2 hours ago
የቅዱስ ላሊበላን ታሪክና መንፈሳዊ ትርጉም የሚዳስስ መጽሐፍ በሁለት ቋንቋዎች ተዘጋጀ
#ethiopia | የቅዱስ ላሊበላን ታሪክ፣ መንፈሳዊ ትርጉምና ከአንድ ወጥ አለት ቤተ ክርስቲያናቱን ልዩ ጥበብ ለዓለም ለማስተዋወቅ ያለመ መጽሐፍ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተዘጋጅቷል።
በቅዱስ ላሊበላ ተወልደው አድገው ከልጅነታቸው ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የቆዩት ቀሲስ ፈንታ ታደሰ ዘ ላሊበላ፣ የከተማዋን ታሪክና መንፈሳዊ ቅርሶች በማጥናት፣ በመጻፍና በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ለሕዝብ በማድረስ ለዓመታት ሲሠሩ መቆየታቸውን ገልጸው በተለይም የቅዱስ ላሊበላን ታሪክና በአካባቢው የሚገኙ መንፈሳዊ ቦታዎችን ለሰፊው ሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ የጀመሩትን ጥረት በአሁኑ ወቅትም እያስቀጠሉ ይገኛሉ።
ቀሲስ ፈንታ እንደገለጹት፣ ከዓመታት በፊት የቅዱስ ላሊበላን ታሪክ በቴፕ ካሴት በመቅዳት ለሕዝብ የማቅረብ ሥራ ጀምረዋል። በኋላም በቪዲዮና በቪሲዲ በመቅረጽ የታሪኩን ይዘት ከምስል ጋር በማቅረብ፣ ሰዎች ስለ ቅርሶቹ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ሠርተዋል። ይህ ጥረት በኋላ ወደ መጻሕፍት ጽሕፈት የተሸጋገረ ሲሆን፣ ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ በአማርኛ ቋንቋ የተለያዩ መጻሕፍትን በማዘጋጀት ስለ ቅዱስ ላሊበላና ስለ አካባቢው ታሪክ የሚገኙ መረጃዎችን ለማሰባሰብና ለማቅረብ ጥረት አድርገዋል።
የቀደሙት የታሪክ አዋቂዎች ያካፈሏቸውን ትረካዎች፣ የአካባቢውን ታሪካዊ መረጃዎችና የተለያዩ መጻሕፍትን በማንበብ ያገኟቸውን ግንዛቤዎች በማጣመር የቅዱስ ላሊበላን ታሪክ ለሰዎች በቀላሉ ሊገባ በሚችል መልኩ ለማቅረብ እንደሠሩ አስረድተዋል።
አሁን ይፋ ለማድረግ የተዘጋጁት መጻሕፍት ከቀደሙት ሥራዎቻቸው የሚለዩበት ዋነኛ ገጽታ የቅዱስ ላሊበላን ታሪክ በእንግሊዝኛም ማቅረባቸው ነው። በአማርኛ የቀረበው መጽሐፍ «ቅዱስ ላሊበላ፡ በእምነት የታነጸ ቅዱስ ዓለት» የሚል ርዕስ ሲኖረው፣ የእንግሊዝኛው ርዕስ “A Sacred Rock Built by Faith” ነው። የሥራው ዋነኛ ዓላማ በዓለት ውስጥ ተቀርጸው የተሠሩትን ቤተ ክርስቲያናት ከሥነ ሕንፃ ጥበባቸው ባሻገር ባላቸው መንፈሳዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉም ለማስረዳት መሆኑን ገልጸዋል።
በቀሲስ ፈንታ እይታ፣ የቅዱስ ላሊበላ ቤተ ክርስቲያናት የግንባታ ጥበብ ብቻ ሳይሆኑ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚገኙ ታሪኮችና መንፈሳዊ ምሳሌዎች በምድር ላይ በሕንፃና በቦታ አቀማመጥ የተገለጹበት ድንቅ ውጤት ናቸው። መጽሐፉም ይህንን ግንኙነት በማብራራት፣ በቅርሶቹ ውስጥ የተካተቱ መንፈሳዊ ትርጉሞችን ለአንባቢያን ለማስገንዘብ ይሞክራል።
በተለይም በቅዱስ ላሊበላ የሚገኙት አሥሩ የዓለት ቤተ ክርስቲያናት በሦስት ምድቦች እንደሚታዩ በመግለጽ፣ በአንዳንድ የቱሪዝም ትረካዎችና በታሪክ ገለጻዎች የሚሰሙ የቁጥር ልዩነቶችን ለማብራራት ጥረት አድርገዋል። በተለይ ደብረሲና እና ጎልጎታ የሚባሉት ቦታዎች በአንድ ምድብ ውስጥ እንደሚቆጠሩ በማስረዳት፣ በመረጃ ላይ የተመሠረተ የታሪክ ገለጻ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
መጽሐፉ ከቤተ ክርስቲያናቱ ብቻ በላይ በቅዱስ ላሊበላና በዙሪያዋ የሚገኙ ተራሮችን፣ የውኃ ማፋሰሻዎችንና ሌሎች መንፈሳዊ ትርጉም ያላቸውን ቦታዎችም ይዳስሳል። እነዚህ ቦታዎች ከምድራዊትና ከሰማያዊት ኢየሩሳሌም፣ ከኖኅ መርከብና ከሌሎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪኮች ጋር በምሳሌነት የሚገናኙበትን መንገድ ያብራራል። ይህም ቅዱስ ላሊበላን ከታሪካዊ ቅርስነቷ ባሻገር በመንፈሳዊ ትርጉም የተሞላች ስፍራ እንደሆነች ለማሳየት ያለመ ነው።
ቀሲስ ፈንታ በተጨማሪም የቅዱስ ላሊበላን ታሪክ ሲያስጎበኙ ከሚያጋጥሟቸው ችግሮች አንዱ የታሪክ መረጃዎችን በትክክል ሳይመረምሩ ማቅረብ መሆኑን ጠቅሰዋል። አንዳንድ ጊዜ በመጻሕፍት የተጻፈውና በቦታው ላይ የሚታየው ሁኔታ በተለያየ መልኩ ሊተረጎም እንደሚችል በመግለጽ፣ አስጎብኚዎችና የታሪክ ጸሐፊዎች ምንጮችን በጥንቃቄ በማንበብና በማነጻጸር ለሕዝብ ትክክለኛ ገለጻ እንዲያቀርቡ አሳስበዋል።
የመጽሐፉ ዝግጅት በአካባቢው ያሉ ታሪካዊ ትረካዎችን በመሰብሰብ፣ የተለያዩ የጽሑፍ ምንጮችን በማንበብና የቅርሶቹን አቀማመጥ ከመንፈሳዊ ትርጉማቸው ጋር በማገናኘት የተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል። በዚህም የላሊበላን ታሪክ ለማወቅ ለሚፈልጉ ተመራማሪዎች፣ ተማሪዎች፣ አስጎብኚዎችና ለሰፊው ሕዝብ ጠቃሚ የመረጃ ምንጭ እንደሚሆን ተስፋ አድርገዋል።
መጽሐፉ በእንግሊዝኛና በአማርኛ ቋንቋዎች በአማዞን የሕትመት መድረክ ለአንባቢያን እንዲደርስ መዘጋጀቱን ቀሲስ ፈንታ ገልጸዋል። በዚህም በኢትዮጵያ ያሉ አንባቢያንን ብቻ ሳይሆን፣ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንንና ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ፍላጎት ያላቸውን የዓለም ሕዝቦች ለማድረስ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የቅዱስ ላሊበላ ታሪክን ማወቅ የአንድን ከተማ ታሪክ ከመረዳት በላይ ለኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ኩራትን ለማጠናከርና ቅርሶችን ለመጠበቅ ያለውን ጠቀሜታ አጉልተዋል። በተለይ ወጣቱ ትውልድ ስለ ቅርሶቹ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ፣ የአገሩን ታሪክ እንዲያውቅና ለቀጣዩ ትውልድ እንዲያስተላልፍ ጥሪ አቅርበዋል።
መጽሐፉን ለማግኘት፦ "A Sacred Rock Built by Faith – Amazon" (https://a.co/d/08eeJyZc)
በጌትነት ተመስገን
#lalibela #saintlalibela #ethiopia #ethiopianheritage #rockhewnchurches #lalibelahistory #ethiopianorthodox #orthodoxtewahedo #ethiopianculture #religiousheritage #worldheritage #unescoheritage

3 hours ago
እንኳን ለልደታ ለማርያም አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏
ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ በትንቢቱ ኢሳ 7፡14 "ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች" ብሎ የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡ ይህች ቀን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት በመዝ 44÷9 "የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" ብሎ የተናገረላት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተገኘችባት ናት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕይ 12÷1 "ፀሐይን የተጎናጸፈች፣ ጨረቃን የተጫማች፣ አስራ ሁለት የክዋክብት አክሊል በራሷ ላይ ያላት" ብሎ የመሰከረላት የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችባት ቀን ናት፡፡ የእርስዋም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን ሲገለጽ የነበረ መሆኑን ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ያስረዳናል፡፡
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግንቦት አንድ ቀን (የግንቦት ልደታ) የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ‹‹የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት›› ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡ ጠቢቡ ንጉስ ሰሎሞን በመኃልይ 4÷8 "ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ፡ ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፡፡" ብሎ እንደተናገረ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት መሰረት የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡
ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት 1 ቀን በ15 ዓ.ዓ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለእመቤታችን ልደት "ማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ/ ማርያም ግን ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች፡፡ በማለት እርሷ በደፈረሰው ዓለም በንጽሕና፣ በቅድስናና በድንግልና ስታበራ እንደነበርና ኋላም የዓለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መውለዷን አመስጥሮ ተናግሯል።
ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ የተባለው የነገረ ማርያም ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ሰሎሞን እመቤታችን በሊባኖስ እንደምትወለድ አስቀድሞ ሰሎሞን ስለእመቤታችን የተናገረውን ቃል መፈጸሙን ሲያመሰጠር "የአናብስት ልጅ አልኩሽ፡፡ ሙሽራዪት ሆይ ከሊባኖስ ተራራ ነዪ፤ ከአንበሶች ጒድጓድ ወጥተሽ ነዪ፤ ከምርጥ ነገድነት የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ዜና እጅግ ግሩም ነው፡፡" ይላል፡፡ እመቤታችንም በሊባኖስ ተራራ እንድትወለድ ምክንያት የሆነው በማሕፀን ሳለች የአርሳባንን ልጅ ዓይን በማብራቷና ሳሚናስ የሚባለውን የጦሊቅን ልጅ ከሞት በማስነሳቷ አይሁድ በቅናት ተነሳስተውባቸው ስለነበር ሐናና ኢያቄም ወደ ሊባኖስ ተራራ እንዲሄዱ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ስለነገራቸው እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ ስለታላቅ መንፈሳዊ ተልዕኮ ሲባል ከሚያውቁት ቦታ መራቅን፣ ከለመዱት ቀዬ መሰደድን ከእመቤታችን የተረዱት ገዳማውያንም ዓለምን ንቀው ስሟን ስንቅ አድርገው ይመንናሉ። ገዳማቸውን ስንደግፍ ፣ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን።
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

