4 hours ago
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ተካሂዷል
ለሚንስትርነት ስፍራው እጩዎች በጠ/ሚ አማካኝነት አቀርበዋል
👉አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
👉ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
👉ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) የገንዘብ ሚኒስትር
👉 ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በድጋሚ የትምህርት ሚኒስትር
👉 ወ/ሮ ሀና አርያስላሴ የፍትህ ሚኒስትር
👉አቶ መሀመድ እድሪስ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር
👉 አቶ አዲሱ አረጋ የግብርና ሚኒስትር
👉 ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር
👉 ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
👉 ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር
👉 ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ የንግድና ቀጠናዊ ስትትር ሚኒስትር
👉 ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ለባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር
👉 አቶ አወሉ አብዲ የስራና ክህሎት ሚኒስትር
👉 አቶ በረከት ፍስሃፅዮን የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር
👉 አቶ ሳዳት ነሻ የሎጅስቲክስ ሚኒስትር
👉 ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
👉 አቶ ሙሳ አደም የሰላም ሚኒስትር
👉 ፍሬህይወት ታምሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
👉ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ የገቢዎች ሚኒስትር ሆነው እንዲሾሙ በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
#ዳጉ_ጆርናል

20 hours ago
በአዳማ ከተማ በሽርክና አብራት በምትሰራው ባልደረባዋ ላይ የአሲድ ውሀ የደፈችው ግለሰብ ተያዘች
በአዳማ ከተማ ደበላ ክፍለ ከተማ ኢሬቻ ቀበሌ በጋራ በመሆን ዳይመንድ የማሳጅ አገልግሎት አቋቁመው ሲሠሩ በቆዩ ሁለት ወጣቶች መካከል በተፈጠረ የገንዘብ አለመግባባት ባለደረባዋ ላይ የአሲድ ውሀ የደፈችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዳማ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።
መብራቴ ጅሬኛ እና ኬርያ እንድሪስ የተባሉ ሃያዎቹ አጋማሽ ዕድሜ ላይ የሚገኙት ሁለቱ ወጣቶች ቀደም ሲል በነበራቸው የሥራ ልምድ ተነሳስተው በ2018 ዓ.ም ጥር ወር ላይ ገንዘባቸውን በማዋጣት ሥራውን ጀምረው በሂደቱም ስኬታማ በመሆን ሌሎች ሁለት ሴት ሠራተኞችን ጭምር ቀጥረው ሲሠሩ ቆይተዋል።
ይሁን እንጂ ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ በገንዘብ ወጪ ዙሪያ አለመግባባት መፈጠሩን የአዳማ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሚኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታምራት ጌታሁን ለብስራት ሬድዮ ገልጸዋል።
ሁኔታው እየባሰ ሲሄድም መብራቴ መግባባት ካልቻልን ገንዘባችንን ተካፋለን በተናጠል እንሥራ የሚል ሐሳብ ያቀረበች ሲሆን በኬርያ በኩል ግን ፈቃደኝነት ባለመኖሩ አለመግባባቱ እስከ ድብድብ ደርሶ ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ አስማምቷቸው እንደነበር ተነግራል።
የሰፈነው ስምምነት ለቀናት እንኳን ሳይዘልቅ በነበረ የገንዘብ ጫና ውዝግብ ኬርያ ቀደም ሲል በያዘችው ቂም በስልክዋ ስትጫወት በነበረችው መብራቴ ላይ ከፍተኛ የአሲድ ውሀ በጭንቅላቷ ላይ ደፍታባታለች።
ጉዳቱን ተከትሎ የአካባቢው ማህበረሰብ በሰጠው ፈጣን ትብብርና በፖሊስ ርብርብ ተጎጂዋ ወዲያውኑ ወደ ሕክምና ተወስዳለች።ተጠርጣሪዋም በቁጥጥር ሥር የዋለች ሲሆን ፖሊስ ጉዳዩን አጣርቶ ለፍትህ እንደሚያቀርብ ኮማንደር ታምራት ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
በትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል Photo

18 hours ago
ክፍያ እና ብድርን የሚያሳልጥ የዲጂታል ክፍያ ስርዓትን በ100 ሺህ ለሚቆጠሩ ነጋዴዎች ተደራሽ ለማድረግ ስምምነት ተደረገ
ስምምነቱን ያካሄዱት ኢታ ሶሉሽንስ እና ቪዛ ናቸዉ ። ለነጋዴዎች ክፍያን የሚያቀል ፣ ንግድን የሚያዘምን እና የዲጂታል ግብይት ታሪካቸዉን መነሻ በማድረግ ብድር የሚያመቻቸዉ "ዙሪያ "የተሰኘዉን ዲጂታል የቢዝነስ አዉቶሜሽን በኢትዮጵያ ለሚገኙ ነጋዴዎች ለማዳረስ ስምምነቱን አካሄደዋል ።
የኢታ ሶሉሽንስ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ተመስገን ገብረህይወት እንደተናገሩት ስምምነቱ ዙሪያ የተሰኘዉን የዲጂታል ክፍያ መቀበያ ማሽን ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚገኙ 148 ሺህ ነጋዴዎች ለማድረስ የተደረገ ነዉ ማለታቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል ።
ለነጋዴዎች በካርድ ፣ በኪዉአር (QR) ኮድ ፣የሞባይል ገንዘብ እና ከሂሳብ ወደ ሂሳብ የሚደረጉ ክፍያዎችን በአንድ መሳሪያ ላይ ማስተናገድ የሚቻልበት ዕድል መፈጠሩ ተገልጿል ።
ይህንንም የካርድ ክፍያ ከትልልቅ ሱቆች ጀምሮ እስከ ጥቃቅን መደብሮች ተደራሽነቱን ለማስፋቱ እየተሰራ መሆኑ የተገለፀዉ ። ይህም ቴክኖሎጂ ለነጋዴዎች የዕለት ተዕለት የንግድ እንቅስቃሴያቸውን በቀላሉ ለማወቅ ከማስቻሉም በዘለለ በግብይት ታሪካቸዉ ላይ በመመስረት የብድር ተጠቃሚ የሚሆኑበትንም ዕድል ያሰፋል ነዉ የተባለዉ ።
ኢታ ሶሉሽንስ ከአለምአቀፉ የብድር ተቋም ጋር በመተባበር ከባንኮች ጋር የብድር ስምምነት ይደርጋል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዉ በግብይት እንቅስቃሴያቸው ብቁ የሆኑ ነጋዴዎች የብድር ተጠቃሚ ይሆናሉ ማለታቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል ።
በመባ ወርቅነህ

