1 day ago
የኢትዮጵያ የውጭ ፖሊሲ የሽግግር ምዕራፍ
**************
የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ታሪክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ነጻነቷንና ሉዓላዊነቷን ከማስከበር ባለፈ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ውስጥ ቀደምትና ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቅ ቢሆንም፣ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች የሀገራችን የውጭ ፖሊሲ ከውስጣዊ ደኅንነትና ሉዓላዊነትን ከማስከበር ባሻገር ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን በሙሉ አቅም ለመጠቀም ውስንነቶች ነበሩበት።
በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን የውጭ ፖሊሲው በዋናነት የምዕራባውያንን ድጋፍ በማጠናከርና ሉዓላዊነትን በማስከበር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ በደርግ ዘመን ደግሞ የሶቭየት ኅብረትን የርዕዮተ-ዓለም ካምፕ በመከተል በደኅንነትና የወታደራዊ ትስስር ላይ ያተኮረ አካሄድን ይከተል ነበር።
ከ1983 ዓ.ም በኋላ የወጣው ፖሊሲ ደግሞ ድህነትን መዋጋትን ዋና መሠረት በማድረግ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲንና የጎረቤቶች ሰላምን ማዕከል ያደረገ ቢሆንም፣ የዓለም አቀፍ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች መለወጥ፣ የጂኦ-ፖለቲካ ፉክክር መጨመር እና የሀገር ውስጥና የአካባቢው ለውጦች ፖሊሲውን ማሻሻልና ማሳደግ አስፈላጊ አድርገውታል።
በቅርብ ዓመታት ደግሞ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በቀጥታ ከዓለም አቀፍ ተቀባይነት ፍለጋ በመውጣት፣ በክልላዊና ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ንቁ አጀንዳ ሰጭነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ዲፕሎማሲያዊ ሚና ወደ መጫወት ተሸጋግሯል።
ዓለም ከአንድ ወገን የበላይነት ወደ ባለብዙ ወገን መሸጋገሯ ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አቅጣጫዎቿን እንድታሰፋና የፖሊሲ አማራጮቿን እንድታበዛ ያስገደዳት ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ፍላጎትን ለማሟላት፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግና የኃይል ሽያጭን ጨምሮ ክልላዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር አዲስ አቀራረብ ተከትላለች።
በዚህም መሠረት ቀደም ሲል ከነበራት በተወሰኑ ምዕራባውያን ወይም ታላላቅ ኃይሎች ላይ የተመሠረተ ግንኙነት በመውጣት፣ ከሁሉም ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ተግባራዊ የዲፕሎማሲ አቅጣጫ መከተል ጀምራለች።
የዚህ የውጭ ፖሊሲ ትልቁ የስኬት ማሳያ ሀገራችን የብሪክስ አባል መሆኗ ሲሆን፣ ይህም በዓለም አቀፍ የፋይናንስና የንግድ ሥርዓት ውስጥ ድምጿ እንዲሰማ፣ ከአስደናቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለቤቶች እንደ ቻይና፣ ህንድ፣ ብራዚልና ሩሲያ ጋር ያላትን ትስስር እንድታጠናክርና አማራጭ የልማት ፋይናንስ ምንጮችን እንድታገኝ በር ከፍቷል።
በሌላ በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅና ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀንድ የንጹሕ ኃይል አቅርቦት ማዕከል ያደረጋት ሲሆን፣ ለሱዳን፣ ጂቡቲ እና ኬንያ እየቀረበ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል የቀጣናውን የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከሩ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሀገራት ዘንድ ያላትን ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት አሳድጎታል።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የተመጣጠነና የብዙ ወገን ዲፕሎማሲ በመከተል በታላላቅ ኃይሎች ፉክክር ውስጥ ገለልተኝነቷንና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ እየሠራች ትገኛለች።
የብሪክስ አባልነት፣ የኢኮኖሚና የኃይል ዲፕሎማሲ እንዲሁም በቀጣናው የሚደረጉ የሰላም ማስከበር እንቅስቃሴዎችም ብሔራዊ ጥቅሟን ከቀጣናዊ ትስስር እና ከዓለም አቀፍ ትብብር ጋር አጣጥማ በመጓዝ የጀመረችውን የአጀንዳ ሰጭነት ሚና አጠናክራ እንድትቀጥል የሚያስችሏት ናቸው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopianforeignpolicy #brics #gerd #የመደመርመንግሥት

Comments