18 hours ago
Harar Jugol – The Living Museum
ሐረር ጁጎል – ሕያው ሙዚየም
#ethiopia | ሐረር በየዕለቱ ሰላም፣ መቻቻል እና አብሮነት የሚኖሩባት ከተማ ናት።
ሐረር በዓለም ላይ ሦስት የዓለም ቅርስ እውቅናዎችን ያጎናጸፈች ልዩ ታሪካዊ ከተማ ናት።
መዲናቱል አውሊያ – የቅዱሳን ከተማ
የምሥራቅ አፍሪካ ቲምቡክቱ
የታሪካዊው የአዳል ሱልጣኔት ዋና ከተማ
የምሥራቅ አፍሪካ ታሪካዊ የንግድ ማዕከል
በእስልምና ዓለም አራተኛዋ ቅድስት ከተማ በመሆን የምትከበር
የድሮውና የዘመናዊው ዓለም የሚገናኙባት ልዩ ከተማ
የሐረርን የበለጸገ ታሪክ፣ ባህል፣ ልዩ የስነ-ሕንፃ ቅርስ እና እንግዳ ተቀባይነት ለመመስከር ይጎብኙ። በየአደባባዩ ታሪክ ይነገራል፤ እያንዳንዱ ጉብኝትም የማይረሳ ተሞክሮ ይሆናል።
Harar is the City of Peace, Tolerance, and Solidarity, where these values are lived every day.
A rare city embraced by three UNESCO World Heritage recognitions, Harar is a treasure unlike any other.
Harar Medinat al-Awliya – The City of Saints
The Timbuktu of East Africa
Former capital of the Adal Sultanate
A historic center of East African trade
Revered as the fourth holiest city in Islam
Where the old meets the new in perfect harmony
Visit Harar to discover its rich history, vibrant culture, remarkable architecture, and warm hospitality. Every corner tells a story, and every visit becomes an unforgettable experience.
ሐረር በዩኔስኮ (UNESCO) በአንድ የዓለም ቅርስነት ዕውቅና የተሰጠው ሲሆን ይህም "ሐረር ጁጎል፣ የተመሸገች ታሪካዊ ከተማ" በመባል ይታወቃል። እ.ኤ.አ. በ2006 "ሐረር ጁጎል፣ የተመሸገች ታሪካዊ ከተማ" በሚል ኦፊሴላዊ ስም በዓለም ቅርስነት መዝገብ ውስጥ ሰፍሯል።
ይህ ስፍራ አንድ የዓለም ቅርስ ቢሆንም፣ ዩኔስኮ ለዚህ ቦታ "የላቀ ሁለንተናዊ እሴት" (Outstanding Universal Value) የሰጠው በሦስት ዋና ዋና የባህል መስፈርቶች (iv እና v) ላይ በመመስረት ነው።
1. ልዩ የሕንፃ ጥበብ ውህደት
ሐረር የአፍሪካ እና የእስልምና ወጎች ያልተለመደ ውህደትን ትወክላለች። የከተማዋ አቀማመጥ እና የ"ሐረሪ" ቤቶች ዲዛይን—በመሃል ላይ በሚገኙ ግቢዎች እና ውስጣዊ ግድግዳዎቻቸው ላይ በሚታዩ ውስብስብ እና ያሸበረቁ የእንጨት ቅርጻ ቅርጾች የሚታወቁ—በክልሉ ከሚገኙ ሌሎች የእስልምና ከተሞች የተለዩ ያደርጓታል። ይህም የኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች እና የሰፊው የእስልምና ዓለም ለዘመናት የነበራቸው መስተጋብር ውጤት የሆነ ልዩ ማንነትን ፈጥሯል።
2. ልዩ የሆነ የሃይማኖት ፋይዳ
ብዙውን ጊዜ በእስልምና አራተኛዋ የተቀደሰች ከተማ ተብላ የምትጠራው (ከመካ፣ ከመዲና እና ከኢየሩሳሌም በመቀጠል)፣ ሐረር ትልቅ መንፈሳዊ ማዕከል ናት። በከተማዋ ግንብ ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ የሃይማኖት ስፍራዎች ይገኛሉ፦
ሦስቱ ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የቆዩትን ጨምሮ 82 መስጊዶች።
ለአካባቢው ቅዱሳን እና እስላማዊ ታላላቅ ሰዎች የተገነቡ 102 መቃብሮች (ሸሪዎች)።
3. "ሕያው" የሆነ ታሪካዊ የከተማ ገጽታ
እንደ ብዙዎቹ የቅርስ ስፍራዎች ሳይሆን፣ ሐረር የመካከለኛው ዘመን የከተማ አወቃቀሯን በመጠበቅ እንደ ዘመናዊ የባህል ማዕከል የምታገለግል "ሕያው" የቅርስ ከተማ ናት። በ13ኛው እና በ16ኛው ክፍለ ዘመን መካከል የተገነባው "ጁጎል" (የመከላከያ ግንብ)፣ አሁንም የድሮዋን ታሪካዊ ከተማ ይከብባል። ይህም የባህላዊ ማህበራዊ አደረጃጀትን፣ የመንገድ አቀማመጥን እና ቀደም ሲል ኢትዮጵያን ከአረብ ባሕረ ገብ መሬት እና ከዓለም ገበያዎች ጋር ያገናኙ የነበሩ ጥንታዊ የንግድ መስመሮችን ጠብቆ እንዲቆይ አድርጓል።
ሐረር በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ዘጠኝ የዓለም ቅርስ ቦታዎች አንዷ ነች። ሌሎችም የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የስምየን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የአክሱም ሥልጣኔ፣ የፋሲል ግቢ (ጎንደር)፣ የአዋሽ ሸለቆ፣ የታችኛው ኦሞ ሸለቆ፣ የቲያ ሐውልቶች እና የኮንሶ የባህል መልክዓ ምድር ይገኙበታል።
Harar is officially recognized by UNESCO as a single World Heritage site: Harar Jugol, the Fortified Historic Town. It was inscribed on the World Heritage List in 2006 under the official name Harar Jugol, the Fortified Historic Town.
