2 days ago
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።
በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።
ከሰኔ 3-5/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና 173,699 ተማሪዎች ውስደው ነበር።
ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 135,003 (77.72%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።
ተማሪዎችም ውጤታቸውን https://amhara.ministry.et... የሚለውን አድራሻ በመፃፍ ፤ በሚመጣው ቅጽ ላይ የተማሪ መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት ፤ ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡
በተጨማሪም emacs_ministry_result_qmt_bot ላይ መመልከት ይችላሉ።
ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው https://amhara.ministry.et... ላይ በመግባት ቅሬታቸው ማቅረብ እንደሚችሉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።
2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
tikvahethiopia

11 days ago
በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እነ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና 52 ተከሳሾች የተከሰሱበትን ክስ ይከላከሉ ወይስ በነጻ ይሰናበቱ የሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ሳይሰጥበት በድጋሚ ተራዘመ።
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ የቀድሞ የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለው እንዲሁም ዶ/ር ካሳ ተሻገር፣ ዶ/ር ጫኔ ከበደን ጨምሮ በድምሩ 52 ተከሳሾች የፍርድ ውሳኔ ሳያገኙ ላለፉት ሦስት ዓመታት ገደማ በእስር ላይ ይገኛሉ።
ክሱ የተመሠረተው መጋቢት 2016 ዓ.ም ሲሆን፣ ጉዳዩ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሕገ መንግሥትና ፀረ-ሽብር ወንጀሎች ችሎት እየታየ ይገኛል።
ተከሳሾቹ በተለያዩ ወቅቶች ካለባቸው የጤና ችግር ጋር በተያያዘ፣ ከቤተሰብ ጥየቃ፣ ከሰብአዊ መብት ሁኔታ፣ እና ሌሎችም ደረሰብን በማለት በሚያቀርቧቸው ቅሬታዎች ዙሪያ ችሎቱ የተለያዩ ቀጠሮዎችን በመስጠት ጉዳያቸውን ሲመለከት የቆየ በመሆኑ የተከሰሱበትን ዋናው የክስ መዝገብን የማየት ሂደት በተለዋጭ ቀጠሮዎች ከ 4 ጊዜ በላይ ሲራዘም ቆይቷል።
በዋናው የሽብር ክስ መዝገብ ላይ ብይን ለመስጠት ቀደም ሲል ለሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ችሎቱ ጉዳዩን በተጨማሪ ዝግጅት አጠቃሎ ለማቅረብ ለዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለተለዋጭ ቀጠሮ አስተላልፎት ነበር።
ችሎቱ ዛሬ የሚሰጠው ብይን ተከሳሾቹ የተከሰሱበትን ክስ ይከላከሉ ወይስ የነጻ ይሰናበቱ የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ እንደሚሆን ቢጠበቅም በድጋሚ በተለዋጭ ቀጠሮ ለ ጥቅምት 6/2019 ዓም በመስጠት ውሳኔውን አራዝሞታል።
ፍርድ ቤቱ ብይኑን ማጠናቀቁን ገልጾ ነበር፤ ይሁን እንጂ የተወሰኑ ተከሳሾች በችሎት ባለመገኘታቸው ብይኑን ለንባብ ማቅረብ እንደማይችል በመግለጽ ንባቡን አላደረገም።
በዛሬው ችሎት ፍርድ ቤቱ ያሰማዋል ተብሎ ሲጠበቅ ከነበረው ብይን በተጨማሪ ከተከሳሾቹ አንዱ ከሆኑት ከዶ/ር ካሳ ተሻገር እና ከጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ስልክ ቁጥር ጋር በተያያዘ ቁጥራቸውን ሌላ ሰው እየተጠቀመበት መሆኑን በመግለጽ ከእዚህ ቀደም በችሎቱ ያቀረቡትን ቅሬታ በተመለከተ ኢትዮ ቴሌኮም ለችሎቱ ይሰጠዋል ተብሎ የሚጠበቀውን ምላሽ የመስማት ጉዳይ ነበር።
ከዶ/ር ካሳ ተሻገር እና ከጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ስልክ ቁጥሮች ጋር በተያያዘ ኢትዮ ቴሌኮም የላከውን ምላሽ ችሎቱ በንባብ አሰምቶታል።
በምላሹ መሠረት፣ የሁለቱ ተከሳሾች ስልክ ቁጥሮች ለረዥም ጊዜ ከአገልግሎት ውጭ በመቆየታቸው በኩባንያው አሠራር መሠረት ጊዜው አልፎበት (expire አድርጎ) ለሌሎች አዳዲስ ተጠቃሚዎች መዘዋወራቸውን ኢትዮ ቴሌኮም አረጋግጧል።
በዋናው ጉዳይ ላይ የሚጠበቀው ብይን ተከሳሾቹ አቃቤ ሕግ ባቀረበባቸው ማስረጃ ላይ ተመስርተው ክሱን ሊከላከሉ ይገባል ወይስ አቃቤ ሕግ ክሱን በበቂ ማስረጃ ስላላስረዳ በነጻ ሊሰናበቱ ይገባል የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ነው።
የተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል "ተከሳሾቹ ከእዚህ ቀደም በችሎት ውሎዎች ላይ አቃቤ ሕግ ካቀረባቸው የድምጽ፣ የጽሑፍ እና የፎረንሲክ ማስረጃዎች ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን ማቅረባቸውን"ገልጸዋል።
ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን ይህን አስተያየት እና አቃቤ ሕግ ያቀረበውን ማስረጃ መርምሮ፣ ማስረጃው ክሱን በበቂ ሁኔታ የሚያስረዳ ሆኖ ካገኘው ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ፣ ካላገኘውም ተከሳሾቹ ያለ ተጨማሪ ክርክር በነጻ እንዲሰናበቱ ብይን የሚሰጥበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቅ ነበር ብለውናል።
ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን ሙሉ ተገኝነት መሠረት በማድረግ ብይኑን ወደ ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ችሎቱን ዘግቷል።
የበጀት ዓመቱ መጠናቀቁን ተከትሎ የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ውስብስብነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የፌዴራል የመጀመሪያ፣ ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች በየአመቱ ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ለ2 ወራት በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩ መሆኑ ይታወቃል።

25 days ago
" ህጋዊው የውል ማሻሻያ ለ2 ዓመታት ይቆያል " - ቢሮው
በአዲስ አበባ የ2019 በጀት ዓመት የቤት ኪራይ ዓመታዊ የጭማሪ ጣሪያ 11.5 በመቶ ሆኖ እንዲጸድቅ መደረጉ ይታወሳል።
ከዚህ ተመን በላይ መጨመር በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ህጋዊው የውል ማሻሻያም ለ2 ዓመታት ይቆያል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።
ከህጋዊ አሰራር ውጪ የሚደረጉ "የመንደር ውሎች" የተከለከሉ ሲሆን ውል በማያድሱና ህግ በሚተላለፉ አካላት ላይ ቅጣት ይጣላል።
የውል እድሳት ጊዜያቸው አልፎ አከራይም ተከራይም አብረው ኖረው እድሳት ሳይፈጽሙ እስከ 2 ወር ከቆዩ የ1 ወር የቤት ኪራይ ቅጣት ይጣልባቸዋል።
ውል ሳያድሱ 3 ወር እና ከዚያ በላይ የቆዩ የ2 ወር የቤት ኪራይ ቅጣት ይከፍላሉ።
አዲስ ተከራይ አስገብተው ውል ያላደሱ እና ያላስመዘገቡ የ1 ወር የቤት ኪራይ ይቀጣሉ።
በጥቆማ ወይም በክትትል ውል ያላደሱ ወይም ያላስመዘገቡ መሆናቸው ከተረጋገጠ ደግሞ ከ1 እስከ 3 ወር የሚደርስ የኪራይ መጠን ቅጣት እንደሚጣልባቸው ቢሮው አሳውቋል።
የቤት ኪራይ የውል እድሳት በክፍለ ከተማ፣ በወረዳ ጽህፈት ቤቶች ወይም በ"መሶብ" ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች ማከናወን ይቻላል ተብሏል።

