Logo
AHADU RADIO FM 94.3
2 hours ago
ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሃብት አቅም ለማስተዋወቅ 3ኛውን የአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት ፖሊሲ ፎረም መጠቀም እንዳለባት ተገለፀ

መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር ያዘጋጀችው 3ኛው የአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት ፖሊሲ ፎረም በሀገራት መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ማጠናከር ላይ ትኩረት በማድረግ ከማክሰኞ እለት ጀምሮ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

የምጣኔ ሃብት ባለሙያ አቶ ዘላለም በቀለ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካም ሆነ በመላው አህጉሪቱ ያለውን የራሷን የኢኮኖሚና የተፈጥሮ ሀብት አቅም በመለየት፣ የንግድ ማስተዋወቅ ስራዎችን በስፋት መስራት እንዳለባት ተነግረዋል ፡፡

ይህ ፎረም አፍሪካውያን ሀገራት በንግድ፣ በፋይናንስና በመሰረተ ልማት ዘርፎች እርስ በርሳቸው በመደጋገፍ ኢኮኖሚያቸውን የሚያሳድጉበት ትልቅ እድል የሚፈጥር እንደሆነም መቁመዋል።

ኢትዮጵያ ፎረሙ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ ለኢኮኖሚ እድገቷ ወሳኝ የሆኑ እንደ የባህር በር እና የንግድ መስመር ያሉ ሀገራዊ አጀንዳዎቿን ለተሳታፊ ሀገራት ለማሳወቅና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ለማሰባሰብ መጠቀም አለባት ያሉት ደግሞ መምህርና ፖለቲከኛ ዶ/ር ጌትዬ ትርፌ ናቸው።

ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት በተፈጥሮ ሀብት የበለጸጉ ቢሆኑም፣ ሀብታቸውን በአግባቡ ባለመጠቀማቸው ተገቢውን ጥቅም እዳላገኙ ባለሙያዎቹ ገልፀዋል ፡፡ በዚህ ረገድ ሀገራቱ በጋራ መስራት እንደሚገባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።

በደረጄ መንግስቱ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
3 hours ago
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የጥራት ጉድለት በታየባቸው ሰባት የመድኃኒት ምርቶች ላይ ማሳሰቢያ አወጣ

መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የጥራት ጉድለት በታየባቸው እና ከገበያ እንዲሰበሰቡ በተወሰነባቸው ሰባት የመድኃኒት አይነቶች ላይ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

ባለስልጣኑ ይህንን ማስጠንቀቂያ ያወጣው የኬንያ የመድኃኒት ተቆጣጣሪ አካል በሀገሪቱ በገበያ ላይ በተገኙ የተወሰኑ ምርቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን መነሻ በማድረግ ነው።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመድኃኒት ጥራት እና ደህንነት ክትትል ክፍል አማካሪ ዶ/ር ኤልሳቤት ወልደማርያም ለአሐዱ ሬዲዮ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ እና ኬንያ ሰፊ ድንበር የሚጋሩ በመሆናቸው እነዚህ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ዕድል አላቸው።

በተለያዩ የጥራት እና የደህንነት ጉድለቶች ምክንያት ከገበያ እንዲሰበሰቡ ከተደረጉት ሰባት የመድኃኒት አይነቶች መካከል በህንድ የተለያዩ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የተመረቱት ፍላዛርት ሽሮፕ ፣ ሄፓካል 25000 ፣ ቱናክላቭ እና ክላክሲ 1.2 ግራም የተባሉ የመድኃኒት አይነቶች ይገኙበታል።

በተጨማሪም በቻይና ኩባንያ የተመረተው ሜታሚድ መርፌ እና በኬንያ አምራች የተመረተው ክሎክሳም ሽሮፕም ከተሰበሰቡት የመድኃኒት አይነቶች ውስጥ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

በዚህም የክልል ተቆጣጣሪ አካላት የእነዚህን ምርቶች ስርጭት እና አጠቃቀም በቅርበት እንዲከታተሉ ያሳሰበው ባለስልጣኑ ህብረተሰቡም ምርቶቹ በእጁ የሚገኙ ከሆነ እንዳይጠቀምባቸው ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

በፋሲል አረጋይ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
5 hours ago
በማህበራዊ ሚዲያ በሚደረጉ የመኖሪያ ቤት ምግብ ሽያጮች ላይ የጤና ስጋት ጥቆማ ከደረሰ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ

መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች አማካይነት የኦንላይን የምግብ ማዘዣዎችን በመቀበል፣ በግል መኖሪያ ቤቶችና በድብቅ ቦታዎች ተዘጋጅተው የሚቀርቡ የምግብ ምርቶች ላይ የጤናና የደህንነት ስጋት መኖሩ ከተጠቆመ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ለአሐዱ አስታውቋል።

ተቋሙ የብቃት ማረጋገጫ (ሰርተፊኬት) ሰጥቶ እውቅና ከሰጣቸው ህጋዊ የምግብና የጤና ተቋማት ውጭ በኦንላይንና በመኖሪያ ቤቶች ደረጃ በድብቅ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተቋሙ አስቀድሞ የማወቅና የመቆጣጠር አሰራር እንደሌለው ለአሐዱ የተናገሩት የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ወርቅነሽ ብርቄ ናቸው

ነገር ግን በማህበራዊ ሚዲያ በሚደረጉ የቤት ለቤት የምግብ ዝግጅትና ሽያጮች ላይ በህብረተሰቡ በኩል የጥራት፣ የደህንነት ወይም የጤና ስጋት መኖሩን የሚያመላክቱ ጥቆማዎች ከደረሱ፣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥቆማውን መሰረት በማድረግ የተገለጹትን ቦታዎች በመፈተሽና በመቆጣጠር አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ተናግረዋል።

ማንኛውም የምግብ ዝግጅትና ማቅረብ ስራ ላይ ለመሰማራት የሚፈልግ አካል አስቀድሞ ወደ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመቅረብ የብቃት ማረጋገጫ መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርበታል ብለዋል።

አስፈላጊውን ደረጃ አሟልተው የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሳይይዙ ምግብ ማዘጋጀትና ማሰራጨት በራሱ ህገ-ወጥነት በመሆኑ፣ በጥቆማ በሚደረጉ ፍተሻዎች ጥፋተኛ ሆነው በተገኙ አካላት ላይ ተጠያቂነት እንደሚሰፍን አሳስበዋል።

አክለውም ፤የባለስልጣኑ ባለሞያዎች መስፈርቱን አሟልተው የተመዘገቡ ህጋዊ ተቋማትን በቀጣይነት በዓመት አራት ጊዜና እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው የክትትልና የቁጥጥር ስራ እንደሚያከናውኑባቸው ገልጸዋል።