በኢትዮጵያ የአፍና የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች እጥረት መኖሩ ተገለፀ
በአገሪቱ የአፍና የጥርስ ጤና ችግሮች በስፋት የሚታዩ ቢሆንም በዘርፋ የህክምና ባለሙያዎች እጥረት መኖሩን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ አስታውቋል።
በማህበረሰቡ ዘንድ ከሚስተዋሉ የጥርስ ጤና ችግሮች መካከል በዋናነት የህፃናትና የአዋቂዎች ጥርስ መበስበስ፣ የድድና የጥርስ አቃፊ አጥንት ሕመም፣ የጥርስ መርገፍ እንዲሁም የአፍና የከንፈር ካንሰር ይገኙበታል።
በሆስፒታሉ የጥርስና ማክሲሎፌሻል ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም የፊትና መንጋጋ ቀዶ ጥገና ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አዲስ ካሳሁን ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ጥርስን እስከ ማጣት ሊያደርስ የሚችለው የድድና የጥርስ አቃፊ አጥንት ህመም 18.7 በመቶ ስርጭት ሲኖረው የጥርስ መርገፍ ደግሞ 1.8 በመቶ ስርጭት እንዳለው ተናግረዋል።
የሕክምና ኮሌጁም ከመደበኛው የጥርስ ህክምና በተጨማሪ የአፍ፣ የመንጋጋና የፊት ቀዶ ጥገና ሕክምናን እንደሚሰጥ ገልጿል።ተቋሙም በየቀኑ ከ90 እስከ 140 የሚደርሱ ታካሚዎችን በማስተናገድ ሕክምናን እየሰጠ መሆኑን ዶክተር አዲስ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
በፈረንጆቹ 2022 የታተመውና በ2018 አ/ም የተሰበሰበው መረጃን ያካተተው የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ በኢትዮጵያ የሚገኙት 1 ሺህ 745 የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች ብቻ ናቸው።በዘርፋ የተሰማሩ የባለሙያዎችን ቁጥር አስመልክቶ ወቅታዊና የተጠናቀረ መረጃ ባለመኖሩ በአሁኑ ወቅት ያለው ቁጥር ከዚህ የተለየ ሊሆን እንደሚችልም ዶክተር አዲስ ገልጸዋል።
በሰብል አበበ

Sponsored by
Surafel
15 hours ago
የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ
ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ መንግሥት አስጠነቀቀ
የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ አዲግራት ከተማን መቆጣጠሩን ሲነገር፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ድርጊት "ወረራ" ሲል በይፋ ኮንኗል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ለብሉምበርግ እንደተናገሩት፣ የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ አሳስበዋል። ይህ መግለጫ የኤርትራ ጦር ሀገሪቱን በቀጥታ መውረሩን ያረጋገጠ ይፋዊ አቋም ነው።
ይህ ውጥረት የተፈጠረው ህወሓት ከሌሎች አማፂ ቡድኖች ጋር አብሮ አዲስ ጥቃት ከከፈተ በኋላ ነው። መንግሥት እንደሚለው፣ ኤርትራ እነዚህን አማፂያን ከጀርባ ስትደግፍ ቆይታ አሁን ደግሞ ጦሯን በቀጥታ በማስገባቷ ሁለቱ አገራት ወደ ቀጥተኛ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

17 hours ago
የኤርትራ ጦር አዲግራት ከተማ ቢገባም
👉 ኤርትራ አስተባብላለች
የኢትዮጵያ መንግሥት ጦር ከአዲግራት ወደ መቀሌ ይጓዝ የነበረ የኤርትራ ጦር ቅፍለትን በሰዉ አልባ አዉሮፕላን መምታቱ ተነገረ።
የኤርትራ ጦር አዲግራት ከተማ ከገባ አራት ቀናት እንዳለፈዉ ነዋሪዎችና የከተማይቱ ባለሥልጣትናት አስታወቁ።ኤርትራ አስተባብላለች።ዉቅሮ አካባቢ የከባድ መሳሪያ ተኩስ መሰማቱ ተነግሯልም።

ጃፓን ለየመን እና ለጅቡቲ የ10 ሚሊዮን ዶላር የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ ለመስጠት ወሰነች
የጦርነቱ ተፅዕኖ ወደ ጎረቤት ሀገራት መዛመቱን እና በየመን እየከፋ የመጣውን የሰብአዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ጃፓን ለየመን እና ለጅቡቲ የ10 ሚሊዮን ዶላር የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ እንደምትሰጥ አስታውቃለች።
የጃፓን መንግስት እርዳታውን ማክሰኞ ዕለት ማጽደቁን የሀገሪቱ ኤምባሲ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጿል።እርዳታው የባብ አል-መንደብ ወሽመጥ ዙሪያን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላምና መረጋጋትን ለመደገፍ አልሞ የተዘጋጀ መሆኑም ተነግሯል።
የጃፓን መንግስት ይህ የባህር ወሽመጥ በኢነርጂ ደህንነት ረገድ ለጃፓንም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ “እጅግ ከፍተኛ አስፈላጊነት” ያለው መሆኑን ገልጿል።
በዚህም መሰረት የመን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ፣ በዓለም አቀፉ የሬድ ክሮስ ኮሚቴ እና በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በኩል 8 ሚሊዮን ዶላር የምታገኝ ሲሆን፣ ጅቡቲ ደግሞ በተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ በኩል 2 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳታል ተብሏል ።
በሚኪያስ ጸሐዬ

19 hours ago
የፖለቲካ አለመረጋጋትን ተከተሎ ሄይቲ ምርጫዋን አራዘመች
የምርጫ ኮሚሽኑ የዕጩዎች ምዝገባ ጊዜን እስከ ጥቅምት 21 ቀን ድረስ ያራዘመ ሲሆን የተሻሻለ የብሔራዊ ምርጫ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ላይ ይገኛል።
በሄይቲ ቀጣይነት ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት በመከሰቱ ምክኒያት ሀገሪቱ ልታካሂደው ያቀደችውን ምርጫ ማራዘሟን አስታውቃለች።የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን የተሻሻለ ብሔራዊ የምርጫ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ጊዜያዊ የምርጫ ኮሚሽኑ ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ ከፖለቲካ ተዋንያን ጋር ከተደረጉ ውይይቶች በኋላ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰኔ 2 ቀን 2026 የወጣውን የምርጫ አዋጅ ለማሻሻል ጥቅምት 5 ቀን 2026 የፀደቀውን ድንጋጌ በማስመልከት፣ የተወሰኑ የምርጫ ሂደት መርሃ ግብሮች እንዲቀየሩ ተደርጓል ብሏል።
ኮሚሽኑ አክሎም የምርጫ ቅስቀሳው ጊዜ የታገደ መሆኑን ገልጾ ከተፈቀደላቸው የፖለቲካ አካላት ጋር የተሻሻለ የምርጫ ማዕቀፍን አዘጋጅቶ ሲያጠናቅቅ አዳዲስ ቀናትን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማስተናገድ ሲባል ኮሚሽኑ የዕጩዎች የኦንላይን ምዝገባዎች እንዲቀጥሉ አሳስቧል።
ፕሬዝዳንትን ፣ የምክር ቤት፣ የክፍለ ሀገር እና የከተማ አስተዳደር አባላትን ለመምረጥ ታስቦ የነበረው ጠቅላላ ምርጫ ታህሳስ 13 ይካሄዳል ተብሎ ታቅዶ ነበር። ሀገሪቱ ከ2016 ጀምሮ ምንም አይነት ጠቅላላ ምርጫ ስላላካሄደች በህዝብ የተመረጡ ብሔራዊ ባለስልጣናት የሏትም።
እ.ኤ.አ. ሀምሌ 2021 የፕሬዝዳንት ጆቨኔል ሞይስ መገደልን እና የህግ መውጫ ዘመናት መጠናቀቅን ተከተሎ ሄይቲ ወደ ከፋ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ገብታለች። በአሁኑ ወቅት ይህችን የካሪቢያን ሀገር እ.ኤ.አ. በ2024 የተዋቀረ ጊዜያዊ የፖለቲካ ስርዓት እየመራት ይገኛል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አሬል ሄንሪ በታጣቂዎች ጫና ስልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ የተዋቀረው ጊዜያዊ የፕሬዝዳንት ምክር ቤት፣ በሹመት ወደ ስልጣን በመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አሊክስ ዲዲየር ፊልስ-አይሜ ከሚመራውና በአዋጅ ከሚያስተዳድረው የካቢኔ አካል ጋር በመሆን ሀገሪቱን እያስተዳደሩ ይገኛሉ።
ስላማዊ ነጋሲ

