Logo
Tikvah-University
2 hours ago
#odabultumuniversity

በ2019 ዓ.ም በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መደበኛ ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● ስምንት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

የምዝገባ ቦታ፡-
● በዩኒቨርሲቲው አዲሱ ካምፓስ

@tikvahuniversity
Tikvah-University
6 hours ago
#dillauniversity

በ2019 ዓ.ም ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ (Freshman) ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በተመሳሳይ በ2ኛ ዲግሪ (Masters) እና በ3ኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራሞች ለመማር አመልክታችሁ ተቀባይነት ያገኛችሁ አዲስ ገቢ የድኅረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

በ2019 ዓ.ም ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 19 እና 20/2019 ዓ.ም መሆኑ ተመላክቷል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

● ከ9-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
● የ8ኛ ክፍል ፈተና ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፣
● አንድ የሰነድ መያዣ ክላሰር።

የምዝገባ ቦታ፦
ኦዳያኣ ግቢ የሬጅስትራር ህንፃ ቁጥር 609 በአካል

@tikvahuniversity
Tikvah-University
6 hours ago
#uog

በ2019 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በተመሳሳይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

የምዝገባ ቦታ፡-
● ለማኅበራዊ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በማራኪ ግቢ
● ለተፈጥሮ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በአጼ ቴዎድሮስ ግቢ
● ለድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች በግቢው ረዳት ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች

አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሰቲው ከመሔዳችሁ በፊት በኦንላይን (Registration.uog.edu.et) ምዝገባችሁን እንድትፈጸሙ ተብሏል። (የምዝገባ ሒደቱ ቅደም ተከተልን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)

@tikvahuniversity
Tikvah-University
7 hours ago
#debarkuniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን አራዝሟል።

የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 28-29/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ለሪማዲያል ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ ተማሪዎች መረጃ ባለመላኩ የምዝገባው ወቅት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በመሆኑም አዲስ ለተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ የሚደረግ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
1 day ago
8ኛ ዙር የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን። 

የስልጠናው ይዘቶች፦
👉 English Grammar
👉 Professional English Speaking & Pronunciation
👉 Business & Workplace Communication
👉 Professional Writing & Email Etiquette
👉 Listening & Comprehension
👉 Public Speaking & Presentation
👉 Interview Preparation
👉 Conversational Fluency Practice

ስልጠናዎቹ በሦስት ደረጃ ተከፍለው መሰረታዊ (A1 and A2)፣ ማዕከላዊ (B1 and B2) እና ከፍተኛ ደረጃ (C1 and C2) ተብሎ የሚሰጡ ይሆናል።

የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥

☎️  0906777799 / 0906777755

አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ

ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com

Instagram: https://www.instagram.com/...
Telegram: https://t.me/sagetrainingi...
Tikvah-University
1 day ago
#pioneer_college

🔥 አስደሳች ዜና ከፓዩኒዬር ኮሌጅ   

የዕውቅና ፈቃድ ያለው ፓዩኒዬር ኮሌጅ፤ ለ2019 ዓ.ም ተማሪዎች ብቻ የሚያገለግል የትምህርት ክፍያ ዋጋ ቅናሽ አድርገናል❗️

ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዕውቅና ባገኘንባቸው የዲግሪ ፕሮግራሞች፦

► የሕክምና ዶክትሬት
► የጥርስ ሕክምና ዶክትሬት
► ፋርማሲ
► ሜዴካል ላብራቶሪ ሳይንስ

🔔 ምዝገባ ጀምረናል!

በጤናው መስክ ተወዳደሪ ሆኖ ለመገኘት ካሰቡ አሁኑኑ ፓዩኒዬር ኮሌጅ ይመዝገቡ!

አድራሻ
ከጀርመን አደባባይ ወደ ለቡ መብራት በሚሰደው መንገድ

☎️  0902442244 / 0902443344

www.pioneercollege.edu.et
Tikvah-University
1 day ago
#rayauniversity

ራያ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ትምህርት ዘመን የአንደኛ ሴሚስተር የነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 16-18/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በተጠቀሱት ቀናት በተቋሙ ዋና ሬጂስትራር ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ምዝገባ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ ልብስ መያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል።

▬▬▬▬▬▬
በተለያየ ምክንያት ትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል የሚፈልጉ ነባር እና አዲስ ተማሪዎችን በተመለከተ ከዩኒቨርስቲዎቹ ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
20 hours ago
#astu