ህብረተሰቡም በጤናና በምግብ ደህንነት ላይ ስጋት የሚፈጥሩ መሰል ህገ-ወጥ አሰራሮችን ሲታዘብ ጥቆማ በመስጠት መተባበር እንዳለበት ጠቁመዋል።

በወልደሐዋርያት ዘነበ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo
AHADU RADIO FM 94.3
7 hours ago
ሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ላይ የስያሜ ለውጥ ተደረገ

መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) እንደ አዲስ የተቋቋሙት ሁለት ሚኒስቴር መ/ቤቶች ቀድሞ "የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር" የነበረው በአዲሱ "የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር" በሚል ተለውጧል።

ቀድሞ "የቱሪዝም ሚኒስቴር" የነበረው በአዲሱ "የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር" በሚል መቋቋማቸው ተጠቁሟል።

7ተኛው የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ልዩ ስብሰባው በፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላት ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ እየመከረ ይገኛል።

የምክር ቤት አባልና የመንግሥት ተወካይ የተከበሩ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት ላይ አጭር ማብራሪያ አቅርበዋል።

በቀረበው ማብራሪያም ከዚህ በፊት በነበሩት 22 አስፈፃሚ አካላት ላይ የቁጥር ልዩነት እንደሌለና ከቁጥር አንፃር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በነበሩበት 22 ሆነው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

ይህም ሆኖ በሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ላይ ብቻ የስያሜ ለውጥ መደረጉንና ሁለት ሚኒስቴሮች አንደ አዲስ መቋቋማቸው ተብራርቷል።

በተጨማሪም ቀድሞ "የፕላንና ልማት ሚኒስቴር" የነበረው "የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር" በሚል እና ቀድሞ "የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር" የነበረው "የሎጂስቲክስ ሚኒስቴር" በሚል ስያሜያቸው መቀየሩ ተገልጿል።

በሚኒስቴር መ/ቤቶቹ ላይ ማሻሻያው ያስፈለገበት ምክንያት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እና ከተልዕኳቸው ጋር ለማጣጣም መሆኑም ተብራርቷል።

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
1 day ago
ራስን ማጥፋትን የተመለከቱ የሚድያ ዘገባዎች መፍትሔ አመላካች መሆን እንደሚገባቸው ተገለጸ

የመገናኛ ብዙኃን እና በጉዳዩ ላይ መረጃ የሚሰጡ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ራስን ከማጥፋት እና ከአዕምሮ ጤና ጋር የተያያዙ ዘገባዎቻቸው መፍትሔ አመላካች እና ተስፋ የሚሰጡ ሊሆኑ እንደሚገባ የኢትዮጵያ የአዕምሮ ሕክምና ማኅበር ገልጿል።

የማኅበሩ ተወካይ እና የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶክተር እስጢፋኖስ እንዳላማው፣ "አሁን ላይ በመገናኛ ብዙኃን የአዕምሮ ጤናን አስመልክቶ የሚበርቡ ዘገባዎች ቁጥር ማሻቀቡ የሚበረታታ ቢሆንም፤ በተለይም ከራስ ማጥፋት ጋር ተያይዞ በልዩ ሁኔታ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎች የሙያ ሥነ-ምግባርን ያልተከተሉ ናቸው" ብለዋል።

ራስን የማጥፋት መረጃዎችን የድርጊቱን አፈጻጸም በዝርዝር ማቅረብ ሌሎች ሰዎች ራሳቸውን እንዲያጠፉ ሊገፋፋ እንደሚችል የጠቆሙት ዶክተር እስጢፋኖስ፣ "ዘገባዎች ሰዎች ከችግሩ የሚወጡበትን እና የሚታከሙበትን መንገድ የሚያመላክቱ መሆን አለባቸው" ብለዋል።

ማኅበሩ በስፋት የሚታየውን ችግር ለማቃለል ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን እና በቀጣይም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሠራ አስታውቋል።

በስፍራሽ ደመላሽ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
1 day ago
ዘምዘም ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡ 22 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታወቀ

👉 ባንኩ "ዘምዘም ሪሚት" የተሰኘ ዲጂታል የሐዋላ አፕሊኬሽን ይፋ አድርጓል

ዘመዘም ባንክ በአምስት ዓመት የስራ ጉዞ ውስጥ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡ 22 ቢሊዮን ብር መድረሱን እና 1.1 ሚሊዮን የሚሆኑ ደንበኞችን ማፍራቱን አስታውቋል ።

ባንኩ ይህንን ያስታወቀው መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም "በማይነጥፍ ጽናት ወደ ላቀ ምዕራፍ " በሚል መሪ ቃል አምስተኛ የስራ ዓመቱን ባከበረበት ወቅት ነው ።

ባንኩ በአምስት ዓመት የስራ ጉዞ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አማራጮችን በማስፍት ፣ የፋይናንስ ተደራሽነትን በማሳደግ እና የሸሪዓ መርሆችን በመከተል ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በማቅረብ ተጨባጭ ዕድገት ማስመዝገቡን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ መሊካ በድሩ ተናግረዋል ።

በአሁኑ ወቅት የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 31 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን የባንኩ የቅርንጫፍ ቁጥር 141 መድረሱን አክለው ገልፀዋል ።

ከዚህ በተጨማሪም የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 5.6 ቢሊዮን ብር እንደደረሰና የፋይናንስ አቅሙን እንዲሁም የዕድገት መሰረቱን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ እንደቻለ ተገልጿል ።

ባንኩ በቀጣዮቹ ዓመታት የዲጂታል ለውጡን በማፍጠን እና የደንበኞችን ችግር የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማሻሻል እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ትብብሩን በማጠናከር በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ በወለድ ነፃ ባንክ ለማሳደግ እንደሚሰራ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አብራርተዋል ።

የአምስተኛ ዓመት አከባበሩን አስመልክቶ "ዘምዘም ሪሚት" የተሰኘ ዲጂታል የሐዋላ አፕሊኬሽን ይፋ አድርጓል።

በተመስገን ተጋፋው

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
1 day ago
የዘመን ባንክ አጠቃላይ ሀብት ከ116 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱ ተገለጸ

ባንኩ በዛሬው ዕለት የባለአክሲዮኖች 18ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 13ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዷል።

በዚህ ወቅት የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 116 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት ደግሞ 10 ቢሊዮን ብር ገደማ ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን ይፋ አድርጓል።

