነሳው የቀይ ባህር ጉዳይ ላይ ሰፊ ወይይት አድርገዋል።
በቀይ ባህር ላይ የካርጎና መርከቦች የነፃ ዝውውር መብት መከበር እንዳለበት መሪዎቹ ያረጋገጡ ሲሆን፣ የቀይ ባህር አስተዳደር እና ቁጥጥር ብቸኛ ኃላፊነትና መብት ቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ያሉ ሀገራት ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።
የዓባይ ወንዝን ጨምሮ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን የሚገዙ ዓለም አቀፍ ህጎች መከበር እንዳለባቸው የጠቀሰው የመሪዎቹ መግለጫ፣ ጉዳት የሚመጣ መሆን እንደለሌበት ጠቅሰው በቅድሚያ ማስታወ፣ በምክክርና በስምምነት መስራት አስፈላጊ ነው ሲሉ አሳስበዋል።
አክለውም፤ የታችኛውን የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት የውሃ ጥቅም የሚጎዱ ማንኛቸውንም በአንድ ወገን ብቻ የሚወሰዱ እርምጃዎች በጽኑ እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል። ግብፅ፤ ኢትዮጵያን የተናጠል እርምጃ እየወሰደች መሆኗን ስትገልጽ መቆየቷ የሚታወስ ሲሆን ይህ የጋራ መግለጫቸውም የተለመደውን የግብፅን አቋም ያንፀባረቀ ነው።
በሌላ በኩል ደግም የሶማሊያ የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ የገለፁት መሪዎቹ፣ የሶማሊያን ግዛታዊ አንድነት የሚሸረሽሩ ማንኛቸውንም ጣልቃ ገብነቶች፣ በተለይም ለሶማሊላንድ የሉዓላዊ ሀገርነት እውቅና የመስጠት ጥረቶችን ውድቅ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪም ሶማሊያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የምታደርገውን ጥረት በመደገፍ ለአፍሪካ ህብረት የማረጋጋት ተልእኮ (አውሶም) ዘላቂ በጀት እንዲመደብ ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም ለሱዳን ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና ህጋዊ ብሔራዊ ተቋማት አለን ያሉትን ድጋፍ እናረጋግጣለን ያሉ ሲሆን ከህጋዊ ተቋማት ውጪ ትይዩ አካላትን ማቋቋምም ሆነ የውጭ ቅጥረኛ ተዋጊዎችን ማሳተፍ ተቀባይነት እንደሌለው አሳስበዋል።አራቱ ሀገራት የጉባኤውን ውሳኔዎችና ስምምነቶች አፈጻጸም የሚከታተል እና በየጊዜው እየተሰበሰበ ቅንጅታቸውን የሚያጠናክር በጋራ የሚከታተል ቡድን ለማቋቋም ተስማምተዋል።
[Addis Maleda]

የግብፅ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን መሪዎች በኢትዮጵያ ግጭትና በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የጋራ መግለጫ አወጡ
ግብፅ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን በክልሉ እየተባባሰ የመጣውን ግጭት ለመፍታት ፖለቲካዊ እና ሰላማዊ መፍትሄዎች እንዲኖሩ ጥሪ አቀረቡ።
የአራቱ ሀገራት መሪዎች ማለትም የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ እና የሱዳን ጦር አዛዥ አብዱልፈታህ አል ቡርሀን በግብፅ ኒው አላሜይን ከተማ ባደረጉት ስብሰባ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።
መግለጫው የኢትዮጵያን በርካታ ፖሊሲዎች የሚቃወም ሲሆን፣ አዲስ አበባን ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላቸውን ልዩነት የሚያሰፋ ነው።
የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ኤርትራን ጨምሮ ግብፅ እና ሱዳን በመንግሥቱ ላይ የሚዋጉትን የታጣቂዎች ጥምረት ይደግፋሉ ሲል ሲከስ, ባለስልጣናቱ ግን ተሳትፎውን አስተባብለዋል።
የኤርትራ የመረጃ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በበኩላቸው አዲስ አበባ በኤርትራ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ምክንያት እየፈለገች ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። እንዲሁም መሪዎቹ የቀይ ባህር ቁጥጥር በባህር ዳርቻ ሀገራት እጅ ብቻ መሆን እንዳለበት የገለጹ ሲሆን፣ ይህም የባህር በር ፍላጎት ላላት ኢትዮጵያ የተሰጠ ምላሽ ተደርጎ ታይቷል።
ግብፅና ሱዳንም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ በታችኛዋ ሀገራት ላይ ጉዳት የሚያደርሱ «የአንድ ወገን የተናጥል እርምጃዎችን» አስመልክቶ ስጋታቸውን አንስተዋል።

