ንስር ማይክሮፋይናንስ በበጀት ዓመቱ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ
ንስር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አክሲዮን ማኅበር በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከታክስ በፊት 522 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ይፋ አደረገ። ተቋሙ ከታክስ በኋላ ያስመዘገበው የተጣራ ትርፍም 384 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ደርሷል።
ተቋሙ 13ኛውን መደበኛ እና 5ኛውን አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ባካሄደበት ወቅት እንዳስታወቀው፤ የተጣራ ትርፉ ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ207 ነጥብ 6 በመቶ ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል። በዚህም ለአንድ ሺህ ብር የአክሲዮን ድርሻ 625 ብር የትርፍ ድርሻ ተመድቧል።
በበጀት ዓመቱ በርካታ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ዘርፍ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፤ የተቋሙ አጠቃላይ ሀብት ከ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወደ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሏል።
በተመሳሳይ የተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ 6 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር፣ የብድር መጠኑ ደግሞ 6 ነጥብ 69 ቢሊዮን ብር ደርሷል። የተቋሙ የተበላሹ ብድሮች ምጣኔ 2 ነጥብ 87 በመቶ ብቻ ሆኖ በብሔራዊ ባንክ ከተቀመጠው ገደብ በታች መገኘቱ ተጠቁሟል።
ንስር ማይክሮፋይናንስ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ሀብቱን ወደ 34 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ማውጣቱን ገልጿል።
በዚህም በ2019 ዓ.ም ብቻ 10 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት አጠቃላይ ቅርንጫፎቹን 30 ለማድረስ፣ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ የጀመረውን የዘመናዊ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ግንባታ ለማጠናከር እንዲሁም የዲጂታል አገልግሎቱን ይበልጥ ለማስፋፋት አቅዶ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።
በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል

2 days ago