While it is a single site, UNESCO’s recognition is based on three primary cultural criteria (iv and v) that define why it holds "Outstanding Universal Value":
1. Unique Architectural Synthesis
Harar represents an exceptional fusion of African and Islamic traditions. Its urban layout and "Harari" house designs—characterized by central courtyards and intricate, colorful interior woodwork—are distinct from other Islamic cities in the region. This creates a unique architectural identity resulting from centuries of interaction between the Ethiopian highlands and the wider Muslim world.
2. Exceptional Religious Significance
Often described as the fourth holiest city in Islam (after Mecca, Medina, and Jerusalem), Harar serves as a major spiritual center. Within its walls, the city contains an extraordinary concentration of religious sites:
82 mosques, three of which date back to the 10th century.
102 shrines dedicated to local saints and Islamic figures.
3. A "Living" Historic Urban Landscape
Unlike many archeological sites, Harar is a "living" heritage city that has preserved its medieval urban fabric while functioning as a modern cultural hub. Its "Jugol" (defensive wall), built between the 13th and 16th centuries, still encloses the historic old town, maintaining the traditional social organization, street patterns, and ancient trade routes that once connected Ethiopia to the Arabian Peninsula and global markets.
Harar is one of nine total recognitions in the country. The others include the Rock-Hewn Churches of Lalibela, the Simien Mountains National Park, the Kingdom of Aksum, Fasil Ghebbi (Gondar), the Lower Valley of the Awash, the Lower Omo Valley, the Tiya Stelae, and the Konso Cultural Landscape.
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#visitharar #hararjugol #ethiopia #unesco #heritage #culture #tourism #landoforigins #ሐረር #የዓለም_ቅርስ #ቱሪዝም

3 days ago
“ታሪክ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም-የነፍስ መገለጥ እንጂ”
ጋዜጠኛ ዮናስ አየለ እንደጻፈው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአሚኮ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ አዳምጬ እንደጨረስኩ በቃለ ምልልሱ በርዕሰ ጉዳይ ደረጃ ጎልተው ከወጡ ዋና ዋና ጭብጦች መካከል አንዱ ነገረ ታሪክ እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ታሪክ-የሀገር ውስጥና የውጭ፤ የሩቅና የቅርብ ዘመን! ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያንጸባረቁትን ሚዛናዊና አምክኖአዊ የታሪክ እይታና ድምዳሜያቸውን አለማድነቅ ንፉግነት ነው፡፡ የአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዛዊ የታሪክ ጸሐፊና ፖለቲከኛ ሎርድ አክተን “History is not a burden on the memory but an illumination of the soul” ብሎ ሲጽፍ “ታሪክ የነፍስ መገለጥ እንጂ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም” ማለቱ ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ አንኳር ጉዳዮች እስከዛሬ ድረስ በሀገራችን የታሪክ አጻጻፍ(Historiography) እና በሕዝባዊ ትርክቶቻችን(በሚዲያዎችን ጭምር) በሚገባቸው ልክ ያልተወሱ፤ ቢወሱም ፈራ ተባ እየተባሉ የሚጠቀሱ፤ አለፍሲልም ባልተገባ የፖለቲካ እይታ ደንቃራ ተደርገው የተወሰዱ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of the history) ሆነው የኖሩ ስብራቶቻችን ነበሩ፡፡ ከነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ዋነኛዎቹ አንዱ የሕዝቦች ትስስር እና መስተጋብር ታሪክ ሲሆን ሌላኛው በአገረ መንግስት ምሥረታ ውስጥ የሸዋ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ሚናን የተመለከቱት ናቸው፡፡
