Logo
AHADU RADIO FM 94.3
የጋሞ ብሔረሰብ ባህላዊ የፍትሕና የእርቅ እሴት የሆነውን ዱቡሻ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ሂደት ላይ መሆኑ ገለፀ ።

መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የጋሞ ብሔረሰብከሚታወቅባቸው እሴቶች መካከል ዱቡሻ ባህላዊ የፍትሕ፣ የእርቅና የሕዝብ መሰብሰቢያ እና መገለጫ አንዱ ነው።

የጋሞ ዞን  ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ግባዬ ግልጮ ዱቡሻ ለትውልድ ለማስተላለፍ እና ወጣቶች እንዲያውቁት እና እንዲጠብቁት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ዱቡሻ በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት፣ ሕግና ደንብ ለማውጣት እንዲሁም የማኅበረሰቡን አንድነት ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀዋል ።

የዱቡሻ  ስርዓትን በአለምአቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ እና በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ሂደት መጀመሩን ተናግረዋል ።

ግጭት እና አለመግባባቶች በሽምግልናና በእርቅ ሥርዓት እንዲፈቱ የሚያደርግ እንዲሁም መረጃ  ያልተሟላባቸው ወይም በድብቅ የተፈጸሙ የወንጀል በማጣራትና በመሃላ ሥርዓት የሚመረመርበት ባህላዊ እሴት መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል ።

ዱቡሻ የጋሞ ብሔረሰብ ባህላዊ ዕውቀት ፣ የማኅበረሰብ አንድነትን የሚያንጸባርቅ እንዲሁም የጋሞ ሕዝብ ባህልና ትውፊት ሚገለጽበት መንገድ መሆኑ ተመላክቷል ።

በቃልኪዳን ኃይሉ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.