በትግራይ ክልል ከሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ወደ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተመደባቸሁ ተማሪዎች፣ ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ጥሪ እስኪደረግላችሁ ባላችሁበት በትዕግስት እንድትጠብቁ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አሳስቧል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
1 day ago
#hawassauniversity

በ2019 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 03 እና 04/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➻ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
➻ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➻ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➻ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➻ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➻ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
➻ የስፖርት ልብስ።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
1 day ago
#ethiopianpublicserviceuniversity

በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት እንዲከታተሉ የመንግሥት ሠራተኞች ዕጩ ተማሪዎችን መልምለው እንዲልኩ የመንግሥት ተቋማትን መስከረም 08/2019 ዓ.ም በጠየቀው መሰረት፣ ተቋማቱ አስፈላጊውን መረጃ ሞልተው ለዩኒቨርሲቲው መላካቸው ተገልጿል፡፡

በዚህም ማስረጃዎቹን በትምሀርት ሚኒስቴር እና በዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት የቅበላ መስፈርት መሰረት በማጣራት ለመግቢያ ፈተና የሚቀርቡ ዕጩዎችን ዩኒቨርሲቲው ለይቷል፡፡

የመግቢያ ፈተናው መስከረም 27/2019 ዓ.ም በጠዋት እና በከሰዓት ፈረቃ፣ አዲስ አበባ ሲኤምሲ መንገድ ጉርድ ሾላ አለፍ ብሎ በሚገኘው በዩኒቨርስቲው ዋና ግቢ ይሰጣል ተብሏል፡፡

ለሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) የተመዘገቡ ዕጩዎችን በማጣራት በቅርብ ቀናት እንደሚገለፅ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity Photo
Tikvah-University
1 day ago
#kabridaharuniversity

በ2019 ዓ.ም ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የቅድመ-ምረቃ (ፍሬሽማን እና ሪሚዲያል) ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 02 እና 03/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
በዩኒቨርሲቲው ዋና ሬጂስትራር ጽ/ቤት

በተገለጹት ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ትምህርት ማስረጃዎችን መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
1 day ago
#haramayauniversity

በ2019 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርታችሁን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ አዲስ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ከጥቅምት 05-08/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
ሐረማያ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➻ የ8ኛ ክፍል ሰርቲፍኬት፣
➻ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➻ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሰርቲፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➻ 6 ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፎች፣
➻ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

ከላይ የተገለፁትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ጉርድ ፎቶግራፍ ስካን በማድረግ በሶፍት ኮፒ መያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
2 days ago
#y12hmc

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለ2019 ትምህርት ዘመን በሕክምና ዲግሪ ፕሮግራም (Doctor of Medicine) ለመማር ላመለከቱ የምልመላ ጊዜው መራዘሙን ገልጿል።

የፅሑፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን 👇
ሰኞ ጥቅምት 02/2019 ዓ.ም ጠዋት 2:00 ሰዓት

የቃል ፈተና የሚሰጥበት ቀን 👇
ሐሙስ ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም ጠዋት 2:00 ሰዓት

አመልካቾች የተጠቀሱትን ቀናት በማወቅ ለፈተናዎቹ ዝግጅት እንዲያደርጉ ኮሌጁ አስገንዝቧል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
2 days ago
#ambouniversity

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ.ም በማስተርስ እና በፒ.ኤች.ዲ ፕሮግራሞች ቅበላ ላገኙ አመልካቾች ጥሪ አድርጓል።

በምስሉ ላይ በተገለፁት 16 የድኅረ-ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ቅበላ ያገኛችሁ አመልካቾች ከመስከረም 26-28/2019 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ጽ/ቤት በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ተብሏል።

አመልካቾች በተገለፁት ቀናት ብቻ ሪፖርት እንዲያደርጉ ያስገነዘበው ዩኒቨርሲቲው፤ ትምህርት ጥቅምት 02/2019 ዓ.ም እንደሚጀምር ገልጿል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
3 days ago
የጂ.አይ.ኤስ. (Geographic Information System) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!