8 days ago
“ ሮናልዶ ስለ ቆይታው በራሱ ይወስናል ” ጆርጅ ጄሱስ
“ ለመፍታት ቀላል ነገር ነው የተፈጠረው "
የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጆርጅ ጄሱስ ስለ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወቅታዊ ሁኔታ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኙ በሰጡት ቃል “ አሁንም ሁሉም ነገር ክፍት ነው በሩ አልተዘጋም “ ሲሉ መመለስ እንደሚችል ተናግረዋል።
“ ሮናልዶ ስለወደፊት ቆይታው በራሱ ይወስናል “ ያሉት አሰልጣኙ “ እኔ አይደለሁም ይሄን የምወስነው ብለዋል።
የተፈጠረውን ክስተት “ አለመግባባት ነው ” ሲሉ የገለፁት ጆርጅ ጄሱስ “ ለመፍታት በጣም ቀላል ነገር ነው "ሲሉ ተናግረዋል።
ሮናልዶ በቀጣይ ጥሪ ይቀርብለት እንደሆነ የተጠየቁት አሰልጣኙ “ እሱ መጫወት ከፈለገ ለምን አይሆንም "ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
@tikvahethsport kidusyoftahe “ ስለ ሮናልዶ ከጨዋታው በኋላ እንነጋገራለን ” ጆርጅ ጄሱስ “ ሮናልዶ የፖርቹጋል ምልክት ነው " የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጆርጅ ጄሱስ ከነገው የኖርዌይ ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ እያደረጉ ይገኛሉ። ከሮናልዶ ጋር ችግራቸውን ለመፍታት ዝግጁ ስለመሆናቸው የተጠየቁት አሰልጣኙ “ አሁን ትኩረቴ ጨዋታው ላይ ነው “ ብለዋል። “ ነገርግን ይሄን ስል የክርስቲያኖ ሮናልዶን ጉዳይ…

"ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሁልጊዜም የፖርቱጋል ታላቁ የእግር ኳስ ምልክት ሆኖ ይኖራል" — ብሩኖ ፈርናንዴዝ
#ethiopia | የፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን አማካኝ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ በሰጠው አስተያየት፣ ሮናልዶ ለሀገሩ እና ለብሔራዊ ቡድኑ ያበረከተው አስተዋጽኦ እና ታላቅነት በምንም መልኩ የማይቀየር መሆኑን ገለጸ።
ብሩኖ ከሮናልዶ ጋር መነጋገሩን ጠቅሶ፣ "ክርስቲያኖ ለብሔራዊ ቡድናችን እና ለሀገራችን ሁልጊዜም ቢሆን የሁሉጊዜም ታላቁ ምልክት እንደሆነ እና እንደሚቀጥል ነግሬዋለሁ" ሲል ተናግሯል።
የፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን የተከፋፈለ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ አንድ እንደሆነ እና ይህ አንድነት ለቡድኑ ስኬት ወሳኝ መሆኑን ገልጿል።
መፈታት ያለባቸው ጉዳዮች በቡድኑ ውስጥ በሚደረግ ውይይት ለሁለቱም ወገኖች መልካም በሆነ መንገድ መጠናቀቅ እንዳለባቸው አስምሮበታል።
ሮናልዶ ከታሪክ ታላላቅ ተጫዋቾች ተራ መመደቡ ብቻ ሳይሆን፣ በሁሉም ፖርቱጋላውያን ልብ ውስጥ ሁልጊዜም ልዩ እና የጸና ቦታ ያለው ተጫዋች መሆኑን አረጋግጧል።
#portugal #ronaldo #cristianoronaldo #brunofernandes #football #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments