(ዘ-ሐበሻ ዜና) 'ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት' የተሰኘው ስብስብ በቅርቡ ሶስት ሰላማዊ የፖለቲካ ታጋዮች መታሰራቸውን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ፣ ድርጊቱ በሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ጫና እንደሚያሳድር ገልጾ፣ መንግስት የታሰሩትን ግለሰቦች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አሳሰበ። ስብስቡ በዚሁ ወቅታዊ መግለጫው "የሠላማዊ ትግል በሮችን በሙሉ ዘግቶ የጦርነት በሮች እንዲከፈቱ ሳይታክት የሚሠራ አለ ወይ?" ሲል ጠንከር ያለ ጥያቄ አቅርቧል።
ስብስቡ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብለው የሚያምኑት አቶ አበበ አካሉ፣ አቶ ይስኃቅ ወልዳይ እና ጠበቃ አበራ ንጉሥ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ለእስር መዳረጋቸው በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሯል። ይህንን ክስተትም እጅግ አስደንጋጭ ሆኖ እንዳገኘው አስታውቋል።
አሁን ስራ ላይ ባለው ህገ መንግስት አንቀጽ 29 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ ማንኛውም ሰው ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን በነጻነት የመግለጽ፣ በምንም አይነት የማሰራጫ ዘዴ መረጃን የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት መብቱ የተረጋገጠ መሆኑን መግለጫው አስታውሷል። ይሁን እንጂ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ፣ ከህገ መንግስቱ ባፈነገጠ መልኩ ከውዳሴ በስተቀር ምንም አይነት የተቃውሞ እና የትችት ድምጾች እንዳይሰሙ ማሳደድ ያልተጻፈ ህግና መርህ መሆኑን ስብስቡ በመግለጫው አትቷል።
ይህ አካሄድ "ሰላማዊ ትግል ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ሌሎች አማራጮች እንዲናኙ የሚሰራ ግራ ሃይል ተፈጥሯል ወይ?" የሚል ጥርጣሬ እንዳሳደረበት 'ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት' በግልጽ አስቀምጧል። በመሆኑም መንግስት በጠባብ ቀዳዳ የምትታየውን የፖለቲካ ምህዳር ጭራሹኑ ከማጥፋት ክፉኛ ሊጠነቀቅ ይገባል በማለት፣ በእስር ላይ የሚገኙት የሰላማዊ ፖለቲካ ታጋዮች የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪውን አስተላልፏል።

2 days ago