ካርታ በእርሳስ አይሳልም-ኤርትራ‼️
የኤርትራ አዲስ መግለጫ የኤርትራ ህዝብ ያካሄደው ትግል ነፃነትን ለማስመለስ የተደረገና የኢትዮጵያን ወረራ ለመቀልበስ የተከናወነ መሆኑን አውስቶ ‹‹በዚህ መራራና ረጅም የትግል ጉዞ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ የሞራልና ሌሎችም ድጋፎች ማግኘቱ የሚካድ አይደለም›› ብሏል፡፡ ጨምሮም ‹‹አሁን የሚሰማው የታሪክ ማዛባት ጫጫታ ግን ሊበሏት ያሰቧትን ጥንቸል ጅግራ ይሏታል እንደማለት ነው›› ያለው መግለጫው ‹‹የአለም ካርታ በተረት ተረት፣ ከአቅም በላይ በመመኘት፣ የቀይ ባህር መስኮት በመፈለግና ለጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በመቅረብ›› የማይለወጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በማጠቃለያውም ‹‹የአለም ካርታ በእርሳስ የሚሳል ሳይሆን በአለም አቀፍ ህግና ስምምነቶች የሚገዛ የሉአላዊነትና የግዛት አንድነት ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህም የኤርትራ ሉአላዊነት በደምና በህግ የተረጋገጠና የተገደበ ነው፡፡ እሱን የሚነካም ወዮለት፡፡ አራት ነጥብ›› ብሏል፡፡
ኤርትራ ‹‹ኢትዮጵያን የባህር በር ለማሳጣት በተደረገ ሴራ የተፈጠረች አገር›› ናት የሚለው ፍራጃ ተቀባይነት የለውም ብሏል።
Seledadotio

1 day ago