Logo
YeneTube
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊትና የትግራይ የሰላም ኃይል የዓዲግራት ከተማንና እንዳስላሴ ሽረን መቆጣጠራቸውን ታውቋል።

የአካባቢው ነዋሪዎችን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ሁለቱም ከተሞች ነጻ የወጡት በትላንትናው ዕለት ነው።

ዓዲግራት ከተማን አቋርጠው ዕዳጋ ሐሙስ ደርሰው የነበሩ የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ሐይሎች ተገፈተው ወደ ድንበር ከተማ ማፈግፈጋጠቸውንም ዜናው አክሏል።  

ዜና ወኪሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናትን አግኝቶ ለማናገር ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለትም ገልጿል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያለፈለጉ አንድ የትግራይ ሰላም ኃይል ባለስልጣን በበኩላቸው በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የምትገኘው የሐውዜን ከተማና  በትግራይ ማዕከላዊ ዞን እምባስነይቲ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችው ነበለት ከተማ በፌደራል የመከላከያ ሰራዊትና በትግራይ የሰላም ኃይሎች ቁጥጥር ሥር መሆናቸውን ገልጸዋል።

ምንጭ :- ዶቼ ቬለ ዜና ከነጻ ምንጭ ማረጋገጥ አልቻልኩም ብሏል
@Yenetube Fikerassefa
21 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.