👉 ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ጂኦ-ስፓሻል ባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና
👉 ArcGIS + QGIS + Spatial Analysis + Remote Sensing በአንድ ላይ
👉 ንድፈ ሀሳብን ከእውነተኛ የካርታ ስራ እና ተግባራዊ ትንተና ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና

የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥

☎️  0906777799 / 0906777755

አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ

ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com

Facebook: https://www.facebook.com/s...
Telegram: https://t.me/sagetrainingi...
Tikvah-University
3 days ago
#aastu

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በጂኦተርማል ኢንጂነሪንግ እና በጂኦተርማል ጂኦሳይንስ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ለመጀመር የውጪ ስርዓተ ትምህርት ግምገማ አካሒዷል።

በዩኒቨርሲቲው የማዕድን ፍለጋ፣ ማውጣት እና ማበልፀግ የልህቀት ማዕከል የውጪ ስርዓተ ትምህርት ግምገማውን አድርጓል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከማዕድን ሚኒስቴር ከቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኦፐሬሽንስ እና ከኮርቤቲ ጂኦተርማል የተውጣጡ ባለሙያዎች በስርዓተ ትምህርት ግምገማው ተሳትፈዋል።

የሚጀመሩ የማስተርስ ፕሮግራሞች
● MSc in Geothermal Geoscience
● MSc in Geothermal Engineering

የሚጀመር የፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራም
● PhD in Geothermal Geoscience

@tikvahuniversity
Tikvah-University
3 days ago
#jimmauniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም ወደ ተቋሙ የተመደቡ የመጀመሪያ ዓመት (Freshman) ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
● የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
● የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በግብርና ኮሌጅ እና በቬተርናሪ ሕክምና ኮሌጅ

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው
● የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
● አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ
● የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ልብስ

ወደ ተቋሙ የተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ በሌላ ማስታወቂያ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
4 days ago
7ኛ ዙር የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማ እና ሴኩሪቲ ሶሉሽን (CCTV Camera Installation and Security Solution)ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!

👉 ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ቴክኒሽያኖች የሚሰጥ ስልጠና
👉 CCTV Camera Installation + Biometric Attendance + Networking + Alarm Systems በአንድ ላይ
👉 ንድፈ ሀሳብን ከእውነተኛ የገጠማ እና የጥገና ስራዎች (Hands-on Practice) ጋር በማዛመድ የሚሰጥ
👉 ሃይክ ቪዥን ካሜራዎችን በመጠቀም እና በሃይክ ቪዥን ባለሙያዎች ድጋፍ የሚሰጥ

የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥

☎️  0906777799 / 0906777755

አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ

ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com

Facebook: https://www.facebook.com/s...
Telegram: https://t.me/sagetrainingi...
Tikvah-University
4 days ago
#pioneer_college

🔥 አስደሳች ዜና ከፓዩኒዬር ኮሌጅ   

የዕውቅና ፈቃድ ያለው ፓዩኒዬር ኮሌጅ፤ ለ2019 ዓ.ም ተማሪዎች ብቻ የሚያገለግል የትምህርት ክፍያ ዋጋ ቅናሽ አድርገናል❗️

ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዕውቅና ባገኘንባቸው የዲግሪ ፕሮግራሞች፦

► የሕክምና ዶክትሬት
► የጥርስ ሕክምና ዶክትሬት
► ፋርማሲ
► ሜዴካል ላብራቶሪ ሳይንስ

🔔 ምዝገባ ጀምረናል!

በጤናው መስክ ተወዳደሪ ሆኖ ለመገኘት ካሰቡ አሁኑኑ ፓዩኒዬር ኮሌጅ ይመዝገቡ!

አድራሻ
ከጀርመን አደባባይ ወደ ለቡ መብራት በሚሰደው መንገድ

☎️  0902442244 / 0902443344

www.pioneercollege.edu.et
Tikvah-University
4 days ago
#ጥቆማ

እንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም ክፍያ በማንኛውም ጊዜ እና በየትኛውም ቦታ ሆነው ይማሩ!

ትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን እና የተማሪዎችን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ለማሻሻል ባዘጋጀው ፖርታል ይጠቀሙ! ብቃትዎን ያሳድጉ!

ፖርታሉ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ለሁሉም የክፍል ደረጃዎች የተዘጋጀ ነው።

በድምፅ፣ በፅሑፍ እና በምስል በተቀናበሩ ማስተማሪያዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋን ለማሻሻል የሚያስችል ትምህርት ያገኛሉ።

ፖርታሉ በስማርት ስልክ፣ በስማርት ቴሌቪዥን፣ በታብሌት እና በኮምፒውተር ዌብ መፈለጊያ ላይ ይሰራል፡፡ ፖርታሉን ለመጠቀም ኢንተርኔት የሚያስፈልግ ቢሆንም ገንዘብ አይቆርጥም።

ወደ ፖርታሉ ይግቡ👇
http://learn-english.moe.g...