21 hours ago
በጋና የመገበያያ ገንዘብን ለጌጣጌጥ እና ለኬክ ማስጌጫነት የተጠቀሙ ሰባት ሴቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የጋና ማዕከላዊ ባንክ አገራዊ የመገበያያ ገንዘብን ለተገቢው አገልግሎት ብቻ ማዋል እንደሚገባ እና በገንዘብ ማስጌጥ ህገ-ወጥ መሆኑን ቀደም ብሎ ማሳሰቡ ይታወሳል።
የጋና ማዕከላዊ ባንክ ከጋና ፖሊስ አገልግሎት ጋር በመተባበር ባካሄደው ዘመቻ በዋና ከተማዋ አክራ የሀገሪቱን የመገበያያ ገንዘብ ለጌጣጌጥ፣ ለአበባ እቅፍ እና ለኬክ ማስጌጫነት በመጠቀም ሲሸጡ የነበሩ ሰባት ሴቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
እርምጃው የተወሰደው የሀገሪቱን ህጋዊ የመገበያያ ገንዘብ አግባብ ባልሆነ መልኩ የመጠቀም እና የመንከባከብ ልማድን ለመግታት በተደረገ አገር አቀፍ ቁጥጥር መሆኑ ተገልጿል።
የጋና ማዕከላዊ ባንክ ባለፈው ወር ባወጣው መግለጫ የሴዲ ኖቶችን ለጌጣጌጥም ሆነ ለተለያዩ የአበባ እቅፎች መስሪያነት መጠቀም በህግ የተከለከለ መሆኑን አስጠንቅቆ ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ላይ ገንዘብን መበተን፣ ኖቶችን መበጠስ፣ በላያቸው ላይ መጻፍ ወይም የባንክ ኖቶችን ማበላሸት ፈጽሞ የተከለከሉ ድርጊቶች እንደሆኑ ባንኩ አሳስቧል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰባቱ ተጠርጣሪዎች በጋና ህግ መሰረት ክስ የሚመሰረትባቸው ሲሆን፣ የገንዘብ መቀጮ ወይም የእስራት ቅጣት ሊጠብቃቸው እንደሚችል ተጠቅሷል።
ባንኩ አክሎ እንደገለጸው ሴዲ የሀገሪቱ ህጋዊ የመገበያያ ገንዘብ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ተገቢውን ክብር እና እንክብካቤ ሊያደርግለት እንደሚገባ አሳስቧል።
ሰላማዊ ነጋሲ

23 hours ago
የሱዳን ጦር ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ጦርነትን ለማስቆም የሚደረጉ ድርድሮችን ውድቅ አደረጉ
ጄነራሉ ሁሉንም ግዛት ከRSF መልሰው እንደሚቆጣጠሩም ቃል ገብተዋል
ማክሰኞ እለት ተባብሶ በቀጠለው ግጭት የምዕራብ ኮርዶፋን ግዛት ቢያንስ 10 ሰላማዊ ሰዎች የተገደሉበት ሲሆን በብሉ ናይል ግዛት ደግሞ 5,500 ሰዎች ተፈናቅለዋል።
አል-ቡርሃን በከፊል በወታደራዊው ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይል (RSF) ቁጥጥር ስር ያሉትን እያንዳንዱን መሬት መልሰው እንደሚቆጣጠሩ ቃል ገብተዋል። እንዲሁም የሶስት ዓመት ተኩል ጦርነትን ለማስቆም የሚደረጉ ድርድሮችን ውድቅ ማድረጋቸው ነው የተሰማው።
እንዲሁም ማክሰኞ ዕለት በሰሜን ሱዳን መሮዌ አካባቢ በሚገኘው ቪሌጅ 5 በተባለ ቦታ በተደረገ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል ሲል የሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የሱዳን ሠራዊት እና የRSF አዛዦች ከፊል ወታደራዊው ኃይል ከሱዳን ሠራዊት ጋር ሊዋሃድበት በነበረው እቅድ ዙሪያ አለመግባባት ከተፈጠረ በኋላ እ.ኤ.አ ከ2023 ጀምሮ ሲዋጉ ቆይተዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በአለም አቀፍ ተቋማት ግምት መሰረት ይህ ግጭት አስር ሺዎችን የገደለ ሲሆን 13 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን አፈናቅሏል።አል-ቡርሃን ጦርነቱን መቀጠላቸውን ባስታወቁበት ወቅት በአካባቢው የበጎ አድራጎት ድርጅት እንደተገለጸው በሱዳን ምዕራብ ኮርዶፋን ግዛት በ RSF ጥቃት 10 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል። በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል።
የዳር ሃማር ድንገተኛ አደጋ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ RSF በኤን ናሁድ ምስራቃዊ ገጠራማ አካባቢዎች በሚገኘው አቡ አጃል መንደር ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተለያዩ ጥሰቶችን ፈጽሟል ሲል ከሰዋል።የሱዳን ሠራዊት በአቅራቢያው ወደምትገኘው ሰሜን ኮርዶፋን ግዛት ውስጥ ድሎችን ካስመዘገበ በኋላ RSF በምዕራብ ኮርዶፋን ኃይሉን እየሰበሰበ ይገኛል።
በሌላ በኩል በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት፣ የጸጥታውን ሁኔታ መባባስ ተከትሎ ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ ከ5,500 በላይ ሰዎች ከመንደሮቻቸው መፈናቀላቸውን አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ማክሰኞ ዕለት አስታውቋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ የሱዳን አካላት ጦርነቱን ለማስቆም በሚደረጉ ንግግሮች ላይ መሪነቱን መውሰድ እንዳለባቸው ተናግረዋል።
የአሜሪካ የዓረብ እና አፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ ሰኞ ዕለት በኤክስ ገጻቸው ላይ በሰጡት አስተያየት ሰላም ሊመጣ የሚችለው በሱዳናውያን ባለቤትነት እና መሪነት በሚካሄድ አጠቃላይ ብሔራዊ ውይይት እና ወደ ሰላማዊ መንግስት በሚደረግ ሽግግር ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።
የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ወር እንደገለጸው የሱዳን ሠራዊት ኃይሎችም ሆኑ RSF እንዲሁም የሁለቱ ወገኖች መሪዎች «ለሱዳን ህጋዊ እና ህገ-መንግስታዊ አስተዳደር ውክልና አይሰጡም»።

