Logo
Getu Temesgen
የስማርት መብራት ቴክኖሎጂ ማሳያ ማዕከል ተከፈተ
‎
‎#ethiopia | የኤሌክትሪክ መብራት ቴክኖሎጂ ከተለመደው ብርሃን አቅርቦት ባለፈ በስልክ መቆጣጠር፣ የኃይል አጠቃቀምን ማሻሻልና ለተለያዩ የአጠቃቀም ፍላጎቶች መላመድ ወደሚችልበት ዘመን እየተሸጋገረ መሆኑ ተገለጸ።
‎
‎ይህንን የቴክኖሎጂ ለውጥ ከኢትዮጵያውያን ሸማቾችና የግንባታ ዘርፍ ባለሙያዎች ጋር ለማቀራረብ፣ ሲግኒፋይ ከአካባቢያዊ አጋሩ ብሉ ስፓርክ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ የፊሊፕስ ስማርት ላይት ማሳያ ማዕከል ከፍቷል።
‎
‎ማዕከሉ የተለያዩ የመብራት ቴክኖሎጂዎችን በተጨባጭ ለመመልከትና ለመሞከር የሚያስችል ሲሆን፣ ጎብኚዎች የብርሃን መጠንን መቆጣጠር፣ ቀለሙን መቀየርና ለጥናት፣ ለእረፍት ወይም ለሌሎች ተግባራት የሚስማሙ የብርሃን አቀማመጦችን ማዘጋጀት እንደሚቻል ማዕከሉ በተከፈተበት መርሐግብር ላይ ተገልጿል።
‎
‎በማዕከሉ የሚታዩት የኤልኢዲ እና ዘመናዊ የመብራት መፍትሔዎች የብርሃን ጥራትንና የኃይል አጠቃቀምን በአንድ ላይ ለማየት ዕድል ይፈጥራሉ። ይህም ለቤት ባለቤቶች፣ ለአርክቴክቶች፣ ለዲዛይነሮችና ለሕንጻ ተቋራጮች ከግዢ በፊት የተለያዩ አማራጮችን እንዲያወዳድሩና ለፍላጎታቸው የሚስማማውን እንዲመርጡ ያግዛል ተብሏል።
‎
‎በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት የኔዘርላንድ መንግሥት በኢትዮጵያ ምክትል አምባሳደር ፓውላ ሽንደለርን ጨምሮ የንግድ አጋሮች፣ ነጋዴዎች፣ የሕንጻ ንድፍ ባለሙያዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
‎
‎የማዕከሉ መከፈት በኢትዮጵያ የዘመናዊ መብራት ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማስፋፋትና ሸማቾች የተለያዩ የብርሃን መፍትሔዎችን በተግባር እንዲያውቁ ለማስቻል የታለመ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
‎
‎#ethiopia #addisababa #philipslighting #smartlighting #lightingtechnology #ledlighting #energyefficiency #innovation #technology #signify #bluespark #smarthome
‎

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.