በመጀመሪያ የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች በኩታ ገጠም ቀዬዎቻቸው እና የታሪክ እድል በፈጠረላቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የባህል አጋጣሚዎች እንደሌሎች ማህበረሰቦች ሁሉ መጋባት መዋለዳቸው፤መተሳሰር መዋሀዳቸው ሀቅ የመሆኑን ያህል የታሪክ ጥናት እና የትርክቶቻችን ማጠንጠኛ አለመሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ በባሰ ሁኔታ ደግሞ በነገሥታቱ መካከል የነበረው የፖለቲካ ጋብቻና የመሪዎቻችን ማህበራዊ መሠረት ጉዳይ ነውር እስኪመስል በእውነታው ልክ ሳይጠናና፣ሳይነገርለት ዘመናት አልፈዋል ፡፡ በሌላ በኩል በሸዋና አካባቢው ለረዥም ዘመን የኖሩ ሕዝቦች በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት የተጫወቱት ሚናና የሚጋሩት ቀደምት የሥልጣኔ ባለቤትነት (ታሪክ ሰሪነት-Agency) ግጥምጥሞሽ በሀገር መሪ ደረጃ መወሳታቸው እጅግ ጉልህ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ እውነታዎች ያለጥርጥር ታሪካችንንና የታሪክ ምልከታችንን ደጋግመን መመርምር እንዳለብን የሚያስገነዝቡና የወገንተኝነት ጥያቄ በሚነሳባቸው ሃይማኖታዊ የታሪክ ምንጮች እንኳን የተቀመጡ ገሃድ እውነታዎች ናቸው፡፡ መመርመር ለሚፈልግ አጥኚ እነዚህ የታሪክ እውነታዎች በየነገሥታቱ ዜና መዋዕሎች (የዐጼ አምደ ጽዮን፣ ዐጼ ሱስንዮስ፣የዐጼ ገላውዲዮስ፣ የዐጼ ሠርጸ ድንግል ወዘተ)፤ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የታሪከ ነገሥት ቅጂዎች፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ አውሮፓውያን ተጓዦችና ጸሐፊያን (ፍራንስስኮ አልቫሬዝ፣ ፔድሮ ፔዝ፣ ማኑኤል አልሜዳ፣ ጄሮኒሞ ሎቦ፣ ጀምስ ብሩስ፣ ኮንቲ ሮሲኒ ወዘተ ) መዝግበው በተውልን ሰነዶች ሰፍረው የምናገኛቸው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ ቱባ መረጃዎች ናቸው፡፡
ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ የተወልን የጽሑፍ ሰነድና ሌሎች ሀገርኛ የቃል መረጃ ምንጮች ዐፄ ልብነድንግል(1498-1532 ዓ.ም.) እንደ መሪ የአማራና የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ምናልባትም የሌሎች ሕዝቦችም ማህበራዊ ዳራ የነበራቸው ንጉሠ ነገሥት እንደሆኑ የሚያስረዱ ሲሆን አልቫሬዝ የንጉሱ የእናት ወንድም የነበሩት አጎታቸው ዶሪ ባህረ ነጋሽ ኦሮሞ እንደነበሩና ባህረ ነጋሽ ዶሪ ሲሞቱ ሥልጣኑ በቀጥታ ወደልጃቸው ቡሎ መሸጋገሩን ጭምር በአይኑ ያየውን ጽፏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በትኩረት መታየት የሚገባው ጉዳይ ስለዐጼ ልብነ ድንግል የጦር አዛዦች የተነገሩ የቃል መረጃዎች ናቸወ፡፡ ከእነዚህ መካከል የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት የቦረንትቻ ባሕል ያውቅ እንደነበር በተክለጻዲቅ መኩሪያ መጻፉና ከዐጼ ልብነድንግል የጦር አዛዦች አንዱ የነበረው ቱሉ ደገልሀን በመራው ከኢማም አሕመድ ጋር የተካሄደ ጦርነት የዐጼው ጦር ሲያፈገፍግ ንጉሠ ነገሥቱ “ሁሉም ቢፈራ ቱሉ እንዴት ፈራ? ” ማለታቸው ስለሠራዊታቸው ሥብጥር የሚነግረን ነገር አለ፡፡
ኦቶማን ቱርኮችን እና የዘመኑ ተላላኪዎቻቸውን ለመዋጋት የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት አንድ አካል ሆነው እስከ ኤርትራ ድረስ ዘምተው ስለነበሩ የኦሮሞ ተዋጊዎች ተጋድሎ የዐጼ ሠርጸድንግል(1542-1590 ዓ.ም.) ዜና መዋእል በግልጽ አስፍሯል፡፡ እነዚህ የኦሮሞና የሌሎች ሕዝቦች ተወላጅ ወታደሮች ትግራይ እንጢጮ አካባቢ ያካሄዱትን አውደ ውጊያ ዜና መዋዕሉ ይተርካል፡፡ ለመንግሥታቸውና ለሀገራቸው እስከባሕር ጠረፍ ድረስ ዘምተው ዋጋ መክፈላቸውም ተመዝግቧል፡፡ የዐጼ ሱስንዮስ(1607-1632 ዓ.ም.) ዜና መዋእል እና በዘመኑ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ የአውሮፓ(የፖርቱጋል) ተጓዦች የጻፏቸው የመረጃ ምንጮች ንጉሠ ነገሥቱ ግንደበረት፣ሐምቦና አካባቢው ቤታቸው እንደነበር፤ አጎታቸው ለማሞ እንደሚባል፣ ወላጅ እናታቸው(ሐመልማል ወርቅ) የአዛዥ ኩሎ ልጅ የነበረች፤ የዚሁ የሐመልማል ወርቅ ጎሳ ተወላጅ የሆነ ቡኮ የተባለ ኦሮሞና ሠራዊቱ ለአባይ ቅርብ የሆነች ምዕራብ ሸዋ ላይ ዐጼ ሱስንዮስ ሲያገኙት የነበረውን ደስታና የፍቅሩን ጽናት ዜና መዋዕሉ ሳይሰስት ጽፎታል፡፡ ዐጼ ፋሲል(ከ1632 እስከ 1667 ዓ.ም.) አባቱ ሱስንዮስ እናቱ የወሎ ቃሉ ሰው(እቴጌ ሥልጣን ሞገሳ የሚል ስም የተሰጣት) እንደሆነች የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1620ዎቹ ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ፖርቱጋላዊ ቄስ ጄሮኒሞ ሎቦ ስለዐጼ ፋሲል እናትና ኦሮሞ ዘመዶቻቸው በአይን ምስክርነት የሚያውቀውን ጽፏል፡፡ የእቴጌ ሥልጣን ሞገሳ አያት ስለብዝሀ ሃይማኖት አስፈላጊነት የነበራቸውን ግልጽ ፖሊሲ ጭምር ሎቦ ዘግቦታል፡፡ የዐጼ በካፋ(1721-1730 ዓ.ም.) እና የዐጼ ኢዮአስ(1747-1761 ዓ.ም.) ጎንደር መቼም ለሕዝቦች ውህደትና ትስስር ጥሩ ማሳያ ነበረች፡፡ የየጁ ኦሮሞ ገዢ የነበረው የአሚቶ ሴት ልጅ ዝነኛዋ ውቢት ልጇ ዐጼ አዮአስ ነበር፡፡ ኢዮአስ ከኦሮሞ አጎቱ ከደጃች ሉቦ ጋር ሥልጣኑን በጎንደር እንዴት እንዳጸና፤ የቤተ መንግሥቱም የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ እንደነበረ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕልና በጀምስ ብሩስ ቅጽ ሁለት መጽሀፍ የተመዘገቡ የታሪክ መረጃዎች ያስረዱናል፡፡