የባንኩ የማርኬቲንግና ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግሩም ታሪኩ የባለአክሲዮኖች የትርፍ ድርሻ 53.9 በመቶ ገደማ መድረሱን ተናግረዋል።

አቶ ግሩም አክለውም የባለአክሲዮኖች ስብሰባ እና የቦርድ ምርጫ ሂደቶች ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎችን ፣ የንግድ ሕጉንና ሕጋዊ አሰራሮችን በተከተለ መልኩ መከናወናቸውን አስረድተዋል።

በተጨማሪም ባንኩ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚመሩትን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ እና ሌሎች ተያያዥ ውሳኔዎችን ማሳለፉንም ገልፀዋል።

በደረጄ መንግስቱ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
1 day ago
መንግስት ሙስና እና የዘመድ አሰራርን ለማስቀረት ጠንካራ እርምጃ ሊወስድ መሆኑን አስታወቀ

ሙስናን እና የወገንተኝነት አሰራርን ለማስቀረት መንግስት ጠንካራ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ባካሄደበት እለት ነው፡፡

በዚህም በሃገር ሰላም፣ አገልግሎት አሰጣጡ የተሻለ ለማድረግ፣ ምርታማነት እንዲጨምር እና ጠንካራና ቁጥጥር ያለበት የበጀት አካሄድን አጠናክረው እንደሚሰሩም አንስተዋል፡፡

በተለይ ለህብረ ብሔራዊ ሃገረ መንግስት ግንባታ ወሳኝ የሆነው የወል ትርክት ተገቢውን ትኩረት እንደሚያገኝ ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የሰላም ሁኔታዎችን የበለጠ ለማስጽናት የውይይትና የይቅርታ መንገድ እንደሚከተሉም አመላክተዋል፡፡ እንዲሁም ጸጥታና ደህነነት ዝግጅትና ክትትል ብሎም ስምሪት እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡

የሚዲያ ምህዳሩ ህግን ሃገራዊ እሴቶችን እና ፍላጎቶችን ባከበረ መልኩ እንዲንቀሳቀስ እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሰረት እንደ መሶብ አንድ ማዕከል ያሉ አገልግሎቶችን እስከታችኛው እርከን ለማድረስ እና የተጀመረውን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም በማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲዘምን ይደርጋልም ብለዋል፡፡

በአለምነው ሹሙ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
22 hours ago
በ 2019 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 65 በመቶ የጤና መድህን ሽፋንን ደግሞ 85 በመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተገለጸ

የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ በ 2019 በጀት ዓመት በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ አበይት ተግባራ እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት የሀገሪቱን የኃይል ተደራሽነት 65 በመቶ ለማድረስ ታቅዷል ብለዋል።

በሌላ በኩል የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ሽፋንን ወደ 85 በመቶ ከፍ ለማድረግ ፣ በትምህርት ቤት የተማሪዎች የምገባ ሽፋንን ወደ 70 በመቶ ለማሳደግ እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃና የደን ሽፋንን አሁን ካለበት 26 በመቶ በላይ ከፍ ለማድረቅ መታቀዱን ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የንጹህ ውሃ አቅርቦት ተጠቃሚነትን በስፋት ማዳረስ እንዲሁም የመሶብ አገልግሎት ማዕከላት ቁጥርና አቅም በከፍተኛ ደረጃ እንዲበራከቱ ማድረግ ሌላው የመንግስት አቅጣጫ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህንን ዕቅድ እውን ለማድረግ መንግስት አዳዲስ አሰራሮችና አደረጃጀቶች እንደሚከተል የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ የዓመቱን ዕቅድ የሚያስፈጽሙ አካላት ዋዛ ፈዛዛ ልምምዶችን በመተው በትጋትና በህዝብ አገልጋይነት ስሜት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በስፍራሽ ደመላሽ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
21 hours ago
የማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራች አቶ ወንዱ በቀለ የዐይን ብሌናቸውን ለገሱ

የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ለአቶ ወንዱ በቀለ ቤተሰቦች የምስጋና የክብር ምስክር ወረቀት አበርክቷል።

የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም ረፋድ ነበር።

አቶ ወንዱ በቀለ በኢትዮጵያ በካንሰር በሽታ ቁጥጥር እና በሕፃናት ሕክምና ድጋፍ ዙሪያ የሚሰራው "ማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን" (የቀድሞው ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ) መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ነበሩ።

በሙያቸው የቢዝነስ አስተዳደር ባለሙያ የሆኑት አቶ ወንዱ በቀለ፣ የበጎ አድራጎት ሥራቸውን እንዲጀምሩ ያደረጋቸው ልጃቸው ሕፃን ማቲዎስ ወንዱ በደም ካንሰር ሕመም ምክንያት በሕፃንነቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ነበር።

የልጃቸውን ሕልፈት መታሰቢያ በማድረግ ሚያዝያ 9 ቀን 1996 ዓ.ም (በ2004 እ.ኤ.አ) ድርጅቱን መሠረቱ።

ተቋሙ በካንሰር ለተያዙ አቅም የሌላቸው ሕፃናትና ወላጆቻቸው የምክር፣ የመጠለያ፣ የሕክምና ቁሳቁስ እና የፋይናንስ ድጋፍ ይሰጣል።

በተጨማሪም፤ የካንሰር ተጋላጭነትን ለመቀነስ ጥብቅ የትንባሆ ቁጥጥር ሕጎች በሀገሪቱ እንዲወጡ ከጤና ሚኒስቴር እና ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመሆን ከፍተኛ የፖሊሲ ሙግት አድርገዋል።

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
23 hours ago
ቲክቶክ አዲስ የኤ.አይ የገበያ ረዳት እና የአንድ ክሊክ ክፍያ ስርዓት ይፋ አደረገ

ቲክቶክ ተጠቃሚዎች በቀጥታ ከንግድ ምልክቶች (Brands) ዕቃዎችን መግዛት እንዲችሉ የሚያስችል አዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የገበያ ረዳት የክፍያ ሥርዓት ይፋ ማድረጉን አስታወቀ።

ይህ አዲስ ሥርዓት ተጠቃሚዎች የተለያዩ ምርቶችን እንዲያገኙ እና በቀላሉ እንዲገዙ ለመርዳት የተነደፈ የኤ.አይ የውይይት ረዳት ነዉ። ሥርዓቱ ተጠቃሚዎች ከመተግበሪያው ዋናው የቪዲዮ ገጽ ሳይወጡ በአንድ ክሊክ ብቻ በቀጥታ ዕቃዎችን መግዛት ይችላሉ።

