የትውልድ ቅብብሎሽ፡ የቀደምት አባቶቹን አርበኝነት ከዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ አዋህዶ የተገነባው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
**********************
ኢትዮጵያ የውጭ ወረራዎችን እና የውስጥ ተግዳሮቶችን ጨምሮ በርካታ ፈተናዎችን አልፋ ለዛሬው ቁመናዋ የበቃችው በልጆቿ የማይበገር የሀገር ፍቅር፣ የጽናትና የመስዋዕትነት እሴት ነው።
ይህ ከትውልድ፣ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣው የአልበገር ባይነት መንፈስ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ድል ከአሁኑ ዘመናዊና ኃያል የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጋር የሚያያይዝ የማይበጠስ ጠንካራ ገመድ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥንካሬና አይበገሬነት በድንገት የተገነባ ሳይሆን፣ በሺዎች ዓመታት የሚቆጠሩ ዘመናትን ከተሻገረ የታሪክ ማህደር ውስጥ የተቀዳ ቱባ እሴት ነው።
በዓድዋ ተራሮች ላይ በጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ደማቁን ምዕራፍ የጻፉት አባቶቻችን በዘመናዊ መሣሪያ የተደራጀውን ወራሪ ኃይል በሀገር ፍቅርና አልደፈርም ባይነት ያሸነፉበት መንፈስ በካራማራ እንዲሁም በተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይም ሲንጸባረቅ ቆይቷል።
ይህ ታሪካዊ የትውልድ ቅብብሎሽ የሚያሳየው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የውጊያ ስንቅና ዋነኛ የድል ምስጢር ከቴክኖሎጂና ከቁሳዊ ዝግጅት በላይ በደሙ ውስጥ የሚዘዋወረው የማይበገር የሀገር ፍቅር ወኔና የመንፈስ ጽናት መሆኑን ነው።
ቀደምት አባቶች የሀገርን ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር ሳያስደፍሩ ጠብቀው ያስረከቡትን አደራ፣ የዛሬው ትውልድ ሠራዊት አቅሙን በዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ፣ በስልጠናና በቴክኖሎጂ በማበልጸግ አደራውን በላቀ ብቃት በመወጣት ላይ ይገኛል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የትናንቷ ኢትዮጵያ ታሪክና አደራ ጠባቂ ብቻ ሳይሆን ለነገይቱ ኢትዮጵያ ሰላም፣ ልማትና ሕልውናም ዋስትና ሆኖ ቆሟል።
ሠራዊቱ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ክብር ከማንኛውም ውስጣዊና ውጫዊ ስጋት የመጠበቅ ተልዕኮውን በከፍተኛ ዲስፕሊንና ጽናት እየተወጣ ይገኛል።
የሠራዊቱ ዋነኛ የኃይል ምንጭ ከራሱ ከሕዝቡ የወረሰው ሕዝባዊ ባህሪው ነው። አባላቱ ለሀገር ሉዓላዊነትና ለሕዝብ ደህንነት ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን አሳልፈው ለመስጠት ያላቸው ዝግጁነት መከላከያ ሠራዊቱ በሕዝባዊና ሀገራዊ ፍቅር ጽኑ መሠረት ላይ የታነጸ መሆኑን ያረጋግጣል።
የመከላከያ ሠራዊቱ የአይበገሬነት ምስጢር ትናንት ከዓድዋ፣ ከካራማራና ከተለያዩ ገድሎች የወረሰውን የቀደምት አባቶች የሀገር ፍቅርና የጀግንነት እሴት ከዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ፣ ከቴክኖሎጂ የበላይነትና ከስትራቴጂያዊ አደረጃጀት ጋር አዋህዶ መገንባቱ ነው።
በሃና ምንዳሁን
#ethiopia #ethiopiandefenseforces #ethiopianpatriotism #heroiclegacy #adwavictory #ebc

17 hours ago