1 day ago
በአዲስ አበባ የ4 ዓመት ህፃን ልጅ በማታለል ሊሰርቅ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ዋለ
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ሠዓት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ቤላ 18 መናፈሻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
ተጠርጣሪ ጠጋለም መርሻ በዛ የተባለ ግለሰብ አዶናይ ግዛቸው የተባለችን የ4 ዓመት ህፃን ከዘጠኝ ዓመት እህቷ ስጦታ ግዛቸው ጋር እየተጫወተች ባለችበት ወቅት ግለሰቡ ወደ እነርሱ በመቅረብ ህፃን አዶናይን ከእህቷ በመነጠል ይዟት ይሄዳል፡፡
ህፃኗም በፍርሃትና ድንጋጤ ውስጥ ሆና ግለሰቡ እንዲለቃት ብትጠይቀውም ብስኩትና ከረሜላ እገዛልሻለሁ በሚልና በማስገደድ ከአካባቢው ይዟት ሊሰወር ሲል በወቅቱ ከስራ ወደ ቤቱ ሲመለስ በነበረ የፖሊስ አባል እጅ ከፈንጅ ሊያዝ መቻሉን በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የጉራራና አካባቢው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ በተገቢው ማስረጃ የማጣራት ተግባሩን እያከናወነ መሆኑን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ህብረተሰቡም ልጆቹ የሚውሉበትንና የሚጫወትበትን ቦታ በማረጋገጥ ጥበቃ ሊያደርግ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

አጂባደም ኸልዝኬር ግሩፕ በአዲስ አበባ አዲስ የታካሚዎች መረጃ መስጫ ቢሮ ከፈተ።
በቱርኪዬ ከጤና አገልገሎት ሰጪ ተቋማት ስመጥር የሆነው አጂባደም ኸልዝኬር ግሩፕ በአዲስ አበባ አዲስ የታካሚዎች መረጃ ቢሮ መክፈቱን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ታካሚዎች እና ቤተሰቦቻቸው በቱርክ ስለሚገኙ ልዩ የህክምና አገልግሎቶች እና የህክምና አማራጮች መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በሀገር ቤት ሆነው ከሀኪሞች ጋር በቀጥታ መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል አገልግሎት ይሰጣልም ተብላል።
ማዕከሉ፤ የታካሚዎችን ነባር የህክምና መረጃዎችን ግምገማ ከማከናወን እና ተጨማሪ የባለሙያ ምክር ከመስጠት ጀምሮ እስከ ህክምና ዕቅድ ዝግጅት፣ የጉዞ ዝግጅት ማስተባበር እና ከህክምና በኋላ የሚደረግ ክትትል ድረስ ባሉት ሂደቶች ሁሉ ለታካሚዎች ድጋፍ እንደሚሰጥ የአጂባድም ኸልዝኬር ግሩፕ የአለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት ሚስተር ኢሊያስ ቤንቬኒስቴ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
የጤና መረጃ መዓከሉ ትኩረት ከአደረገባቸው የጤና ዘርፎች ውስጥ የኒውሮሎጂ እና ኒውሮሰርጀሪ፣ የኩላሊትና ጉበት ንቅለ ተከላ ፣ የሜዲካልና ራዲዬሽን ኦንኮሎጂ ወይም ካንሰር፣ እና አይ.ቪ.ኤፍ እንዲሁም የፅንስና ማህፀን ህክምናዎች ይገኙበታል ተብሏል።
ቢሮው ለታካሚዎች አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ በኢትዮጵያና በቱርክ ሀኪሞች መካከል የልምድ ልውውጥ፣ የስልጠናና የልዩ ሙያ እድሎችን በማመቻቸት የሁለቱን ሀገራት የጤና ትብብር ያጠናክራል ሲሉ ሚስተር ኢሊያስ ጨምረው ተናግረዋል።
አጂባደም በዓለም ዙሪያ 30 ሆስፒታሎችና 15 ክሊኒኮች ያሉት ሲሆን፣ ይህ የአዲስ አበባው ማዕከል በዓለም አቀፍ ደረጃ 52ኛው የመረጃ ቢሮው መሆኑም ተገልፃል።

ሊዮኔል ሜሲ የእግር ኳስ ታሪክን ወደ አዲስ ከፍታ አሻሽሏል🐐
🔝 67 ዓለም በብሔራዊ ቡድን ጨዋታ አሲስቶች ( ይህ በታሪክ ውስጥ ከፍተኛው ነዉ)
🔝 426 አጠቃላይ አሲስቶች (ይህ በእግርኳስ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛው የአሲስት ቁጥር ነዉ)
🔝 192 የብሔራዊ ቡድን የጎል አስተዋጽዖዎች (ይህ በብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች በታሪክ ውስጥ ከፍተኛው ቁጥር ነዉ)
🔝 1 ሺህ 357 አጠቃላይ የእግርኳስ ህይወት የግብ አስተዋጽዖዎች (ይህ በእግርኳስ ታሪክ ውስጥ ከየትኛዉም ተጨዋች ከፍተኛው ነዉ)
አርጀንቲናዊያን ሜሲን እያነቡ እየሸኙት ነዉ።
የእግርኳስ ንጉሥ ነዉ ሊዮኔል ሜሲ👑

👕 208 የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች
⚽ 126 ግቦች
🅰️ 67 አሲስቶች
🌎 1 የአለምዋንጫ
🏆 2 ኮፓ አሜሪካ ዋንጫዎች
🌐 1 ፋይናሊዚማ
🐐 ሊዮኔል ሜሲ
#ዳጉ_ጆርናል
⚽ 126 ግቦች
🅰️ 67 አሲስቶች
🌎 1 የአለምዋንጫ
🏆 2 ኮፓ አሜሪካ ዋንጫዎች
🌐 1 ፋይናሊዚማ
🐐 ሊዮኔል ሜሲ
#ዳጉ_ጆርናል
1 day ago
ሊዮኔል ሜሲ በመጨረሻ የብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታ በፍጹም ቅጣት ምት ግብ አስቆጥሯል። አርጀንቲና ቤኒንን 3 ለ 0 እየመራች ሲሆን ሜሲ ከግቡ በተጨማሪ ሁለተን ግቦች አመቻችቶ አቀብሏል።
ፍጹም ያማረ ፍጻሜ
#ዳጉ_ጆርናል
ፍጹም ያማረ ፍጻሜ
#ዳጉ_ጆርናል
Sponsored by
Surafel
1 day ago
የሊዮኔል ሜሲ የሽኝት ጨዋታን ለመታደም ከፈረንሳይ ቦነስአይረስ የደረሰዉ ደጋፊ ሲጠየቅ
"እኔ ከፈረንሳይ ነዉ የመጣሁት። ሜሲ እንደ አባቴ ነዉ" ብሏል።
የሜሲ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ የመሸኛ ጨዋታ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በኤስታዲዮ ሞኑሜንታል ከቤኒን ጋር ይጀመራል።
የሜሲ ዉብ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የእግርኳስ ታሪክ ምዕራፍ ዛሬ ባማረ መልኩ ይዘጋል።