ረዳቱ የውይይቱን ሁኔታ በመረዳት የተጠቃሚዎችን ምርጫዎች ያስታውሳል፣ ስለ ምርቱ ዝርዝር መግለጫዎች፣ መጠን እና የዕቃው መኖር አለመኖር መረጃ ይሰጣል በተጨማሪም የትራንስፖርት መረጃዎችን እና ግዢውን ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ዝርዝር መረጃዎችን በቅጽበት ይሰጣል።

እንደ ቴክ ክራንች ዘገባ የቲክቶክ በገበያ ላይ ያለው ተፅዕኖ እያደገ የመጣ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ይፋ በሆነው ሪፖርት በዩናይትድ ስቴትስ ብቻ 54 ሚሊዮን የሚሆኑ አሜሪካውያን በቲክቶክ ቪዲዮዎች አነሳሽነት ግብይት ይፈጽማሉ።

ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ገጽ የተወሰደ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
1 day ago
የጉራጌ ክትፎና የየም ብሔረሰብ ባህላዊ የመድሀኒት ለቀማን ጨምሮ 11 ቅርሶችን በዩኒስኮ ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

የጉራጌ ክትፎ እና የየም ብሔረሰብ ባህላዊ የመድሀኒት ለቀማን እንዲሁም ያሆዴ፣ መሳላ፣ ሄቦ እና ሴራ የተሰኙትን የተለያዩ ብሔረሰቦች ዘመን መለወጫ በዓል ጨምሮ 11 ቅርሶች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) እንዲመዘገቡ እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለአሐዱ አስታውቋል።

በክልሉ በዩኔስኮ የተመዘገበው የጢያ መካነ ቅርስ በርካታ ጥቅሞችን እያስገኘ እንደሚገኝ የጠቆሙት የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ደግነህ ቦጋለ አንድ ቅርስ ዓለም አቀፍ ቅርስ ሆኖ ሲመዘገብ በርካታ ጎብኚዎችን እንደሚስብ አንስተዋል።

በክልሉ ቋሚ፣ ተንቀሳቃሽና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ያጠቃለለ በአጠቃላይ 11 ቅርሶች በዩኒስኮ እንዲመዘገቡ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
ከእነዚህ መካከል የሀድያ ዘመን መለወጫ ያሆዴ፣ የከምባታና ጠንባሮ ዘመን መለወጫ መሳላ፣ የየም ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ሄቦ፣ እና የሀላባ ዘመን መለወጫ ሴራ እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

ከእነዚህ በተጨማሪም የጉራጌ ክትፎ አዘጋጃጀትና ጥበብ ሥርዓት እንዲሁም የጆካ ጊጫ የሚሰኘው የጉራጌ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት እና የየም ብሔረሰብ ባህላዊ የመድሀኒት ለቀማ በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ ክልሉ በክልልነት ከተደራጀ በኋላ ባለፉት 3 ዓመታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራበት መቆየቱን አስገንዝበዋል።

ምክትል ሀላፊው አክለውም እነዚህ ቅርሶች አሁን አሁን ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታና የሚዳስሱ መረጃዎች ተሰብስበው በፋይል መልክ እየተቀመጡ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።

ቅርሶች እንክብካቤ እና ጥበቃ እንዲደረግላቸው በዩኔስኮ ቢመዘገቡ የተሻለ ነው ተብሎ እንደሚወሰድ አንስተዋል።
ይህንን ተከትሎም ከታችኛው መዋቅር የሚቀርቡ በርካታ ጥያቄዎች መኖራቸውን ገልፀው ቢሮው ለፌደራል እና ተጠሪ ለሆኑ ተቋማት ጥያቄዎችን በማቅረብ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በስፍራሽ ደመላሽ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo
AHADU RADIO FM 94.3
1 day ago
በአሽከርካሪዎች እና አሠሪዎች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያግዝ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

በአሽከርካሪዎች እና አሠሪዎች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ወደ ሕግ ከመውሰድ ይልቅ በሦስትዮሽ ውይይት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙ ተገለጸ።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን እና የትራንስፖርት ሠራተኞች ፌዴሬሽን በጋራ የተፈራረሙት ሲሆን፣ የአሽከርካሪዎችን መብትና ጥቅም በማስከበር አላስፈላጊ ወጪና የጊዜ ብክነትን ለማስቀረት ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ለአሐዱ ሬድዮ እንዳስታወቁት፣ ስምምነቱ የጡረታ አበልን፣ የሥራ ውልን እና ሕጋዊ ማዕቀፎችን በማጠናከር አስተማማኝ የሥራ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ ነው።

አሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ዘርፉ ዋና አንቀሳቃሽ በመሆናቸው የመብት እና ጥቅም ጥያቄዎቻቸው ምላሽ ማግኘት እንዳለባቸው አቶ ብርሃኔ ገልጸዋል።

የአሽከርካሪዎች መብት እና የሥራ ዋስትና ካልተረጋገጠ የትራንስፖርት ዘርፉም ሆነ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ሊጎዳ እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን፣ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሥራ ዋስትናቸውን የሚያሻሽሉ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ተብሏል።

በደረጄ መንግስቱ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
1 day ago
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጭ ንግድ 11.2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ

የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የ2018 በጀት ዓመት የመንግስት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ በበጀት ዓመቱ ሀገሪቱ ከፍተኛ የተባለውን 11.2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷን አስታውሰው ይህ ገቢ በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ያገኘችው ገቢ 4.5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ተናግረዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪዎች እድገት በተመለከተ 15.8 በመቶ ውጤት ማስመዝገቡን እና የብድር አቅርቦት ወደ 1.3 ትሪሊዮን ብር ማደጉን አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ገቢ ከ 1ትሪሊየን 9 መቶ ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ጠቁመዋል።

የሰብል ምርት ከ 7 ዓመት በፊት ከነበረበት 3 መቶ 35 ኩንታል ወደ 1.3 ቢሊዮን ኩንታል ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።

ይህ ውጤት የመንግስት አመራሮች ባደረጉት ጥረት የመጣ መሆኑን አንስተው “ሀገሪቱ በተለያዩ ውስጣዊ እና ውጫዊ ጫና ሆና የተገኘ ውጤት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል” ብለዋል።

የተገኘው ውጤት ኢትዮጵያ የምታስመዘግበው ውጤት ፈተናዎች የሚቋቋም ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያሳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም “መንግስት የኢትዮጵያን ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ያለውን አቅም በማደራጀት የሀገሪቱን እድገትና ብልፅግና ያረጋግጣል” ብለዋል።

በሕይወቴ ጌትነት

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
1 day ago
መንግስት በ2019 በጀት ዓመት ትኩረት የሚያደርግባቸውን 8 አበይት ጉዳዮች ይፋ አደረገ