3 months ago
ኢትዮጵያውያን ላይ የተጣለው የአውሮፓ ቪዛ ገደብ በይፋ ተነሳ
አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጥሎ የነበረው የቪዛ ገደብ በመነሳቱ የሼንገን (Schengen) ቪዛ አሰራር ዳግም ተግባራዊ ሆኗል።
የቪዛ ሂደቱ ወደ ቀድሞው መደበኛ ጊዜ ተመልሷል።
የባለ ብዙ ጊዜ መግቢያ (Multiple-entry) ቪዛዎች ላይ ተጥለው የነበሩ ገደቦች ተነስተው እንደ ቀድሞው በመደበኛ ደንቦች እንዲስተናገዱ ተደርጓል።
tikvahethiopia
አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጥሎ የነበረው የቪዛ ገደብ በመነሳቱ የሼንገን (Schengen) ቪዛ አሰራር ዳግም ተግባራዊ ሆኗል።
የቪዛ ሂደቱ ወደ ቀድሞው መደበኛ ጊዜ ተመልሷል።
የባለ ብዙ ጊዜ መግቢያ (Multiple-entry) ቪዛዎች ላይ ተጥለው የነበሩ ገደቦች ተነስተው እንደ ቀድሞው በመደበኛ ደንቦች እንዲስተናገዱ ተደርጓል።
tikvahethiopia
3 months ago
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች
ከመጪው ሰኔ 24/2018 ዓ/ም ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች የተዘጋጀ የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ (Admission Card) በፈተና አስተዳደር ሲስተም (https://exam.eaes.et/) ከ03/09/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለክልል ትምህርት ቢሮ፣ ለዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለትምህርት ቤት ተወካዮች መለቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
አገልግሎት መ/ቤቱ ፦
1. እያንዳንዱ ተፈታኝ ተማሪ በአድሚሽን ካርዱ ጀርባ ላይ የትምህርት ቤቱን ወይም የወረዳው አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ማህተም የተደረገበትን አድሚሽን ካርድ ከትምህርት ቤቱ ወስዶ በእጁ መያዝ መያዝ እንዳለበት አሳስቧል።
2. በምዝገባ ወቅት በተፈታኙ ወይም በመዝጋቢው የተከሰተ የትምህርት መስክ ፣ የጾታ ፣ የፎቶ እና መሰል ማስተካከያዎች ካሉ ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በፊት ለትምህርት ቤቱ ማሳወቅና ሂደቱን ጠብቆ መስተካከሉንም ከትምህርት ቤቱ ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጿል።
3. እያንዳንዱ ተፈታኝ አድሚሽን ካርዱን ወደ መፈተኛ ማዕከል ሆነ መፈተኛ ክፍል ለመግባት የሚጠቀምበት በመሆኑ በአግባቡና በጥንቃቄ እንዲይዝ አሳስቧል።
4. ተፈታኞች ፈተና ላይ ከአድሚሽን ካርድ በተጨማሪ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል።

በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ወሰነ።
ሆኖም ችሎቱ ተጠርጣሪዎች ለዋስትና የሚያቀርቡትን የገንዘብ መጠን ለመወሰን ለሰኞ ግንቦት 3/2018 ዓም ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል።
አቃቢ ህግ በበኩሉ አምስተኛ ተከሳሽ ከሆነው መንሱር ጀማል በቀር የዋስትና መብታቸው ቢከበር እንደማይቃወም ለችሎቱ አሳውቋል።
ችሎቱ በበኩሉ አቃቢ ህግ በአምስተኛ ተከሳሽ መንሱር ጀማል ዋስትና ጉዳይ ላይ አቃቢ ህግ ያለውን ተቃውሞ በጽሁፍ ለግንቦት ሦስት እንዲያቀርብ ትእዛዝ ሰጥቷል።

Sponsored by
Surafel
3 months ago
የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል
ነጭ ናፍጣ በሊትር 180.46 ብር ገብቷል። ቤንዚንም በሊትር 167.50 ብር ሆኗል።
ከዛሬ ሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉን ማደያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ደብዳቤ፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋን መሰረት በማድረግ ከሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን ያስረዳል።
በደብዳቤው በተገለጸው መሰረት በሊትር፦
- ነጭ ናፍጣ 180.46 ብር
- ቤንዚን 167.50 ብር
- ኬሮሲን 320.66 ብር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ 170.62 ብር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ 167.37 ብር
- የአውሮፕላን ነዳጅ 319.76 ብር ሆኗል።
በተጨማሪም ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ በቅሎ ቤት ፣ ሳሪስ አካባቢ ባሉ ማደያዎች ቅኝት ያደረገ ሲሆን፣ ማደያዎቹ ሽያጭ እያከናወኑ ያሉት በተሻሻለው ዋጋ መሰረት ነው።
የማደያዎቹ ሠራተኞች ቤንዚን 167.50 ብር፣ ነጭ ናፍጣ 180.46 ብር እየሸጡ፣ ሹፌሮችም በዚሁ መሰረት እየቀዱ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በነዳጅ ምርቶች ላይ ከአንድ ወር በፊት የዋጋ ጭማሪ ተደርጎ ነበር።

" በአደባባይና በጎዳና ላይ የሚካሄድ የሃይማኖት ስብከት ይቁም " - ጉባኤው
የመቐለ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 26/2018 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በአደባባይና ጎዳና ላይ የሚካሄድ የሃይማኖት ስብከት እንዲቆም አሳስቧል።
ጉባኤው በመቐለ አደባባዮችና ጎዳናዎች ከተለመደው ባፈነገጠ መልኩ በድምፅ ማጉያ የተደገፉ የሃይማኖት ስብከቶች እየታዩ መሆኑን ጠቅሶ፤ ተፈናቃዮች ቀያቸውን ለቀው በስቃይ ባሉበትና ህዝቡ በከባድ ችግር ውስጥ በተዘፈቀበት ሁኔታ በሃይማኖት ሽፋን ሰላም የሚያውኩ አካላት አደብ መግዛት እንዳለባቸው በአፅንኦት ገልጿል።
ህዝብ እና ተሸከርካሪዎች በብዛት በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች ከህዝብ ፈቃድ ውጪ በድምፅ ማጉያ የሚካሄድ ስብከት መቆም እንዳለበት አሳስቧል።
በተለያዩ አማኞች መኖሪያና የአምልኮ ቦታዎች ድንጋይ የመወርወር፣ በመጥፎ ቃላት የማንቋሸሽና አካል የማጉደል ተግባራት እንዳሉና ይህን ከጅምሩ ሥርዓት ማስያዝ እንደሚገባ አሳስቧል።
ማንኛውም ሰው በሚከተለው ሃይማኖት ምክንያት ለስድብና አካል ጉዳት መዳረግ ሃይማኖት የሚፃረር ተግባር በመሆኑ አንዱ የሌላውን ክብርና እሴት ከሚጎዳ ስብከት መቆጠብ እንዳለበትና ህዝቡ ካለበት ተደራራቢ ፈተና አንጻር በሃይማኖት ሽፋን ሌላ መከራ መጋበዝ እንደማይገባ መክሯል።
ይህ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፣ የእስልምና ፣ የካቶሊክና የወንጌላውያን አማኞች በጋራ ያቋቋሙት ነው።

ኃላፊው በተሾሙ በ45 ቀናት ተነሱ።
የትግራይ የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ በተሾሙ በ45 ቀናት ውስጥ ከኃላፊነት መነሳታቸው ምንጮች ገለፁ።
ለስራ አስኪያጁ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለፁት የካቲት 30/2018 ዓ/ም የኤጀንሲው ስራ አስኪያጅ ሆኖው የተሸሙት አባዲ ገ/ስላሴ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል።
ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም በፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ሃላፊው በሁለት መስመር ፅሁፍ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገዋል።
ሃላፊው በተሾሙ በ45 ቀናት ውስጥ ለምን ከሃላፊነት እንደተነሱ በደብዳቤው በግልፅ ባይቀመጥም ስራ አስኪያጁ " ወደ ህወሓት በማዳላት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራ አደናቅፈዋል " በሚል ምክንያት እንደሆነ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቁመዋል።
ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ሚያዝያ 13/2018 ዓ.ም ለሚድያ የሰጡት መግለጫ በክልሉ መንግስታዊ ሚድያዎች ተዛብቶ መሰራጨቱ በመግለፅና በመወቀስ Landa Report እና ላዛ ትግርኛ ለተባሉ የግል ሚድያዎች ሚያዝያ 14/2018 ዓ.ም ተጨማሪ ማስተካከያና ማብራርያ መስጠታቸው ይታወሳል።
ቴሌቪዥን ጣብያው የፕሮግራሞች ዳይሬክተር ጋዜጠኛ አፈወርቂ ገ/ሂወት የስራ አስኪያጁ ስራ ደርበው እንዲሰሩ ከፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ደብዳቤ እንደደረሳቸው ሰምተናል።
አባዲ ገ/ስላሴ ከጦርነት በፊት እና በኋላ የትግራይ ቴሌቬዥንን ለረጅም ዓመታት የመሩት ተሻለ በቀለ ተክተው መሾማቸው መዘገባችን ይታወሳል።

አቶ ዳዊት ገበየሁ እና አቶ ገደኖ ካዋይታ ተፈረደባቸው።
⚫ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲሆን የተለገሰ 6,594 የቤት ክዳን ቆርቆሮ ተሸጦ ለግል ጥቅም ውሏል ፤ 3,702,466.67 ብር ነው ተሽጦ የተበላው።
የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ዳዊት ገበየሁ እና የግብርና መምሪያ የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኃላፊ የነበሩት አቶ ገደኖ ካዋይታ ላይ የፍርድ ውሳኔ ማሳለፉን የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሀባ ቀውያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ግለሰቦቹ " የመንግስትን የሥራ ኃላፊነት በማይመች አኳኋን መምራት እና የሙስና ወንጀል " ጥፋተኛ መሆናቸውን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል ሲሉ ፕሬዚዳንቱ አሳውቀዋል።
ተከሳሾቹ በ2014 ዓ.ም በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲሆን ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የተለገሰውን 6,594 የቤት ክዳን ቆርቆሮ ሸጠው ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው በማስረጃ መረጋገጡን አቶ ሙሀባ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ተከሳሾች ለግል ጥቅማቸው ያዋሉት ሀብት ግምቱ ብር 3,702,466.67 (ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሁለት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ስልስት ብር ከስልስ ሰባት ሳንቲም) መሆኑን ጠቅሰው ፤ የተገኘው ጥቅምና በህዝብ ላይ የደረሰው ጉዳት እንዲሁም የወንጀሉ ዓላማ ከባድ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ግምት ውስጥ ማስገባቱን ገልጸዋል።
እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ፣ ፍርድ ቤቱ በመመሪያው መሠረት ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸው በ15 ዓመት ጽኑ እስራትና በ50,000 ብር መቀጮ እንዲቀጡ መነሻ ቅጣት ወስኖ ነበር።
ይሁን እንጂ ተከሳሾቹ ፦
- ከዚህ በፊት የወንጀል ሪከርድ የሌላቸው፣
- የቤተሰብ አስተዳዳሪና ለረዥም ጊዜያት ያገለገሉ በመሆናቸው፤
- በተለይ 1ኛ ተከሳሽ "እምርታ" የተሰኘ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ስራ አስኪያጅ የነበሩ መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለእያንዳንዳቸው ሦስት የቅጣት ማቅለያዎች መያዛቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አብራርተዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ፍርድ ቤት የሚከተለውን የመጨረሻ ውሳኔ ማስተላለፉን አቶ ሙሀባ ቀውያ ገልጸዋል።
1ኛ ተከሳሽ አቶ ዳዊት ገበየሁ ፦ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ከሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በሚቆጠር በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 20,000 የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ፤
2ኛ ተከሳሽ አቶ ገደኖ ካዋይታ ፦ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ከመስከረም 14 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሚቆጠር በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 20,000 የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወስኗል።
በተጨማሪም ተከሳሾቹ ለግል ጥቅማቸው ያዋሉትን ብር 3,702,466.67 ለመንግስት በጋራ እንዲመልሱ መወሰኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።
አቶ ዳዊት ገበየሁ በዚሁ ፍ/ቤት በሌላ የወንጀል መዝገብ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በ7 ዓመት ጽኑ እስራትና በ5,000 ብር መቀጮ ተፈርዶባቸው የነበረ መሆኑን አቶ ሙሀባ ገልጸው፤ ሁለቱም የወንጀል ቅጣቶች ተደምረው ተከሳሹ በአጠቃላይ በ20 ዓመት ጽኑ እስራትና በ25,000 ብር የገንዘብ መቀጮ የሚቀጡ መሆኑን አስታውቀዋል።

የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቆናል።
በሌላ በኩል ፦
- የሬሜዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም ➡️ ግንቦት 19 ኢድ አልአድሃ
- የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም
- የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሃምሌ 29 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም
- የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ጥናትና ምርምር መረጃ መሰብሰብ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ... ይሰጣል።

ባሕር ዳር ላይ ሰው ገድሎ የተሰወረው ተጠርጣሪ መቐለ ላይ በትግራይ ክልል ፖሊስ ተያዘ።
በባሕርዳር ከተማ ማህሌት ማሩ የተባለችን እንስት " የአድማ ብተና " አባል በሆነው ተጠርጣሪ ያምራል አለበል አለሙ " ተደፍራ እና ተገድላ ተገኘች " የሚል መረጃ ሲሰራጭ ነበር።
የግድያ ጥቃቱ የደረሰበትን ሁኔታ በተመለከተ፣ ከስፍራው የወጣውና በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው አብዛኛው መረጃ፣ ተጠርጣሪው እንስቷ ከምትሰራበት ሆቴል እየተስተናገደ አምሽቶ " አስገድዶ ወደ ሌላ ሆቴል በመውሰድ ከደፈራት በኋላ ገደላት " የሚል ነው።
የወንጀል ድርጊቱ ብዙዎችን ያቆጣ ነው።
የወንጀል ድርጊቱን በመፈጸም የተጠረጠረው ግለሰብ ድርጊቱን ፈጽሞ ከአካባቢው ተሰውሮ ነበር።
ምንም እንኳን የአማራ ክልል ፖሊስ ስለ ግድያው ዝርዝር መረጃ ይፋ ባያደርግም ህዝቡ ያለበትን እንዲጦቅም ጥሪ አቅርቦ ፍለጋ ሲያካሂድ ነበር።
ዛሬ የአማራ ፖሊስ ይፋ ባደረገው መረጃ በነፍስ ግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው ያምራል አለበል አለሙ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ፖሊስ " ያምራል አለበል አለሙ የተባለው ተጠርጣሪ ግድያ ፈጽሞ ከአካባቢው በመሰወር ለረጅም ጊዜ ሲፈለግ ቆይቷል " ብሏል።
ለመያዝ ክትትል ሲደረግ ቆይቶ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ተሸሽጎ እንደሚገኝ በመረጋገጡ በተደረገ የተቀናጀ ስራ በቁጥጥር ስር ሊውል እንደቻለ አማራ ፖሊስ ገልጿል።
የአማራ ክልል ፖሊስ፣ የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ላበረከተው የላቀ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል።
በሌላ በኩል ቲክቫህ ኢትዮጵያ እንስቷ በምን ሁኔታ ግድያ እንደተፈጸመባት አንድ የአማራ ክልል ፖሊስ አካልን ጠይቆ " ምርመራ ላይ ስለሆነ የሚገልጹት ምርመራ የሚሰሩት ናቸው " ብለዋል።
እስካሁን ባለው ክትትል ስለእንስቷ አሟሟት የተገኘ መረጃ ካለ በድጋሚ እንዲገልጹ ስንጠይቃቸውም፣ " ገና ምርመራ ላይ ያለ ጉዳይ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

