አድማስ ዩኒቨርሲቲ 18ኛውን ዓመታዊ የምርምር ጉባኤ አካሄደ!
#ethiopia አድማስ ዩኒቨርሲቲ "በምስራቅ አፍሪካ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዋና ዋና ተልዕኮዎች ስኬቶች ተጋጣሚዎች እና እድሎች፡ የጥራት ትምህርት አሰጣጥ፣ ተዛማጅ ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት" በሚል መሪ ቃል 18ኛውን ዓመታዊ የምርምር ጉባኤውን በዛሬው እለት አካሂዷል።
በጉባኤው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሞላ ፀጋይ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ጥራት ያለው ከፍተኛ ትምህርት፣ ችግር ፈቺ ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ለአንድ ሀገር እድገትና ለስርዓተ ትምህርት መሻሻል ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አድማስ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ድረስ 17 ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤዎችን፣ 7 የተማሪዎች የምርምር ሲምፖዚየሞችን እና በርካታ አካዳሚያዊ ውይይቶችን ማዘጋጀቱን አብራርተዋል።
በተጨማሪም አዳዲስ የምርምር ውጤቶችን ለማውጣትና ለማህበረሰቡ ለማድረስ ዩኒቨርሲቲው በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር በጀት መድቦ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በጉባኤው ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ተመራማሪዎች፣ አወያዮች እና ጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢዎች ተገኝተዋል::
ይህ ጉባኤ በተሳታፊዎች መካከል የእውቀትና ልምድ ልውውጥ የሚደረግበትና ውጤታማ ውይይት የሚካሄድበት መድረክ እንደሚሆን ታምኖበታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen

14 hours ago