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ መንግስት በ2019 በጀት ዓመት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የሚንቀሳቀስባቸውን ስምንት ዋና ዋና ጉዳዮች  ይፋ አደረጉ።

የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንቱ መንግስት በበጀት ዓመቱ በዋናነት ሰላም ለሀገር እድገትና ግስጋሴ ያለውን ከፍተኛ ዋጋ በማጤን ህብረትን ፣ ትብብርን እና ኢትዮጵያን የሚያስቀድም ተግባር ያከናውናል ብለዋል።

በተጨማሪም ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
 
በማህበራዊ ዘርፍ የትምህርት ፣ የጤና እና የማህበራዊ ጥበቃ ስራዎችን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማዕከል ያደረገ ልማት ትኩረት እንደሚሰጥበት የገለጹት ፕሬዝዳንቱ ለእድገት ቁልፍ ፋይዳ ባላቸው የኢንዱስትሪና የግብርና ግብዓቶች እንዲሁም በዘመናዊ የመሰረተ ልማት ግንባታ ሀገራዊ አቅም ራሱን እንዲችል ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል። 

በኢኮኖሚና ፋይናንስ ዘርፍ ደግሞ የፕሮጀክትና የፕሮጀክት ፋይናንስ አፈፃፀም ዘመናዊ ፣ ቀልጣፋ እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል።

የታክስ መሰረትን በማዘመን ዕዳን ወግ ባለው መልኩ ማስተዳደር እና የመንግስት ገቢና ወጪን በአግባቡ የመቆጣጠር አቅም እንዲያድግ ልዩ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል። 

በአስተዳደር እና የውጭ ግንኙነት መስክም በፌዴራል መንግስት እና በክልሎች መካከል ያለው የስራ ቅንጅት እና የአፈጻጸም ክትትል እንከን አልባ እንዲሆን እንደሚሰራ ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

አክለውም የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተፅዕኖ ፈጣሪነት በማሸጋገር በተለይም ወዳጆችን በማብዛት እና ለቀጠናዊ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ቅድሚያ የሚሰጡ ተነሳሽነቶችን በማጎልበት አለም አቀፍ ተቀባይነትን ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በፋሲል አረጋይ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo
AHADU RADIO FM 94.3
1 day ago
የሚመዘገበው የሞት መጠን 16% ብቻ እንደሆነ ተገለጸ

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከሚከሰተው ሞት 16% ያህሉ ብቻ እንደሚመዘገብ ተፅዕኖ ኤች.ዲ.ኤስ.ኤስ ፕሮጀክት አስታውቋል።

የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር አለመመዝገቡ ለሞት የሚዳርጉ ምክንያቶችን በትክክል ለማወቅ በሚደረገው ጥረት ላይ ክፍተት መፍጠሩን የፕሮጀክቱ ምክትል ዳይሬክተር አቶ በአንተዓለም የሻነው ለአሐዱ ሬድዮ ተናግረዋል።

እንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ከሞት ምዝገባው በተጨማሪ የልደት ምዝገባውም በተመሳሳይ ደረጃ "ውስን" የሚባል ነው።

የሚመዘገበው አብዛኛው የልደት እና ሞት ክስተት በጤና ተቋማት የሚፈጸም ሲሆን፣ በቤት ውስጥ የሚወለዱ እና የሚሞቱ ሰዎች የመመዝገብ እድላቸው በእጅጉ ያነሰ እንደሆነ ተነግሯል።

በልደት እና ሞት ላይ የተሟላ መረጃ አለመኖሩ የሀገሪቱን የስነ-ህዝብ ሁኔታ በትክክል ለመረዳት እና የጤናው ዘርፍ ውሳኔዎች ላይ ተጽዕኖ ማሰደሩ ተገልጿል።

ይህን መረጃ ለማስተካከልና ችግሩን ለማቃለል የስነ-ህዝብ እና ጤና መረጃ ጥናት የሚያካሂዱ ተቋማትን በኔትወርክ ማስተሳሰርና ስራውን ዘላቂ ማድረግ ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ዳይሬክተሩ አቶ በአንተዓለም ተናግረዋል።

ኔትወርኩ በመንግስት ተቋም ስር ቋሚ የስራ ክፍል እንዲሆን፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የማስተባበርና የመደገፍ ሚናውን እየተወጣ ነው ተብሏል።

በአበረ ስሜነህ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
2 days ago
ኢትዮጵያ ከጄኔቫው የፈንጂ ማስወገድ ማዕከል ጋር የፈጸመችው ስምምነት የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ተሰሚነት እንደሚያጎለብት ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከጄኔቫ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ፈንጂ ማስወገድ ማዕከል ጋር የፈጸመችው ስምምነት በምሥራቅ አፍሪካ የዘርፉ ዋና ማዕከል እንድትሆን እና ዲፕሎማሲያዊ ተሰሚነቷን እንድታጎለብት እንደሚያግዛት ተገልጿል።

ስምምነቱ የፈንጂ ማስወገድ ሥራዎችን ለማጠናከር፣ የመረጃ አያያዝን ለማዘመንና የባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ ያስችላል ተብሏል።

የጂኦፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ ዶክተር ተሻለ ሰብሮ እንደገለጹት፣ ስምምነቱ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ልምድ በማሳደግ ለሌሎች ሀገራት ሙያዊ ድጋፍ ለመስጠት ዕድል ይፈጥራል። በተለይም ጦርነት በተካሄደባቸው የአፍሪካ ሀገራት ድጋፍ መስጠት በሰብዓዊ ሥራዎች ያላትን ተሳትፎና ዓለም አቀፍ ተሰሚነት ያጠናክራል።

ፖለቲከኛ እና መምህር ዶክተር ጌትዬ ትርፌ በበኩላቸው፣ ከማዕከሉ ጋር የሚደረገው ትብብር የሀገሪቱን የሙያ፣ የልምድ እና የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ባለሙያዎች እና ተቋማት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመቅሰም አቅማቸውን እንደሚያጎለብቱም ጠቁመዋል።

ትብብሩ የሀገር ውስጥ የፈንጂ አደጋን ከመቀነስ ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በአካባቢውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የዲፕሎማሲ ተሰሚነት ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን ባለሙያዎቹ አብራርተዋል።

በአበረ ስሜነህ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
2 days ago
የኢትዮጵያ ከባድ ጭነት አሽከርካሪዎች ጅቡቲ ከገቡ በኋላ ደህንነታቸውን ለመከታተል የሚያስችል አዲስ ሥርዓት እንደዘረጋ ፌዴሬሽኑ አስታወቀ