14 hours ago
አድማስ ዩኒቨርሲቲ 18ኛውን ዓመታዊ የምርምር ጉባኤ አካሄደ!
#ethiopia አድማስ ዩኒቨርሲቲ "በምስራቅ አፍሪካ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዋና ዋና ተልዕኮዎች ስኬቶች ተጋጣሚዎች እና እድሎች፡ የጥራት ትምህርት አሰጣጥ፣ ተዛማጅ ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት" በሚል መሪ ቃል 18ኛውን ዓመታዊ የምርምር ጉባኤውን በዛሬው እለት አካሂዷል።
በጉባኤው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሞላ ፀጋይ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ጥራት ያለው ከፍተኛ ትምህርት፣ ችግር ፈቺ ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ለአንድ ሀገር እድገትና ለስርዓተ ትምህርት መሻሻል ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አድማስ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ድረስ 17 ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤዎችን፣ 7 የተማሪዎች የምርምር ሲምፖዚየሞችን እና በርካታ አካዳሚያዊ ውይይቶችን ማዘጋጀቱን አብራርተዋል።
በተጨማሪም አዳዲስ የምርምር ውጤቶችን ለማውጣትና ለማህበረሰቡ ለማድረስ ዩኒቨርሲቲው በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር በጀት መድቦ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በጉባኤው ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ተመራማሪዎች፣ አወያዮች እና ጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢዎች ተገኝተዋል::
ይህ ጉባኤ በተሳታፊዎች መካከል የእውቀትና ልምድ ልውውጥ የሚደረግበትና ውጤታማ ውይይት የሚካሄድበት መድረክ እንደሚሆን ታምኖበታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen

ኤርትራ በኢትዮጵያ ጋር በተፈጠረው ውጥረት ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀች
ሁለቱ ጎረቤት አገራት በውጥረት መባባስና ሰፊ ግጭት ሊነሳ ይችላል በሚል ስጋት መካከል፣ ጦርነቱን የጀመረው ማን እንደሆነ እርስ በርሳቸው እየከሰሱ ነው።
ኤርትራ በትግራይ ክልል አካባቢ ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ፣ ኢትዮጵያ “የጦርነት አዋጅ አውጃለች” በማለት የገለጸችውን እርምጃ ተከትሎ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) “አጸፋዊ የመከላከያ እርምጃዎችን” እንዲወስድ ጠይቃለች።
የኤርትራ ጥያቄ የቀረበው፣ አዲስ አበባ ለተመድ የደኅንነት ምክር ቤት በላከችው ደብዳቤ፣ አስመራን “ሙሉ ወረራ” ፈጽማለች በማለት ከከሰሰች ከአንድ ቀን በኋላ ነው። ኢትዮጵያ በደብዳቤዋ፣ የኤርትራ ወታደሮች እስከ 60 ኪሎ ሜትር (37 ማይል) ድረስ በትግራይ ክልል ውስጥ ገብተው መገኘታቸውን ገልጻለች።
ኤርትራ ምን አለች?
በቅዳሜው ዕለት ለተመድ የደኅንነት ምክር ቤት በላኩት የተለየ ደብዳቤ፣ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ፣ የኤርትራ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቷል የሚለው ክስ፣ ኢትዮጵያ የጥቃት ጦርነት ለመጀመር ምክንያት ለመፍጠር የምታደርገው ሙከራ ነው ብለዋል።
ኤርትራም ተመድ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቃለች፤ በተለይም የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር ምዕራፍ ሰባትን በመጥቀስ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቃለች። ይህ የቻርተሩ ምዕራፍ በዓለም አቀፍ ሰላምና ደኅንነት ላይ ስጋት ሲፈጠር ከኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ እስከ ወታደራዊ እርምጃ የሚደርሱ ውሳኔዎችን እንዲወስድ ለደኅንነት ምክር ቤቱ ሥልጣን ይሰጣል።
የሁለቱ አገራት ክስና የግጭቱ መነሻ
ሁለቱ ጎረቤት አገራት በትግራይ ክልል ዙሪያ የተፈጠረውን ጦርነት የጀመረው ማን እንደሆነ እርስ በርሳቸው እየከሰሱ ነው። ኢትዮጵያ ኤርትራ የታጣቂ ቡድኖችን እየደገፈች ነው ትላለች።
ባለፈው ወር ሰባት የታጣቂ ቡድኖችን ያቀፈ ጥምረት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መንግሥት ለመጣል በማለም፣ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ በሚገኙ የፌዴራል መንግሥቱ ጦር ኃይሎች ላይ ጥቃቶችን ፈጽሟል።
ከዚያ በኋላ የኤርትራ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ገብተዋል የሚሉ ሪፖርቶች ቀርበዋል። አዲስ አበባም አስመራ የትግራይ ሕዝባዊ ነፃነት ግንባርን (TPLF) እየደገፈች ነው በማለት ከሳለች።
የኢትዮጵያ ጦር በዚህ ሳምንት የTPLF ታጣቂዎችን ወደ ኋላ በመግፋት የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን መቀሌን መቆጣጠሩን ገልጿል። በተጨማሪም በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የኤርትራ ወታደሮች ላይ የድሮን ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታውቋል።
የኤርትራ የመጨረሻ ጥያቄ
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ በቅዳሜው ዕለት በላኩት ደብዳቤ፣
“ኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት የደኅንነት ምክር ቤት፣ ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ አውጃለች የተባለውን አሳፋሪ የጦርነት አዋጅ በጽኑ እንዲያወግዝና ተገቢውን የመከላከያ እርምጃ እንዲወስድ ትጠይቃለች” ብለዋል።
ማሳሰቢያ፦ ይህ ትርጉም በሰጠኸኝ የዜና ጽሑፍ ላይ የተመሠረተ ነው። በዜናው ውስጥ የቀረቡት የወረራ፣ የድንበር ጥሰትና የጦርነት ክሶች የሁለቱ አገራት አቋሞች ናቸው፤ በዚህ ትርጉም ብቻ የተረጋገጡ እውነታዎች እንደሆኑ መወሰድ የለባቸውም።
የዜናው ምንጭ፦ አልጀዚራ፣ ኤኤፍፒ እና ኤፒ
@Yenetube Fikerassefa

የመደመር መንግሥት ታሪክን በዘመናዊነት የማደስ ጥበብ
***********
የታላቅ ህዝብ ታሪካዊ ቅርስ እና ድል የዛሬዋ ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊ የብልፅግና ምዕራፍ የምታደርገው ጉዞ መሰረትና ህያው ምስክር ነው።
ጥንታዊ ቅርሶቻችንን በመጠበቅ፣ የታሪክ አደራችንን በዘመናዊ መልክ በማደስ እና ለትውልድ የሚሻገር አዲስ እሴት በመፍጠር ረገድ ባለፉት ዓመታት የተሰሩ ታላላቅ ስራዎች ሀገራዊ ፍቅራችንን እና የጥበብ ጥጋችንን በተግባር ያሳዩ ናቸው።
የሀገራችን የነጻነትና የድል ምልክት የሆነውን የጀግኖች ህዝቦችን ኩራት የዓድዋ ድል ክብር የሚገልፅ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በዘመናዊ የሙዚየም ንድፍና ቴክኖሎጂ ግብዓት ተገንብቶ ለአገልግሎት በቅቷል።
ይህም የቀደሙ አባቶቻችንን ገድል ለትውልድ ከማስተላለፉም በላይ፣ ከውጭ ሀገራት የተመለሱና የተሰበሰቡ ታሪካዊ ቅርሶችን በደህንነት አቃፎ የያዘ ታላቅ የመዘክር ማዕከል ለመሆን በቅቷል።
ከዚሁ ጎን ለጎን በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ እና በሸገር ማስዋብ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የመንግስትና የህዝብ ቅንጅት ያሳዩ በርካታ የቱሪዝምና የቅርስ እድሳት ስራዎች ተከናውነዋል።
በጎንደር የአፄ ፋሲል ቤተ-መንግስትና አካባቢው ጥንታዊ ውበቱ ሳይጎዳ ታድሶ ለጎብኚዎች ምቹ በሆነ መልኩ ተዘጋጅቷል፤ በባሌ የተፈጥሮና የባህል ሃብቶችን አጣምረው የያዙ ማዕከላት በዘመናዊ መልክ ተገንብተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ በተለየም በአርባምንጭ ተንሳፋፊ ሪዞርት በመስራት አርባ ምንጭ የ40 ምንጮች መገኛ መሆኗን ያስመሰከረ ሆኗል።
እንዲሁም በአፋርና በሶማሌ ክልሎች የነበሩ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ መስህቦች የገበታ ለትውልድ አካል በመሆን በዘመናዊ ዲዛይን ታድሰውና አዲስ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ተደርጎላቸው ለክልሎቹ አዲስ የኢኮኖሚና የቱሪዝም ህይወት ዘርተዋል።
በተጨማሪም በመዲናችን አዲስ አበባ የተሰሩት የሸገር ማስዋብና፣ የአንድነት ፓርክ፣ የሳይንስ ሙዚየምና የወንዞች ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች መዲናዋን የዘመናዊነትና የተፈጥሮ ውበት መገናኛ አድርገዋታል።
እነዚህ ስራዎች በሙሉ ኢትዮጵያ የታላቅ ታሪክ ባለቤት ብቻ ሳትሆን፣ ያንን ታሪክና ቅርስ በዘመናዊ እይታ አድሳና አስውባ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡ ህያው ማረጋገጫዎች ናቸው።
በልዩ እሸቱ
#የመደመርመንግሥት #ethiopia #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ

Sponsored by
Surafel
15 hours ago
የካይሮ የሴራ እንቅስቃሴ እና የኢትዮጵያ የማይናወጥ የከፍታ ጉዞ
******************
የታሪክ የሉዓላዊነትና የነፃነት ተምሳሌት የሆነችው ኢትዮጵያ ከውስጥና ከውጭ የሚሰነዘሩባትን ሁለገብ ተፅእኖዎችና መሰናክሎች አልፋ የብልፅግና ጉዞዋን በፅናት እያስቀጠለች ትገኛለች።
ሀገራችን ያላትን ሰፊ ለም መሬት፣ የተትረፈረፈ የውሃና የማዕድን ሀብት እንዲሁም ታላቅ የሰው ሀይል ከህዝቧ የኑሮ ደረጃ ጋር ለማጣጣምና ድህነትን ታሪክ ለማድረግ በፈጣን የልማት ሂደት ላይ ትገኛለች።
ይሁን እንጂ የኢትዮጵያን ሰላምና እድገት ለማጨናገፍ ከታሪካዊ ጠላቶችና ከእነሱ ጋር ከተሰለፉ የውስጥ ከዳተኞች የሚሰነዘሩት ትንኮሳዎችና የጥፋት እንቅስቃሴዎች ዛሬም የሀገራችንን ሉአላዊነት ለመሸርሸር ያለሙ መሆናቸው ይታወቃል።
የዓባይ ወንዝን ፍሰትና ፍትሃዊ ጥቅም በተመለከተ የካይሮ መንግስት የሚከተለው ፖሊሲ የኢትዮጵያን የመልማት መብት ለመገደብ ያለመና በቅኝ ግዛት ዘመን የቆዩ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ውሎች በማንሳት ላይ የተመሰረተ ነው።
እነዚህ ጠላቶች ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ከመጀመሪያው አንስቶ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ መስኮች ለማደናቀፍ የውስጥ ተላላኪዎችን በመሳሪያነት በመጠቀም ቀጠናው ሰላም እንዳያገኝ ሲጥሩ ቆይተዋል።
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ የናይል ወንዝን በፍትሃዊ፣ ምክንያታዊና በታችኞቹ የተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉዳት በማያደርስ መርኋ መሰረት ውሃውን ለልማቷ እያዋለች ትገኛለች።
ታላቁ የህዳሴ ግድብ የደለል ክምችትን በመቀነስ የጎርፍ አደጋን በመከላከልና ንፁህ የኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት ሀገራት በማቅረብ የምስራቅ አፍሪካን የኃይል እጥረት የሚቀርፍና እውነተኛ ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን የሚያረጋግጥ ዘመናዊ መሰረተ ልማት መሆኑ በተግባር ተረጋገጧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲሱ የመደመር መንግስት ምስረታ ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር፤ እንደ ሀገር ቀድሞ አለመዘጋጀት የሚያስከፍለውን ዋጋ ለመገንዘብ የጣሊያን ዳግም ወረራን መለስ ብሎ መቃኘት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው፤ ኢትዮጵያ ያሰበችውን ታሳካለች ጠላቶቿንም አስወግዳ ጉዞዋን በፍጥነት ትቀጥላለች ሲሉ አስምረውበታል።
አክለውም ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝ የምትጠቀመው የሌሎችን ድርሻ ለመጋፋት ሳይሆን ህዝቧን ከጨለማ ለማውጣትና ከጎረቤቶቿ ጋር በጋራ ለማደግ መሆኑን ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በጠንካራና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተገነባ መከላከያ ሰራዊት በፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት በዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምና እንደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የከተሞች ኮሪደር ልማትና በግብርና እራስን የመቻል እንቅስቃሴ ባሉ ታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች የቀጠናውን መሪነቷን አጠናክራለች።
ከአፍሪካ ሁለተኛ ባለ ብዙ ቁጥር ህዝብ ያላት ሀገር እንደመሆኗ በቀጠናው ዘላቂ ሰላምና የጋራ ብልፅግና ለማረጋገጥ በታሪካዊ ስህተት ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ በሰጥቶ መቀበል መርህ እውን ለማድረግ ብሄራዊ አጀንዳ አድርጋ እየሰራች ሲሆን ጥያቄውም በአለም አቀፍ ደረጃ ድጋፍ በማግኘት ላይ ይገኛል።
እንደ ዓድዋ ድል ሁሉ የባህር በር ማግኘት ለዛሬው ትውልድ የህልውናና የሁለተኛው ትውልድ የመልማት የመበልፀግና የሀገር ፍቅር ንቅናቄ ጉዳይ መሆኑ የውጭ ጫናዎችና ጂኦፖለቲካዊ ተቃውሞዎች የህዝቡን አንድነት የበለጠ የሚያጠናክሩት በመሆናቸው ኢትዮጵያውያን በጋራ በመቆም ለቀጣዩ ትውልድ የበለፀገች ሀገር የማስረከብ አርበኝነትን በተግባር መወጣት ይገባናል።
በብሌን ደምበሎ
#ethiopia #የመደመርመንግሥት #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ

17 hours ago
ከማንቸስተር ዩናይትድ በኩል ምን አይነት ደካማ የመከላከል ስራ ነው የታየው? ትኩረትህ ሙሉ በሙሉ ኳሷ ላይ መሆን ሲገባው፣ እንዴት ተቀናቃኝህን ብቻ ትመለከታለህ? በአንድ ተጫዋች በልጠህ 11 ለ 10 እየተጫወትክ እንዲህ አይነት ርካሽ ግብ ማስተናገድ እጅግ የሚያሳፍር እና የሚያስቆጭ ነው! በእውነትበጣም አሰቃቂ የመከላከል ስህተት ነው!
ጨዋታው አልቋል፡ ማን.ዩናይትድ 1 -1 ቶተንሃም
እናንተስ ጨዋታውን እንዴት አያችሁት?
ጨዋታው አልቋል፡ ማን.ዩናይትድ 1 -1 ቶተንሃም
እናንተስ ጨዋታውን እንዴት አያችሁት?
19 hours ago
በሊዝበን ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንድ እስከ አምስት ተከታትለው በመግባት አሸነፉ
**********
በፖርቹጋል በተካሄደው የሊዝበን ማራቶን የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ያሉትን ደረጃዎች ይዘው በመግባት አሸንፈዋል።
አትሌት መስከረም ማሞ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ከ04 በመጨረስ ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ፤ ጠጅቱ ስዩም ደግሞ በ7 ማይክሮ ሰከንድ ዘግይታ ሁለተኛ ሆናለች።
በሻንኬ ኢሙሼ፣ ስንታየሁ ጥላሁን እና አበበች አፈወርቅ ከሦስት እስከ አምስት ያሉትን ደረጃዎች በመያዝ በሊዝበን ጎዳናዎች የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ አድርገውል።
በወንዶች ዘርፍ ዳሳለኝ ይሌ አራተኛ ሲወጣ ፣ አብዲ አሊ እና ደምሱ ገመዳ ሰባተኛ እና ስምንተኛ ደረጃን አግኝተዋል።
በአዲስ የሺዋስ
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

20 hours ago
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊትና የትግራይ የሰላም ኃይል የዓዲግራት ከተማንና እንዳስላሴ ሽረን መቆጣጠራቸውን ታውቋል።
የአካባቢው ነዋሪዎችን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ሁለቱም ከተሞች ነጻ የወጡት በትላንትናው ዕለት ነው።
ዓዲግራት ከተማን አቋርጠው ዕዳጋ ሐሙስ ደርሰው የነበሩ የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ሐይሎች ተገፈተው ወደ ድንበር ከተማ ማፈግፈጋጠቸውንም ዜናው አክሏል።
ዜና ወኪሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናትን አግኝቶ ለማናገር ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለትም ገልጿል።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያለፈለጉ አንድ የትግራይ ሰላም ኃይል ባለስልጣን በበኩላቸው በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የምትገኘው የሐውዜን ከተማና በትግራይ ማዕከላዊ ዞን እምባስነይቲ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችው ነበለት ከተማ በፌደራል የመከላከያ ሰራዊትና በትግራይ የሰላም ኃይሎች ቁጥጥር ሥር መሆናቸውን ገልጸዋል።
ምንጭ :- ዶቼ ቬለ ዜና ከነጻ ምንጭ ማረጋገጥ አልቻልኩም ብሏል

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዘለንስኪ የትራምፕን ውሳኔ ‹‹ለአጋሮቻችን የማይጠበቅና ደካማ ነው›› አሉ፡፡ ፕሬዝደንት ትራምፕ በትላንትናው እለት ከሩሲያው አቻቸው ጋር በስልክ ከተወያዩ በኋላ አንድ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ስምምነትም ሩሲያ በሚሊዮን ቶን የሚቆጠር ነዳጅ ለአሜሪካና ለተቀረው አለም እንድታቀርብ የሚያስችል ነው፡፡ በስምምነቱ መሰረት ሩሲያ በፍጥነት 300,000 ቶን ነዳጅ ማቅረብ የሚጠበቅባት ሲሆን እስከ ኖቬምበር 1 ደግሞ ተጨማሪ 500,000 ቶን ለማቅረብ ተስማምታለች፡፡
ከዚያም በአጭር ጊዜያት ውስጥ ሌላ አንድ ሚሊዮን ቶንና ቀጥሎም 3 ሚሊዮን ቶን ነዳጅ እንደምታቀርብ ስምምነቱ ያሳያል፡፡ ይህንን ስምምነት በተመለከተ ፕሬዝደንት ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ ‹‹የነዳጅ ዋጋ ከእንግዲህ እየወረደ ይመጣል›› በማለት የፃፉ ሲሆን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ደግሞ ‹‹እውነት ለመናገር ፑቲንን አመሰግነዋለሁ›› ብለዋል፡፡ ይህ ውሳኔ የዩክሬይኑን ፕሬዝደንት ዘለንስኪን እጅግ አስቆጥቷል፡፡ ውሳኔው ይፋ ከሆነ ከደቂቃዎች በኋላ በማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ ‹‹ከአጋሮቻችን የማይጠበቅ ደካማ ውሳኔ ነው›› በማለት ፅፈዋል፡፡
እርምጃውንም ‹‹ለፑቲን የቀረበ ስጦታ ነው›› በማለት አጣጥለውታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ሩሲያ በዩክሬይን ላይ በፈፀመችው ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ይህንን በተመለከተ ዘለንስኪ በማህበራዊ ሚዲያቸው ‹‹ፑቲን ትላንት ለፈፀመው ስምምነት ዩክሬይንን በመደብደብ አመሰግናለሁ ብሏል›› በማለት ገልፀዋል፡፡

21 hours ago
የኢትዮጵያ የውጭ ፖሊሲ የሽግግር ምዕራፍ
**************
የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ታሪክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ነጻነቷንና ሉዓላዊነቷን ከማስከበር ባለፈ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ውስጥ ቀደምትና ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቅ ቢሆንም፣ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች የሀገራችን የውጭ ፖሊሲ ከውስጣዊ ደኅንነትና ሉዓላዊነትን ከማስከበር ባሻገር ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን በሙሉ አቅም ለመጠቀም ውስንነቶች ነበሩበት።
በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን የውጭ ፖሊሲው በዋናነት የምዕራባውያንን ድጋፍ በማጠናከርና ሉዓላዊነትን በማስከበር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ በደርግ ዘመን ደግሞ የሶቭየት ኅብረትን የርዕዮተ-ዓለም ካምፕ በመከተል በደኅንነትና የወታደራዊ ትስስር ላይ ያተኮረ አካሄድን ይከተል ነበር።
ከ1983 ዓ.ም በኋላ የወጣው ፖሊሲ ደግሞ ድህነትን መዋጋትን ዋና መሠረት በማድረግ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲንና የጎረቤቶች ሰላምን ማዕከል ያደረገ ቢሆንም፣ የዓለም አቀፍ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች መለወጥ፣ የጂኦ-ፖለቲካ ፉክክር መጨመር እና የሀገር ውስጥና የአካባቢው ለውጦች ፖሊሲውን ማሻሻልና ማሳደግ አስፈላጊ አድርገውታል።
በቅርብ ዓመታት ደግሞ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በቀጥታ ከዓለም አቀፍ ተቀባይነት ፍለጋ በመውጣት፣ በክልላዊና ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ንቁ አጀንዳ ሰጭነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ዲፕሎማሲያዊ ሚና ወደ መጫወት ተሸጋግሯል።
ዓለም ከአንድ ወገን የበላይነት ወደ ባለብዙ ወገን መሸጋገሯ ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አቅጣጫዎቿን እንድታሰፋና የፖሊሲ አማራጮቿን እንድታበዛ ያስገደዳት ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ፍላጎትን ለማሟላት፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግና የኃይል ሽያጭን ጨምሮ ክልላዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር አዲስ አቀራረብ ተከትላለች።
በዚህም መሠረት ቀደም ሲል ከነበራት በተወሰኑ ምዕራባውያን ወይም ታላላቅ ኃይሎች ላይ የተመሠረተ ግንኙነት በመውጣት፣ ከሁሉም ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ተግባራዊ የዲፕሎማሲ አቅጣጫ መከተል ጀምራለች።
የዚህ የውጭ ፖሊሲ ትልቁ የስኬት ማሳያ ሀገራችን የብሪክስ አባል መሆኗ ሲሆን፣ ይህም በዓለም አቀፍ የፋይናንስና የንግድ ሥርዓት ውስጥ ድምጿ እንዲሰማ፣ ከአስደናቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለቤቶች እንደ ቻይና፣ ህንድ፣ ብራዚልና ሩሲያ ጋር ያላትን ትስስር እንድታጠናክርና አማራጭ የልማት ፋይናንስ ምንጮችን እንድታገኝ በር ከፍቷል።
በሌላ በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅና ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀንድ የንጹሕ ኃይል አቅርቦት ማዕከል ያደረጋት ሲሆን፣ ለሱዳን፣ ጂቡቲ እና ኬንያ እየቀረበ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል የቀጣናውን የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከሩ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሀገራት ዘንድ ያላትን ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት አሳድጎታል።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የተመጣጠነና የብዙ ወገን ዲፕሎማሲ በመከተል በታላላቅ ኃይሎች ፉክክር ውስጥ ገለልተኝነቷንና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ እየሠራች ትገኛለች።
የብሪክስ አባልነት፣ የኢኮኖሚና የኃይል ዲፕሎማሲ እንዲሁም በቀጣናው የሚደረጉ የሰላም ማስከበር እንቅስቃሴዎችም ብሔራዊ ጥቅሟን ከቀጣናዊ ትስስር እና ከዓለም አቀፍ ትብብር ጋር አጣጥማ በመጓዝ የጀመረችውን የአጀንዳ ሰጭነት ሚና አጠናክራ እንድትቀጥል የሚያስችሏት ናቸው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopianforeignpolicy #brics #gerd #የመደመርመንግሥት