መነሻውን ወሎ በማድረግ ጎንደር ጸንቶ የኖረው የየጁ ሥርወ መንግሥት(ወረ ሼኮች) መሥራቾች የመርሳው አባ ጌትዬ፣ የልጃቸው ጓንጉል አባ ሴሩ እንዲሁም የልጅ ልጃቸው የራስ አሊ ጓንጉል(አሊ ትልቁ) ታሪክ በኢዮአስ ዜና መዋዕል፣ በጀምስ ብሩስ መጽሐፍና በሌሎች በርካታ ሰነዶች ታሪካቸው ተዘግቧል፡፡ በኋላ ላይ በሽፈራው በቀለ(ፕሮፌሰር) እና ሞላ ትኩዬ የቀረቡ ጥልቅ ጥናቶች ይህን እውነት በዝርዝር ያስረዱናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው እንደጠቀሱት የእነዚህ መሪዎች የፖለቲካ ጋብቻ ታሪክ የሚያሳየን በሄዱበት አገር ሁሉ የሕዝቦች ትሥሥር እና የፖለቲካ ጋብቻ የኖረ ታሪካችን እና የጉልበታችን ምንጭ እንደነበረ ነው፡፡ በዳግማዊ ዐጼ ቴዎድሮስ ዘመን የተጻፉ የታሪክ ሰነዶች የወሎዋ ገዢ ወርቂቱ ወዳጆ(የማመዶች ሥርወ መንግሥት መሪ የኢማም አሊ አባ ቡላ ባለቤት) ንጉሥ ምኒልክ ከመቅደላ እስር ቤት እንዲያመልጡ ያደረጉ፤ አጃቢ ሠራዊት አሰማርተው ምኒልክን እስከሸዋ የሸኙ እንደነበሩ በዋናነት ከጸሓፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ ታሪከ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ ዜና መዋዕል እና በመቅደላ አምባ እስር ላይ የነበሩ አውሮፓውያን ከጻፏቸው መረጃዎች እንረዳለን፡፡
ሥልጣኔዎቻችን ሁሉ ተደምረን ያሳካናቸው እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው አንስተዋል፡፡ የዐድዋ ዘመቻና ድሉ ለዚህ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተጨባጭ የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1888 ዓ.ም. ለዓድዋ ዘመቻ ከመላው ኢትዮጵያ የተመመው ሠረዊት ወፍላ ላይ የነበረው ሠልፍ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል እንኳን እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ “የመኳንንቱ የጦር መሣሪያ፣ወርቁ፣ ጣፋ፣ ብሩ፣ ሙጣው፣ ጫሜው፣ ሎሚታውና ኩፊታው፣ ከሌቻው፣ ወርቅ ለምዱ እንደጸሐይ ሲያበራ ዋለ፡፡” እንደጸሐይ የበራውን ሕብረ ባሕልና ሕብረ ማንነት ትርክቶቻችን በልኩ አጉልተው ያውቃሉ?
ሸዋና አካባቢው(ወሎን ጨምሮ) እንደ አንድ ጂዞ ስትራቴጂ ሥፍራ የሕዝቦች ውህደትና ትስስር መሠረት ሆኖት የመልክዓ ምድር መገኛው ለግብርና እና ለውጭ ንግድ የተመቸ በመሆኑ በኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ታሪክ ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው መግቢያ አስታውሰውናል፡፡ ሸዋና አካባቢው ከመንግሥታት ምስረታ ጋር በተገናኘ ከዘጠነኛው አንስቶ እስካሁን ያለው ረዥም የታሪክ ጉዞ በርግጥም ሊነገር፣ ሊተነተን የአደባባይ ትርክት አካል ሊደረግ የሚገባው እውነት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሸዋ ሡልጣኔት ምስረታ( እ.አ..አ.896 ዓ.ም.) እስከ ዓድዋ ድል(1888 ዓ.ም.) ሥላወሷቸው የአርጎባ(የወላስማ/ወሊ አስማ ሥርወ መንግሥት)፣ የአማራ(ሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት)፣ ኦሮሞ(ቱለማው በተለይ)፣ወርጂ፣ ጉራጌ፣ ጋፋት፣ ወዘተ ሕዝቦች ትስስርም ይሁን የፖለቲካ ጋብቻ የተመለከተ ታሪክ ከበቂ በላይ የታሪክ ማስረጃ ምንጮች ቢኖሩንም በታሪክ ግርዶሹ ምክንያት የወል ትርክት አካል መሆን አልቻለም፡፡
ኤንሪኮ ቼሩሊ ከሐረር አግኝቶ ያሳተመው በአረብኛ የተጻፈው የሸዋ ሡልጣኔት ዜና መዋዕል እንደሚያመለክተው ሡልጣኔቱን እ.አ.አ. በ896/7 የመሰረቱት የማህዙሚ ጎሳ አባላት ናቸው፡፡ መንግሥታቸውም ከ9ኛው እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በተከታታይ በገዙ አሥራ አራት ሱልጣኖች እንደጸና የታሪክ መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ የሸዋ ሙስሊም ሡልጣኔቱ መቀመጫ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ 70 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኝ ወለላ የተባለች ሥፍራ እንደነበረች የጆርጅ ደብሊው ቢ ሀንቲንግፎርድ(1989) ጥናት ያመለክታል፡፡ የማህዙሚ ሥርወ መንግሥት ከመጨረሻዎቹ መሪዎች አንዱ የነበረው ሡልጣን ድልመራህ ወርጂዎች የይኖሩበት በነበረው አካባቢ በ1270ዎቹ በነበረ የርስ በርስ ጦርነት ድል ሳይቀናው ሲቀር ሕይወቱን ለማትረፍ ዐጼ(የአማራ ገዥ?) እንደሄደ ይህው የአረብኛ ዜና መዋእል ያስረዳል፡፡ የማህዙሚዎች የሸዋ ሡልጣኔት የተተካው በዋናነት የአርጎባዎች አገር በሆነው ይፋት(ዊፋት) ላይ በወላስማዎች ነበር፡፡ ወላስማዎች ከአጎራባቾቻው ጋር እየተጋቡ፣ እየተስማሙም እየተጋጩም የይፋት ሡልጣኔትን ከ13ኛው እስከ 15ኛው ክፍለ ዘመን ከሸዋ እስከ ምሥራቃዊ የኢትዮጵያ ጠረፍ እንዳስተዳደሩ ስፍር ቁጥር የሌለው የሰነድ( የኢብን ካልዱን ተማሪ የነበረው አል ማቅሪዚ ጽሑፍ- ኪታብ አል ኢልማም)፣ የአርኪዮሎጂና የቃል መረጃ ምንጮች አሉ፡፡