@tikvahuniversity
Tikvah-University
4 days ago
#wallagauniversity

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ተቋሙን ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት ለማሸጋገር በሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፣ ተቋማዊ አቅም፣ የሰነድ ዝግጅት እና የሰው ኃይል ልማት ላይ ውይይት አካሒዷል።

ወደ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመሔድ የተገኘ የቤንችማርኪንግ ተሞክሮ በመድረኩ ቀርቧል።

ዩኒቨርሲቲው ለራስ ገዝነት ሽግግር አስፈላጊ በሆኑ የዲጂታላይዜሽን፣ የውስጥ ገቢ አቅም ማጠናከር እና መሠል ሥራዎች ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተስፋዬ ለማ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

የሽግግር ሰነዶችና ፖሊሲዎች ማዘጋጀት፣ የራስ ገዝነት ጽ/ቤት ማቋቋም፣ የምርምርና የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር እንዲሁም ተቋማዊ የሽግግር ካርታ ማዘጋጀት ቀጣይ ሥራዎች መሆናቸው በውይይቱ ተጠቁሟል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
4 days ago
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም ያስቀመጠውን የዩኒቨርሲቲ መቁረጫ ነጥብ ያመጡና በፖሊስ ሙያ ዘርፍ ለማገልገል የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለአራት ዓመታት በፖሊስ ሳይንስ በዲግሪ ፕሮግራም አስተምሮ በረዳት ኢንስፔክተር ማዕረግ በማስመረቅ በፌደራል ፖሊስ የሥራ ክፍሎች በማስመደብ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

መስፈርቶች፦
➻ በፖሊስ መኮንንነት ሀገሩን ለማገልገል ፍላጎት ያለው/ያላት፣
➻ ከወንጀል ነጻ ስለመሆናቸው ከሚኖሩበት አካባቢ ፖሊስ ጽ/ቤት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
➻ ለፖሊስ ስልጠና ብቁ የሆነ አካላዊ አቋምና የአዕምሮ ጤንነት ያለው/ያላት፣
➻ ከማንኛውም ደባል ሱስ ነጻ የሆነ/የሆነች፣
➻ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ያልሆነች፣
➻ ከተመረቁ በኋላ ለሰባት ዓመታት በተማሩበት የፖሊስ ሙያ በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ተመድቦ ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑ፣
➻ ሴት አመልካቾች ከእርግዝና ነጻ መሆን አለባቸው፣
➻ ከዚህ በፊት የፖሊስ/የመከላከያ ስልጠና ያልወሰዱ፣
➻ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጥን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችሉ።

በ2017 ዓ.ም እና በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ መቁረጫ ውጤት ያላቸው ወይም በ2017 ዓ.ም እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት የማለፊያ ውጤት ያመጡ ማስረጃ በማቅረብ ማመልከት ይችላሉ።

➻ ቁመት፦ ለወንድ 1.65 ሜ. እና ከዚያ በላይ ፤ ለሴት 1.55 ሜትር እና ከዚያ በላይ
➻ ዕድሜ፦ ከ18 እስከ 28 ዓመት

በትምህርት ወቅት ወርሃዊ የኪስ ገንዘብ፣ የምግብ እና የጤና አገልግሎት በተቋሙ ይሸፈናል።

የምዝገባ ጊዜ 👇
እስከ መስከረም 29/2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ

ኦንላይን ለመመዝገብ 👇
https://forms.gle/cPBiWRzU...

@tikvahuniversity
Tikvah-University
5 days ago
🌻 የአዲስ ዓመት 25% ቅናሽ ዛሬ ይጠናቀቃል!
 
8ኛ ዙር የሞባይል ጥገና (Advanced Mobile Maintenance) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!!
 
👉 የሞባይል ስልክ ሃርድዌር እና ሶፍትዌር ክፍሎች የተግባር ጥገና
👉 የሞባይል የብልሽት ፍተሻ (Troubleshooting) ሂደቶች የተካተቱበት
👉 ከንድፈ ሃሳብ እስከ ወርክሾፕ ተግባራዊ ጥገና አካቶ የሚሰጥ ስልጠና
 
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
 
☎️ 0906777799 / 0906777755
 
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ
 
ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com
 
Facebook: https://www.facebook.com/s...
Telegram: https://t.me/sagetrainingi...
Tikvah-University
5 days ago
#moe

በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እና አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ከክልሉ ውጪ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች ከመመደብ ጋር ተያይዞ የተነሱ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ እየሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በምደባው ሒደት የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ ተጠናቆ ተማሪዎቹ በጊዜያዊነት ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡበት ቀን ይፋ እስከሚደረግ ድረስ፣ ተማሪዎቹ ባሉበት ሆነው በትዕግስት እንዲጠብቁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

@tikvahuniversity