12 days ago
በአንድ ጥያቄ ውስጥ የተደበቀው የኢትዮጵያ የአብሮነት ፍልስፍና
**********************
"እንዴት ሰንብታችኋል?" የሚለው ለኢትዮጵያውያን ከሰላምታ በላይ ትርጉም ያለው ቃል ነው። በዚህ ጥያቄ ውስጥ "ደህና ነህ?" የሚል ብቻ ሳይሆን፣ "ምን አጋጠመህ? እንዴት አለፍክ? ምን ልረዳህ?" የሚል የመተሳሰብ፣ የመደማመጥ እና የአብሮነት መንፈስ ተደብቆ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ማኅበራዊ እሴት ውስጥ ጥያቄ ማለት መረጃ መፈለግ ብቻ አይደለም። ሰውን ማስታወስ፣ ሁኔታውን መረዳት፣ ችግሩን መስማት እና አብሮ መፍትሔ መፈለግም ጭምር ነው። ይህም የማኅበረሰባችንን የአብሮነት መሠረት ያንጸባርቃል።
እንዲሁ የሀገር ጉዳዮችም በአንድ ወገን ውሳኔ ሳይሆን፣ እርስ በርስ በመጠያየቅ፣ በመደማመጥ፣ በመከባበር እና በጋራ መፍትሔ በመፈለግ ዘላቂ መልስ ያገኛሉ። ስለዚህ የምክክር መንፈስ በውይይት አዳራሾች ብቻ የሚወለድ ሳይሆን፣ በየቤታችን፣ በየመንደራችንና በየዕለቱ በምንለው "እንዴት ሰንብታችኋል?" ውስጥ ለዘመናት ሲኖር የቆየ ማኅበራዊ እሴት ነው።
ከሐምሌ 8 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ መድረክም ይህ የመደማመጥ መንፈስ በሰፊው ታይቷል። ከተለያዩ ክልሎች፣ ማኅበረሰቦች እና ሙያዎች የመጡ ተመካካሪዎች ሐሳባቸውን በመግለጽና ሌሎችን በማዳመጥ የጋራ መፍትሔ የሚፈለግበት መድረክ መፍጠር ተችሏል።
በዚሁም የሀገራዊ ምክክር መንፈስ ለኢትዮጵያ እንግዳ የሆነ አዲስ ሐሳብ ሳይሆን፣ በማኅበራዊ ባህላችን ውስጥ ለዘመናት የቆየ የመደማመጥና የመተሳሰብ እሴት ዘመናዊ መገለጫ ነው።
ይህ የተጻፈ ሕግ አልነበረም፤ ግን ከብዙ ሕጎች በላይ ሰዎችን ያስተሳሰረ የማኅበረሰብ ሥርዓት ነበር። የኢትዮጵያ ባህል ከሽማግሌ ሥርዓት እስከ ዕርቅ፣ ከጎረቤት መተጋገዝ እስከ ቤተሰብ ውይይት መጀመሪያ መጠየቅን፣ ማዳመጥን እና መረዳዳትን ያስቀድማል።
ዛሬም ኢትዮጵያ የምትፈልገው ይህንኑ መንፈስ ነው። መጀመሪያ መጠየቅ፣ ከዚያ ማዳመጥ፣ ከዚያ መረዳት፣ በመጨረሻም አብሮ መፍትሔ መፈለግ ለሀገር እድገት በአንድ ላይ መቆምን ያረጋግጣል።
የአንድ ሕዝብ የመተሳሰብና የመደማመጥ መጀመሪያ የሆነው የአብሮነት መሠረት ከተለያዩ የሐሳብ ልዩነቶች የሚመጣ ምክክር ነው።
ከሁሉም በላይ ደግሞ በኢትዮጵያውያን ዕለታዊ ሕይወት ውስጥ ለዘመናት የተገነባ የመተሳሰብና የምክክር ባህል ምልክት ነው።
ከብዙ ሺህ ቃላት በፊት አንድ ጥያቄ ነበር። ‘እንዴት ሰንብታችኋል?' የሚለው ጥያቄ! የኢትዮጵያውያንን የመተሳሰብ እና የመደማመጥ ባህልን በሚያሳይ አንድ ምሳሌ ነው።
በልዩ እሸቱ
#ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation #nationaldialogue #culturalvalue #nationbuilding

ጀግንነት በሰላማዊ ግንባር | የቀድሞ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ #nationaldialogue #peacefuldialogue #nationbuilding #ethiopianunity #peaceandconsensus
12 days ago
ሀገራዊ ምክክር፡- ኢትዮጵያ የነገ መሠረቷን የምትጥልበት ታሪካዊ ጉዞ
************************
ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከምሁሩ እስከ አርሶ አደር፣ ከሸኽ እስከ ቄስ ከከተማው እስከ ገጠሩ ማኅበረሰብ ድረስ "አጀንዳችሁ ሀገርን ያቀናል፤ ብንመክርበት ለመግባባት መንገዳችን ይበጃል" በሚል እምነት ሥራውን የጀመረው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ በመዲናዋ አዲስ አበባ ተመካካሪዎችን በማሰባሰብ የምክክር ጉባኤውን በይፋ ከጀመረ ቀናትን አስቆጥሯል።
የምክክሩ ሂደት ልዩነቶች እንደ ስጋት ሳይሆኑ፣ እንደ ሀገራዊ ፀጋና በረከት የሚታዩበትን አዲስ የፖለቲካ ባህል ለማጎልበት ያለመ ነው። የተለያዩ ሐሳቦች በመደማመጥ ወደ ጋራ መግባባት የሚያመራ ሂደት እንዲጠናከርም ይጠበቃል።