መነሻውን ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ያደረገው የክርስቲያኑ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት በአካባቢው ያሉ ሕዝቦች ተዋህደው ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጋራ የመሠረቱት እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡ አማራዎች፤ አርጎባዎች፣ ወርጂዎች፣ ጋፋቶች፣ ጉራጌዎች እና ኦሮሞዎች፣ አፋሮች፣ ሐረሪዎች ወዘተ በዚህ የሸዋ መንግሥታት የተጽዕኖ ምህዳር(Orbit) ውስጥ እንደሚገኙ ዜና መዋእሎች፣ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የአርኪዮሎጂ ማስረጃዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ የቃል መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ ለምሳሌ ታደሠ ታምራት(ፕሮፌሠር) ከ13ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያንና መንግሥትን ግንኙነት ታሪክ ባጠኑበት መጽሐፋቸው የገላንና ያያ ሰዎች ሸዋ ውስጥ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በኦዳ ዛፍ (ኮቢል የሚባል ዋርካ) ሥር ሃይማኖታዊ ሥርዓት ይፈጽሙ እንደነበር ገድለ አቡነ ቀውስጦስን ጠቅሰው ጽፈዋል(ገጽ 184)፡፡ ሸዋ የባለ ብዙ ማንነት ሕዝቦች ሀገር ከመሆኗ ባሻገር በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች ላይ መረጃ የተወልን መነኩሴው አባ ባህሪይ እንደገለጸው “ሸዋ የመንግሥት ሀገር ነች” (ገጽ 130)፡፡ በየዘመናቱ ከሸዋ የተነሱ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ፈረሰኛ ሠራዊታቸውን ይዘው በሰሜን እስከ ኤርትራ(በዐጼ ሠርጸ ድንግል ዘመን- የኤርትራዋ ባሬንቱ የዚህ የታሪክ ሂደት ውርስ አይደለችም ማለት አይቻልም፡፡) በምሥራቅ እስከ ዘይላ(ከዐጼ አምደጽዮን እስከ ገላውዲዮስ ዘመን)፣ በምዕራብ እስከ ሱዳን ፋዞግሊ(ዐጼ ሱስንዮስ ዘመን) በደቡብ እስከ ሞያሌ ተንቀሳቅሰው በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫተዋል፡፡
እነዚህ የሸዋ እና አካባቢው ሕዝቦችና ገዢዎች ትልቁን ንቅናቄያቸውን ያደረጉት ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዐጼ ምኒልክና ራስ ጎበና ዳጬ የቱለማ ኦሮሞ፤ የሸዋ አማራ እና የሌሎችም ውህድ የሆነ ጦራቸውን አዝምተው ወሎ ወግተው ወረኢሉን የመንሥታቸው መቀመጫ ያደረጉት አርሲ፣ወለጋ፣ከሐረር ከመዝመታቸው በፊት ነበር፡፡ የመጫ ኦሮሞ ተወላጁን የጎጃሙን ንጉስ ተክለሃይማኖት(አዳል ተሰማ) በቱለማው መሪ ራስ ጎበና ዳጪ እምባቦ ላይ ያስገበሩት የጂኦ ፖለቲካዊ እና የሕዝቦች ትስስር እድሎች ጉልበት ፈጥሮላቸው፤ ኃይል አጎናጽፏቸው እንጂ በአጋጣሚ አይደለም፡፡ በርግጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፖለቲካችን ደንቃራነት የፈጠረውን የታሪክ ግርዶሽ ያሸነፉ ፋና ወጊ ጥናቾች መውጣት ጀምረዋል፡፡ አንዱ “Invisible Actors: The Oromo and the Creation of Modern Ethiopia(1855-1913)” በሚል ርዕስ በብሪያን ጀምስ ዬትስ(2002) በኤሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ ከተጠናው እጅግ ጠቃሚ የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ጥናት ሲሆን ሌላው የደቻሳ አበበ(ዶ/ር) ጎበና ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው የዘመናዊት ኢትዮጵያን እውን መሆን ያለ ምኒልክና ያለ ጎበና እንደማይታሰብ ሲጠቅሱ ይህንን እውነታ ማጉላታቸው ይመስለኛል፡፡
የሕዝቦች ትስስርና የፖለቲካ ጋብቻ በአማራና በኦሮሞ ሕዝብ መስተጋብር ብቻ የታጠረ አልነበረም-ሊሆንም አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥልጣኔ መጋመዱ ረቂቅ ነው፡፡ ከጥንታዊ አክሱም ዘመን ጀምሮ በዝነኞቹ የአክሱም መቃብር ሀውልቶች እና በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከምናገኛቸው የኪነ ሕንጻ ትእምርቶች(Symbols) መካከል የውሸት በሮች (False Doors) እና የውሸት መስኮቶች(False windows) የሙታን መንፈስ(ኤከራ) መመላለሻ እንደሆኑ በጥናት የተረጋገጠ ነው (ቢትራይስ ፕሌይን Annales d'Éthiopie 1965) ፡፡ ይህ የኤከራዎች መመላለስና የመነጋገር ባህል እና እምነት ከደቡባዊ ግብጽ አንስቶ እስከ ሰሜን ኬንያ ድረስ በሚኖሩ የኩሽ ሕዝቦች በሰፊው የሚታወቅ ረዥም ዘመን ያስቆጠረ ልምምድ ነው፡፡
ሌላው በልኩ ያልተጠና እና በትርክቶቻችን ውስጥ ትኩረት ያልተሰጠው በሕዝቦች መካከል ያለ ሥልጣኔ ትስስር ታሪክ የእያንዳዱን የዛግዌ ነገሥታት የሥልጣን ዘመናትን የተመለከተ ነው፡፡ ከታሪክ ነገሥት፣ ከልዩ ልዩ ዜና መዋዕሎች፣ ከፖርቱጋል ተጓዦች(ፓኤዝና አልሜዳ) ከብሪቲሽ ሙዝየም እንዲሁም ከኮንቲ ሮሲኒ የተገኙት ምንጮች የሚረጋግጡት የሁሉም የዛግዌ ዐጼዎች( ከአንድ ሁለቱ በስተቀር) የሥልጣን ዘመን 40፤40 ዓመታት ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ በኦሮሞ የገዳ ሥርዓት የአንድ ትውልድ የሥልጣን ዑደት ጋር አንድ አይነት የሆነው በአጋጣሚ ነው ወይስ ዛግዌዎች እና ኦሮሞዎች የኩሽ ሕዝቦች በመሆናቸው ቀዳሚ ከሆነው የጋራ ሥልጣኔያቸው የሚቀዳ የአስተዳደር ሥርዓት ነው? እነዚህስ ሀቆች የወል ትርክቶቻችን መመሆን አለመቻላቸው በፖለቲካ ደንቃራነት የተፈጠረ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of history) እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል? በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትና እና በሸዋ በሚገኘው የአዳዲ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኪነሕንጻ መካከል ያለው ፍጹም ተመሳሳይነት ምንጩ ምንድነው? ሊጠና፣ ሊነገር ልንማርበት ይገባል፡፡