4 months ago
የሴኔጋል መንግስት በግብረ ሰዶማዊነት ላይ ጠንካራ እርምጃ የሚወስድ አዲስ ህግ አፀደቀ።
የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ በሀገሪቱ ግብረ ሰዶማውያንን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀጣ አዲስ ህግ በፊርማቸው አፅድቀዋል።
ይህ አዲስ ህግ ቀደም ሲል በግብረ ሰዶማዊነት ድርጊት ላይ ተጥሎ የነበረውን ከፍተኛ የእስር ቅጣት ወደ 10 ዓመት ከፍ አድርጎታል።
" ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ድርጊቶች " ተብለው የተመደቡ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነቶች ላይ የሚጣለው ቅጣት ከነበረበት 1-5 ዓመት ወደ 5-10 ዓመት ከፍ እንዲል ተደርጓል።
አዲሱ ህግ ከእስር በተጨማሪ ከ2 ሚሊዮን እስከ 10 ሚሊዮን የሴኔጋል ፍራንክ ($3,500 - $17,600) የሚደርስ ከፍተኛ የገንዘብ መቀጮ ደንግጓል። ይህም ቀደም ሲል ከነበረው (1.5 ሚሊዮን ፍራንክ) እጅግ የላቀ ነው።
ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያስተዋውቁ ወይም የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ ግለሰቦች ከ3 እስከ 7 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ ህጉ ይፈቅዳል።
አፀያፊ የተባለውን ይህን ድርጊት የሚያበረታታ ማንኛውም ድርጊት እንደ ወንጀል እንዲታይ ተደርጓል።
ህጉ ያለምንም ማስረጃ ሌላውን ሰው በግብረ ሰዶማዊነት ወንጀል የሚከስ ማንኛውንም አካል በወንጀል እንደሚቀጣ አካቷል።
ይህ ጠንካራ ህግ ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ እና የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኡስማን ሶንኮ በምርጫ ወቅት ለህዝባቸው የገቡትን ቃል የፈጸሙበት ነው ተብሏል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ ውሳኔውን " እጅግ አሳሳቢ " ሲሉ የገለጹት ሲሆን ህጉ ሰብአዊ መብቶችን የሚጥስ መሆኑን ተናግረዋል።
በተቃራኒው በሴኔጋል የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት እና ማህበራት ግብረ ሰዶማዊነት "የምዕራባውያን ባህል መጫኛ መሳሪያ ነው" በሚል ጠንካራ ቅጣት እንዲጣል ሲወተውቱ ቆይተዋል ተብሏል።
ከባለፈው የካቲት ወር ጀምሮ በሴኔጋል በርካታ ሰዎች በግብረ ሰዶማዊነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
አዲሱ ህግ ተጠርጣሪዎቹ ላይ የሚጣለውን ቅጣት የበለጠ በማክበድ በሀገሪቱ ያለውን ጥብቅ ቁጥጥር የሚያጠናክር ነው።
በተለይም ድርጊቱ የተፈጸመው ለአካለ መጠን ባልደረሱ ህፃናት ላይ ከሆነ ከፍተኛው ቅጣት እንደሚተገበር ህጉ ይገልጻል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አቋርጧቸው ከነበሩ በረራዎች መካከል የትኞቹን በድጋሚ አስጀመረ ?
በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ግጭት ምክንያት በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቀጠናው ያደርጉት የነበረውን በረራ በጊዜያዊነት ማቋረጣቸው ይታወቃል።
በሳምንት ከ 100 በላይ ምልልሶችን ያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ ወደ መካከለኛው ምስራቅ እና ገልፍ ሃገራት ያደርጋቸው የነበሩ በረራዎችን ካቋረጡ አየር መንገዶች መካከል አንዱ ነው።
ለሳምንታት ተቋረጦ የቆየው በረራ ወደ አንዳንድ የቀጠናው አካባቢዎች በድጋሚ ማስጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዛሬው ዕለት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ "የመሻሻል ነገሮች በምናይባቸው አካባቢዎች በተወሰነ ደረጃ በረራ እንደገና አስጀምረናል" ብለዋል።
በረራ የጀመረባቸው አካባቢዎች :-
• ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ውስጥ ዱባይ በቀን አንድ በረራ ፣
• አቡዳቢ በቀን አንድ በረራ ፣
• ሻርጃ በቀን አንድ በረራ
• ሳውዲ አረቢያ (ደማም ከተማ) በቀን አንድ በረራ
• ጆርዳን አማን በቀን አንድ በረራ ናቸው።
ይሁን እንጂ አቶ መስፍን ዶሃ (ኳታር)፣ ባህሬን፣ ኩዌት እንዲሁም ቴላቪቭ እና ቤሩት በረራ እንደተቋረጠባቸው መሆኑን አሳውቀዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዝርዝር ምን አሉ ?
" እንደሚታወቀው በገልፍ አካባቢ ጦርነት ከተጀመረ አንድ ወር አካባቢ ሆኖታል።
ጦርነቱ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ገልፍ እና መካከለኛው ምስራቅ አገሮች የሚያደርገውን በረራ በተወሰነ ደረጃ ለጊዜው አቋርጧል።
ይህ በመሆኑ ምክንያት ወደ መካከለኛው ምስራቅ እና ገልፍ የሚሄዱ መንገደኞች እያጓጓዝን አይደለም፤ ያ በመንገደኛ ቁጥራችን ላይ የተወሰነ ተፅዕኖ ያሳድራል።
ይሁን እንጂ በሌሎች በምንበርባቸው ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቻችን ላይ ያለንን በረራ በማጠናከር ከዚህ ከገልፍ እና መካከለኛው ምስራቅ ያጣነውን መንገደኛ ቁጥር ሌላ ቦታ በመብረር በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ለማካካስ ሞክረናል።
በዚህ መንገድ እየቀጠልን ነው፤ ሁኔታውን እየተከታተልን ነው የመሻሻል ነገሮች በምናይባቸው አካባቢዎች በተወሰነ ደረጃ በረራ እንደገና አስጀምረናል ያ እየቀጠለ ነው ያለው።
በረራ ተቋርጦ ከነበረባቸው መካከል አሁን መብረር የጀመርንባቸው ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ውስጥ ዱባይ በቀን አንድ በረራ እያደረግን ነው፣ አቡዳቢ በቀን አንድ በረራ እያደረግን ነው፣ እንዲሁም ሻርጃ በቀን አንድ በረራ እያደረግን ነው።
በተጨማሪም ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ደማም የምትባል ከተማ አቋርጠን ነበር እሱን በረራ ቀጥለናል።
ይሁን እንጂ ዶሃ (ኳታር) ፣ ባህሬን ፣ ኩዌት እንዲሁም ቴላቪቭ እና ቤሩት በረራ እንዳቋረጥን ነው።
እንግዲህ በረራ ስናቋርጥ የበረራ ደህንነትን ትክክለኛ ትንተና አካሂደን ያለውን ሁሉ መረጃ አገናዝበን መብረር ሴፍ (safe) ነው የምንል ሲሆን ብቻ እንበራለን።
በተጨማሪም ጆርዳን አማን አቋርጠን ነበር እሱን ሁለት በረራ ነበረ አሁን በአንድ በረራ ጀምረናል " ብለዋል።