ኢትዮጵያውያን ከጥንት አያት ቅድመ አያቶቻቸው ያካበቱት ታላቅ ጥበብ ቢኖር አለመግባባቶችን በውይይትና በሽምግልና የመፍታት ባህል ነው። ከዋርካ ሥር በመሰባሰብ ቅራኔዎችን ማለዘብ፣ በባህላዊ የእርቅ ሥርዓቶች ስብራቶችን ጠግኖ ግንኙነቶችን ማደስ የዚህች ሀገር የቆየና የማይነጥፍ እሴት ነው።
ኢትዮጵያ በታሪኳ የጀግንነት ድሎችንና የጥንካሬ ማረጋገጫዎችን እንዳስመዘገበች ሁሉ፣ ፈታኝ የሚባሉ ጊዜያትንም አሳልፋለች።
ያልተፈቱ የፖለቲካ ችግሮች፣ የታሪክ ቅሬታዎች እና የፍትሕ ጉድለቶች በሕዝቦች መካከል እንደ ዘመናት እንቅፋት ሆነው ቆይተዋል። እነዚህ ተግዳሮቶችም አንዳንዴ የግጭትና የመከፋፈል እሳትን እየለኮሱ የአለመግባባት መንፈስ እንዲነግስ አድርገዋል።
ዛሬ ግን ያንን የቁስልና የቅሬታ ምዕራፍ የመዝጊያው ጊዜ ደርሷል። ኢትዮጵያ ከአራቱም ማዕዘን ከተሰባሰቡ በልጆቿ ጥበብ ልዩነቶቿን በጠረጴዛ ዙሪያ ልትፈታ ቁጭ ብላለች።
የዚህ ሀገራዊ ምክክር መዳረሻ ግቡም ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በመቋጨት፣ ለመጪው ትውልድ የተረጋጋች፣ ያደገችና የተባበረች ኢትዮጵያን ማስረከብ ነው።
ይህ ምክክር ከላይ የተጫነ ውሳኔ ሳይሆን፣ መነሻውን ከታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል ያደረገ ሕዝባዊ ሂደት ነው። ከወረዳ ጀምሮ የተካሄደው አጀንዳ የማሰባሰብ ተግባር፣ እያንዳንዱ ዜጋ የችግሩ ተናጋሪ ብቻ ሳይሆን የመፍትሔውም አካል መሆኑን ያረጋገጠ ነበር።
የብዙኃኑ ኢትዮጵያዊ ብሶት፣ ጥያቄ እና የነገ ተስፋ በሂደቱ ውስጥ ተንጸባርቋል። እያንዳንዱ ዜጋም በሀገሩ የወደፊት አቅጣጫ ላይ የራሱን ዐሻራ እንዲያሳርፍ ወርቃማ ዕድል ፈጥሯል።
ውስብስብ ችግሮችን በውይይት የመፍታት፣ ለዘመናት ሥር የሰደዱና ፈታኝ የሆኑ ጉዳዮችን በመግባባት ለመቋጨት እየተካሄደ ያለው የሀገራዊ ምክክር ሂደት፣ የኢትዮጵያን አዲስ አቅጣጫ ያሳያል።
ኢትዮጵያ ከግጭት ይልቅ ውይይትን፣ ከመከፋፈል ይልቅ መግባባትንና አንድነትን የምትመርጥበት ታሪካዊና አዲስ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። ይህ ምዕራፍ ደግሞ የነገዋን ሀገር በፅኑ መሠረት ላይ የመገንባት ታላቅ ጉዞ ነው።
በመቅደላዊት ደረጀ
#ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation #nationbuilding #nationaldialogue

17 days ago
የ4 ሺህ ድምፆች ውክልና፡- ሀገራዊ ምክክሩ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ሲያድስ
*********************
የጥይት ቋንቋን በሰለጠነ የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት የጦር ሜዳ ጀግንነትን ደግሞ በሐሳብ ልዕልና ለመተካት የሚያስችለው አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በኢትዮጵያ ተከፍቷል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 4 ሺህ ተመካካሪዎች ያካተተውን ሰፊ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን ተከትሎ፣ ይህ ታሪካዊ ክስተት ሀገራችን ከጦርነት አዙሪት ወጥታ ወደ ዘላቂ ሰላምና የሀገር ግንባታ የምትሸጋገርበት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑ ተመላክቷል።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በማኅበረሰቡ ዘንድ እንደ ገዳ እና የሽምግልና ሥርዓቶች ያሉ የዳበረ የውይይትና የችግር አፈታት ባህል ቢኖርም፣ የፖለቲካው ማኅበረሰብ ግን ከዚህ እሴት ባለመቅዳቱ "አሸናፊ ወደ ቤተመንግሥት፣ ተሸናፊ ወደ ግዞት" የሚል አጥፊ የፖለቲካ ባህል ስር ሰዶ ቆይቷል።
ይሁንና አሁን የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ይህንን የተዛባ የፖለቲካ ትርክት በማረም ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ሂደት ነው።