22 hours ago
የእስራኤል ድሮን በኤርትራ‼️
ዘ- ጆርዳን ታየምስ የተባለው የደህንነት ሚዲያ መነሻውን ከእስራኤል ያደረገ አንድ የስለላ ድሮን በኤርትርራ ላይ የብዙ ሰአት ቅኝት ሲያደርግ ማምሸቱን ዘግቧል።
የሰሜኑ ጦርነት ወደ ኤርትራ መሬት እየተጠጋ ነው ያለው ይህ ጋዜጣ፣ አዲስ አበባ እራስን ለመከላከል በምታደረርገው ውጊያ ላይ እስራኤል አስፈላጊ የሆኑ ወታደራዊ የሳተላይት መረጃዎችን በመስጠት ውጊያው የቀይባህር መስመርን ሳያውክ እንዲጠናቀቅ እስራኤል የዶናልድ ትራፕን አመራር እያሳመነች ነው ብሏል።
እስራኤል በአፍሪካ ቀንድ ላይ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ሲቃወምና ሲያወግዝ የነበረው የ35 አመቱ የአስመራው አገዛዝ ላይ ለውጥ እንዲመጣ ከፍተኛ ስራን እየሰራች መሆኑን የጠቀሰው ይህ ጋዜጣ፣ ግብፅ ኤርትራን በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ የረጅም ግዜ ውጊያ እንዲፈጠር አቅዳ እየሰራች ቢሆንም እስራኤል የጦርነቱን ሁኔታ አይታ የሲና በረሀን ለመቆጣጠር አዲስ ውጊያ መክፈት አስፈላጊነቱን እያጤነችበት ነው ሲል ነው የዘገበው።
እስራኤል ዜጎቿ ወደግብፅ መሬት እንዳይሄድ ያሳሰበችው ትናት ነው።
ሱሌማን አብደላ
Seledadotio

ለአስታጥቃቸው ይሁን ስጦታ ሊበረከት ነው
ጥቅምት 7 2019 ዓ.ም የምስጋና መርሀ- ግብር የሚደረግለት የቴአትር ባለሙያ አስታጥቃቸው ይሁን ታሪኩ በዶክመንተሪ ሊሠራ ነው።
ቦሌ ፍላሚንጎ በሚገኘው የህፃናትና ወጣቶች የቴአትርና የሲኒማ ኮምፕሌክስ ከ10 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው በዚህ የምስጋና መርሀ ግብር ስለ ከያኒው ምስክርነት የሚሰጡ ባለሙያዎች የሚታደሙ ሲሆን ልዩ ልዩ የጥበብ ዝግጅቶችም ይኖራሉ ተብሏል።
ተመስጋኙ የኪነ ጥበብ ባለሙያ አስታጥቃቸው ይሁን እና ቤተሰቡ የምስጋና መርሀ ግብሩን እንዲያዘጋጅ ይሁንታቸውን በህጋዊ መንገድ ለተወዳጅ ሚድያ የሰጡ ሲሆን በምስጋና መርሀ ግብሩ እለት ለሚታየው ዶክመንተሪም ቃለ ምልልስና መረጃ ሰጥተዋል።
የአስታጥቃቸው ልጆች ወይዘሮ መልካም አስታጥቃቸው እና የኤሌክትሪክ መሀንዲስ ዮርዳኖስ አስታጥቃቸው እንዳሉት አባታቸው እዩኝ እዩኝ የማይል ሥራውን ግን አድምቶ የሚሠራ ለብዙዎች ተምሳሌት የሆነ ሰው መሆኑን ተናግረዋል።
በቀረፃ ሥራው ወቅት ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን 10 የሚጠጉ የአስታጥቃቸው ኦሪጅናል ስክሪፕቶችን የተመለከተ ሲሆን ወደፊትም ሥራዎቹ መታተም እንዳለባቸው ምክረ- ሀሣብ ቀርቧል።
በአስታጥቃቸው እጅ ከሚገኙ የቲያትር ስክሪፕቶች መካከል ተናጋሪው ዲዳ የተሰኘው የሬድዮ ድራማ የሚገኝበት ሲሆን የፃፈበት ጊዜም 1975 እንደሆነ ታውቋል።ሌላው በሚያዝያ 30 1989 የዛሬ 30 አመት የተፃፈው ባለ 11 ገፅ የሬድዮ ድራማ ባለሱሪው የሚል ርዕስ የሰጠው ነው።ሳልሣዊው ባልንጀራ ባለ 3 ገቢር ተውኔት ሲሆን በ1975 ለእይታ የበቃ ነው።ሌሎች ስክሪፕቶቹም ፍፁም ቅጣት፣ ቅሌት በድንኳን፣ፈታኙ አስክሬን 1985(የሬድዮ ድራማ)፣ቀባሪ ያጣ በድን 1974ባለአንድ ገቢር ድራማ፣ በ1983 የተፃፈው ድርሳነ ፀጋ፣ አንቺን አሉ እናትነሽ በእጁ ከሚገኙ ድርሰቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
በኢትዮጵያ የቴአትርና የጥበብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አሻራ ያሳረፈው ሁለገብ ከያኒ አስታጥቃቸው ይሁንን ለማመስገንና የ69ኛ ዓመት ልደቱን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ከተወዳጅ ሚድያ ጋር በባህር ማዶና በአገር ቤት የሚኖሩ ወዳጆቹ ከፍተኛ ትብብር ያሳዩ ሲሆን በአሁኑሰዓትም መርሀ ግብሩን እውን ለማድረግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ታውቋል።
ከያኒ አስታጥቃቸው ይሁን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1974 ዓ.ም በቴአትር ጥበብ የተመረቀ ሲሆን፣ ይህም ዩኒቨርሲቲው በዘርፉ ማስተማር ከጀመረበት ሁለተኛው ባች (ምሩቃን) ያደርገዋል።
ከተመረቀበት ዓመት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በሥነ-ፅሁፍና ቋንቋ ኤክስፐርትነት የተቀጠረው ከያኒው፣ ላለፉት 37 ዓመታት በጥበቡ ዓለም ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ሀገሩን ህዝቡን በታማኝነት አገልግሏል።
አስታጥቃቸው አጠቃላይ ከ60 በላይ የተውኔት ፅሁፎችን ያበረከተ ሲሆን፣ በርካታ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ድራማዎችን፣ መጣጥፎችን፣ አጫጭር ልቦለዶችንና ግጥሞችን ፅፏል።
አስታጥቃቸው ይሁን ፋንታ ከ1990-1995 ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤትን በዋናሥራ አስኪያጅነት ያገለገለ ሲሆን በሥነ ምግባሩ እና በትህትናው በብዙዎች የሚወደድ የጥበብ ሰው እንደሆነ ይታወቃል።
በዚህ መርሀ ግብር ላይ ታላላቆች የቴአትር ፈርጦች አያልነህ ሙላት፣ ጌትነት እንየው፣ ተስፋዬ ሲማ ፣ ተፈሪ አለሙ እና ሌሎችም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እንደሚገኙ ተነግሯል ።
በምስጋና መርሀ ግብሩ ላይ ለከያኒው ለየት ያለ ስጦታ እንደሚበረከትለት ታውቋል።