2 days ago
ያለ ፈቃዷ ከወሲብ ንግድ ሰራተኛዋ ላይ ኮንዶም ያወለቀው ግለሰብ በ5 ዓመት እስራት ተቀጣ
በእንግሊዝ የግለሰቧን ፈቃድ ሳይጠይቅ በወሲብ ወቅት ኮንዶም ያወለቀ አንድ ሰው የወሲብ ሰራተኛን በመድፈር ለአምስት ዓመታት ተቀጥቷል። የ46 ዓመቱ አይሰን ቪር ራጋኒት፣ የዌስትዉድ ሮድ፣ ስቶክፖርት ነዋሪ፣ በነሐሴ ወር በዮርክ ክራውን ፍርድ ቤት በችሎት ከቀረበ በኋላ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
ዛሬ ማክሰኞ ዕለት ዳኛ ሲን ሞሪስ ጥፋቱን የፈጸመው የተጎጂውን ፈቃድ በግልጽ መጣስን እንደሆነ ዳጉ ጆርናል ከዘገባዎች ተመማክቷል። ራጋኒት በጥፋተኝነት ውሳኔው ምክንያት በወሲብ ወንጀለኞች መዝገብ ላይ ላልተወሰነ ጊዜ ተፈርዶበታል። የሰሜን ዮርክሻየር ፖሊስ ራጋኒት በጥቅምት 2024 በሰሜን ዮርክሻየር በሚገኘው ቤቷ ውስጥ ተጎጂውን ለማግኘት በኦንላይን ቦታ ማስያዝ በኩል ተገናኝተዋል።
ከስራዋ ጋር በተያያዘ ስሟን የመደበቅ መብቷን የተጠቀመችው ተጎጂዋ "በድረገጿ ላይም ሆነ ከግንኙነቷ በፊት ደንበኞች ኮንዶም መጠቀም እንዳለባቸው ግልጽ አድርጋለች።ይሁን እንጂ፣ በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ወቅት ራጋኒት እሷ ሳታውቅ ወይም ፈቃድ ሳትሰጥ ሆን ብሎ ኮንዶሙን አውልቆ ግንኙነቱን ቀጥሏል።
ሴትየዋ ወዲያውኑ ተቃውሞዋን ገልጻለት እንዲሄድ ከነገረችው በኋላ፣ ጉዳዩን ለፖሊስ አሳወቀች። የፖሊስ ቃል አቀባይ እንደገለጹት፣ ፖሊሶች በኋላ ላይ በራጋኒት ሞባይል ስልክ ውስጥ፣ በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ወቅት ያለአጋር ፈቃድ ኮንዶም ስለማስወገድ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ጨምሮ የተለያዩ መረጃዎችን አግኝቷል።
አጣሪዎች እንደገለጹት፣ ወንጀሉ ከመፈጸሙ ጥቂት ቀደም ብሎ አንዳንድ ቪዲዮዎች በዚህ ዙሪያ ተመልክቶ ነበር። ራጋኒት ክሱን የካደ ሲሆን፣ በደፈራ ወንጀል ክስ ላይም ጥፋተኛ አለመሆኑን ተናግሯል፤ ሆኖም የዳኞች ቡድን በአንድ ድምፅ ጥፋተኛ መሆኑን ወስነዋል። ተጎጂዋ በሰጠችው የግል መግለጫ ላይ "ክስተቱ ከተፈጸመ በኋላ፣ መጀመሪያ ላይ አዳዲስ ደንበኞችን ለማግኘት እጅግ በጣም ተረብሼና ተጨንቄ ነበር።" ስትል ተደምጣለች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በሱዳን ሰላማዊ ሰዎች ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶችን አወገዘ
ምክር ቤቱ በሱዳን ሰላማዊ ሰዎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የድሮን እና ሌሎች ጥቃቶችን በማውገዝ በሀገሪቱ ላለው ቀውስ “ምንም ዓይነት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ” አስጠንቅቋል።
መግለጫው የወጣው የዓለም የምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኮርዶፋን የምግብ አቅርቦት ጭኖ በነበረ የጭነት መኪና ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ባስታወቀበት ወቅት ነው።
በጄኔቫ በተካሄደው ስብሰባ 47 አባላት ያሉት ምክር ቤቱ ለሱዳን ያዋቀረውን ገለልተኛ ዓለም አቀፍ የእውነታ አጣሪ ተልዕኮ የስራ ጊዜ ለማራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በ28 የድጋፍ እና በ10 የተቃውሞ ድምጽ አጽድቋል።
ሱዳን ምክር ቤቱ ያቀረበችውን ቅሬታ ከግምት ውስጥ ማስገባት አለመቻሉን በመግለጽ አባል ሀገራቱ ይህን እርምጃ ውድቅ እንዲያደርጉት አሳስባለች።እ.ኤ.አ በሚያዝያ 2023 በሱዳን ጦር እና በከፊል-ወታደራዊው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የተጀመረው ጦርነት የአስር ሺዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ከ13 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ደግሞ አፈናቅሏል።
የተመድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዚህ ዓመት የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ውስጥ ብቻ በድሮን ጥቃቶች ከ1,100 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

በፌርፎርድ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ለማድረስ አቅዶ የነበረ የ22 ዓመት እንግሊዛዊ በዩኬ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለ
የእንግሊዝ ፖሊስ ማክሰኞ ዕለት እንደገለጸው፤ አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር በሚያገለግለው የራፍ ፌርፎርድ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር አካባቢ የታሰበውን የሽብር ጥቃት ዝግጅት ተሳትፎበታል በሚል ጥርጣሬ አንድ የ22 ዓመት እንግሊዛዊ በለንደን በቁጥጥር ስር ውሏል።
የብሪታንያ ፖሊስ እንዳስታወቀው፣ ግለሰቡ በለንደን የተያዘው አሜሪካ፣ በኢራን ላይ ጥቃት ለማድረስ የምትጠቀምበትን የራፍ ፌርፎርድ አየር ኃይል ጦር ሰፈርን ለማጥቃት የታቀደውን ሴራ በተመለከተ እየተካሄደ ባለው ምርመራ አካል እንደሆነ ተናግሯል።
የፀረ-ሽብርተኝነት ፖሊስ ክፍሉ ግለሰቡ በዌስትሚኒስተር አካባቢ መያዙንና ፖሊሶች በዚያው አካባቢ የሚገኝን አንድ መኖሪያ ቤት መበርበራቸውን ገልጿል። ተጠርጣሪው በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር ይገኛል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የተያያዘ ስጋት በመኖሩ ምክንያት አሜሪካ B-1 ቦምብ ጣይ ጄቶቿን ከጦር ሰፈሩ እንድታወጣ አድርጓል ካሉ በኋላ ይህ እስራት የአለም አቀፍ ትኩረትን የሳበው ምርመራ የቅርብ ጊዜ እርምጃ ነው።
ኢራን በተሰነዘረባት ክስ ላይ ምንም አይነት እጅ እንደሌላት አስተባብላለች።