በርግጥም ታሪካችን ትዝታችን ላይ የተጫነ ሸክም ሳይሆን የነፍስ መገለጥ ነው የሚያሰኘው የሕዝቦች ትሥሥር፣ ውህደት የሥልጣኔ መጋራትና መወራረስ ታሪክ መታወቁ መንፈስን ሃርነት ማውጣቱ ይመስለኛል፡፡

4 days ago
የሐረማያ ሐይቅ ማንሰራራት፦ የአረንጓዴ ዐሻራ ትሩፋት ማሳያ
********************
በተፈጥሯዊ እና በሰው ሰራሽ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ደርቆ ወደ አቧራማ ሜዳነት ተቀይሮ የነበረው ታሪካዊው ሐረማያ ሐይቅ አሁን ላይ በዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አማካኝነት ወደ ቀድሞ ይዘቱ ተመልሷል።
የሐረማያ ሐይቅ በዚህ መልኩ ማገገሙ በዕቅድ እና በጋራ ጥረት የተራቆቱ ሌሎች ተፋሰሶችንም ወደነበሩበት ሁኔታ መመለስ እንደሚቻል የሚያሳይ ሕያው ማረጋገጫ ሆኗል።
ሐረማያ ሐይቅ ለሐረማያ እና ለሐረር ከተሞች፣ ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ለአካባቢው ነዋሪዎች ዋነኛ የንጹህ መጠጥ ውኃና የግብርና መሠረት የነበረ ቢሆንም፣ በከፍተኛ የደን መጨፍጨፍ እና በደለል መሞላት ምክንያት ውኃ የመያዝ አቅሙን አጥቶ ተስፋ ተቆርጦበት የነበረ ነው።
ሆኖም ባለፉት ዓመታት በሐይቁ የላይኛው ተፋሰስ አካባቢዎች በተከናወነ የችግኝ ተከላ እና የእርከን ሥራ ወደ ሐይቁ ይገባ የነበረውን ከፍተኛ ደለል ከምንጩ መግታት ተችሏል።
በሌላ በኩል በሐይቁ ዙሪያ በተሠሩ የውኃ ማሳረፊያዎች አማካኝነት የዝናብ ውኃ ወደ መሬት እንዲሰርግ በማድረግ የሐይቁን ከርሰ ምድር ውኃ ክምችት እንዲጨምር ሆኗል።
በዚህም ሐይቁ ዳግም ውኃ መያዝ በመጀመሩ ቀደም ሲል አካባቢውን ለቀው የተሰደዱ በርካታ አእዋፍ፣ የጠፉ ዓሳዎች እና ሌሎች የውኃ ሕይወቶች እየተመለሱ ይገኛሉ።
የሐረማያ ሐይቅ ተሞክሮ ነገ የሚካሄደው የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ተራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ሳይሆን የታመመ ተፈጥሮን አክሞ የማዳን ሀገራዊ ጥረት መሆኑን የሚያስረግጥ ነው።
ይህ ተሞክሮ እያንዳንዱ ችግኝ የተራቆቱ አካባቢዎችን መልሶ የማቋቋም፣ የውኃ አካላትን የመታደግ እና የተጎዳ ተፈጥሮን የማከም ወሳኝ ድርሻ ይጫወታል።
ነገ በአንድ ጀምበር በጋራ የምናኖረው አረንጓዴ ዐሻራ የዛሬን የተፈጥሮ ቁስል እያከመ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ በውኃ ሀብት እና በልምላሜ ሙሉ የሚያደርግ ታሪካዊ ተግባር ነው።
በሐና ምንዳሁን
#ethiopia #climateaction #greenlegacy #800milliontrees #lakeharamaya #ebc #ebcdotstream

10 days ago
ታሪካዊ ቅርሶችን ከመታደግ እስከ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻነት የሐረር አስደናቂ የቱሪዝም ስኬት
*****************************
መንግሥት ካስቀመጣቸው አምስት ቁልፍ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ምሰሶዎች መካከል አንዱ የሆነውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ፣ በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ ሰፊ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ጥንታዊ ውበቷን ከዘመናዊ ገጽታ ጋር በማሰናሰል አዲስ ገጽታን የተላበሰችው ሐረር፣ አሁን ላይ እየተተገበረ ባለው የኮሪደር ልማት እና የቅርሶች ዕድሳት ሥራ የቱሪዝም ዘርፉን ይበልጥ አነቃቅታለች።
የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ሀብት የሆኑት የሐረር ጀጎል ጥንታዊ፣ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች ይዘታቸውን ጠብቀው እንዲለሙ እና ለትውልድ እንዲተላለፉ የመደመር ዕሳቤ ያመጣው ሕያው ትሩፋት ነው።
ይህ በዘርፉ የተሰጠው ልዩ ትኩረት ለአደጋ ተጋልጠው የነበሩ ቅርሶችን ከማዳኑም ባሻገር፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋት እና የጎብኚዎችን ቆይታ በማራዘም ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ አቅም በእጅጉ አሳድጎታል።
በክልሉ የተከናወኑት ስኬታማ የቱሪዝም ማጎልበት ተግባራት፣ ከውጭ ሀገር ቱሪስቶች በተጨማሪ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች እና የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ሐረርን በስፋት እንዲጎበኙ እና አስደናቂ ውበቷን ለዓለም እንዲያስተዋውቁ ሰፊ ዕድል ፈጥሯል።
የመደመር ትውልድ የትናንትን ታሪክ ከዛሬ ጋር በማስተሣሠር፣ ከትናንት ወረቶቻችን መልካሙን ወስዶ በማላቅ፣ የዛሬውን ጥረት አክሎበት ለነገው ትውልድ የሚያኮራ ቅርስ እያስተላለፈ ይገኛል።
ትናንት የነበሩንን ጠንካራ ነገሮች ሳናፈርስ፣ ያለፈውን ስብራት ጠግነን በማብቃት የሠራነው ታሪክ በእውነትም ትውልድ የማይዘነጋው አኩሪ ገድል ነው።
በአዲስ መልክ እና ቀለም የተዋበው ጀጎል የሐረርን ቀደምት ሥልጣኔ እየመሰከረ የሀገርንም ገጽታ እየገነባ ይገኛል። - መረጃው የሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።