" ሰባቱ ወዲያው ተገደሉ። አንዱን የሞተ መስሏቸው ጥለውት ሄዱ። አልሞተም ግን እግሩ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ስድስቱ በሰፊ ጉድጓድ በአንድ ቦታ ተቀብረዋል " - የፋብሪካው ሠራተኞች
➡️ " አንድ የከባድ መኪና ሹፌር እና ረዳትም ተገድለው ተገኝተዋል። የሰዎች መታገት የተለመደ ሆኗል። የጸጥታ አካላት አሉ ግን እያዩ እንዳላዩ ነው የሚሆኑት " - ነዋሪ
በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞችን እና ሌሎችን ጨምሮ በሁለት ቀናት ብቻ ዘጠኝ ሰዎች ሲገደሉ፣ ሌሎች መጎዳታቸውን የፋብሪካው ሠራተኞች እና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ጉዳዩን ያጣራ አንድ የአካባቢው ነዋሪ በሰጠን ማብራሪያ፣ የፋብሪካው ሠራተኞች በታጣቂዎች የተገደሉት መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ/ም መሆኑን ገልጾ። " አንድ የፋብሪካውን አመራር ለማጥቃት ሂደው ነው ሰባቱን አጃቢዎቹን የገደሏቸው " ብሏል።
ጥቃት አድራሾቹ፣ " መሬታችን ተወስዷል " የሚል ጥያቄ እንዳላቸውም ገልጿል። ጥቃቱ የደረሰው " ጮሬ " በሚባለው የፋብሪካው ካምፕ መሆኑን ያስረዳው ነዋሪው፣ " ሟቾቹ የስኳር ፋብሪካው የጥበቃ ሠራተኞች ናቸው። ታጣቂዎቹ ድንገት መጥተው ተኩስ ፈጽመውባቸው ወዲያው ነው ጫካ የሚገቡት " ሲልም ተናግሯል።
በተያያዘ፣ " ሰባቱ ሰዎች ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፊት መተሐራ እና ወለንጭቲ መካከል የከባድ መኪና ሹፌር እና ረዳትም ተገድለው ተገኝተዋል። በአካባቢው የሰዎች መታገት የተለመደ ሆኗል። የጸጥታ አካላት አሉ ግን እያዩ እንዳላዩ ነው የሚሆኑት " ሲልም ገልጿል።
ሌላኛው ነዋሪ፣ ከ2010 ጀምሮ በየዓመቱ እስከ ዘጠኝ ሰው " የሚገደልበት " ሁኔታ መኖሩን አስረድተው፣ " ህዝቡ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እያገኘ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።
የሰሞኑን ጎድያ በተመከለተም፣ " በአንድ መኪና ላይ ነው ሰባቱንም የመንግስት ተቀጣሪዎች፤ የስንት ልጆች አባቶችን በአንድ ቀን ገድለውብናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ሰሞኑን የተገደሉት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች " ትልልቅ ሰዎች ናቸው " ሲሉ ያስረዱ አንድ ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ የፋብሪካው ሠራተኛ ደግሞ፣ ጥቃቱን " አሳዛኝ " ሲሉ ጠርተውታል።
ሰባቱ ሠራተኞች የተገደሉት አንድ የፋብሪካውን አመራር አጅበው በነበረበት ወቅት መሆኑን ተናግረዋል።
የታጣቁት አካላት የፋብሪካው ሠራተኞች ላይ ተኩስ የከፈቱባቸው " ገና ከፒካፕ መኪና ላይ ሳይወርዱ " መሆኑን፣ በዚህም ሌሎቹ ሲገደሉ አብረው የነበሩት አመራሩ " የውሃ ቦይ ውስጥ ገብተው፣ እየተሳቡ " የተኩሱን ቦታ በመራቅ በህይወት መትረፋቸውን አስረድተዋል።
እኚሁ የፋብሪካው ሠራተኛ፣ ይህ ጥቃት ተፈጽሟል ብሎ ለመናገር እንኳ ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ሌላኛው የፋብሪካው ሠራተኛ በበኩላቸው፣ ግድያው የተፈጸመበት " ጮሬ " በተሰኘው ቦታ አጠገብ መሆኑን ገልጸዋል።
በአጠቃላይ ከሟቾቹ ጋር ዘጠኝ ሰዎች ነበሩ ብለው፣ " ሰባቱ ወዲያው ተገደሉ። አንዱ የሞተ መስሏቸው ጥለውት ሄዱ። አልሞተም ግን እግሩ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። አንዱ ደግሞ ተርፏል " ብለዋል። " ስድስቱ በሰፊ ጉድጓድ በአንድ ቦታ ተቀብረዋል " ነው ያሉት።
አዲስ የመጡት የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ለሟች ቤተሰቦች " በየቤታቸው ሂደው ለእያንዳንዳቸው 150 ሺሕ ብር ሰጥተዋል። 'የተማረ ልጅ ካላቸው በቋሚነት ሥራ እንቀጥራን፣ ካልተማሩ በመደብ 6 የአባታቶቻቸውን ቦታ ይይዛሉ' ሲሉም ቃል ገብተዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ጥቃቱ ከደረሰ በኋላ ያለውን ድባብ ሲያስረዱ ደግሞ፣ ለጊዜው "መከላከያ ገብቷል" ብለዋል።
የአካባቢው ነዋሪ ግን፣ " በአካባቢው የጸጥታ ችግር ተንሰራፍቷል። በሰላም ወጥቶ መግባት በጣም አስቸጋሪ ሆኗል " ሲሉም የሁነቱን አሳሳቢነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ከአንድ ወር በፊት ሁለት ልጆች ታግተው 2 ሚሊዮን ብር ተጠይቆባቸው ነበር። 2 ሚሊዮን ብር ተሰብስቦ አንድ ልጅ ወስዶ ሰጣቸው። በኋላም ለቀቋቸው። ከፍተኛ ድብደባ እና ራሳቸውን እስኪስቱ ድረስ የረሃብ ስቃይ አድርሰውባቸው መንገድ ላይ ነው የጣሏቸው " ሲሉም አስታውሰዋል።
" ገንዘቡን ያደረሰው ልጅ ግን ተገድሏል" በማለት አዝነዋል። ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መካከል አንዱ በበኩላቸው፣ ታጣቂዎቹ "ከአዳማ መተሐራ መንገድ በኃይለኛው እያገቱ ነው፤ ተሳፋሪም መውሰድ ጀምረዋል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የስኳር ፋብሪካውንም ሆነ ሌሎች የአካባቢውን ኃላፊዎች ለማግኘት ለቀናት ያደረገው ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን፣ ጥረቱ ይቀጥላል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#tikvahethiopiafamilyaa

" ይህ አይነቱ የወንጀል ድርጊት በአከባቢው ሲፈፀም የመጀመሪያ ነው። የሞት ፍርድ ውሳኔም የመጀመሪያ ነው " - አቶ ነጋልኝ ዓለሙ
በቡርጂ ዞን በውርስ ምክንያት 3 የቤተሰባቸውን አባላትን በጥይት ደብድበው የገደሉ ተከሳሾች በሞት እንዲቀጡ ተወሰነ።
ይህ በአከባቢው የመጀመሪያው የሞት ፍርድ ውሳኔ እንደሆነ ተገልጿል።
የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ነሐሴ 16/2017 ዓ/ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ገደማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሶያማ ዙሪያ ወረዳ ገራ ቀበሌ መሆኑን በዞን ፍትህ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ነጋልኝ ዓለሙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በዚሁ ቀበሌ አቶ ዋቶ ወርቁ የተባሉ አዛውንት ዕድሜያቸው እየገፋ መምጣቱን ተከትሎ በአከባቢው ባህል መሰረት ልጆቻቸውን ጠርተው የመሬት ውርስ ክፍፍል ማድረግ ይጀምራሉ።
ይህ እየሆነ ባለበት በሂደቱ ተቃርኖ የነበራቸው የአዛውንቱ የመጀመሪያ ልጅ እና የልጅ ልጃቸው ሁለቱም የክላሽ ኮቭ መሳሪያ በመታጠቅ በቤተሰብ አባላቱ ላይ ተኩስ መክፈታቸውን አቶ ነጋልኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በጥቃቱ አዛውንቱ አቶ ዋቶ ወርቁን እና ሁለት ልጆቻቸው ወዲያውኑ ሲሞቱ ሁለት የቤተሰብ አባላት ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ አርባምንጭ ሪፌራል ሆስፒታል መላካቸውን ገልፀዋል።
ፖሊስም ግለሰቦቹን ከነመሳሪያቸው ኤግዚቢትነት በመያዝ ምርመራ ማድረግ ይጀምራል። መዝገቡንም አደራጅቶ ለዞኑ ዐቃቤ ሕግ ያቀርባል።
ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን በማደራጀት በሁለቱ ተከሳሾች ላይ በዋና ወንጀል አድራጊነት ፦
• በሶስት የግድያ ወንጀል ክስ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 539/1/ሀ መሠረት በከባድ የሰዉ ነብስ ማጥፋት ወንጀል
• ሁለት በህይወት በተረፉ የግል ተበዳዮች ወንጀል ሁለት ክስ በወንጀል ህግ አንቀጽ 27 እና 539/1/ሀ መሠረት ክስ ማቅረቡን አቶ ነጋልኝ አስረድተዋል።
ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበው የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈፀማቸው ተጠይቀው " አልፈፀምንም " በማለት ክደዉ ተከራክረዋል።
አቃቤ ህግ በሰዉና በሰነድ ማስረጃ አምስቱንም ክስ በሚገባ ያስረዳ ሲሆን ተከሳሾች የቀረበባቸዉን ክስ መከላከል ባለመቻላቸው የቡርጂ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተከሳሾችን በቀረበባቸው ክሶች ጥፋተኛ ናቸው ብሏል።
የፈፀሙት ወንጀል ጭካኔ የተሞላበትና አስነዋሪ መሆኑ ፤ በአከባቢው ከዚህ ቀደም ተደርጎ የማይታወቅ ፤ ከሁለት በላይ የሆነ የቤተሰብ አባላት ላይ በአንድ ጊዜ የተፈፀመ ግድያ መሆኑን ከግምት ውስጥ ገብቷል።
ፍርድ ቤቱ ሁለቱም ተከሳሾች በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።
ይህ አይነቱ የወንጀል ድርጊት በአከባቢው ሲፈፀም የመጀመሪያ ነው ያሉት አቶ ነጋልኝ የሞት ፍርድ ውሳኔም በዞኑ የመጀመሪያ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ/ም

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥነት ያለዉ አዲስ የታርጋ ለውጥ ለማድረግ ሲያከናውን የቆየውን የቅድመ ዝግጅት ስራ አጠናቆ በቅርቡ አዲስ የተሸከርካሪ ሰሌዳ መለያ ቁጥር (ታርጋ) መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ።
የታርጋ መስጠት ስራዉ ከመጀመሩ በፊት ግለሰቦች ወይም ተቋማት የሚፈልጓቸዉን የሰሌዳ ቁጥሮች አጫርቶ ላሸነፉ አካላት ለመስጠት እንደሚፈልግ ገልጿል።
የስርጭት ስራዉ ከመጀመሩ በፊት ግለሰቦች ወይም ተቋማት የሚፈልጉትን ቁጥር በመለየት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ 5ኛ ፎቅ በመቅረብ ከ17/07/18 ዓ/ም ጀምሮ ባለዉ አንድ ሳምንት ጊዜ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