በኦሮሚያ ክልል በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት የሚያገኙ እናቶች ቁጥር መጨመሩ ተገለፀ
ቀደም ባሉት ዓመታት 60 በመቶ የሚሆኑ እናቶች በሰለጠኑ ባለሙያዎች አማካኝነት በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት ያገኙ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 80 በመቶ እናቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸዉን የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል ።
ይህም በወሊድ ወቅት በሚከሰት የደም መፍሰስ ምከኒያት የሚከሰት ሞት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ አስተዋጽኦ ማድረጉን የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረጀ አብደና ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል ።
በክልሉ በ2018 በጀት ዓመት በወሊድ ወቅት ከሚከሰት የደም መፍሰስ ጋር በተያያዘ 13 እናቶች ህይወታቸዉን ማጣታቸዉን ያስታወሱት ምክትል ኃላፊዉ ይህም ሊሆን የቻለዉ በፀጥታ ችግር እና በተለያዩ መንስኤዎች መሆኑን አስረድተዋል።
በዚህም የተነሳ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም ባለመምጣታቸዉ ለህልፈት መዳረጋቸውን ገልፀው ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀርም ቁጥሩ እየቀነሰ መምጣቱን ጠቅሰዋል።
ከወሊድ አገልግሎት ጋር በተያያዘ የሪፈራል ስርዓት በመጠናከሩ እና በጤና ተቋማት ኢኒሼቲቮች ተግባራዊ መደረጋቸው የእናቶች ሞት እንዲቀንስ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተነግሯል ።

በኦንላይን ለሚፈፀሙ የህፃናት ጥቃቶች በመሪነት የተጠረጠረው ህንዳዊ ግለሰብ ፍርድ ቤት ቀረበ
የአካል ብቃት አሰልጣኝ ከመሆኑ አስቀድሞ ለትምህርት ወደ ፈረንሳይ ያቀናው ህንዳዊው ሮሃን ራኔ በህፃናት ላይ አስቃቂ ድርጊት እና ስቃይ ፈፅሟል በሚል ክስ ሰኞ ዕለት ፓሪስ ውስጥ በሚገኝ ፍርድ ቤት ቀርቧል።
መርማሪዎች እንደሚሉት ግለሰቡ በዲስኮርድ የመልእክት መለዋወጫ መድረክ አማካኝነት ይሰራ የነበረ የኒዮ-ናዚ የህፃናት ብዝበዛ መረብ መሪ ነው። ሴቶች ልጆችን በኦንላይን አማካኝነት የወሲብ ድርጊቶችን እንዲፈፅሙ እና በራሳቸው አካል ላይ ጉዳት እንዲያደርሱ ያስገድድ ነበር የተባለው ይህ ህንዳዊ በዝግ ችሎት ክሱ መታየት ጀምሯል።
ቡድኑ አሜሪካ፣ ኔዘርላንድ፣ ብሪታንያ እና ኢስቶኒያን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት የሚገኙ ህፃናትን ለአካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ዳርጓል ተብሎ ይታመናል።
እንደ መርማሪዎች ገለፃ የጥቃቱ አድራሾች ከጀርመን፣ ኒውዚላንድ እና አሜሪካ የመጡ ወንዶች ናቸው። እንዲሁም ቡድኑ የዘረኝነት እና የአይሁድ ጠልነት አመለካከቶችን የሚያስፋፋ እንደነበር ተገልጿል።
በደቡብ ምስራቅ ፈረንሳይ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ለመማር መጥቶ በኋላ ላይ የአካል ብቃት አሰልጣኝ የሆነው የ29 ዓመቱ ህንዳዊ ሮሃን ራኔ በቡድኑ መርማሪዎች ዘንድ የቡድኑ ዋነኛ መሪ ተደርጎ ተገልጿል። እ.ኤ.አ በ2021 በቁጥጥር ስር የዋለው ተከሳሹ ነጭ ቲሸርት ለብሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል።
ግለሰቡ በህፃናት ላይ አስቃቂ ድርጊት በመፈጸም፣ በቡድን የተደራጀ የገንዘብ ዝርፊያ እና የህፃናት የወሲብ ምስሎች እና ቪዲዮዎችን ማሰራጨት በሚሉ ክሶች እየተዳኘ ይገኛል። ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘም እስከ እድሜ ልክ እስራት ሊቀጣ ይችላል ነው የተባለው።

ኬንያ የመጀመሪያው የኢቦላ በሽታ በሀገሯ መገኘቱን ማረጋገጫ ሰጠች
👉ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መነሻውን አድርጎ የተጓዘው ታካሚም በናይሮቢ ህይወቱ አልፏል
ኬኒያ የመጀመሪያውን የኢቦላ ቫይረስ ተጠቂ ማረጋገጧን የጤና ሚኒስትሩ አደን ዱዋሌ አስታውቀዋል። ህይወቱ ያለፈው ኬኒያዊ ዜጋ ላለፉት ሰባት ዓመታት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኑሮውን ያደረገ ሲሆን፣ ወደ ኬኒያ ከመመለሱ ከአንድ ወር አስቀድሞ በህመም ተይዞ ነበር።
ታካሚው በጤና ተቋማት ህክምናን ከተከታተለ በኋላ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ጎረቤት ሀገር ኡጋንዳ ተጉዟል። ከዚያም ከኡጋንዳ በጃምቦጀት አውሮፕላን ተሳፍሮ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 3 ቀን ከቀኑ 7 ሰአት ከ10 ደቂቃ ላይ ናይሮቢ ከሚገኘው ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሷል።
በአውሮፕላን ማረፊያው የተለመደውን የህዝብ ጤና ምርመራ ካደረገ በኋላ፣ ዘመድ አዝማዶቹ እና ጓደኞቹ በቀጥታ ከኤርፖርት ወደ ናይሮቢ ሆስፒታል ወስደውት ወዲያውኑ በለይቶ ማቆያ እንዲገባ የተደረገ ሲሆን በሆስፒታል ቆይታው በ‘ቡንዲቡግዮ የኢቦላ ዝርያ መያዙ ተረጋግጦ ህይወቱ አልፏል።
የጤና ባለስልጣናት ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ ለመከላከል ፈጣን እርምጃዎችን የወሰዱ ሲሆን ከሟቹ ጋር ንክኪ ነበራቸው የተባሉ የቤተሰብ አባላትና የጤና ሰራተኞችን ጨምሮ 28 ግለሰቦችን ለይተዋል።በኮንጎ፣ በኡጋንዳ እና በናይሮቢ የተደረገው የታካሚው የአውሮፕላን በረራ እንዲሁም ከቤተሰብ እና ከህክምና ባለሙያዎች ጋር የነበረው ንክኪ አሁን ላይ በመንግስት የክትትል ሰንሰለት ውስጥ ተካቷል።
ኢቦላ በበሽታው ከተያዘ ሰው ሰውነት ውስጥ ከሚወጡ ፈሳሾች ወይም በበሽታው ከተበከሉ ነገሮች ጋር ቀጥተኛ ንክኪ በሚፈጠርበት ወቅት የሚተላለፍ አደገኛ በሽታ በመሆኑ የጤና ባለስልጣናት የኢቦላን ስርጭት ለመቆጣጠር የተለዩትን ግለሰቦች በቅርበት እየተከታተሉ ይገኛሉ።
ትግስት ላቀው

