የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ም/ቤት የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ መደበኛ ጉባኤውን አጠናቀቀ
**********************
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባዔውን የቀረቡለትን አዋጆች በሙሉ ድምፅ በማጽደቅ እና ባለፉት አምስት ዓመታት ህዝብን ሲያገለግሉ የነበሩ አባላቱን በክብር በመሸኘት አጠናቅቋል።
ምክር ቤቱ በጉባዔው ቆይታው የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የዋና ኦዲተርን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶች ላይ የተወያየ ሲሆን፣ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።
በዚሁ ወቅት ለተሰናባች የምክር ቤት አባላት የእውቅና ምስክር ወረቀት ያበረከቱት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ አባላቱ ባለፉት አምስት ዓመታት በክልሉ ለተመዘገቡ ሁሉን አቀፍ የልማትና የመልካም አስተዳደር ለውጦች ትልቅ አቅም መሆናቸውን በመግለጽ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ተሰናባች አባላቱ ያካበቱትን ልምድና እውቀት በመጠቀም በቀጣይ በሚሰማሩበት መንግስታዊና ማህበራዊ የኃላፊነት መስክ ሀገራቸውን በትጋት እንዲያገለግሉም አሳስበዋል።
የምክር ቤቱ ዋና አፌ ጉባዔ አቶ ወንድሙ ኩርታ በበኩላቸው፤ የምክር ቤቱ አባላት ባለፉት አምስት ዓመታት ለህብረተሰቡ ጠቃሚ የሆኑ ደንቦችን በማውጣት፣ የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓቱን እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ በመዘርጋት እንዲሁም ወቅታዊ ግብረ-መልስ በመስጠት ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነታቸውን በብቃት ተወጥተዋል ብለዋል።
አክለውም ምክር ቤቱ በቀጣይም የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በሰለሞን ባረና

10 days ago