8 ፍሬያማ ዓመታት፤ ትሩፋት ላለው ሕይወት!
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ በደንበኞቻችን እና በኩባንያችን ቤተሰብ አጠራር "ፍርዬ" ባለፉት ስምንት ዓመታት ባሳዩት ወደር የለሽ ጽናት፣ ብስለትና ቁርጠኛ አመራር ተቋማችን ዘመን ተሻጋሪና አመርቂ ታሪካዊ ስኬቶችን እንዲያስመዘግብ አስችለዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ከስምንት ዓመታት በፊት አንጋፋውን ኩባንያችንን ሲረከቡ፣ ተቋሙ ሰፊ መሠረተ ልማትና እምቅ አቅም ቢኖረውም ወደ ተጨባጭ ውጤት ያልተቀየረ፣ “ያንቀላፋ ግዙፍ” (The Sleeping Giant) ተብሎ የሚታወቅ፣ በከፍተኛ የዕዳ ጫና የተተበተበ፣ የታሪፍ ውድነት ቅሬታ የነበረበት እንዲሁም የአገልግሎት አማራጮቹ በ3ጂ እና በጥቂት አካባቢዎች ብቻ በ4ጂ የሞባይል ዳታ የተገደቡበት እንደነበር ይታወሳል።
ሆኖም ‘ኢትዮ ቴሌኮምን በመቀየር የሀገራችንን ዕድገት ማፋጠን እንችላለን’ የሚል የጋራ ራዕይ በማስረጽ፣ ሰውን ያማከለ (Human Centric) እሴትን በማስፈንና ልህቀትን (Excellence) መርህ በማድረግ መላውን ሠራተኛ በአንድ ዓላማ አሰልፈዋል። የተቀመጡትን ስትራቴጂያዊ ግቦች መላው የተቋማችን ቤተሰብ በከፍተኛ ዲሲፕሊንና ትጋት ወደ ተግባር በመቀየሩም፣ ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ለሀገር ኩራት የሆነ ተቋም እንደገና መገንባት ተችሏል።
በዋና ሥራ አስፈጻሚያችን የላቀ አመራር መሠረታዊውን የቴሌኮም ግንኙነት (Connectivity) አገልግሎት ለሁሉም ዜጎች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ በተከናወኑ መጠነ-ሰፊ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያና ማሻሻያ ሥራዎች፣ የደንበኞቻችን ቁጥር ከ37.9 ሚሊዮን ወደ 90.1 ሚሊዮን አድጓል፤ 99.8 በመቶ ሕዝባችን የአውታረ መረብ (Network) ሽፋን ሲያገኝ ደንበኛ የመሸከም አቅማችን 115.1 ሚሊዮን ደርሷል። የ4ጂ የሕዝብ ሽፋናችን ከ82.2 በመቶ በላይ የደረሰ ሲሆን፣ ሀገራችን ዘመናዊውን የ5ጂ ቴክኖሎጂ ቀድመው ተግባራዊ ካደረጉ ጥቂት የአፍሪካ ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ በማድረግ ዛሬ አገልግሎቱ በ33 ከተሞች ተደራሽ እንዲሆን ተደርጓል።
በፋይናንስ አስተዳደር ረገድ በተወሰዱ ቁልፍ እርምጃዎች የኩባንያችን ዓመታዊ ገቢ ከ37.16 ቢሊዮን ብር ወደ 215.8 ቢሊዮን ብር፣ ከወለድና ከታክስ በፊት ያለው ትርፍ (EBITDA) ከ14.9 ቢሊዮን ብር ወደ 92.99 ቢሊዮን ብር አድጓል። በተጨማሪም በአቅራቢዎች የፋይናንስ ድጋፍ (Vendor Financing) ለተገነቡ መሠረተ ልማቶች የተወሰደው 1.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብድር ሙሉ በሙሉ ተከፍሎ ተጠናቋል።
በዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ሃሳብ አመንጪነት የሀገራችን ፈር ቀዳጅ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት የሆነውን “ቴሌብር”ን እውን በማድረግ፣ የክፍያ ሥርዓቱን ከማዘመን ባለፈ ሁሉን አቀፍ የፋይናንስ ተደራሽነትን ከማረጋገጥ ባሻገር አጠቃላይ የዲጂታል ሥነምህዳሩን ለማነቃቃት ተችሏል። ያለማስያዣ የሚሰጡ የብድር አገልግሎቶችን፣ የቁጠባ ባህልንና አጠቃላይ የዲጂታል ግብይትን ወደ ማኅበረሰቡ በማስረጽ፣ ቴሌብር ዛሬ ከ60 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ምርጫ በመሆን ከ9.13 ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት ማስተናገድ ችሏል።
ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ የተደረጉት ዘመኑን የዋጁ ሦስት ስትራቴጂዎች ኩባንያችንን ከመሠረታዊ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢነት ወደ የተቀናጀ የዲጂታል መፍትሔዎች መሪነት አሸጋግረውታል። የዳታ ማዕከልና የቴሌክላውድ አገልግሎቶች፣ ዘኔክሰስ፣ ቴሌስትሪም፣ ዘመን ገበያ እንዲሁም የፋይበር መስመር ዝርጋታና የሆራይዘን ፋይበር ኢኒሼቲቮች በማከናወን የማኅበረሰቡን አኗኗር በማቅለል፣ የመንግሥት ተቋማትን አሠራር በማዘመንና የንግድ እንቅስቃሴን በማቀላጠፍ የሀገራችንን ዲጂታል ራዕይ ዕውን የማድረግ ሂደትን በግንባር ቀደምትነት መርተዋል።
በክብርት ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ አመራር ተነድፎ በመተግበር ላይ የሚገኘው “ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028” (Next Horizon: Digital and Beyond 2028) ስትራቴጂ የሀገራችንን የልማት አቅጣጫና የዘርፉን የወደፊት ዕድሎች ያገናዘበ ነው።
ለተቋማችን ታላቅ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን መሳካት ጉልህ አሻራ ያሳረፉት፣ በኢትዮ ቴሌኮም ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ዋና ሥራ አስፈጻሚና ለመላው የሀገራችን ሴቶች የጥንካሬ ተምሳሌት የሆኑት ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የተሰማንን ልባዊ ደስታ እየገለጽን፣ በቀጣዩ የሥራ ዘመናቸው የላቀ ውጤትና ስኬት እንዲጎናጸፉ ከልብ እንመኛለን።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ በተቋማችን ውስጥ ባሳዩን ፍቅር፣ የማይናወጥ ጥንካሬና የቁርጠኝነት ተምሳሌትነት ምንጊዜም በልባችን በከፍተኛ አክብሮትና ፍቅር የሚኖሩ ሲሆን፤ መላው የተቋማችን ቤተሰብ እርሳቸው የጣሉብንን አደራ በጽናት ይዞ ይቀጥላል።
በዚህም የ'ቀጣዩ አድማስ' ስትራቴጂን ከዳር በማድረስ፣ የሚገነቡ መሠረተ ልማቶችና የሚቀርቡ ዲጂታል መፍትሔዎች ለሕዝባችን ተጨባጭ ፋይዳ እንዲሰጡ በማድረግ የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ በማፋጠን ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ ሁሌም የሚኮሩብን ታታሪ ቤተሰብ ሆነን እንዘልቃለን።

24 hours ago
የእስራኤል ኃይሎች በየቀኑ ፍልስጤማውያንን መግደላቸውንና መጉዳታቸውን ቀጥለዋል ሲሉ ከ100 በላይ የመብት ቡድኖች አስታወቁ
በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረገ ከአንድ ዓመት በኋላ፣ ከ100 በላይ የሰብአዊ፣ የሰብአዊ መብቶች እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንደገለጹት፣ ይህ ስምምነት በወረቀት ላይ ብቻ የሚገኝ ነው ብለዋል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱ በስም ብቻ ነው ያለው፣ የእስራኤል ኃይሎች በየቀኑ ፍልስጤማውያንን መግደላቸውንና መጉዳታቸውን ቀጥለዋል፣ እንዲሁም በእርዳታ፣ በመሳሪያዎችና በግንባታ ቁሳቁሶች ላይ የተጣሉ ገደቦች ቤተሰቦች እንዳያገግሙ ይከለክላሉ”ሲሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት፣ የሕፃናት አድን ድርጅት፣ ኦክስፋም፣ ግሪንፒስ እና ሌሎች በርካታ ዓለም አቀፍ ቡድኖች ትራምፕ በጋዛ የሰላም ቦርድ ማዕቀፍ ውስጥ ግጭቶችን ለማስቆም ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ 1,400 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል። ከነ፣ኒህ ውስጥ ቢያንስ 327 ሕፃናት ናቸው።
በኤፍራታ ሚሊዮን
#ዳጉ_ጆርናል

ፑቲን ኢራን ጦርነቱ ለማቆም ምን እንደምትፈልግ ለትራምፕ ተናገሩ
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱን ለማስቆም የኢራንን ቅድመ ሁኔታዎች ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተላልፈዋል ሲሉ ክሪምሊን አስታወቀ
“ፑቲን ከኢራን ፕሬዝዳንት ጋር በመተባበር የግጭቱን አፈታት በተመለከተ የኢራን ወገን ለትራምፕ ያላቸውን አመለካከት አስተላልፈዋል” ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለሩሲያ ሚዲያዎች ገልፀዋል።
ትራምፕ አርብ ዕለት ከፑቲን ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል፣ ሩሲያ በሚቀጥሉት ወራት ከአንድ ሚሊዮን ቶን በላይ ናፍጣ ወደ ውጭ እንድትልክ ፈቅደዋል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ስምምነቱን የፈረሙት የአሜሪካ እና የእስራኤል ጦርነት በኢራን ላይ ባደረገው ጦርነት ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ በማሰብ ነው ብለዋል።
በስምኦን ደረጄ

1 day ago
ንስር ማይክሮፋይናንስ በበጀት ዓመቱ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ
ንስር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አክሲዮን ማኅበር በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከታክስ በፊት 522 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ይፋ አደረገ። ተቋሙ ከታክስ በኋላ ያስመዘገበው የተጣራ ትርፍም 384 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ደርሷል።
ተቋሙ 13ኛውን መደበኛ እና 5ኛውን አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ባካሄደበት ወቅት እንዳስታወቀው፤ የተጣራ ትርፉ ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ207 ነጥብ 6 በመቶ ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል። በዚህም ለአንድ ሺህ ብር የአክሲዮን ድርሻ 625 ብር የትርፍ ድርሻ ተመድቧል።
በበጀት ዓመቱ በርካታ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ዘርፍ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፤ የተቋሙ አጠቃላይ ሀብት ከ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወደ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሏል።
በተመሳሳይ የተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ 6 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር፣ የብድር መጠኑ ደግሞ 6 ነጥብ 69 ቢሊዮን ብር ደርሷል። የተቋሙ የተበላሹ ብድሮች ምጣኔ 2 ነጥብ 87 በመቶ ብቻ ሆኖ በብሔራዊ ባንክ ከተቀመጠው ገደብ በታች መገኘቱ ተጠቁሟል።
ንስር ማይክሮፋይናንስ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ሀብቱን ወደ 34 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ማውጣቱን ገልጿል።
በዚህም በ2019 ዓ.ም ብቻ 10 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት አጠቃላይ ቅርንጫፎቹን 30 ለማድረስ፣ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ የጀመረውን የዘመናዊ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ግንባታ ለማጠናከር እንዲሁም የዲጂታል አገልግሎቱን ይበልጥ ለማስፋፋት አቅዶ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።
በሰብል አበበ

#kue
በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ውጤት ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ሦስት ፓስፖርት መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
ፋይዳ መታወቂያ እና TIN No.
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
የትምህርት ማስረጃዎቹ ስካን ተደርገው በአንድ PDF ሶፍት ኮፒ መዘጋጀት አለባቸው። ስካን የተደረገ ጉርድ ፎቶ ሶፍት ኮፒ መያዝ አይዘንጉ።
@tikvahuniversity

#samitech
አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!! samcomptech
በጥራት፣ በብራንድ እና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።
ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለብዎትን ወሳኝ ነገሮች በደንብ እናስረዳለን።
ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።
⭐ በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!!
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነትና አድራሻ ለማየት👇
samcomptech sww2844
0928442662 / 0940141114
Telegram 👇
https://t.me/samcomptech