ወደ ጂቡቲ የሚገቡ የኢትዮጵያ ከባድ ጭነት አሽከርካሪዎችን ደኅንነት እና የሚደርስባቸውን ችግር በቀላሉ ለመከታተል የሚያስችል አዲስ ሥርዓት መዘርጋቱን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን ነው።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ብርሃኔ ዘርዑ፣ "አሽከርካሪዎች የሀገር ድንበር ካለፉ በኋላ ለመቆጣጠር የሚያስችለው ይህ አሠራር የተዘረጋው ከጂቡቲ ትራንስፖርት ፌዴሬሽን ጋር በተደረገ ስምምነት ነው" ብለዋል።

አሠራሩን ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችሉ የሰነድ ሥራዎች በመጠናቀቃቸው በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሏል።

አዲሱ ሥርዓት የአሽከርካሪዎችን ደኅንነት እና የተሽከርካሪዎችን ሁኔታ ለማረጋገጥ እንደሚረዳ አቶ ብርሃኔ ጠቁመዋል።

አሠራሩን በተግባር ለሚያውሉ አካላት ለአንድ ወር ያህል ስልጠና እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ይህ ሥርዓት ባለመኖሩ በተሽከርካሪዎች ላይ እንግልት መድረሱን አሰና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጫና ፈጥሮ መቆየቱን ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል። አዲሱ አሠራር ተሽከርካሪዎች በተመደበላቸው ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚያደርግም ተገልጿል።

በተመስገን ተጋፋው

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
2 days ago
ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ኾነው ተመረጡ።

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ኾነው ተመርጠዋል።

የኢፌዲሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት 7ኛው የፓርላማ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

ምክር ቤቱ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚልን የፌደሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አድርጎ መርጧል። አቶ ደስታ ሌዳሞ ደግሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ኾነው ተመርጠዋል።

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
2 days ago
አቶ አህመድ ሽዴ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በመሆን ተመረጡ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በቀጣይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርን እና ሌሎችንም ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
2 days ago
ወ/ሮ አየለች እሸቴ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ በመሆን ተመረጡ

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ሲሰሩ የቆዩት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በሙሉ ድምጽ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ በመሆን ተሹመዋል።

ምክር ቤቱ በቀጣይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርን እና ሌሎችንም ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
2 days ago
"ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ የዴሞክራሲ ባህልም የሚፈተነው በምርጫ ወቅት ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)

የአዲሱ መንግሥት ምሥረታና የ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተካሂዷል። በዚሁ ስብሰባም ምክር ቤቱ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)ን አሁንም በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሰይሟቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እያደረጉት ባለው ንግግር
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በድምጻቸው ቅቡል መንግሥት ለማጽናት ለታመኑ ከ 54 ሚሊየን በላይ መራጮች ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

"ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ የዴሞክራሲ ባህልም የሚፈተነው በምርጫ ወቅት ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ህዝቡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ሕልውናውን ለማጽናት መምረጡ የዴሞክራሲያዊ ባህላችን መሰረት እየጠነከረ መምጣቱን በግልጽ አሳይቷል ብለዋል።
ማንኛውም ምርጫ አሸናፊና ተሸናፊ ፓርቲ ሊኖረው እንደሚችል አንስተው፣ ነገር ግን "ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ እንደማይኖራት" አረጋግጠዋል።
እንደ ሀገር የሚጠብቀንን ማንኛውንም ፈተና መሻገር የምንችለው

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
2 days ago
በቀጣይ የህገመንግስት ማሻሻያ እንደሚኖር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) አስታወቁ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

በዚህ ወቅት ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆኑ ተሹመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ (ዶ/ር) ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር በሀገራዊ ምክክሩ ምክረ ሐሳቦች መሠረት የሕገመንግስት ማሻሻያ እንደሚደረግ አሳውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የጠላቶቿን እኩይ ተግባርና የሚደቀኑባትን ተግዳሮቶች በብቃት ለመመከት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጓን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በምርጫው ለተሳተፉ 54 ሚሊዮን ዜጎች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ሂደቱም በብዙ መልኩ ትርጉም ያለው እንደነበር አስታውሰዋል።

"ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ የዴሞክራሲ ባህልም የሚፈተነው በምርጫ ወቅት ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕዝቡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ሕልውናውን ለማጽናት ድምፅ መስጠቱ የዴሞክራሲያዊ ባህላችን መሰረት እየጠነከረ መምጣቱን በግልጽ ያሳየ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በማንኛውም ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሸናፊና ተሸናፊ ሊሆኑ ቢችሉም "ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ የላትም" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሀገራዊ ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች በፍጥነት እየተለዋወጡና ኢ ተገማች እየሆኑ መምጣታቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም አስቀድሞ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች ቀደም ሲል ዝግጁ ባለመሆኗ ከፍተኛ ዋጋ መክፈሏን አስታውሰው አሁን ግን ካለፉት ስህተቶቿ በመማር ተግዳሮቶችን ለመመከት የሚያስችል ዝግጅት ማድረጓን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በቀጠናው ላይ ውሳኔ ሰጪነቷን በጉልበቷ የምታረጋግጥ መሆኗንና ይህንንም ያለማንም እገዛ እንደምታከናውን በመግለጽ የተያዘውን መዳረሻ ለማሳካት በሚገጥሙ እንቅፋቶች ሳትወድቅ ጉዞዋን እንደምትቀጥል ጠቁመዋል።

በውጭ ተጽዕኖ ስር ሳይወድቁ በሀገር በቀል ጥበብ ለመመራት የሚከለክል ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ጠ/ሚ ዐቢይ ሀገር ለዘመናት በመጤ ስልትና ባህል ማለፏንና ተጽዕኖዎችን ለመቆጣጠር አቋራጭ መንገዶች ሲወሰዱ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ሆኖም ኢትዮጵያዊነት ሊቀጥል የቻለው በመደመር እሳቤ እንደነበርና አሁንም የሚያዋጣው መንገድ ይኸው መሆኑን ተናግረዋል።

አክለውም ለነገ የምንሻገርበት የታሪክ አተያይ መስተካከሉን ጠቅሰው የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ስርዓት ከአንድ ዘርፍ ጥገኝነት ወጥቶ የብዝኃ-ዘርፍ ማቀናጀትና መተግበር ላይ ያተኮረ እንዲሆን መደረጉን ገልጸዋል።

ጠንካራ ቁጥጥርና ክትትል ያለበት የበጀት አካሄድን እንደሚከተሉም ያነሱ ሲሆን ለህብረ ብሔራዊ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ወሳኝ የሆነው የውል ትርክት ተገቢውን ትኩረት ያገኛል ብለዋል።