#ethiopia #ebc #harariregion #tourism #heritage

18 days ago
🏃♀️🏃♂️ የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በሐረር በድምቀት ተካሔደ!!
መነሻና መድረሻውን ሐረር በር ላይ በማድረግ ፕሮፌሽናል አትሌቶችና ከአዲስ አባባ ተጓዥ ተሳታፊዎችን ያካተተ ልዩ የ10ኪ.ሜ ውድድር በወንዶችና በሴቶች ደስ በሚል ድባብ ተካሒዷል።
በተጨማሪም ተተኪዎችን ለማፍራት ከ16 ዓመት በታች ታዳጊ አትሌቶች የተሳተፉበት የ1.5 ኪ.ሜ ውድድርና ከ11 ዓመት በታች ልጆች የተሳተፉበት የ1 ኪ.ሜ.ውድድር ሌላው የዕለቱ ድምቀት ነበር፡፡
የአገራችን አትሌቲክስ ለማሳደግና ተተኪዎች ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮም በስያሜና የቴክኖሎጂ አጋርነት ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር እየሠራ የሚገኝ ሲሆን ወደ ፊትም በአትሌቲክሱ ዘርፍ የምናደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክረን እንቀጥላለን።
#ethiotelecomgreathararrun #greatethiopianrun #harar #telebirr #ethiotelecom

Sponsored by
Surafel

21 days ago
በሐረሪ ክልል በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወነው ተግባር የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር አድርጓል
******************
በሐረሪ ክልል በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወነው ተግባር የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር ማድረጉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት፥ በክልሉ ገጠርና ከተማ በቱሪዝም ዘርፍና በኮሪደር ልማት የተከናወነው ተግባራት ውጤት አምጥተዋል።
በተለይ የመስህብ ስፍራዎችን በማልማት፣ አገልግሎት በማሻሻል እና ቅርሶችን በመንከባከብ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
በዚህም ሐረር ከተማና በክልሉ የሚገኙ ቱሪስት መስህብ ስፍራዎችን የሚጎበኙ የቱሪስቶች ቁጥር መጨመሩን ጠቁመዋል።
በተለይ በበጀት ዓመቱ 14ሺህ 700 የውጭ ቱሪስቶች እንዲሁም ከ180ሺህ በላይ የአገር ውስጥ ቱሪስቶች ሐረርንና በውስጧ የሚገኙ የመስህብ ስፍራዎችን መጎብኘታቸውን ተናግረዋል።
እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ፥ በክልሉ የሚገኙ የመስህብ ስፍራዎችን የሚጎበኙ የውጪና የአገር ውስጥ ቱሪስቶች ቁጥር በየዓመቱ እድገት እያሳየ መጥቷል።
በክልሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎች መከናወናቸው ፣ የቱሪስት መዳረሻዎች የማልማትና የማስተዋወቅ ስራዎች እንዲሁም የአገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ጥራት ማሻሻል ለተገኘው ውጤት ጉልህ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል።
እንዲሁም ዓለም አቀፍ የጀጎል ቅርስ፣ የኮሪደር ልማት እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሰጠው እውቅና ለአገር ውስጥ ቱሪስቶች ፍሰት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።

25 days ago
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሐምሌ 7/1940 ዓ.ም በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጨለንቆ አቅራቢያ በምትገኝ ፈንዲዴ በተባለች መንደር ተወለዱ።
እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በትውልድ መንደራቸው ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን በሐረር በሚገኘው የላዛሪስት አባቶች የዘርዐ ክህነት ትምህርት ቤት በመግባት መንፈሳዊ ጥሪያቸውን ጀመሩ።
ከዚያም በአዲስ አበባ በሚገኘው የካፑቺን ፍራንቸስካውያን የፍልስፍናና ቲዎሎጂ ኮሌጅ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ወደ እንግሊዝ ሀገር በማምራት በለንደን ዩኒቨርሲቲ በሶሺዎሎጂ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
እ.አ.አ ሰኔ 1976 ምስጢረ ክህነትን የተቀበሉ ሲሆን
የማኅበረ ልዑካን አባቶች ላዛሪስት ገዳም ያፈራቸው ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ጥር 17/1990 ዓ.ም ጵጵስናን ፤ የካቲት 7/2007 ዓ.ም በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አማካኝነት የካርዲናልነት ማዕረግን ያገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ታሪክ ከብፁዕ ጳውሎስ አድዋ ቀጥሎ ካርዲናል የሆኑ ሁለተኛው ጳጳስ ናቸው።
ብፁዕ ካርዲናል በኢትዮጵያ በሰላም ሚኒስቴር ስር ተቋቁሞ የነበረው የብሔራዊ እርቅና ሰላም ኮሚሽን ውስጥ በሊቀመንበርነት አገልግለዋል።
ብፁዕነታቸው ለቅድስት መንበር ባቀረቡት የጡረታ ጥያቄ መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ ጥያቄያቸውን መቀበላቸውን በቅድስት መንበር ልዪ መልዕክተኛ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ጉጀሮቲ አማካይነት ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል።
