ለአስታጥቃቸው ይሁን ስጦታ ሊበረከት ነው
ጥቅምት 7 2019 ዓ.ም የምስጋና መርሀ- ግብር የሚደረግለት የቴአትር ባለሙያ አስታጥቃቸው ይሁን ታሪኩ በዶክመንተሪ ሊሠራ ነው።
ቦሌ ፍላሚንጎ በሚገኘው የህፃናትና ወጣቶች የቴአትርና የሲኒማ ኮምፕሌክስ ከ10 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው በዚህ የምስጋና መርሀ ግብር ስለ ከያኒው ምስክርነት የሚሰጡ ባለሙያዎች የሚታደሙ ሲሆን ልዩ ልዩ የጥበብ ዝግጅቶችም ይኖራሉ ተብሏል።
ተመስጋኙ የኪነ ጥበብ ባለሙያ አስታጥቃቸው ይሁን እና ቤተሰቡ የምስጋና መርሀ ግብሩን እንዲያዘጋጅ ይሁንታቸውን በህጋዊ መንገድ ለተወዳጅ ሚድያ የሰጡ ሲሆን በምስጋና መርሀ ግብሩ እለት ለሚታየው ዶክመንተሪም ቃለ ምልልስና መረጃ ሰጥተዋል።
የአስታጥቃቸው ልጆች ወይዘሮ መልካም አስታጥቃቸው እና የኤሌክትሪክ መሀንዲስ ዮርዳኖስ አስታጥቃቸው እንዳሉት አባታቸው እዩኝ እዩኝ የማይል ሥራውን ግን አድምቶ የሚሠራ ለብዙዎች ተምሳሌት የሆነ ሰው መሆኑን ተናግረዋል።
በቀረፃ ሥራው ወቅት ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን 10 የሚጠጉ የአስታጥቃቸው ኦሪጅናል ስክሪፕቶችን የተመለከተ ሲሆን ወደፊትም ሥራዎቹ መታተም እንዳለባቸው ምክረ- ሀሣብ ቀርቧል።
በአስታጥቃቸው እጅ ከሚገኙ የቲያትር ስክሪፕቶች መካከል ተናጋሪው ዲዳ የተሰኘው የሬድዮ ድራማ የሚገኝበት ሲሆን የፃፈበት ጊዜም 1975 እንደሆነ ታውቋል።ሌላው በሚያዝያ 30 1989 የዛሬ 30 አመት የተፃፈው ባለ 11 ገፅ የሬድዮ ድራማ ባለሱሪው የሚል ርዕስ የሰጠው ነው።ሳልሣዊው ባልንጀራ ባለ 3 ገቢር ተውኔት ሲሆን በ1975 ለእይታ የበቃ ነው።ሌሎች ስክሪፕቶቹም ፍፁም ቅጣት፣ ቅሌት በድንኳን፣ፈታኙ አስክሬን 1985(የሬድዮ ድራማ)፣ቀባሪ ያጣ በድን 1974ባለአንድ ገቢር ድራማ፣ በ1983 የተፃፈው ድርሳነ ፀጋ፣ አንቺን አሉ እናትነሽ በእጁ ከሚገኙ ድርሰቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
በኢትዮጵያ የቴአትርና የጥበብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አሻራ ያሳረፈው ሁለገብ ከያኒ አስታጥቃቸው ይሁንን ለማመስገንና የ69ኛ ዓመት ልደቱን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ከተወዳጅ ሚድያ ጋር በባህር ማዶና በአገር ቤት የሚኖሩ ወዳጆቹ ከፍተኛ ትብብር ያሳዩ ሲሆን በአሁኑሰዓትም መርሀ ግብሩን እውን ለማድረግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ታውቋል።
ከያኒ አስታጥቃቸው ይሁን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1974 ዓ.ም በቴአትር ጥበብ የተመረቀ ሲሆን፣ ይህም ዩኒቨርሲቲው በዘርፉ ማስተማር ከጀመረበት ሁለተኛው ባች (ምሩቃን) ያደርገዋል።
ከተመረቀበት ዓመት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በሥነ-ፅሁፍና ቋንቋ ኤክስፐርትነት የተቀጠረው ከያኒው፣ ላለፉት 37 ዓመታት በጥበቡ ዓለም ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ሀገሩን ህዝቡን በታማኝነት አገልግሏል።
አስታጥቃቸው አጠቃላይ ከ60 በላይ የተውኔት ፅሁፎችን ያበረከተ ሲሆን፣ በርካታ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ድራማዎችን፣ መጣጥፎችን፣ አጫጭር ልቦለዶችንና ግጥሞችን ፅፏል።
አስታጥቃቸው ይሁን ፋንታ ከ1990-1995 ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤትን በዋናሥራ አስኪያጅነት ያገለገለ ሲሆን በሥነ ምግባሩ እና በትህትናው በብዙዎች የሚወደድ የጥበብ ሰው እንደሆነ ይታወቃል።
በዚህ መርሀ ግብር ላይ ታላላቆች የቴአትር ፈርጦች አያልነህ ሙላት፣ ጌትነት እንየው፣ ተስፋዬ ሲማ ፣ ተፈሪ አለሙ እና ሌሎችም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እንደሚገኙ ተነግሯል ።
በምስጋና መርሀ ግብሩ ላይ ለከያኒው ለየት ያለ ስጦታ እንደሚበረከትለት ታውቋል።

8 hours ago