Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢራን አብዮታዊ ዘብ የየብስ ኃይል አዛዥ የሆኑት ሞሀመድ ካራሚ፣ በምዕራብ ኢራን የሚገኙት ታጣቂዎች ከቀጠናው ውጭ ባሉ ጠላቶች ወይም በአሸባሪ ቡድኖች ሊፈጸም ለሚችል ማንኛውም "የተሳሳተ ስሌት" አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

አዛዡ በኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ የሀምዜ ሰይድ አል-ሹሀዳ ዕዝ ታጣቂዎች በስለላ መረጃ፣ በዘመቻ ዝግጁነት እንዲሁም እምነትን፣ ቴክኖሎጂን እና ዘመናዊ ሳይንሶችን በማቀናጀት ለማንኛውም ስጋት ቆራጥ እና የማያዳግም ምላሽ ለመስጠት በተሟላ ዝግጁነት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ይህ በእንግሊህ እንዳለ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ እና የኦማን አቻቸው በድር አል-ቡሳይዲ ምሽት ላይ በስልክ ባደረጉት ውይይት በቀጠናው ወቅታዊ የፖለቲካ እና የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ኢራናዊው ከፍተኛ ዲፕሎማት በቴሌግራም ገጻቸው ይፋ አድርገዋል።

ኦማን እና ኢራን በሁለቱም ሀገራት የውሃ ክልል በሚያዋስነው የሆርሙዝ ስትሬት አዲስ የባህር ላይ መስመር ለመክፈት ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ። ይህንን ተከትሎም ባለፈው ምሽት አራግቺ ለኢራን ካቢኔ ባቀረቡት ሪፖርት፣ በቴህራን እና በሙስካት (ኦማን) መካከል እየተካሄደ ያለው ይህ የውሃ መስመር ድርድር "ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ እየተቃረበ" መሆኑን አረጋግጠዋል።

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.