Logo
SeledaPost
ግብፅ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ተጨማሪ ግድቦችን እንድትገነባ «አልፈቅድም» ስትል አስጠነቀቀች

ግብፅ ኢትዮጵያ በዓባይ (ብሉ ናይል) ወንዝ ላይ ተጨማሪ የውሃ ግድቦችን እንድትገነባ በፍፁም የማትፈቅድ መሆኑን የሀገሪቱ የውሃ ሀብት እና መስኖ ሚኒስትር ሀኒ ሴዊላም አስታወቁ። ሚኒስትሩ ይፋዊ መግለጫ የሰጡት ኢትዮጵያ በወንዙ ላይ ተጨማሪ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ልትገነባ ነው መባሉን ተከተሎ ካይሮ በውሃ ደህንነቷ ላይ ያደገባትን ስጋት በድጋሚ ባንጸባረቀችበት ወቅት ነው።

ሚኒስትር ሀኒ ሴዊላም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ኢትዮጵያ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በአጠቃላይ አራት ግድቦችን በወንዙ ላይ ለመገንባት ያወጣችው እቅድ አዲስ አለመሆኑን እና ግብፅ ቀደሞውኑ የምታውቀው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። ሆኖም «የግብፅ መንግስት እነዚህ ተጨማሪ ፕሮጀክቶች ወደፊት እንዲገፉ እና እንዲተገበሩ ይፈቅዳል ወይ? መልሱ አይሆንም ነው» ሲሉ ካይሮ የተፋሰሱን የታችኛ ሀገራት መብት የማይጠብቅ እና ህጋዊ አሰሪ ውል የሌለውን ማንኛውንም ተቋም አጥብቃ የምትቃወም መሆኗን አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል ሚኒስትሩ ወቅታዊውን የአባይ ወንዝ የውሃ ፍሰት አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ፣ እስከ ነሐሴ ወር መጀመሪያ ድረስ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች ወደ ግብፅ የሚፈሰው የውሃ መጠን ከመደበኛው ወቅታዊ አማካይ መጠን በጥቂቱ ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል። ሆኖም በኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች ያለው የዝናብ ወቅት ገና በጅምር ላይ ያለ እና እስከ ነሐሴ እና መስከረም ወራት ድረስ የሚቀጥል በመሆኑ ሁኔታው የከፋ ድርቅ መከሰቱን የሚያሳይ አይደለም ሲሉ አብራርተዋል።

ግብፅ የሀገሪቱን የውሃ ደህንነት ለማስጠበቅ የዓባይ ወንዝ የጎርፍ ሁኔታን፣ የዝናብ ስርጭትን እና የውሃ ፍሰቱን በላቀ የሳተላይት እና የሃይድሮሎጂ መረጃ መከታተያ ስርአት በየዕለቱ እየተከታተለች መሆኗንም ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል።

Seledadotio
Seledadotio
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.