የጋሞ ብሔረሰብ ባህላዊ የፍትሕና የእርቅ እሴት የሆነውን ዱቡሻ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ሂደት ላይ መሆኑ ገለፀ ።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የጋሞ ብሔረሰብከሚታወቅባቸው እሴቶች መካከል ዱቡሻ ባህላዊ የፍትሕ፣ የእርቅና የሕዝብ መሰብሰቢያ እና መገለጫ አንዱ ነው።
የጋሞ ዞን ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ግባዬ ግልጮ ዱቡሻ ለትውልድ ለማስተላለፍ እና ወጣቶች እንዲያውቁት እና እንዲጠብቁት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ዱቡሻ በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት፣ ሕግና ደንብ ለማውጣት እንዲሁም የማኅበረሰቡን አንድነት ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀዋል ።
የዱቡሻ ስርዓትን በአለምአቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ እና በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ሂደት መጀመሩን ተናግረዋል ።
ግጭት እና አለመግባባቶች በሽምግልናና በእርቅ ሥርዓት እንዲፈቱ የሚያደርግ እንዲሁም መረጃ ያልተሟላባቸው ወይም በድብቅ የተፈጸሙ የወንጀል በማጣራትና በመሃላ ሥርዓት የሚመረመርበት ባህላዊ እሴት መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል ።
ዱቡሻ የጋሞ ብሔረሰብ ባህላዊ ዕውቀት ፣ የማኅበረሰብ አንድነትን የሚያንጸባርቅ እንዲሁም የጋሞ ሕዝብ ባህልና ትውፊት ሚገለጽበት መንገድ መሆኑ ተመላክቷል ።
በቃልኪዳን ኃይሉ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ሥራ ያሸንፍ ወይስ ጩኸት?
ጥበብ ያሸንፍ ወይስ የድምፅ ብዛት?
* የልጅ ተመስገን መለሰ አስገራሚ አቋምና ከሁላችንም የሚጠበቅ የማሰብ ለውጥ!
ሰላም ቤተሰቦቼ!
#ethiopia | ዛሬ በጣም ያስገረመኝን፣ እንድናስብበትና እንድንወያይበት የፈለግኩትን አንድ ጉዳይ ላጋራችሁ ወደድኩ።
የተመስገን ልጆች የባህል ቡድን መስራችና ባለቤት፣ በባህላዊ ውዝዋዜ ጥበብ ላይ ለረጅም ዓመታት የሠራው ወዳጄ ልጅ ተመስገን መለሰ በአደይ ዘመናዊ የጥበብ ሽልማት ውድድር ዕጩ ሆኖ አየሁት።
የሚገርመው ግን ይህን ያህል ሥራ የሠራ የጥበብ ባለሙያ በሕዝብ ድምፅ ብዙም ድጋፍ እንዳላገኘ ስመለከት ግራ ገባኝ። ስለዚህ ደወልኩለትና፣ “አንተ ይህን ያህል ሥራ ሠርተህ፣ ለሀገርህና ለባህልህ ይህን ያህል አስተዋጽኦ አበርክተህ እንዴት የድምፅ ብዛትህ አነሰ?” ብዬ ጠየቅሁት።
የሰጠኝ መልስ ግን ከጠበቅሁት በላይ አስገራሚ ነበር።
“እኔ የውድድር ሰው አይደለሁም፤ የሥራ ሰው ነኝ!” አለኝ።
ከዚያም ሲያብራራ፣ በሥራው እንጂ ሰዎችን ድምፅ እንዲሰጡት በመጠየቅ ሽልማት ማግኘት እንደማይፈልግ ነገረኝ። ቤተሰቡን፣ ወዳጆቹን፣ የሥራ አጋሮቹንና ያሠለጠናቸውን ወጣቶች ሁሉ ቮት እንዲሰጡት ጠይቆ ቢያሸንፍ፣ ሽልማቱን ያስገኘለት የሥራው ጥራት ነው ወይስ የድጋፍ ብዛት የሚለውን ማሰቡን ገለጸልኝ።
እንዲህም አለኝ፦
“በሀገሬ ውስጥ ለረጅም ዓመታት ሠርቻለሁ። ሥራዬ በራሱ ታይቶና ተገምግሞ ካሸነፈ ደስ ይለኛል። ነገር ግን የማውቃቸውን ሰዎች ቮት እንዲሰጡኝ ጠይቄ ሽልማት ማግኘት አልፈልግም። እኔ ሥራዬ እንዲያሸንፍ እፈልጋለሁ።”
ይህን ስሰማ በጥልቅ አሰብኩበት። እውነትም ይህ ለሁላችንም ትልቅ ትምህርት የያዘ ሐሳብ ነው።
ልጅ ተመስገን መለሰ ማን ነው?
ልጅ ተመስገን መለሰ ከልጅነቱ ጀምሮ በኢትዮጵያ ባህልና የኪነጥበብ ዘርፍ፣ በተለይም በባህላዊ ውዝዋዜ ላይ ሲሠራ የቆየ ባለሙያ ነው። የተመስገን ልጆች የባህል ቡድንን በመመሥረት የባህላችንን ውበት፣ ስፋትና ልዩነት ለሕዝብ ለማሳየት ሠርቷል።
በተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ መድረኮች ላይ በመቅረብ፣ የኢትዮጵያን ባህል ለዓለም ለማስተዋወቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። በሕንድ፣ በሱዳንና በናይጄሪያ ጨምሮ በተለያዩ አገራት ባቀረባቸው ትርዒቶች የኢትዮጵያን ባህል አስተዋውቋል።
በተጨማሪም፣ ለባህልና ለጥበብ ባደረገው አስተዋጽኦ እውቅናዎችን እንዳገኘ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ለሠራው ሥራ እውቅና እንደሰጠው ተገልጿል። የእሱና የቡድኑ ሥራ በትምህርት መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ መካተቱም የባህል ሥራው ከመድረክ ትርዒት ባሻገር ለትውልድ የሚተላለፍ እሴት እንዳለው የሚያሳይ ነው።
የምንማረው ምንድን ነው?
ወዳጆቼ፣ ይህ ጉዳይ ስለ አንድ ሰው ድምፅ ብዛት ብቻ አይደለም። በሀገራችን የሽልማት ሥርዓት፣ በጥበብ ዘርፍ የምንሰጠው እውቅናና የሥራን ዋጋ በምንመዝንበት መንገድ ላይ እንድናስብ የሚጋብዝ ነው።
በርካታ ተሰጥኦ ያላቸው ባለሙያዎች፣ አርቲስቶች፣ ደራሲያንና የባህል አስተዋጽኦ አበርካቾች ሊኖሩን ይችላሉ። ሆኖም በማስታወቂያ፣ በድምፅ ማሰባሰብና በማኅበራዊ ጫና የተካኑ ሰዎች ከሌሎች በላይ የሚታዩበት ሁኔታ ሲኖር፣ በእውነተኛ ሥራ የተገኘ ውጤት ወደ ጎን ሊተው ይችላል።
ይህ ማለት ሕዝባዊ ድምፅ የለውም ወይም የድጋፍ ዘመቻ ሁሉ ስህተት ነው ማለት አይደለም። ሕዝብ የሚወደውንና የሚያምንበትን ሰው መደገፉ ተፈጥሯዊ ነው። ግን ሽልማቶች የሚሰጡት ለሙያዊ ብቃት፣ ለፈጠራ፣ ለሥራ ጥራትና ለአስተዋጽኦ ከሆነ፣ እነዚህ መስፈርቶች በተገቢው መንገድ መመዘን አለባቸው።
ሽልማት የሚያሸንፈው የሰው ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ የሥራው ጥራትና የፈጠራው ዋጋም መሆን አለበት።
እንግዲህ ዛሬ ምን እናድርግ?
እኔ ልጅ ተመስገን መለሰን የጥበብ ሥራ ለማየትና ለመገምገም ወደ ውድድሩ ገጽ ገብቻለሁ። የእሱን ሥራ በማየትና በማመን ድምፅ ሰጥቻለሁ።
እናንተም የሥራውን ጥራት ለማየት ጊዜ ውሰዱ። በሙያው የምታምኑ ከሆነ፣ ሥራውን ካያችሁና ከወደዳችሁት፣ በአደይ ዘመናዊ የጥበብ ሽልማት ድረ ገጽ ላይ ገብታችሁ ድምፅ ስጡት።
🔗 የድምፅ መስጫ ሊንክ፦ https://www.adeycontempora...
ይህን ስል ሌሎች ዕጩዎችን ለማሳነስ ወይም ማንም ሰው በድምፅ እንዳያሸንፍ ለመከልከል አይደለም። የምፈልገው ሥራን በሥራው፣ ጥበብን በጥበቡ፣ ብቃትን በብቃቱ እንድንመዝን ነው።
የልጅ ተመስገን መለሰ አቋም የሚያስተምረን አንድ ነገር አለ፤ እውነተኛ የጥበብ ሰው የሚፈልገው የሰዎችን ጩኸት ብቻ ሳይሆን፣ ሥራው በትክክል ታይቶ እንዲመዘን ነው።
ዛሬ ለሀገራችን ባህልና ጥበብ የሚሠሩ ሰዎችን በሥራቸው እናክብር። በእውቀት፣ በብቃትና በእውነተኛ አስተዋጽኦ ላይ የተመሠረተ የእውቅና ባህል እንገንባ።
ሥራ ያሸንፍ! ጥበብ ያሸንፍ! እውነት ያሸንፍ!
እናንተስ ቤተሰቦቼ፣ ስለዚህ ጉዳይ ምን ታስባላችሁ? ሽልማቶች በሕዝብ ድምፅ ብቻ መወሰን አለባቸው ወይስ የሙያ ብቃትና የሥራ ጥራትም የበለጠ ቦታ ሊኖራቸው ይገባል?
ሐሳባችሁን በአስተያየት አጋሩኝ።
ርብቃ
#adeycontemporaryartaward #temesgenlijoch #ethiopianculture #ethiopianart #ጥበብ #ባህል #ጌጡተመስገን

«በሕዝብ ቁስል ላይ እንጨት መስደዱ ሊበቃ ይገባል» — የወሎ ራያ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ
የራያ ስድስቱ ወረዳዎች ጊዜያዊ አስተዳደር የማዋቀር ሂደት ሌላ ግጭትና ጦርነት ከመጋበዙ በፊት በአስቸኳይ እንዲቆም ተጠየቀ።
በራያ ስድስቱ ወረዳዎች እየተካሄደ ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር የማዋቀር ሂደት ገለልተኛ አለመሆኑን እና መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ያላገናዘበ መሆኑን በመጥቀስ ሂደቱ ወዲያውኑ እንዲቆም የወሎ ራያ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ጥሪ አቀረበ።
ኮሚቴው ዛሬ ባወጣው መግለጫ የራያ ህዝብ ማንነትና ወሰን ጥያቄ ሕጋዊ፣ ሰላማዊና አሳታፊ በሆነ መንገድ እልባት ከማግኘቱ በፊት፣ አንድን ወገን ብቻ በሚጠቅም አካሄድ የሚዋቀር ጊዜያዊ አስተዳደር ፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል።
የአካባቢው ችግርም በሕግ፣ በማስረጃ፣ በሕዝብ ተሳትፎ እና በሕዝበ-ውሳኔ ብቻ መፍትሔ ሊያገኝ እንደሚገባ አስገንዝቧል።
በጊዜያዊ አስተዳደሩ ማዋቀር ሂደት ላይ የተነሱ ዋና ዋና ቅሬታዎች፦
ሂደቱን እየመሩ ያሉት አካላት ከፌዴራል መንግሥት ተልእኮ እንደተሰጣቸው ቢገልጹም፣ በይፋ የቀረበ የሥልጣን ሰነድ ወይም ደብዳቤ አለመኖሩ አጠያያቂ አድርጎታል
በራያ አላማጣ እየተካሄደ ባለው ሂደት የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ተፈናቃዮች በቂ ውክልና አላገኙም።
ሂደቱ በስምረት ፓርቲ እና በትግራይ ሰላም ኃይል (TPF) አመራሮች ብቻ የሚመራ በመሆኑ የገለልተኝነት ጥያቄ አስነስቷል።
በ2018 ዓ.ም. የተፈናቀሉ ዜጎች በደህንነትና በክብር ወደ ቀድሞ ቀያቸው ባልተመለሱበት ሁኔታ አስተዳደር ለማዋቀር መቸኮል ተጨማሪ ስጋት ይፈጥራል።
ታጣቂዎች ትጥቅ ባላስረከቡበት፣ እንዲሁም መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም. በሰላማዊ ዜጎች እና በራያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች በገለልተኛ አካል ሳይጣሩ የሚደረግ አደረጃጀት ተቀባይነት የለውም።
የፕሪቶሪያ ስምምነት እና የመከላከያ ሰራዊት ሚና መግለጫው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ የአካባቢውን ሰላምና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚያደርጉትን ጥረት አድንቆ፤ የአስተዳደር ማዋቀር ሂደቱ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መንፈስ እና ከሀገራዊ ምክክር መርሆዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ በሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ብቻ መመራት እንዳበት አሳስቧል።
በማጠቃለያም መንግሥት የጊዜያዊ አስተዳደር ማዋቀሩን አቅጣጫ በይፋ እንዲያብራራ እና የራያ ሕዝብ መብት በሚያስከብር መንገድ ሂደቱን እንዲያስተካክል ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል።