በጉዳዩ ዙሪያ ሙያዊ ትንታኔያቸውን የሰጡት የማኅበራዊ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪው ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት ተሾመ ኢትዮጵያ ጠንካራ የመንግሥት ምስረታ ታሪክ ያላት ሀገር ብትሆንም፣ በውስጣዊ ክፍፍሎች እና የውጭ ኃይሎች የጂኦ-ፖለቲካ ፍላጎት ምክንያት በሚፈለገው ልክ ማደግ አለመቻሏን ይገልጻሉ።
ይሁንና በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በከተማ ልማት እና በዲፕሎማሲ እያስመዘገበች ያለችውን አበረታች ዕድገት ለማስቀጠል፣ ሀገራዊ ምክክሩ ወቅታዊ እና ወሳኝ መድኃኒት መሆኑን አስምረውበታል።
በየትኛውም የዓለም ክፍል ጦርነት ትርፍ አምጥቶ እንደማያውቅና ይልቁንም አምራች ኃይልን እና ሀገራዊ ኢኮኖሚን እንደሚያወድም ያነሱት ምሁሩ፣ የፖለቲካ ልሂቃን፣ የሚዲያ አካላት እና የሃይማኖት አባቶች አጀንዳዎቻቸውን ኦዲት በማድረግ ለትውልድ የሚሻገር ሀገር ለመገንባት በጋራ ሊቆሙ ይገባል ብለዋል፡፡
በየትኛውም ስሌት የምክክር መድረኩን መጀመር በራሱ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ሰላም እና ልማት ለሚሹ ኃይሎች ታላቅ ድል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ኢትዮጵያ በርካታ ዓለም አቀፍ ጫናዎችን ተቋቁማ ታላቁን የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራዊ ስኬቶችን ማስመዝገብ የቻለች ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ መሆን ያለበት ዘላቂ የሀገር ግንባታ ነው።
ሀገረ-መንግሥት የመመስረቱ ሂደት ቀደም ብሎ ቢጠናቀቅም በእኩልነትና በመተባበር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ማኅበረሰባዊ አንድነትን ለመፍጠር መመካከር የግድ ይላል።
ባለፈው ታሪክ ውስጥ የተፈጠሩ ቁርሾዎችንና ህመሞችን በዛሬው ዘመን የሰብአዊ መብት መነጽር ከመመዘን ይልቅ፣ ያለፈውን እንደ መማሪያ በመውሰድ ለጋራ የወደፊት ራዕይ በጋራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡
በዚህ ዘመን እውነተኛ ጀግንነት የሚለካው በጦር ሜዳ ሳይሆን፣ በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ የሰለጠነ ድርድር መሆኑንም ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡
ባለፉት አራት ዓመታት ሰፊ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ከ1 ሺህ 200 በላይ ወረዳዎችን በማዳረስና የኅብረተሰቡን አንገብጋቢ አጀንዳዎች በማሰባሰብ የሁሉንም ድምፅ ያካተተ ዴሞክራሲያዊ ሂደት እያስኬደ ይገኛል።
መላው ማኅበረሰብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየተሳተፈበት የሚገኘው ይህ መድረክ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ሁለት ዓመት ከመዋጋት፣ 20 ዓመት መወያየት ይሻላል" በማለት ያስቀመጡትን መርህ በተግባር የሚተረጉም ነው።
በመሆኑም፣ ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአንድ አዳራሽ የተሰባሰቡበት ታሪካዊ የምክክር መድረክ፣ ዜጎች ልዩነቶቻቸውን በሰለጠነ መንገድ በማንሸራሸር ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረት የሚጥሉበት ወርቃማ እድል ነው፡፡
በበረከት ሽመልስ
#ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation #nationaldialogue #nationbuilding #ebcdotstream

23 days ago
23 days ago
ዳግማዊ ዓድዋ በሰላም እና በምክክር ሊደገም በታሪካዊው ቀን ዋዜማ ላይ ተገኝተናል - ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)
