Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዘለንስኪ የትራምፕን ውሳኔ ‹‹ለአጋሮቻችን የማይጠበቅና ደካማ ነው›› አሉ፡፡ ፕሬዝደንት ትራምፕ በትላንትናው እለት ከሩሲያው አቻቸው ጋር በስልክ ከተወያዩ በኋላ አንድ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ስምምነትም ሩሲያ በሚሊዮን ቶን የሚቆጠር ነዳጅ ለአሜሪካና ለተቀረው አለም እንድታቀርብ የሚያስችል ነው፡፡ በስምምነቱ መሰረት ሩሲያ በፍጥነት 300,000 ቶን ነዳጅ ማቅረብ የሚጠበቅባት ሲሆን እስከ ኖቬምበር 1 ደግሞ ተጨማሪ 500,000 ቶን ለማቅረብ ተስማምታለች፡፡

ከዚያም በአጭር ጊዜያት ውስጥ ሌላ አንድ ሚሊዮን ቶንና ቀጥሎም 3 ሚሊዮን ቶን ነዳጅ እንደምታቀርብ ስምምነቱ ያሳያል፡፡ ይህንን ስምምነት በተመለከተ ፕሬዝደንት ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ ‹‹የነዳጅ ዋጋ ከእንግዲህ እየወረደ ይመጣል›› በማለት የፃፉ ሲሆን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ደግሞ ‹‹እውነት ለመናገር ፑቲንን አመሰግነዋለሁ›› ብለዋል፡፡ ይህ ውሳኔ የዩክሬይኑን ፕሬዝደንት ዘለንስኪን እጅግ አስቆጥቷል፡፡ ውሳኔው ይፋ ከሆነ ከደቂቃዎች በኋላ በማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ ‹‹ከአጋሮቻችን የማይጠበቅ ደካማ ውሳኔ ነው›› በማለት ፅፈዋል፡፡

እርምጃውንም ‹‹ለፑቲን የቀረበ ስጦታ ነው›› በማለት አጣጥለውታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ሩሲያ በዩክሬይን ላይ በፈፀመችው ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ይህንን በተመለከተ ዘለንስኪ በማህበራዊ ሚዲያቸው ‹‹ፑቲን ትላንት ለፈፀመው ስምምነት ዩክሬይንን በመደብደብ አመሰግናለሁ ብሏል›› በማለት ገልፀዋል፡፡

21 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.