የካሽ ሬጂስተር እና የተነጣጠሉ መሣሪያዎችን የአሠራር ፈተና የሚቀርፈው ንብተራ-ደረሰኝ ዲጂታል የክፍያ ደረሰኝ አገልግሎት በይፋ ሥራ ጀመረ
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከፕራይም ኦል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ጋር በመተባበር፣ በዘርፉ የመጀመሪያ የሆነውን ንብተራ-ደረሰኝ የተሰኘ የተቀናጀ የዲጂታል ክፍያና የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ አገልግሎት መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. በትናትናው እለት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በይፋ አስጀምሯል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የሪቴይልና ኤስኤምኢ ባንኪንግ ዋና ሀላፊ አቶ ሙሉቀን ደምሴ የንብተራ-ደረሰኝ አገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸውንና እርስ በእርስ የማይገናኙ የሽያጭ መመዝገቢያ ካሽ ሬጂስተሮችን በአንድ እጅ ብቻ በሚያዝ ዘመናዊ ስማርት ፖስ በመተካት፣ ነጋዴዎች ለደንበኞቻቸው የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላቸዋል ብለዋል።
አክለውም፣ ቴክኖሎጂው በገቢዎች ሚኒስቴር ዕውቅና የተሰጠውን የፕራይም ኦል ትሬዲንግ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ እና የድርጅት ሀብት አስተዳደር ሥርዓት ከባንኩ የዲጂታል መሠረተ ልማት ጋር በማቀናጀት፣ በአንድ ነጻ ስማርት ፖስ አማካኝነት የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ ለማውጣት፣ የክፍያና የንግድ ሥርዓትን ለማዘመን የሚያስችል አስተማማኝ አሠራር መሆኑን ገልፀዋል።
የፕራይም ኦል ትሬዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ውብሸት አዝመራው በበኩላቸው፤ ንብተራ-ደረሰኝ ነጋዴዎች በርካታና የተለያዩ መሣሪያዎችን በመጠቀም ሲሰጡ የነበረውን ኋላቀር አገልግሎት በማስቀረት፣ በንግዱ ዘርፍ ሲስተዋሉ የነበሩትን የአሠራር ፈተናዎች በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በንብተራ ዬዲጂታል የባንክ አገልግሎት ስር በርካታ መተግበሪያዎችን በማካተት፣ ለኅብረተሰቡ ዘመናዊና የተቀላጠፉ የክፍያ አማራጮችን እያቀረበ እንደሚገኝ ተገልጿል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo

ካርታ በእርሳስ አይሳልም-ኤርትራ‼️
የኤርትራ አዲስ መግለጫ የኤርትራ ህዝብ ያካሄደው ትግል ነፃነትን ለማስመለስ የተደረገና የኢትዮጵያን ወረራ ለመቀልበስ የተከናወነ መሆኑን አውስቶ ‹‹በዚህ መራራና ረጅም የትግል ጉዞ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ የሞራልና ሌሎችም ድጋፎች ማግኘቱ የሚካድ አይደለም›› ብሏል፡፡ ጨምሮም ‹‹አሁን የሚሰማው የታሪክ ማዛባት ጫጫታ ግን ሊበሏት ያሰቧትን ጥንቸል ጅግራ ይሏታል እንደማለት ነው›› ያለው መግለጫው ‹‹የአለም ካርታ በተረት ተረት፣ ከአቅም በላይ በመመኘት፣ የቀይ ባህር መስኮት በመፈለግና ለጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በመቅረብ›› የማይለወጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በማጠቃለያውም ‹‹የአለም ካርታ በእርሳስ የሚሳል ሳይሆን በአለም አቀፍ ህግና ስምምነቶች የሚገዛ የሉአላዊነትና የግዛት አንድነት ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህም የኤርትራ ሉአላዊነት በደምና በህግ የተረጋገጠና የተገደበ ነው፡፡ እሱን የሚነካም ወዮለት፡፡ አራት ነጥብ›› ብሏል፡፡
ኤርትራ ‹‹ኢትዮጵያን የባህር በር ለማሳጣት በተደረገ ሴራ የተፈጠረች አገር›› ናት የሚለው ፍራጃ ተቀባይነት የለውም ብሏል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) አዳዲስ ወታደራዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ አማራጮችን አዘጋጅቶ ቢጠብቅም፣ ከህዳር 3ቱ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ (Midterm elections) በፊት በኢራን ላይ ምንም ዓይነት አዲስ ጥቃት እንደማያዙ አስታውቀዋል።
የዚህ ውሳኔ ጊዜ ፖለቲካዊ አንድምታው የጎላ ነው። የህዝብ አስተያየት ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ በአሜሪካውያን ዘንድ ከኢራን ጋር የሚደረግ ጦርነት ከፍተኛ ተቃውሞ የሚገጥመው ሲሆን፣ ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ እየጨመረ የመጣው የነዳጅ እና የምግብ ዋጋ መራጩን ህዝብ ከምርጫው በፊት ክፉኛ እያስቆጣው ይገኛል።
ይሁን እንጂ ትራምፕ ከምርጫው ማግስት ወታደራዊ እርምጃዎችን ሊያጠናክሩ የሚችሉበትን ሰፊ እድል ክፍት አድርገው ትተውታል። በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ጦርነቱን በኃይል "እንደሚያጠናቅቁት" ዛቻ ያሰሙ ሲሆን፣ ከምርጫው በኋላ የቦምብ ጥቃቶችን ማጠናከር "ሊሆን የሚችል" ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህ የፖለቲካ ዲስኩር ጎን ለጎን አሜሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ የባህር ኃይል አባላትን በርካታ የጦር መርከቦችን እና ተጨማሪ አውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከብ ስብስብ ወደ መካከለኛው ምስራቅ በመላክ በቀጠናው ያላትን ወታደራዊ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ አጠናክራለች።
ይህ ሁኔታ አንድ ትልቅ የፖለቲካ ጥያቄን አስነስቷል፦ ትራምፕ በእርግጥም ከጦርነት ራሳቸውን አቅበዋል ወይንስ ከባድ ወታደራዊ ውሳኔዎችን አሜሪካውያን ድምጽ ሰጥተው እስኪያበቁ ድረስ ብቻ እያዘገዩት ነው?

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኢትዮጵያ ትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች ዳግም ባገረሸው ግጭት "እጅግ እንዳሳሰባቸው" አርብ ዕለት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የዋና ጸሃፊው ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ባወጡት መግለጫ፣ ሁሉም ወገኖች "ግጭቱን በአስቸኳይ አቁመው በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ማዕቀፍ ወደ ውይይት እንዲመለሱ" ጉቴሬዝ በጥብቅ አሳስበዋል።
ዋና ጸሃፊው ግጭቱ የቀጠናውን መረጋጋት ይበልጥ ሊያናጋ እንደሚችል በማስጠንቀቅ፣ የኤርትራ ኃይሎች በኢትዮጵያ ውስጥ መግባታቸውን በሚያሳዩት ዘገባዎች ላይ ተጨማሪ ስጋት እንዳደረባቸው ጠቁመዋል። በመሆኑም በቀጠናው የሚገኙ ሁሉም ሀገራት በተመድ ቻርተር መሰረት በማንኛውም ሀገር የግዛት አንድነት ወይም የፖለቲካ ነጻነት ላይ የኃይል እርምጃ ከመውሰድ ወይም ከማስፈራራት እንዲቆጠቡ እንዲሁም በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባት የገቡትን ግዴታ እንዲያከብሩ አስገንዝበዋል።
በተፋላሚ ወገኖች ላይ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉ ሀገራት አቅማቸውን ውጥረቱን ለማርገብ እንዲጠቀሙበት እና ግጭቱን ሊያባብስ ከሚችል ከማንኛውም ድርጊት እንዲታቀቡ የጠየቁት ጉቴሬዝ፣ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሽምግልና ሚናቸውን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ እ.ኤ.አ. ከ2020 እስከ 2022 በትግራይ በተካሄደው ጦርነት በጋራ የቆሙ ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አንዱ ሌላውን የቀጠናውን ሰላም በማናጋት እየከሰሰ ግንኙነታቸው በእጅጉ መሻከሩ ይታወቃል። በተለይም ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር የባሕር በርን (በተለይም የአሰብን ወደብ) ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ተከትሎ፣ አስመራ ወደቡን የሉዓላዊ ግዛቷ አካል አድርጋ በጽኑ በመሟገቷ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት ይበልጥ ተባብሶ ይገኛል።

2 days ago
የስማርት መብራት ቴክኖሎጂ ማሳያ ማዕከል ተከፈተ
#ethiopia | የኤሌክትሪክ መብራት ቴክኖሎጂ ከተለመደው ብርሃን አቅርቦት ባለፈ በስልክ መቆጣጠር፣ የኃይል አጠቃቀምን ማሻሻልና ለተለያዩ የአጠቃቀም ፍላጎቶች መላመድ ወደሚችልበት ዘመን እየተሸጋገረ መሆኑ ተገለጸ።
ይህንን የቴክኖሎጂ ለውጥ ከኢትዮጵያውያን ሸማቾችና የግንባታ ዘርፍ ባለሙያዎች ጋር ለማቀራረብ፣ ሲግኒፋይ ከአካባቢያዊ አጋሩ ብሉ ስፓርክ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ የፊሊፕስ ስማርት ላይት ማሳያ ማዕከል ከፍቷል።
ማዕከሉ የተለያዩ የመብራት ቴክኖሎጂዎችን በተጨባጭ ለመመልከትና ለመሞከር የሚያስችል ሲሆን፣ ጎብኚዎች የብርሃን መጠንን መቆጣጠር፣ ቀለሙን መቀየርና ለጥናት፣ ለእረፍት ወይም ለሌሎች ተግባራት የሚስማሙ የብርሃን አቀማመጦችን ማዘጋጀት እንደሚቻል ማዕከሉ በተከፈተበት መርሐግብር ላይ ተገልጿል።
በማዕከሉ የሚታዩት የኤልኢዲ እና ዘመናዊ የመብራት መፍትሔዎች የብርሃን ጥራትንና የኃይል አጠቃቀምን በአንድ ላይ ለማየት ዕድል ይፈጥራሉ። ይህም ለቤት ባለቤቶች፣ ለአርክቴክቶች፣ ለዲዛይነሮችና ለሕንጻ ተቋራጮች ከግዢ በፊት የተለያዩ አማራጮችን እንዲያወዳድሩና ለፍላጎታቸው የሚስማማውን እንዲመርጡ ያግዛል ተብሏል።
በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት የኔዘርላንድ መንግሥት በኢትዮጵያ ምክትል አምባሳደር ፓውላ ሽንደለርን ጨምሮ የንግድ አጋሮች፣ ነጋዴዎች፣ የሕንጻ ንድፍ ባለሙያዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የማዕከሉ መከፈት በኢትዮጵያ የዘመናዊ መብራት ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማስፋፋትና ሸማቾች የተለያዩ የብርሃን መፍትሔዎችን በተግባር እንዲያውቁ ለማስቻል የታለመ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
#ethiopia #addisababa #philipslighting #smartlighting #lightingtechnology #ledlighting #energyefficiency #innovation #technology #signify #bluespark #smarthome