#ምርጫ2018
ፓርቲዎች ለመጪው ምርጫ እጩዎቻቸውን እያስተዋወቁ ይገኛሉ።
ገዢው ብልፅግና ፓርቲም ለመጪው ምርጫ የሚወዳደሩ እጩዎችን እያስተዋወቀ ሲሆን ከነዚህም እጩዎች መካከል ጋዜጠኛ ፣ አርቲስት ፣ እንዲሁም አርሶ አደር የሆኑ ይገኙበታል።
በአዲስ አበባ ለምክር ቤት እጩ ሆነው ከቀረቡት መካከል አንደኛው በሙዚቃ አቀናባሪነት የሚታወቀው ካሙዙ ካሳ ነው።
ሙዚቀኛው ፥ ስራው አርቲስት ፣ የትምህርት ደረጃው መካከለኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሁም የሚወዳደረው የካ ክፍለ ከተማ መሆኑ ተገልጾ ይፋ ተደርጓል።
ሌላኛዋ የቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛዋ ወ/ሮ በሻቱ ቶሎማርያም እዛው የካ ክፍለ ከተማ እጩ ሆና ቀርባለች።
ከዚህ በተጨማሪ አቶ ሹሜ ግዛው የተባሉ አርሶ አደርም በእጩነት ቀርበዋል።
በዚህ ክፍለ ከተማ ሌሎች በፌዴራል ደረጃ፣ በከተማ፣ በክፍለ ከተማ አመራርነት ላይ የሚገኙ እጩዎችም ቀርበዋል።
ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቀረቡ እጩዎች መካከል ደግሞ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፣ ወ/ሮ አይሻ መሃመድ ፣ ዶ/ር ሌሊሴ ነሜ ይገኙበታል።
መረጃው የየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ/ም

5 months ago
" መጋቢት 15/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11 ሰዓት 30 ላይ ሲስተሙን እንዘጋለን ፤ ከዚያ በኋላ ማንም መመዝገብ አይችልም " - እሸቱ ከበደ (ዶ/ር)
🗓 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መስጫ ትክክለኛ ጊዜው ገና ባይጸድቅም ፈተናው ሰኔ ውስጥ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል !
የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ መጋቢት 15 ቀን 2018 ከቀኑ 11 ሰዓት 30 እንደሚጠናቀቅ፣ ያልተመዘገበ እንደማይፈተን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሳስቧል።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር)፣ ለምዝገባ የተሰጠው የወር ጊዜ መሆኑን ገልጸው፣ " ሁሉም ተሯሩጦ መመዝገብ አለበት፤ ያልተመዘገበ ተማሪ ሳልመዘገብ አምልጦኝ ቢል ምንም ማድረግ አንችልም፤ ቀጣይ አመት ይፈተናል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ወላጆችም ልጆቻቸው መመዝገባቸውን እንዲያረጋግጡ አስገንዝበው፣ " መጋቢት 15/2018 ዓ/ም 11 ሰዓት ተኩል ላይ ሲስተሙን እንዘጋለን፤ ከዚያ በኋላ ማንም መመዝገብ አይችልም " ነው ያሉት።
በጀት ከተመደበ፣ ፈተና አስፈጻሚዎች ከተሰማሩ በኋላ አዲስ ተመዝጋቢ ቢቀርብ ለማስተናገድ እንደሚቸገሩ አስረድተዋል። ትክክለኛ ጊዜው ገና ባይጸድቅም ፈተናው ሰኔ ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
ተመዝጋቢዎች ከ9 እስከ 11 የተማሩበት ውጤት ሊኖራቸው እና አሁን ላይ 12ኛ ክፍል እየተማሩ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልጸዋል። ድጋሚ ለሚፈተኑ ደግሞ 750 ብር ክፍያ በመፈጸም ከዚህ በፊት የተፈተኑበትን አድሚሽን ካርድ ማስገባት፣ https://register.eaes.et ላይ መመዝገብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ይህም 150 ብሩ ለምዝገባ፣ ለእያንዳንዱ ስድስት ፈተና 100 ብር ተደርጎ ተሰልቶ፣ ተፈታኞች " ቢያንስ ኮስት ሸር " እንዲያደርጉ እና " ከፍዬ ነው " በሚል ለፈተናው ትኩረት እንዲሰጡ ታስቦ የተወሰነ መሆኑን ገልጸዋል።
ተፈታኞች በመረጡበት የፈተና ማእከል መፈተን እንደሚችሉ ያስረዱት እሸቱ (ዶ/ር)፣ " ለምሳሌ አምና አርባምንጭ የተፈተነ ተማሪ፣ ዘንድሮ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ከሆነ ለመፈተን አርባምንጭ መሄድ ሳይጠበቅበት አዲስ አበባ ካሉ ትምህርት ቤት አንዱን መርጦ የግል ተፈታኝ ሆኖ ይፈተናል " ብለዋል።

" ለግድያ የሚያበቃ ምንም ዓይነት ጥል ሳይኖር የመኖሪያ ቤቱን በር ከውስጥ በመቆለፍ ወላጅ እናቱንና እህቱን በሳንጃ ነው በጭካኔ የገደለው " - ኢንስፔክተር ደሣለኝ ዳመና
ወላጅ እናቱንና እህቱን በዘግናኝ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ።
አሰቃቂ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ምዕራብ ባድዋቾ ወረዳ ገርቦ ቀበሌ ነው።
በዚሁ ቀበሌ ወላጅ እናቱንና እህቱን በዘግናኝ ሁኔታ በገደለ ግለሰብ ላይ የሞት ፍርድ ውሳኔ መተላለፉን የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግና የምዕራብ ባድዋቾ ወረዳ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።
የምዕራብ ባድዋቾ ወረዳ ፖሊስ የወንጀልና ታክቲክ ጉዳዮች ምርመራ ዘርፍ አስተባባሪ ኢንስፔክተር ደሣለኝ ዳመና ምን አሉ ?
" ተከሳሹ ወጣት ሰንበቶ መንገሻ ይባላል።
ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ለግድያ የሚያበቃ ምንም ዓይነት ጥል ሳይኖር የመኖሪያ ቤቱን በር ከውስጥ በመቆለፍ ወላጅ እናቱንና እህቱን በሳንጃ በጭካኔ ገድሏል።
ፖሊስ ባደረገው ማጣራት፣ ወንጀል ፈጻሚው ወላጅ እናቱን በሳንጃ አንገታቸውን፣ ሆዳቸውንና ጀርባቸውን በመውጋት፣ እንዲሁም ጡታቸውን በመቁረጥ ሕይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል።
ይህን ድርጊት አይታ የጮኸችውን ታናሽ እህቱንም በአንገቷ አካባቢ ደጋግሞ በመውጋት ለሞት ዳርጓክ።
ተከሳሹ ቀደም ሲል የመከላከያ አባል ነበር በሕገ-ወጥ መንገድ ከድቶ (ኮብልሎ) የወጣ ነው። " ብለዋል።
የሀዲያ ዞን ሾኔ ምድብ ችሎት ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ አቶ ግዛቸው ታደሴ በበኩላቸው፤ ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመበትን አኳኋን ከፖሊስ ጋር በመሆን በምርመራ ማጣራታቸውን ገልጸዋል።
ለፍርድ ቤቱም የአስከሬን ምርመራ ማስረጃ፣ ተከሳሹ ለወረዳው ፍርድ ቤት የሰጠው የእምነት ክህደት ቃል እና የሰው ምስክሮችን በማቅረብ ክስ ተመስርቷል።
የክስ መዝገቡን የተመለከተው የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሾኔ ምድብ ችሎት የድርጊቱን አሰቃቂነትና የተከሳሹን የጭካኔ ደረጃ ከግምት ውስጥ በማስገባት ግለሰቡ በሞት እንዲቀጣ በሙሉ ድምፅ ወስኖበታል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ/ም

