የ4 ሺህ ድምፆች ውክልና፡- ሀገራዊ ምክክሩ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ሲያድስ
*********************
የጥይት ቋንቋን በሰለጠነ የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት የጦር ሜዳ ጀግንነትን ደግሞ በሐሳብ ልዕልና ለመተካት የሚያስችለው አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በኢትዮጵያ ተከፍቷል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 4 ሺህ ተመካካሪዎች ያካተተውን ሰፊ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን ተከትሎ፣ ይህ ታሪካዊ ክስተት ሀገራችን ከጦርነት አዙሪት ወጥታ ወደ ዘላቂ ሰላምና የሀገር ግንባታ የምትሸጋገርበት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑ ተመላክቷል።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በማኅበረሰቡ ዘንድ እንደ ገዳ እና የሽምግልና ሥርዓቶች ያሉ የዳበረ የውይይትና የችግር አፈታት ባህል ቢኖርም፣ የፖለቲካው ማኅበረሰብ ግን ከዚህ እሴት ባለመቅዳቱ "አሸናፊ ወደ ቤተመንግሥት፣ ተሸናፊ ወደ ግዞት" የሚል አጥፊ የፖለቲካ ባህል ስር ሰዶ ቆይቷል።
ይሁንና አሁን የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ይህንን የተዛባ የፖለቲካ ትርክት በማረም ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ሂደት ነው።
በጉዳዩ ዙሪያ ሙያዊ ትንታኔያቸውን የሰጡት የማኅበራዊ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪው ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት ተሾመ ኢትዮጵያ ጠንካራ የመንግሥት ምስረታ ታሪክ ያላት ሀገር ብትሆንም፣ በውስጣዊ ክፍፍሎች እና የውጭ ኃይሎች የጂኦ-ፖለቲካ ፍላጎት ምክንያት በሚፈለገው ልክ ማደግ አለመቻሏን ይገልጻሉ።
ይሁንና በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በከተማ ልማት እና በዲፕሎማሲ እያስመዘገበች ያለችውን አበረታች ዕድገት ለማስቀጠል፣ ሀገራዊ ምክክሩ ወቅታዊ እና ወሳኝ መድኃኒት መሆኑን አስምረውበታል።
በየትኛውም የዓለም ክፍል ጦርነት ትርፍ አምጥቶ እንደማያውቅና ይልቁንም አምራች ኃይልን እና ሀገራዊ ኢኮኖሚን እንደሚያወድም ያነሱት ምሁሩ፣ የፖለቲካ ልሂቃን፣ የሚዲያ አካላት እና የሃይማኖት አባቶች አጀንዳዎቻቸውን ኦዲት በማድረግ ለትውልድ የሚሻገር ሀገር ለመገንባት በጋራ ሊቆሙ ይገባል ብለዋል፡፡
በየትኛውም ስሌት የምክክር መድረኩን መጀመር በራሱ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ሰላም እና ልማት ለሚሹ ኃይሎች ታላቅ ድል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ኢትዮጵያ በርካታ ዓለም አቀፍ ጫናዎችን ተቋቁማ ታላቁን የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራዊ ስኬቶችን ማስመዝገብ የቻለች ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ መሆን ያለበት ዘላቂ የሀገር ግንባታ ነው።
ሀገረ-መንግሥት የመመስረቱ ሂደት ቀደም ብሎ ቢጠናቀቅም በእኩልነትና በመተባበር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ማኅበረሰባዊ አንድነትን ለመፍጠር መመካከር የግድ ይላል።
ባለፈው ታሪክ ውስጥ የተፈጠሩ ቁርሾዎችንና ህመሞችን በዛሬው ዘመን የሰብአዊ መብት መነጽር ከመመዘን ይልቅ፣ ያለፈውን እንደ መማሪያ በመውሰድ ለጋራ የወደፊት ራዕይ በጋራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡
በዚህ ዘመን እውነተኛ ጀግንነት የሚለካው በጦር ሜዳ ሳይሆን፣ በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ የሰለጠነ ድርድር መሆኑንም ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡
ባለፉት አራት ዓመታት ሰፊ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ከ1 ሺህ 200 በላይ ወረዳዎችን በማዳረስና የኅብረተሰቡን አንገብጋቢ አጀንዳዎች በማሰባሰብ የሁሉንም ድምፅ ያካተተ ዴሞክራሲያዊ ሂደት እያስኬደ ይገኛል።
መላው ማኅበረሰብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየተሳተፈበት የሚገኘው ይህ መድረክ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ሁለት ዓመት ከመዋጋት፣ 20 ዓመት መወያየት ይሻላል" በማለት ያስቀመጡትን መርህ በተግባር የሚተረጉም ነው።
በመሆኑም፣ ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአንድ አዳራሽ የተሰባሰቡበት ታሪካዊ የምክክር መድረክ፣ ዜጎች ልዩነቶቻቸውን በሰለጠነ መንገድ በማንሸራሸር ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረት የሚጥሉበት ወርቃማ እድል ነው፡፡
በበረከት ሽመልስ
#ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation #nationaldialogue #nationbuilding #ebcdotstream

17 days ago