ዘመን ባንክ 10 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።
ባንኩ የአንድ አክሲዮን ትርፍ ድርሻ 53.9 በመቶ መድረሱን አስታውቋል።
ዛሬ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ስብሰባ ላይ እንዳስታወቀው፣ ከተመዘገበው ከታክስ በፊት ትርፍ ውስጥ 6.75 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘት ችሏል።
የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ እንዬ ቢምር ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ የባንኩ አጠቃላይ ገቢ 17ነጥብ9 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ አጠቃላይ ሀብቱም በ31ነጥብ3 በመቶ በማደግ 116 ቢሊዮን ብር ደርሷል።
2018 በጀት ዓመት ለዘመን ባንክ ጠንካራ የፋይናንስ አፈጻጸምና ቀጣይነት ያለው እድገት የተመዘገበበት ዓመት ነበር ያሉ ሲሆን የተመዘገበው ውጤት የባንኩን ጠንካራ የሥራ አፈፃፀም፣ የደንበኞችና ባለአክሲዮኖችን እምነት እንዲሁም የሠራተኞችን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ገልጸው፤ በቀጣይም በፈጠራና በደንበኛ ተኮር አገልግሎቶች እድገቱን ለማስቀጠል እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ዘበነ በበኩላቸው፣ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 14ነጥብ3 ቢሊዮን ብር፣ ጠቅላላ ካፒታሉ ደግሞ ወደ 26 ቢሊዮን ብር ከፍ ማለቱን ጠቁመዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለተገኘው ስኬት ለሠራተኞች፣ ለደንበኞችና ለአጋሮች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
በዘርፉ ቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያዎች ሲገመገም የዘመን ባንክ የፋይናንስ ውጤት በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከሚታዩ ጠንካራ አፈጻጸሞች መካከል አንዱ እንደሆነ ተመልክቷል።

በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት መኖሪያ ቤት ከ6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ጌጣጌጦችን የሰረቀች ግለሰብ ከነ አባሪዎቿ በቁጥጥር ስር ዋለች
ኢየሩሳሌም በርገኔና አማኑኤል ማቲዮስ የተባሉ ተጠርጣሪዎች አባሪና ተባባሪ በመሆን የስርቆት ወንጀሉን የፈፀሙት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ዲቦራ ፋውንዴሽን ተብሎ ከሚጠራባት ከጠዋቱ 3 ሠዓት አካባቢ ነው ።
ተጠርጣሪዋ ለ 1 ዓመት ከ5 ወር ያህል የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ስትሰራ የነበረች ሲሆን በቤት ውስጥ የነበሩት የእጅ የወርቅ ሰዓት የዋጋ ግምቱ 4 ሚሊዮን 74ሺ 250 ብር፣ 2 የዳይመንድ የእጅ ሰዓት የዋጋ ግምታቸው 2ሚሊየን 149ሺ 600 ብር፣ 1 የጆሮ ጌጥ የወርቅ ያልተመለሰ ግምቱ 126 ሺህ እንዲሁም የተለያዩ ጌጣጌጦች የዋጋ ግምታቸው 5ሺህ ብር፣ 2 የወርቅ ቅብ የእጅ ሰዓት ግምታቸው 3 መቶ 88 ሺህ እና ሌሎች የተለያዩ የዋጋ ግምት ያላቸውን ጌጣጌጦችን ምቹ ሁኔታን በመጠቀም ሰርቃ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ለሚኖር የወንድ ጓደኛዋ ጋር በአደራ ታስቀምጣለች።
የግል ተበዳይም መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም ወደ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ላንቻ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ በመቅረብ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡
የግል ተበዳይን ጥቆማ መሠረት በማድረግ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ሊያውልም ችሏል፡፡ የተጠርጣሪዋ ፍቅረኛ የሆነው አማኑኤል ማትዮስ ከ 4ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣውን 1 የእጅ የወርቅ ሰዓት በ540ሺ ብር አብዱልአፊዝ ነጂብንም ለተባለ ግለሰብ የሸጠ ሲሆን ፖሊስ ገዢውንም በቁጥጥር ስር አውሏል።
ሦስቱንም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር በማዋል ንብረቶቹን ለባለቤቱ ያስመለሰው ፖሊስ አስፈላጊውን ማስረጃ በመሰብሰብ ምርመራው በተገቢው መልኩ ቀጥሏል፡፡
ፖሊስ በክፍሉ ዓቃቤ ህግ በኩል ክስ ለመመሰረት ዝግጅት ላይ ሲሆን ያልተመለሱ ንብረቶችን ለማስመለስም ምርመራ የማስፋት ተግባራት መቀጠላቸውን የላንቻ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ጌታደጉ ወርቁ ተናግረዋል፡፡
ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኛን ሲቀጥር በቂ ተያዥ መኖሩን ማረጋገጥ እንዳለበት ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ውድ ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ላይ በቂ ጥንቃቄና ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበትም መልዕክቱን አስተላልፏል።

ከመካከለኛው ምስራቅ የሚላከው የጥሬ ነዳጅ መጠን በመጨመሩ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ቀነሰ
ከመካከለኛው ምስራቅ የሚላከው የጥሬ ነዳጅ መጠን አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት ከመክፈታቸው በፊት ከነበረበት ደረጃ በላይ መጨመሩን የሚያሳዩ ዘገባዎችን ተከትሎ፣ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ ማሳየቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
የብሬንት ጥሬ ነዳጅ የ1 በመቶ ቅናሽ በማሳየት በበርሜል 101.18 ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ደግሞ የአሜሪካው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዲየት ጥሬ ነዳጅ ዋጋ የ1.03 በመቶ ቅናሽ በማሳየት በበርሜል 90.12 ዶላር ሆኖ ነበር።
ቀደም ሲል እንደተዘገበው፣ ከቀጠናው የሚወጣው የጥሬ ነዳጅ ኤክስፖርት መጠን በሴፕቴምበር 24 እንዲሁም በሴፕቴምበር 27 እና 29 መካከል ከጦርነቱ በፊት ከነበረው መጠን በልጦ ተገኝቷል።ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የጂ 7 ሀገራት ከድንገተኛ አደጋ ተጠባባቂ ቋታቸው 100 ሚሊዮን በርሜል ጥሬ ነዳጅ እና ዲዜል ለገበያ ለማቅረብ ተስማምተዋል።
የ KCM Trade ዋና ተነታኝ ቲም ዋተረር ለሮይተርስ እንደተናገሩት፣ “በባህረ ሰላጤው ቀጠና በሚገኙ የኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ተጨማሪ ጉዳት የመድረሱ ስጋት እስካሁን ያልተወገደ ቢሆንም፣ የሁለቱ ሁኔታዎች መጣመር የነዳጅ ዋጋን ለጊዜው ለማረጋጋት በቂ ነው” ብለዋል።