#tigray
የትግራይ ቴሌቪዥን የዜና ክፍል ዳይሬክተር ዮውሃንስ ብርሃነ እና አክቲቪስት ሰናይት መብርሃቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።
በትግራይ ቴሌቪዥን የዜና ክፍል ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ዮውሃንስ ብርሃነ ትላንት ከሰዓት በኋላ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ከአንድ ምግብ ቤት አውጥተው ወስደውታል ሲሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ምንጮች ገልጸዋል።
ምንጮቹ ጋዜጠኛው የት ፓሊስ ጣብያ እንደታሰረ አስመልክተው ያሉት ነገር የለም።
በሌላ በኩል፤ የህወሓት ቀንደኛ ደጋፊ የሆነችው አክቲቪስት ሰናይት መብራህቱ ከሌሎች 4 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውላ ፍርድ ቤት ቀርባለች።
ሰናይትና አብሯዋት የተጠሩጠሩ ግለሰቦች ከመሬት ሽያጭ የተያያዘ የ16 ሚሊዮን ብር የማጭበርበር ክስ ቀርቦላቸዋል።
ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ካልዋሉ ሌሎች ግብረ አበሮቻቸው የወንጀል ድርጊቱ መፈፀማቸው ጠቅሶ ፓሊስ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቋል።
በመቐለ የሓድነት ክፍለ ከተማ ፍርድ ቤት ፓሊስ ያቀረበው ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ቀን ቀጠሮ ተቀብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ/ም

የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለሥልጣን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ለመቋቋም በአገር ውስጥ የነዳጅ ስርጭት እና ግብይት ላይ ጥብቅ የቁጠባ እርምጃዎች እንዲወሰዱ የሚያዝ አዲስ መመሪያ አውጥቷል።
በመመሪያው መሠረት የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ለማንኛውም የነዳጅ ዓይነት አቅርቦት ለሚከተሉት አካላት ቅድሚያ እንዲሰጡ ታዟል ፦
- ለፀጥታ ተቋማት፣ ቁልፍ ለሆኑ የመንግስት ፕሮጀክቶች እና በተለይም በመጠናቀቅ ላይ ላሉ የልማት ስራዎች።
- ለኢንዱስትሪዎች፣ መሠረታዊ ሸቀጦችን ለሚያመርቱ አምራች ድርጅቶች እና ምርታቸውን ወደ ውጭ ለሚልኩ ተቋማት።
- ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለሚታይባቸው እና የሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት ፍሰት ላለባቸው የኮሪደር አካባቢዎች።
የነዳጅ ቸርቻሮ ማደያዎች ለሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ እንዲሰጡ የታዘዘ ሲሆን፣ ነዳጅ ቁጠባውን ለማጠናከርም አዲስ ክልከላ ተጥሏል።
በዚህም መሠረት ከፋብሪካው ከተገጠመላቸው የነዳጅ ማጠራቀሚያ (ሰልቫቲዮ) ውጭ፣ ተጨማሪ ሰልቫቲዮ አስገጥመው የሚመጡ አሽከርካሪዎችን ማደያዎች እንዳያስተናግዱ እና መሰል ድርጊቶችን ለፀጥታ አካላት እንዲጠቁሙ መመሪያ ተሰጥቷል።
በተጨማሪም ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ (Timing Arrival) መሠረት መድረሻ ቦታቸው መድረሳቸውን ኩባንያዎች በጥብቅ እንዲከታተሉ ታዟል።
በነዳጅ አጓጓዥ ተሽከርካሪዎች ብልሽት እና በሾፌሮች የልምድ ማነስ በሚፈጠሩ አደጋዎች በሚከሰት የነዳጅ ብክነት እንዳይፈጠር ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ለነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
በነዳጅ ቸርቻሪ ማደያዎች በኩልም በከተማ አስተዳደር በክልል /ንግድ ቢሮዎች፣ በዞን/ በከተማ/ እና በወረዳ ንግድ ቢሮ/ ጽህፈት ቤት በኩል በደብዳቤ ለሚስተናገዱ ቀጥታ ተጠቃሚዎች የሚሰጠው ነዳጅ በጥንቃቄ እና ለታለመለት ዓላማ ብቻ መዋል እንዳለበት መመሪያው አሳስቧል።
ባለሥልጣኑ በመጨረሻም ይህንን መመሪያ ተግባራዊ በማያደርጉ እና በነዳጅ ግብይት ሂደት ላይ ሕገ-ወጥ ተግባር በሚፈጽሙ ማንኛውም ተዋናዮች ላይ በአዋጅ እና በመመሪያው መሠረት ጠንካራ እርምጃ እንደሚወሰድ እና ተጠያቂ እንደሚሆኑ በጥብቅ አስጠንቅቋል።

የዒድ አልፈጥር በዓል አርብ (ጁምዓ) ይውላል።
ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ ባለመታየቷ 1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ከነገ ወዲያ አርብ (ጁምዓ) ተከብሮ ይውላል።
ዒድ ሙባረክ !
tikvahethiopia
ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ ባለመታየቷ 1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ከነገ ወዲያ አርብ (ጁምዓ) ተከብሮ ይውላል።
ዒድ ሙባረክ !
tikvahethiopia
5 months ago
የሳዑዲ አረቢያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደገለጸው ዛሬ ረቡዕ አመሻሽ ላይ የሸዋል ወር ጨረቃ ፍለጋ ይካሄዳል።
ዛሬ ጨረቃ ከታየች የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ ሐሙስ ይውላል።
ዛሬ ጨረቃ ካልታየች ነገ ሐሙስ የረመዷን 30ኛው ቀን ሆኖ ይውላል ፤ በዓሉ ደግሞ አርብ ይውላል።
Stay Updated !
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ/ም
tikvahethiopia
ዛሬ ጨረቃ ከታየች የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ ሐሙስ ይውላል።
ዛሬ ጨረቃ ካልታየች ነገ ሐሙስ የረመዷን 30ኛው ቀን ሆኖ ይውላል ፤ በዓሉ ደግሞ አርብ ይውላል።
Stay Updated !
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ/ም
tikvahethiopia
5 months ago
#tigray
ብዛታቸው 30 የሆኑ የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞ ስምና ፊርማቸውን አያይዘው መጋቢት 5/2018 ዓ.ም ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ በፃፉት ደብዳቤ፥ የየካቲት ወር ደመወዛቸው ካልተከፈላቸው ስራ እንደሚያቆሙ አሳውቀዋል።
ወርሃዊ ደመወዛቸው ስላልተከፈላቸው የክልሉ ጤና ባለሙያዎችም ደመወዝ ባለማግኘታቸው ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች መጋለጣቸውን በማመልከት ደመወዛቸው በአስቸኳይ እንዲከፈላቸው በማኅበራቸው በኩል ጠይቀዋል።
የትግራይ መምህራን ማህበርም በበኩሉ የየካቲት ወር ደመወዝ በአስቸኳይ እንዲከፈል ጠይቋል።
በትግራይ 137 ሺህ የሚደርሱ የመንግስት ሰራተኞች አሉ።
ቲህቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
መጋቢት 6 ቀን 2018 ዓ/ም

🇪🇹🇦🇪
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ምክትል ፕሬዝዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዱባይ ገዥ ከሆኑት ግርማዊ ሼኽ መሐመድ ቢን ራሺድ አል መክቱም ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ፤ በሁለቱ ሀገራት እና ሕዝቦች መካከል ባለው ጠንካራ፦
- የቢዝነስ፣
- የትምህርት
- የባህል ትስስር ላይ መምከራቸውን ገልጸው " በቀጣይም ከዚች ጠንካራ፣ ጽኑ እና ውብ ከተማ ጋር ያለው ትስስር በቀጣይ ጉብኝቶች ተጠናክሮ ይቀጥላል " ብለዋል።
በሌላ በኩል የዱባይ ሚዲያ ቢሮ ባወጣው መረጃ፤ ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ዙሪያ መምከራቸውንና የኢኮኖሚ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ትብብርን ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መወያየታቸውን አስታውቋል።
በተጨማሪም ውይይቱ ቀጣናዊ ለውጦችን እንዲሁም በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሰላም፣ ደህንነት እና ልማት ላይ ስላላቸው ተጽዕኖ የተዳሰሰበት እንደነበር ቢሮው ጨምሮ ገልጿል።
ፎቶ፦ ይፋዊ የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የዱባይ ሚዲያ ቢሮ X ገጾች
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ/ም

#update
" የሟቾች ቁጥር 107 ደርሷል " - የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር)
⚫ " ከአንድ ወረዳ ብቻ 102 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ የ50 ሰዎችን አስክሬን ማግኘት አልተቻለም። "
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ፣ካምባ እና ቦንኬ ወረዳዎች በደረሰው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ወደ 107 መድረሱን የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ከሟቾቹ መካከል ከጋጮ ባባ ወረዳ ብቻ 102፣ ከካምባ ወረዳ 2 እንዲሁም ከቦንኬ ወረዳ 3 በድምሩ የ107 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስረድተዋል።
ደምሴ (ዶ/ር) እስካሁን በተከናወነው አስቸጋሪ ፍለጋ የ57 ሰዎች አስክሬን መገኘቱንና በጋጮ ባባ ወረዳ የቀሪ 50 ሰዎች አስክሬን እየተፈለገ መሆኑን ገልፀዋል።
የአከባቢው መልካምድር አስቸጋሪ መሆን አስክሬን ፍለጋውን ከባድ ማድረጉን የገለፁት የዞኑ አስተዳዳሪው ጉዳት ለደረሰባቸውና ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ የዕለት እርዳት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ እየተከታተለ ተጨማሪ መረጃ የምያደርስ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#tikvahethiopiafamilyhawassa