*************************
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ዋና ጉባኤውን ለማካሄድ በዋዜማ ላይ የሚገኘውን ሀገራዊ ምክክር አስመልክተው ከኢቢሲ የዳጉ ፕሮግራም ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ኮሚሽነሩ በቆይታቸው፣ ኢትዮጵያውያን የዓድዋ ድላቸውን በሰላም እና በምክክር ሊደግሙት በታሪካዊው ጉባኤ ዋዜማ ላይ እንገኛለን በማለት ነው ስለ ሀራዊ ምክክሩ የገለጹት።
ኮሚሽኑ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ የገጠሙትን የባህል እና የፖለቲካ ተግዳሮቶች እንዲሁም በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፎ ለዘመናት የተከማቹ ቅሬታዎችን እና ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀጠሮ ለያዘበት ወሳኝ ምዕራፍ መድረሱን ጠቅሰዋል።
ለዚህ ታላቅ ጉባኤ ስኬት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እና ማኅበረሰቦች የተውጣጡ ከ4 ሺህ በላይ ዜጎች እንዲሁም ዳያስፖራዎች አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፣ ከተማዋን እንዲለምዱ እና እርስ በርስ እንዲተዋወቁ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንደተከናወኑ አንስተዋል።
የጉባኤውን መቃረብ አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የ5 ኪሎ ሜትር የሰላም ሩጫ ላይ ከ20 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን መሳተፋቸውን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
በዚህም ወጣቶች እና ጎልማሶች “ሰላም ለሀገራችን” እና “ጦርነት አንሻም” የሚሉ መልዕክቶችን በማስተጋባት ለሰላም ያላቸውን ጽኑ ፍላጎት ማሳየታቸውን ተናግረዋል።
በሂደቱ ሕዝቡ ያቀረባቸውን ከ2 ሺህ በላይ አጀንዳዎች በማጠቃለል 8 ዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ተቀርጸው ይፋ ተደርገዋል።
እንደ ሀገር ግንባታ፣ የፖለቲካ እና የመንግሥት አደረጃጀት እንዲሁም የሰላም ግንባታ ባሉት በእነዚህ መሠረታዊ አጀንዳዎች ላይ ለመምከር ኢትዮጵያውያን ለረቡዕ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ መያዛቸውን ጠቅሰዋል።
እስካሁን ያልተወከሉ የፖለቲካ ድርጅቶች እና በጫካ የሚገኙ ታጣቂ ኃይሎች ተወካዮቻቸውን መርጠው አጀንዳቸውን እንዲሰጡ እና ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ እንዲመጡ ዶ/ር ዮናስ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።
“ሁለት እጆቻችንን ዘርግተን እየጠበቅናቸው ነው፤ ለምክክር የሚረፍድ ጊዜ የለም” ነው ያሉት ዶ/ር ዮናስ በመልዕክታቸው።
ለዚሁ ዓላማ፣ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለሃይማኖት አባቶች እና ለጸጥታ አካላትም የትብብር ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን፣ በተጨማሪም የሰዎችን አዕምሮ የመግዛት እና የመለወጥ ኃይል ላላቸው የመገናኛ ብዙኃንም ትልቅ አደራ ሰጥተዋል።
በዚህ ወሳኝ ታሪካዊ ወቅት ሊሰራጩ የሚችሉ የሐሰት ወሬዎችን እና የተሳሳቱ መረጃዎችን በመከላከል ረገድ በተለይ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና ሌሎች ሚዲያዎች የነቃ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#ethiopia #nationaldialogue #nationaldialogue #socialcontract #nationbuilding #ebc

Sponsored by
Surafel
1 month ago
Ethiopia’s Next Big Leap
*************
The Blueprint for Ethiopia’s Economic Resurgence
#ethiopia #pmabiyahmed #nationbuilding #ethiopiadelivers
1 month ago