ምርታማነት ባህልና ሥርዓትም እንዲሆን የሚሰራ ሲሆን የሰላም ሁኔታዎችን የበለጠ ለማፅናት የውይይትንና የይቅርታን መንገድ እንደሚከተሉም ገልፀዋል።

በሌላ በኩል የተጠናከረ የፀጥታና የደህንነት ዝግጁነት፣ ክትትል እንዲሁም ስምሪት ይኖረናል ሲሉ ተናግረዋል።

ሙስናን፣ ሌብነትን፣ የዘመድ አሰራርንና ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግሥት መረር ያሉ እርምጃዎችን እንደሚወስድም አስታውቀዋል።

በስፍራሽ ደመላሽ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo
AHADU RADIO FM 94.3
2 days ago
ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆኑ ተሾሙ

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምጽ በማግኘት ያሸነፈው የብልጽግና ፓርቲ የፓርቲውን ፕሬዝዳንት ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ በዕጩነት አቅርቧል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ሆነው የቀረቡትን ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመሩ በሙሉ ድምጽ መርጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
2 days ago
መልሶ መጠቀም ላይ ያተኮረ ሐሳብ ያላቸው 41 ስራ ፈጣሪዎችን ደግፎ ለውጤት ማብቃቱን 'ሪች ፎር ቼንጅ' አስታወቀ

ከ74 በላይ ፕሮጀክቶች ጋር በመስራት ላይ የሚገኘው 'ሪች ፎር ቼንጅ ኢትዮጵያ' የተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ግብዓቶችን መልሶ በመጠቀም ዘርፍ ለተሰማሩ 41 ሥራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ በማድረግ ለፍሬ ማብቃቱን ገልጿል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መቅድም ጉልላት፣ ተቋማቸው "በ'ሰርኩላር ኢኮኖሚ' ዘርፍ በሐሳብ ደረጃ ያሉ ጅምር ሥራዎችን ወደ ተግባር ለማሸጋገር እስከ 10 ሺህ ዶላር የሚደርስ የፋይናንስ ድጋፍ፣ የሥልጠና እና የገበያ ትስስር እያመቻቸ ይገኛል" ብለዋል።

በሌላ በኩል በዘርፉ የተሰማሩ ሥራ ፈጣሪዎች የማሽነሪ፣ የካፒታል እና የብድር መያዣ ማጣት ትልቅ ፈተና እንደሆነባቸው ሥራ አስኪያጇ ገልጸዋል።

ይህንን ዘላቂ ችግር ለመፍታት የመንግሥት፣ የፋይናንስ ተቋማትና የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ድጋፍና ትብብር ወሳኝ መሆኑን መቅድም ጉልላት አፅንኦት ሰጥተዋል።

በደረጄ መንግስቱ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
2 days ago
ኢትዮጵያ በዓባይ እና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን ስትራቴጂካዊ ፍላጎት የሚያሳንስ ጥረት እንደማይሳካ ገለጸች

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀጣናዊ የፖለቲካ እና የደህንነት እንቅስቃሴዎች ላይ ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ ሀገሪቱ በዓባይ ወንዝ እና በቀይ ባሕር አካባቢ ያላትን መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በማንኛውም ኃይል ወይም በውጭ ተላላኪ አካላት ሊቀየሩ እንደማይችሉ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ የቀጣናው ሀገራት ከአሸናፊና ተሸናፊ አስተሳሰብ በመውጣት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል።

ሚኒስቴሩ ይፋ ባደረገው መግለጫ የኢትዮጵያ ቅርብ ድንበር ከቀይ ባሕር ዳርቻ የሚገኘው በ48 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ብቻ መሆኑን በማስታወስ በጊዜ ሂደት የፖለቲካ ድንበሮች ቢቀያየሩም ከቀይ ባሕር ጋር ያላት ጥብቅ መልክዓ ምድራዊና ታሪካዊ ትስስር አሁንም የጸና መሆኑን ገልጿል።

በመሆኑም በቀጣናው የባሕር ደህንነትና ስትራቴጂካዊ መዋቅር ላይ በሚደረግ ማንኛውም ውይይት የኢትዮጵያን ሕጋዊ ጥቅም እና ዘላቂ ሚና ማገለል እንደማይቻል አስታውቋል።

ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነውን የናይል ውኃ የምታመነጨው ኢትዮጵያ መሆኗን የገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዓባይ ወንዝ አጠቃቀምና አስተዳደር ዙሪያ የሚደረጉ ማናቸውም ውይይቶች ይህን መሰረታዊ የተፈጥሮ እውነታ ያገናዘቡ መሆን እንዳለባቸው ጠቁሟል።

የውኃውን መነሻና የሀገሪቱን ድርሻ ያላገናዘበ አካሄድ ተቀባይነት እንደሌለውም አስታውቋል።

በፖለቲካዊ ዲስኩር ፣ በማስገደድ እርምጃዎች ወይም በተላላኪ ኃይሎች አማካይነት የሚሰነዘሩ ጥቃቶችና ሀገርን የማተራመስ ሙከራዎች ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ሚና እና ሕጋዊ ጥቅም ከቶውንም ሊያሳንሱት እንደማይችሉ የጠቆመው መግለጫው ሀገሪቱ ሉዓላዊነቷን ፣ የግዛት አንድነቷን እና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር በማንኛውም ጊዜ ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል።

የቀጠናው ተዋናዮች የጋራ ፈተናዎችን በኃይልና በግጭት ከመፍታት ይልቅ በገንቢ ውይይት፣ በአጋርነትና በመልካም ጉርብትና መርሆች ላይ ተመሥርተው በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል።

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo
AHADU RADIO FM 94.3
2 days ago
የመንግሥት እና የግል የሕክምና ተቋማት የመረጃ ልውውጥ ሲስተም በሙከራ ደረጃ መጀመሩ ተገለጸ

የመንግሥት እና የግል የሕክምና ተቋማት የታካሚዎችን መረጃ በወጥነት እንዲለዋወጡ የሚያስችል "ሼርድ ኸልዝ ሪከርድ" የተባለ ዲጂታል ሲስተም በሙከራ ደረጃ መተግበሩን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

አዲሱ አሠራር በኢትዮጵያ የሕክምና ሥርዓቱን ለማዘመንና የጤና መረጃዎችን በተቀናጀ መልኩ ለመያዝ ያለመ ነው ተብሏል።

በጤና ሚኒስቴር የዲጂታል ጤና መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገመቺስ መልካሙ ለአሐዱ ሬድዮ እንደገለጹት፣ ሲስተሙ ታካሚዎች በመንግሥት እና በግል ተቋማት ያላቸውን የሕክምና ታሪክ በቀላሉ ለመለዋወጥ ያስችላቸዋል።