የትውልድ ቅብብሎሽ፡ የቀደምት አባቶቹን አርበኝነት ከዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ አዋህዶ የተገነባው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
**********************
ኢትዮጵያ የውጭ ወረራዎችን እና የውስጥ ተግዳሮቶችን ጨምሮ በርካታ ፈተናዎችን አልፋ ለዛሬው ቁመናዋ የበቃችው በልጆቿ የማይበገር የሀገር ፍቅር፣ የጽናትና የመስዋዕትነት እሴት ነው።
ይህ ከትውልድ፣ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣው የአልበገር ባይነት መንፈስ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ድል ከአሁኑ ዘመናዊና ኃያል የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጋር የሚያያይዝ የማይበጠስ ጠንካራ ገመድ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥንካሬና አይበገሬነት በድንገት የተገነባ ሳይሆን፣ በሺዎች ዓመታት የሚቆጠሩ ዘመናትን ከተሻገረ የታሪክ ማህደር ውስጥ የተቀዳ ቱባ እሴት ነው።
በዓድዋ ተራሮች ላይ በጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ደማቁን ምዕራፍ የጻፉት አባቶቻችን በዘመናዊ መሣሪያ የተደራጀውን ወራሪ ኃይል በሀገር ፍቅርና አልደፈርም ባይነት ያሸነፉበት መንፈስ በካራማራ እንዲሁም በተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይም ሲንጸባረቅ ቆይቷል።
ይህ ታሪካዊ የትውልድ ቅብብሎሽ የሚያሳየው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የውጊያ ስንቅና ዋነኛ የድል ምስጢር ከቴክኖሎጂና ከቁሳዊ ዝግጅት በላይ በደሙ ውስጥ የሚዘዋወረው የማይበገር የሀገር ፍቅር ወኔና የመንፈስ ጽናት መሆኑን ነው።
ቀደምት አባቶች የሀገርን ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር ሳያስደፍሩ ጠብቀው ያስረከቡትን አደራ፣ የዛሬው ትውልድ ሠራዊት አቅሙን በዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ፣ በስልጠናና በቴክኖሎጂ በማበልጸግ አደራውን በላቀ ብቃት በመወጣት ላይ ይገኛል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የትናንቷ ኢትዮጵያ ታሪክና አደራ ጠባቂ ብቻ ሳይሆን ለነገይቱ ኢትዮጵያ ሰላም፣ ልማትና ሕልውናም ዋስትና ሆኖ ቆሟል።
ሠራዊቱ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ክብር ከማንኛውም ውስጣዊና ውጫዊ ስጋት የመጠበቅ ተልዕኮውን በከፍተኛ ዲስፕሊንና ጽናት እየተወጣ ይገኛል።
የሠራዊቱ ዋነኛ የኃይል ምንጭ ከራሱ ከሕዝቡ የወረሰው ሕዝባዊ ባህሪው ነው። አባላቱ ለሀገር ሉዓላዊነትና ለሕዝብ ደህንነት ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን አሳልፈው ለመስጠት ያላቸው ዝግጁነት መከላከያ ሠራዊቱ በሕዝባዊና ሀገራዊ ፍቅር ጽኑ መሠረት ላይ የታነጸ መሆኑን ያረጋግጣል።
የመከላከያ ሠራዊቱ የአይበገሬነት ምስጢር ትናንት ከዓድዋ፣ ከካራማራና ከተለያዩ ገድሎች የወረሰውን የቀደምት አባቶች የሀገር ፍቅርና የጀግንነት እሴት ከዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ፣ ከቴክኖሎጂ የበላይነትና ከስትራቴጂያዊ አደረጃጀት ጋር አዋህዶ መገንባቱ ነው።
በሃና ምንዳሁን
#ethiopia #ethiopiandefenseforces #ethiopianpatriotism #heroiclegacy #adwavictory #ebc

ኢትዮጵያና ኤርትራ እርስ በእርስ መከሰሳቸውን ቀጥለዋል‼
በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት በወንጀላ የተካረረ ሲሆን፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው የደኅንነት ሁኔታ፣ የሰብዓዊ መብቶች ጥሪዎች እና የዓለም አቀፍ ክስተቶች ተበራክተዋል።
ሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ካቋረጡ ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ አንዱ አንዱን የጥቃት ጦርነት ጀምሮብኛል ሲሉ እርስ በእርስ መወነጃጀል ጀምረዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመቐለ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ሰላምና ሥርዓትን ወደነበረበት ለመመለስ እንዲተባበሩ በድምፅ ማጉያ ጥሪ ማቅረቡ የተሰማ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ ጥቅምት አንድ ቀን እንደሚጀምር አመልክቷል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂውማን ራይትስ ዎች በሰሜን ኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ለመፍታት እና ተጨማሪ ወንጀሎችን ለመከላከል አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ እንዲጠራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትን ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የመንግሥትን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ባሉ እስረኞች፣ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ግፍና እንግልት እየደረሰ ነው ሲል አሳስቧል።
ደቡብ አፍሪቃዊቷ ናቪ ፒላይ የሁለት ሺሕ ሀያ ስድስት ዓመተ ምሕረት የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ተገልጿል።

የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል።
በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተደረገውን የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ተከትሎ በርካታ ተማሪዎችና ተፈታኞች ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
አገልግሎቱ ባወጣው አዲስ የክፍያ ተመን፣ ቀደም ሲል 750 ብር የነበረው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ወደ 2,000 ብር ከፍ ብሏል። በተጨማሪም በድህረ-ምረቃ መግቢያ፣ በ12ኛ ክፍል ፈተና እና በሌሎች የማረጋገጫ አገልግሎቶች ላይ ተመሳሳይ የክፍያ ጭማሪ ተደርጓል።
በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን የሰጡ ተማሪዎች፣ አዲሱ የክፍያ ተመን በተለይ ለሥራ አጥና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ተማሪዎችና ቤተሰቦች ተጨማሪ ጫና የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።
በ2017 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ወስዳ እንዳልተሳካላት የገለጸች አንዲት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ፣ ለ16 ዓመታት የለፋችበት ትምህርት ውጤት አልባ ሆኖ እንዳይቀር በድጋሚ 750 ብር እየከፈለች ፈተናውን መውሰዷን ተናግራለች። አሁንም ስላልተሳካላት ለሦስተኛ ጊዜ ለመሞከር እያሰበች ቢሆንም፣ አዲሱ የክፍያ ተመን እንዳስደነገጣት ገልጻለች።
" 2,000 ብር መክፈል በጣም ከባድ ነው። ሥራ አጥ ነኝ፣ በጣም የሚያስጨንቅ ውሳኔ ነው። ለሦስተኛ ጊዜ ለመፈተን እያሰብኩ ነበር። አሁን ግን 2 ሺህ ከፍዬ ከመፈተን ይልቅ አለመፈተንን መርጫለሁ " ብላለች።
የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ለመጀመር እየሞከሩ ያሉ ተማሪዎችም የአገልግሎቱ አዲስ የክፍያ መጠን " ተስፋችንን የበለጠ አጨልሞታል፣ በትምህርት የሚያምኑ ሰዎችን ተስፋ የሚነጥቅ ነው " ብለዋል።
አንድ ተማሪ ለአገልግሎቱ 3,500 ብር እንዲከፈል መጠየቅ ምን ማለት ነው ? ሲሉ የጠየቁት ተማሪዎቹ ትምህርት የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን ራስን ለማሳደግና ለማሻሻል የሚደረግ ነው። ታዲያ የተጋነነ ዋጋ እንድንከፍል የምንደረገው ለምንድን ነው ? " ብለዋል።
" የፈተናው ይዘት በራሱ የተማሪዎችን ችሎታ ለመመዘን አይመስልም " ያሉት ተማሪዎቹ ከ750 ብር ወደ 3,500 ብር ማሳደጉ ተማሪዎች ፈተናውን ደጋግመው እንዳይወስዱ እንቅፋት እንደሚሆን ገልጸዋል።
" አንዳንዴ ገቢ መሰብሰብ ብቻ የሚመስሉ አጋጣሚዎች አሉ " ሲሉ ወቅሰዋል።
ለጤና ባለሙያዎች አሁን ያለው ጊዜ አስቸጋሪ መሆኑን የገለጸ ተማሪ ደግሞ " በኑሮ ውድነቱ ከዘርፉ እየወጣን ነበር፣ አሁን ጭራሽ በሙያው ላይ የበለጠ ተስፋ እንድንቆርጥ እያደረጉን ነው " ብሏል።
ሌላው ተማሪ ደግሞ፣ " 3,500 ብር ከፍሎ መፈተን በጣም ያስፈራል " ሲል፣ ለትምህርት የሚወጡ ወጪዎች ቢያንስ ሁሉንም ያማከሉ መሆን እንዳለባቸው ገልጿል።
" በፈተና መውደቅ አለመውደቅ የተፈታኙ ኃላፊነት ሊሆን ይችላል። ቢያንስ ለመሞከር ግን እንደዚህ በሩ መጥበብ የለበትም " ብሏል።
ሌላ ተማሪ ደግሞ ሰዎች ትምህርት መማር እየፈለጉ ባላቸው ገቢና በኑሮ ውድነት ምክንያት መማር ካልቻሉ፣ ይህ ለሚመጣው ትውልድ የመማር ፍላጎትን ሊያወርድ እንደሚችል ገልጿል።
" ሰዎች እንዳይማሩ በዚህ ልክ ክፍያ መጠየቅ እንዴት ሊብራራ እንደሚችል አላውቅም! " ሲል ተናግሯል።
" ክፍያ የተጨመረበት ዓላማ ራሱ ምን እንደሆነ አይታወቅም። ተማሪ መሆን የሚፈልግ ነው ሁለተኛ ዲግሪውን የሚማረው፣ ስለዚህ ክፍያው ሁሉን ያማከለ ቢሆን ጥሩ ነው " ሲልም ሌላ ተማሪ ገልጿል።
የፈተናዎች ኤጀንሲ ያወጣውን አዲሱን የአገልግሎት ክፍያ መረጃ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ላይ እንዳየ የገለጸ አንድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ፣ መረጃውን በተመለከተበት ወቅት " እውነት ለመናገር ደንግጫለሁ፣ የማዘን ስሜትም ተሰምቶኝ ነበር፤ ያልጠበኩት ውሳኔ ነው " ብሏል።
ተማሪው ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 950 ብር መጠየቁን አግባብነት የሌለው እንደሆነ ገልጿል።
" የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሥራው ትምህርት ነው፣ ክፍያ የለውም፣ ገቢ ወደሚያስገኝ ሥራ አልገባም፣ በቤተሰብ ላይ ጥገኞች ነን። ለፈተና ይሄን ያህል ክፈሉ ብሎ ሌላ ጫና መፍጠር፣ መክፈል በማይችሉት ላይ ችግር መፍጠር ነው " ብሏል።
አክሎም፣ " ተማሪዎችን የሚያገል ደንብ ነው። ፍትሐዊና ሁሉን ያማከለ አይደለም። ትምህርት የመማር መብት አለን፣ እንዳንማር የሚያደርጉ ውሳኔዎች ሊኖሩ አይገባም። አሁን ላይ ትምህርት ከመሠረታዊ መብትነት ይልቅ የተወሰኑ ገንዘብ ያላቸው የሀብታም ልጆች ብቻ እንዲማሩ እየተደረገ ነው " ሲል ተናግሯል።
በተጨማሪም የስም ስህተትን ጨምሮ እንደዚህ ያሉ ስህተቶችን ለማስተካከል የሚጠየቁ ክፍያዎች ሙሉ በሙሉ መቅረት እንዳለባቸው ተማሪዎቹ ገልጸዋል።
" በተቋማት በኩል በሚፈጠሩ ስህተቶች ተማሪዎች ልንጨነቅ አይገባም " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምላሽ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ምላሽ ማግኘት ባለመቻሉ የአገልግሎቱ ምላሽ በዚህ ዘገባ ውስጥ አልተካተተም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#tikvahethiopia
@tikvahethiopia የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ከ750 ወደ 2,000 ብር ከፍ አለ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን የሚያሻሽል አዲስ ደንብ ወጥቷል። በዚህም ቀደም ሲል 750 ብር የነበረው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ ወደ 2,000 ብር ከፍ ብሏል። ከዚህ ውስጥ 500 ብር የምዝገባ፣ 1,500 ብር ደግሞ የፈተና ክፍያ ሲሆን፣ ለውጭ ዜጎች…

Comments