የትኛውም ትውልድ የሀገር ግንባታን ብቻውን ስለማያጠናቅቅ፣ ሁላችንም መሠረቱን የማጠናከር የጋራ አደራ አለብን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
********************
ሀገር መገንባትን መንግሥት፣ ገበያውም ሆነ ማኅበረሰቡ ለብቻቸው ሊወጡት ስለማይችሉ ሁሉም በጋራ ሊረባረብ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ኢትዮጵያ ታከናውናለች" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው መድረክ ላይ እንዳብራሩት፣ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ትውልድ በተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ ብቁ ሆኖ እንዲያድግ እና እንዲበለጽግ ማዘጋጀት እጅግ ወሳኝ ነው።
ለዚህም ጥራት ያለው ትምህርት እና የሥራ ዕድሎች በሰፊው መገኘታቸውን ማረጋገጥ፣ እንዲሁም የምንገነባቸው ተቋማት የትውልዱን አቅም በሚገባ አልምተው የሚያወጡ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የሀገር ግንባታ ሂደት የሁሉንም አካላት ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "የጀመርናቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እውነተኛ ስኬት የሚለካው በሚያመጡት ተጨባጭ ውጤት" ነው ብለዋል።
ሪፎርሞቹ ተወዳዳሪ የሆኑ ኩባንያዎችን መፍጠር መቻላቸውን፣ በቂ የሥራ ዕድል መክፈታቸውን እንዲሁም ለሁሉም ማኅበረሰቦች እና ትውልዶች የሚተርፍ ዘላቂ ብልጽግናን ማምጣት መቻላቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ የሀገራዊ ትራንስፎርሜሽን ጉዞው ስኬታማ መሆን አለመሆኑን እንደሚያመላክት አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ ይህን የለውጥ ምዕራፍ በራስ መተማመን እና በግልጽነት እንደምትጋፈጠው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ሀገራችን በጋራ መከባበር ላይ የተመሠረተ ውይይትን እንዲሁም በላቀ ጥበብ እና በጋራ ዓላማ ወደፊት ለመራመድ የሚያስችሉ ጠንካራ አጋርነቶችን እንደምትፈልግ አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት መላው ዓለም የኢትዮጵያን ትራንስፎርሜሽን ከፊሉ በማበረታታት፣ ከፊሉ ደግሞ በጥርጣሬ እየተከታተለው መሆኑን አንስተዋል።
የመንግሥት ግልጽ ግዴታ ግን የሕዝብን ፍላጎት እና ምኞት ማገልገል፣ ዕድሎችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በሰፊው ማዳረስ፣ እንዲሁም ጠንካራ፣ ፍትሐዊ እና ዘላቂ ተቋማትን መገንባት ስለመሆኑ በአፅንዖት ተናግረዋል።
የትኛውም ትውልድ የሀገር ግንባታ ሥራን ብቻውን ፈጽሞ እንደማያጠናቅቅ በማንሳት እያንዳንዱ ትውልድ ጠቃሚ የሆኑ እሴቶችን የመጠበቅ፣ ስህተቶችን የማረም እና ቀጣዩ ትውልድ የሚገነባበትን መሠረት የማጠናከር የጋራ አደራና ኃላፊነት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ይህ ታላቅ ሥራ "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" እንደሚባል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እርሱም ሀገራችን ወደፊት የምታሳካው ታላቅ የመመንጠቅ ዕድገት መጀመሪያ መሆኑን አብራርተዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #nationbuilding #sharedresponsibility #ethiopiadelivers #ebc

3 months ago
በማህበራዊ ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶችና ሚኒስትሮች ያቀረቡት ሪፖርት #abiyahmed #ethiopia #pmoethiopia #prosperity #socialdevelopment #ethiopianpolitics #nationbuilding
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...

Comments