የመረጃ ልውውጡን ለማሳለጥ ከፋይዳ ዲጂታል ጋር በመተባበር ልዩ የጤና ፋይዳ መታወቂያ በመዘጋጀት ላይ እንደሆነ ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

አክለውም፤ "እስከአሁን አምስት ሺሕ የሚጠጉ መለያዎች በቋት ውስጥ ተካተዋል" ብለዋል።

አሠራሩ በፋይናንስ ተቋማት መካከል ያለውን የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት ወደ ጤናው ዘርፍ የማምጣት እቅድ ስለመያዙ ተገልጻል።

በመሰረት ሙሉ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
2 days ago
አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአገራዊና ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ ማተኮር እንደሚገባ ተገለጸ

አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአገራዊ እና ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ አተኩረው መስራት እንደሚገባቸው አሐዱ ሬድዮ ያነጋገራቸው የጂኦ-ፖለቲካ ተንታኞች ገልጸዋል።

መምህርና ፖለቲከኛ ዶክተር ጌትዬ ትርፌ፣ "የሕዝብ ተወካዮች ከተለመደው የማወደስ ወይም የመንቀፍ ባህል ወጥተው ጠንካራ የቁጥጥር እና የክትትል ሥርዓት በመዘርጋት መስራት ይኖርባቸዋል" ብለዋል።

አክለውም፤ የሕዝብ ተወካዮች አስፈጻሚ አካላት ከተቀመጠላቸው ዕቅድ በላይ እንዲሠሩ ድጋፍ ማድረግ አሰና የተሻሉ አማራጭ ሀሳቦችን ማመንጨት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

የዓለም አቀፍ የፖለቲካ ተንታኝ እና የታሪክ መምህር ዶክተር ደጉ አስረስ በበኩላቸው፣ ተመራጭ የሕዝብ ተወካዮች በፓርላማ ደረጃ ከሚያደርጉት ተሳትፎ ባሻገር በፓርቲያቸው የውስጥ መድረኮች ላይ ጠንካራ ክርክር በማድረግ የሕዝብን ድምፅ ሊያንጸባርቁ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ተንታኞቹ አያይዘው እንዳመለከቱት፣ የአዲሱ ምክር ቤት ተወካዮች የቀጠናው እና የዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን ያገናዘበ አሠራር መከተል ይጠበቅባቸዋል።

በቃልኪዳን ኃይሌ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
3 days ago
ከ30 ዓመት በላይ ያገለገሉ የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ዕገዳ በጊዜያዊነት መነሳቱ ተገለጸ

ከ30 ዓመት በላይ አገልግሎት የሰጡ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ጅቡቲ እንዳይገቡ ተጥሎ የቆየው ዕገዳ በጊዜያዊነት መነሳቱን የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ተሽከርካሪዎቹ ረጅም ጊዜ ያገለገሉ በመሆናቸው አገልግሎት እንዳይሰጡ ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር ይታወሳል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኔ ዘርዑ ለአሐዱ ሬድዮ እንዳስታወቁት መንግስት በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን የሚያበረታታ የፖሊሲ ለውጥ በማድረጉ ረጅም ዓመታት ያስቆጠሩ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ለመቀነስ እየተሰራ ይገኛል።

ፌደሬሽኑ በብድር አዳዲስ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ለማስገባት ጥረት እያደረገ በመሆኑ በቆዩት ላይ ተጥሎ የነበረው ዕገዳ በጊዜያዊነት ተነስቶ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ገልጸዋል።

ረጅም ዓመታት አገልግሎት የሰጡ ተሽከርካሪዎችን ያለበቂ ዝግጅት ከዘርፉ ማስወጣት ተገቢ አለመሆኑን አቶ ብርሃኔ ጠቁመዋል።

አክለውም፤ ለውሳኔው ተግባራዊነት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ በጥናት የተረጋገጠ መረጃ ባይኖርም ከ14 እስከ 15 ሺህ የሚገመቱ የጭነት ተሽከርካሪዎች እንደሚገኙ ይታመናል።

በተመስገን ተጋፋው

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
3 days ago
የኦሮሚያ ጤና ቢሮ የደም እጥረትን ለማቃለል በሆስፒታሎች "ሚኒ ደም ባንክ" ለማቋቋም ማቀዱን አስታወቀ

የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ በሆስፒታሎች የሚያጋጥመውን የደም እጥረት ችግር ለመፍታት በክልሉ ከሚገኙ 17 የደም ባንኮች በተጨማሪ በሆስፒታሎች ደረጃ አነስተኛ የደም ባንክ ወይም "ሚኒ ደም ባንክ" ለማቋቋም ማቀዱን አስታውቋል።

አዲሱ አሠራር ሆስፒታሎች የራሳቸውን ደም በራሳቸው እንዲሰበስቡና እንዲያከማቹ እንዲሁም ደም እና የደም ተዋጽኦዎችን ለሚያስፈልጋቸው ለመስጠት የሚያስችል ነው።

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ደረጀ አብደና ለአሐዱ ሬድዮ እንደገለጹት፤ አሠራሩ በበጀት ዓመቱ አዳዲስ የደም ባንኮችን ከማቋቋም ጎን ለጎን በሆስፒታሎች የሚኒ ደም ባንክ አገልግሎትን ለማስፋፋት ያለመ ነው።

በተለይም የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ሆስፒታሎች የራሳቸው የደም ባንክ እንዲኖራቸው ይደረጋል ተብሏል።

አገልግሎቱ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የወሊድ ሕክምና በሚሰጡ ሆስፒታሎች ላይ የተጀመረ ሲሆን፤ በተያዘው የበጀት ዓመት በሁሉም አካባቢዎች በሚገኙ ሆስፒታሎች ለማስፋት ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል።

በክልሉ የማኅበረሰቡ የደም ልገሳ ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን አቶ ደረጀ ተናግረዋል። ደም መለገስ ላይ የነበሩ የአመለካከት ችግሮችም መፈታታቸውን ገልጸዋል።

በክልሉ ከዓመት ዓመት የሚሰበሰበው የደም መጠን እየጨመረ የመጣ ሲሆን፤ ከተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች እና አባቶች ገዳዎች ጋር በተሠራ ሥራ የማኅበረሰቡን አመለካከት መለወጥ ተችሏል ተብሏል።

በህይወቴ ጌትነት

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