3 days ago
የእስራኤል ተጫዋቾች ከአየርላንድ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች አንዱ ላይ ምራቃቸውን ተፍተዋል ተባለ
ትላንት አየርላንድ እና እስራኤል በሁለተኛው የዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ የመልስ ጨዋታቸው ላይ ዳግም ውጥረት የታየ ሲሆን፣ ይህም ልክ እንደ እግር ኳሱ ሁሉ በፖለቲካዊ ውጥረቶች የተሞላውን የሁለት ሳምንታት ጊዜ አጠናቋል።
ከአንድ ሳምንት በፊት በሃንጋሪ በዝግ ስታዲየም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ አየርላንድ እስራኤልን 3 ለ 0 ከማሸነፏ በፊት፣ አንዳንድ የአየርላንድ ደጋፊዎች እና ፖለቲከኞች ቡድኑ ከእስራኤል ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ እንዲሰርዝ ጥሪ አቅርበው ነበር።
የአየርላንዱ አሰልጣኝ ሄይሚር ሃልግሪምሰን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ "ከእስራኤል ጋር ያደረግነውን ጨዋታ በመጨረሳችን እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ" ብለዋል።"ሁላችንንም አድክሞናል። ለተጫዋቾቹ ትልቅ ክብር እሰጣለሁ። በነበሩት ፈታኝ ጊዜያት እጅግ አስገራሚ ነበሩ፤ እንዲሁም ባለፉት ሁለት ሳምንታት እኛ ያለፍንበትን ፈተና ሌላ ማንኛውም ብሄራዊ ቡድን እንዲያልፍበት አልመኝም" ብለዋል።
አየርላንድ፣ እስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደውን የዘር ማጥፋት ጦርነት አጥብቀው ከሚተቹ የአውሮፓ ሀገራት አንዷ ስትሆን፤ የአየርላንድ እግር ኳስ ማህበር ከጨዋታዎቹ ራሱን እንዲያገል ይደረግበት በነበረው ጫና ምክንያት፣ የእሁዱን ጨዋታ በሰርቢያ በዝግ ስታዲየም ለማካሄድ መርጧል።የአየርላንድ ብዙሃን መገናኛዎች እንደዘገቡት፣ ከአየርላንድ አሰልጣኞች አንዱ የሆኑት ዳሚየን ዶይል በእረፍት ሰዓት አንድ የእስራኤል ተጫዋች ምራቅ ተፍቶብኛል ሲሉ ከሰዋል።
ከጨዋታው በኋላ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለ ምራቅ መትፋት ክስተቱ ጥያቄ የቀረበላቸው የአየርላንዱ አሰልጣኝ ፣ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።ለጋዜጠኞች ሲመልሱም፣ "እዛው ነበርኩ። ምንም አይነት አስተያየት አልሰጥም። የዲሲፕሊን ኮሚቴ የሚመለከተው ጉዳይ ነው" ብለዋል።የእስራኤሉ አሰልጣኝ በበኩላቸው፣ ከሜዳው ዳርቻ ቀድመው ወጥተው ስለነበር የተፈጠረውን ነገር እንዳላዩ ተናግረዋል።

ሀሰተኛ ሰነድ እያዘጋጀ ሲሸጥ የነበረ ተጠርጣሪን ከነ አባሪው በቁጥጥር ስር ዋለ
ተጠርጣሪ ኢብሳ ቶሎሳ ከአባሪው ገለታ ሞቲ ጋር የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶች በማዘጋጀት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ አደባባይ አካባቢ ነው፡፡
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የጎሮ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት እና ከፌደራል ፖሊስ ኢንትሊጀንስ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ክትትል ኢብሳ ቶሎሳ ከአባሪው ገለታ ሞቲ ጋር በመሆን የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ይዘው ለሌላ ግለሰብ ለመሸጥ በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ ከነ ሰነዶቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ተጠርጣሪዎች ከተያዙ በዋላ ፖሊስ የፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ቂሊንጦ አካባቢ በሚገኘው የተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት በተደረገ ብርበራ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች፣ የተለያዩ ተቋማት ሀሰተኛ ሰነዶች፣ የተለያዩ መታወቂያዎች፣ 30 ክብ እና 5 የራስጌ ማህተሞች እንዲሁም 20 ቲተሮች የተገኙ በመሆኑ የምርመራ መዝገብ በማደራጀት ለአቃቤ ህግ በማቅረብ ጉዳያቸው በምርመራ ሂደት ላይ እንደሚገኝ የጎሮ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

በአዲስ አበባ 102 ጤና ጣቢያዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል ተባለ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የእናቶች፣ ሕፃናትና አፍላ ወጣቶች ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ስንዱ መኩሪያ እንደገለጹት በአዲስ አበባ 102 የሕዝብ ጤና ጣቢያዎችና 13 ትላልቅ ሆስፒታሎች ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። በተጨማሪም የግል ጤና ተቋማትም ይህንኑ አገልግሎት በጋራ እና በመመሪያው መስፈርት መሠረት እንዲሰጡ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ አገልግሎቱ የሚሰጠው የሕግ እና የጤና መመሪያዎችን መሠረት በማድረግ እና አስፈላጊ መስፈርቶችን ላሟሉ እናቶች ብቻ መሆኑን አብራርተዋል ። የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት ከተሰጠ በኋላም ተደጋጋሚ ያልታቀደ እርግዝና እንዳይከሰት የቤተሰብ እቅድ ምክርና አገልግሎት አብሮ ይሰጣል ብለዋል።
በ2017 ዓ.ም ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት አፈፃፀም 98.6 በመቶ የነበረ ቢሆንም በ2018 ዓ.ም ላይ ደግሞ ወደ 96 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተመልክቷል ። ለዚህም የመድኃኒትና የግብዓት አቅርቦት እጥረት በምክኒያትነት የተጠቀሰ ሲሆን ችግሩን ለመቅረፍ ከጤና ሚኒስቴርና ከመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር አቅርቦቱን የማስተካከል ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሯ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ያልታቀዱ እርግዝናዎችን ከመሠረቱ ለመከላከል በትምህርት ቤቶችና ወጣቶች በሚበዙባቸው ቦታዎች ላይ ያተኮሩ የእናቶች፣ የአፍላ ወጣቶች እና የቤተሰብ እቅድ ግንዛቤ ማሳደጊያ ፕሮግራሞች በጤና ባለሙያዎች አማካኝነት እየተሰጡ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በሰመሀር አለባቸው

አንቶኒዮ ኮንቴ ቀጣይ ሊይዙት ስለሚችሉት ክለብ ተጠይቀዉ...
"በርከት ያሉ ክለቦች አሉ ቀድሞ በነበራቸው የታሪክ ከፍታ ላይ የማይገኙ። ወደእነዛ ክለቦች ሄጄ አዋራ የሸፈነዉ ታሪካቸዉን አራግፌ እንደገና እንዲያንጸባርቁ ብረዳ እመኛለሁ" ብለዋል።
ምናልባት ስለ ማንችስተር ዩናይትድ እያወሩ ይሆናል የሚለዉ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ጥያቄ አጭሯል።

Comments