" እነ አቶ ጌታቸው 'በዚህ የክስ ሂደት መቆየት ብዙም ትርጉም ስለሌለው ክሱን በዚህ እናቋርጣለን' የሚል ማመልከቻ አስገብተዋል " - አቶ ጣሂር መሐመድ
➡️ " ክሳችንን መቀጠል አስፈላጊ ሆኖ ስላላገኘነው በፍትሃ ብሔር ስርዓት ህግ ቁጥር 278 (1) መሰረት ክሳችንን ሙሉ በሙሉ አንስተናል " - ስምረት ፓርቲ
አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ስምረት ፓርቲ "አወዛጋቢ" ቦታዎችን በተመለከተ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ውሳኔ በመቃወም ምርጫ ቦርድ ላይ ያቀረበው ክስ ማንሳቱን አስታውቋል።
ፓርቲው "በህግ ረገድ መሰረት በሌለው ሰነድ ላይ ተመስርቶ ክርክሩን መቀጠል የክቡር ፍርድ ቤቱን ውድ ጊዜና የህዝብን ሀብት ያለአግባብ ማባከን ሆኖ አግኝተነዋል" ብሏል።
ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየበት ገለልተኛና ህጋዊ አካሄድ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ያለውን "እምነት የሚያጠናክር" መሆኑን የገለጸው ፓርቲው ፣ " በአሁኑ ወቅት ክሳችንን መቀጠል አስፈላጊ ሆኖ ስላላገኘነው በፍትሃ ብሔር ስርዓት ህግ ቁጥር 278(1) መሰረት ክሳችንን ሙሉ በሙሉ አንስተናል " ሲል ገልጿል።
ፍርድ ቤቱ የክስ ማንሻ ማመልከቻውን እንዲቀበል እና መዝገቡ ተዘግቶ ከጉዳዩ እንዲያሰናብተው ፓርቲው ጠይቋል።
ስለጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጻ የሰጡት በክሱ ጣልቃ ለመግባት በሂደት ላይ የነበረው የአብን ፓርቲ አመራር አቶ ጣሂር መሐመድ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ ክሳቸውን ማቋረጣቸውን ዛሬ በችሎት ተገኝተው መስማታቸውን አረጋግጠዋል።
በክሱ " ጣልቃ መግባት የፈለጉት ወደ ስድስት ተቋማት ነበሩ " ያሉት አቶ ጣሂር፣ " ነገር ግን የነአቶ ጌታቸው ስምረት ፓርቲ በጠበቃቸው አማካኝነት ማመልከቻ አለን ብሎ ለዳኛዋ ማመልከቻ ሰጠ " ነው ያሉት።
" አቶ ጌታቸው በማመልከቻቸው 'የፌዴሬሽን ም/ቤትን ውሳኔ አጠቃላይ የፌዴሬሽን ም/ቤቱን ምልዓተ ጉባዔ ሳያሟላ አፈጉባዔው ብቻ የወሰኑት ነው' የሚል ተቃውሞ " የተቀላቀለበት መሆኑን ገልጸው፤ " ነገር ግን በዚህ የክስ ሂደት መቆየት ብዙም ትርጉም ስለሌለው ክሱን በዚህ እናቋርጣለን የሚል ማመልከቻ አስገቡ " ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህ በመነሳት የመሀል ዳኛዋ አስተያየት እንደጠየቁ፣ አብንን ጨምሮ በጣልቃ ገቦቹ በኩል ያሉ አካላት በተለይም የወልቃይት የወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ጠበቃ፣ " 'ከሳሽ ሲከሱ ክሱን ልንከለከል ስንል ባደረግነው እንቅስቃሴ ያወጣናቸው ወጪዎች እንዲከፈሉን' " ሲሉ መጠየቃቸውን ገልጸዋል።
አቶ ጌታቸው ችሎት ቀርበው የነበረው በውክልና መሆኑ በአካል ተገኝተው ክሱን ለመዝጋት እና እግዱን ለማንሳት ለአርብ መጋቢት 5/2018 ዓ/ም ፍ/ቤቱ ቀጠሮ ሰጥቷል ብለዋል።

" የካሜኒ ስም ይቀጥላል ! "
ሞጅታባ ካሜኒን አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ተደርገው ተሾሙ።
የኢራን ከፍተኛ መንፈሳዊ እና ፖለቲካዊ ሥልጣን ያላቸው ባለሙያዎች ጉባዔ ቀጣዩን የኢራን ጠቅላይ መሪ ሾሟል።
በዚህም የቀድሞው የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ ሁለተኛ ልጅ የሆኑትን ሞጅታባ ካሜኒን አዲሱ ጠቅላይ መሪ ሆነዋል።
የ56 ዓመቱ ሞጅታባ ካሜኒ በኢራን ከፍተኛ የፖለቲካ እና የሃይማኖት ስልጣን ያለውን "የበላይ መሪ" ቦታ እንዲይዙ ተመርጠዋል።
ይህ ሹመት የተከናወነው አባታቸው አያቶላ አሊ ካሜኒ በእስራኤል እና በአሜሪካ የአየር ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ ነው።
ምክር ቤቱ ምርጫውን በምስጢር እና በከፍተኛ ጥንቃቄ ሲያካሂድ የቆየ ሲሆን በስተመጨረሻም " የካሜኒ ስም ይቀጥላል " በሚል ሹመቱን ይፋ አድርጓል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ብለው የካሜኒ ልጅ ሹመት "ተቀባይነት የሌለው" ሲሉ የገለጹት ሲሆን አዲሱ መሪ ያለ አሜሪካ ፍቃድ ብዙ ሊቆዩ እንደማይችሉ አስጠንቅቀዋል።
አሜሪካ ከሷ ጋር የሚስማማ የኢራን መሪ በመምረጥ በኩል ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራት ትራምፕ ተናግረውም ነበር።

በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና የተከሰተው ጦርነት በተቀሰቀሰበት ወቅት አንድም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በቀጠናው እንዴት ሊገኝ አልቻለም ?
በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና በተቀሰቀሰው ጦርነት እና አለመረጋጋት ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቀጠናው የሚያደርጋቸውን በረራዎች ለጊዜው ያቋረጠ መሆኑ ይታወቃል።
በወቅቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት ወቅት በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ውስጥ (በአውሮፕላን ማረፊያ) የቆመ ምንም ዓይነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አለመኖሩን አረጋግጦ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ አየር መንገዱ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ቀጠና በሳምንት ከ 100 በላይ በረራዎች የሚያከናውን በመሆኑ በወቅቱ ምንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በቀጠናው እንዴት ሊገኝ አልቻለም ሲል አየር መንገዱን ጠይቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?
" ልክ ጦርነቱ ሲፈነዳ አብዛኛዎቹ አውሮፕላኖቻችን ስኬጁላቸው (Schedule) ወደ አዲስ አበባ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡበት ጊዜ ነበር።
1 አውሮፕላን ብቻ በወቅቱ እስራኤል መሬት ላይ ነበረ ያንን ልክ በምናውቅበት ጊዜ፣ ወዲያውኑ ከእስራኤል ካሉት የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣናት እና የኤርፖርት ባለሥልጣናት ጋር በመነጋገር የእኛን የበረራ ሰራተኞች በአስቸኳይ አምጥተን ያ አውሮፕላን በአንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ እንዲወጣ አድርገናል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁልጊዜ የሚታወቀው ችግሮች ሲፈጠሩ ቶሎ ፈጣን የሆነ ውሳኔ በመስጠት ነው።
ያንን ብናዘገየው ኖሮ አንድ አውሮፕላን እስከ ዛሬ ድረስ እዛ ተዘግቶበት ይቆይ ነበር።
እንደ እድል ሆኖ በወቅቱ ሁሉም አውሮፕላኖቻችን ወደ ኢትዮጵያ በሚመለሱበት ጊዜ ጦርነቱ ቢቀሰቀስም፣ በወቅቱ መሬት ላይ የነበረውንም አውሮፕላናችንን በአጭር ሰዓት ኦፕሬሽኑን ሰርተን ለማምጣት ችለናል " ብሏል።

Comments