ለብፁዕ አባታችን እንኳን ለ50ኛ ዓመት የክህነት በዓልዎ በሰላም አደረስዎት።

26 days ago
የሕጻናትን መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕጻናትን መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ሁሉ አቀፍ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ አሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)።
‘‘የተጠበቁ ሕጻናት ለበለፀገ ትውልድ’’ በሚል መሪ ሃሳብ የአፍሪካ ሕጻናት ቀን ማጠቃለያ ፕሮግራም በሐረር ከተማ ተካሂዷል።
ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ÷ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለነገ ሀገር ተረካቢ ህጻናት አስፈላጊው መሰረተ ልማቶች የማሟላት ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
በተለይም ውብ፣ ምቹና ጽዱ የመዝናኛ እንዲሁም የሕጻናት ማቆያና መንከባከቢያ ማዕከላትንና የመጫወቻ ስፍራዎችን የመገንባትና የማስፋፋት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ከዚሁ ጎን ለጎን የሕጻናት ድጋፍና እንክብካቤ፣ በተለያዩ ዘርፎች ተሳትፏቸውን የማጎልበት እንዲሁም በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ተጎጂ እንዳይሆኑ የመጠበቅ፣ ከጥቃት የመከላከልና ሌሎች በርካታ ስራዎችም መከናወናቸውን አንስተዋል።
የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ሕጻናትን መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከማሕበረሰቡና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሚከናወኑ ሁሉ አቅፍ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር በበኩላቸው÷ በክልሉ በከተማም ሆነ በገጠር ያሉ ህጻናት መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የልማት ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።
የሕጻናት ሁለንተናዊ እድገት ስኬታማ የሚሆነው በመንግስት ጥረት ብቻ አለመሆኑን ጠቁመው÷ በክልሉ ያሉ ህጻናት እኩል ተጠቃሚና ተደራሽነትን ለማጎልበት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎን ማጎልበት እንደሚገባ መጠቆማቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል፡፡

29 days ago
🏃🏾♀️🏃♂️የ2018 ዓ.ም ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በሐረር ከተማ ቲሸርቶችን በቴሌብር እንግዛ!
የ5 ኪ.ሜ የጤና ሩጫ እና የልጆች ሩጫ መነሻና መጨረሻውን በታሪካዊው የጀጎል በር ላይ ያደርጋል።
በቴሌብር በመክፈል በሐረር ከተማ በኢትዮ- ተርክሽ አደባባይ፣ በኢትዮ ቴሌኮም ማዕከላዊ ምሥራቅ ሪጅን ዋና መ/ቤት እና በሁሉም ቅርንጫፍ መ/ቤቶች በመመዝገብ ፈጥነው የመሮጫ ቲሸርትዎን ይውሰዱ።
🗓 እሑድ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሔዳል
በቴሌብር (*127# / https://bit.ly/telebirr_Su... ) አብረን ስንደምቅ እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን #ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን #ስንጭን_እንዲህ_ነን #ስናስጀምር_እንዲህ_ነን

1 month ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ ቴነሲ ግዛት በምትገኘው ሜምፊስ ከተማ፣ "የሐረሪ ቀን" እጅግ ማራኪ በሆነ የባህል ትዕይንት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል። የከተማዋ ከንቲባ ፖል ኤ. ያንግ ጁላይ 1፣ 2026ን በከተማዋ የሐረሪ ቀን እንዲሆን በይፋ ማወጃቸውን ተከትሎ ነው በዓሉ በዚህ ልክ ደምቆ ያለፈው።
ከንቲባ ያንግ እንዳስታወቁት ይህ ታሪካዊ ቀን ከምስራቅ ኢትዮጵያዋ ጥንታዊት እና ባለ ግንብ ከተማ ሐረር የመነጩትን የሐረሪ ማህበረሰብ አባላት የበለጸገ የባህል ቅርስ፣ ታሪክ እና ለማህበረሰቡ እያበረከቱ ያሉትን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ዕውቅና የሰጠ ነው። ዕለቱ በምዕራብ ቴነሲ አካባቢ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀውን የባህል ጥበቃ እና አንድነትን ለማክበር የተዘጋጀውን 26ኛውን ዓመታዊ የሐረሪ ፌስቲቫልን ይበልጥ ያደመቀ ልዩ አጋጣሚ ሆኗል።
የሐረሪ ማህበረሰብ አባል የሆኑት ነመት ሰልማን የዕለቱን ደማቅ አከባበር አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፣ "ይህ አዋጅ ለሐረሪ ማህበረሰብ ትልቅ የኩራት ምዕራፍ ነው" ብለዋል። አክለውም፣ "የሐረሪ ቀን ባህላችንን ጠብቆ ለማቆየት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ ሲሆን፣ በመላው ሜምፊስ ከተማ አንድነትን እና የባህል መግባባትን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው" በማለት የክብረ በዓሉን ስኬት አብራርተዋል።
ይህ በከፍተኛ ድምቀት እና ማራኪ የባህል ትዕይንቶች የታጀበው 26ኛው ዓመታዊ የሐረሪ ፌስቲቫል፣ ከሰኔ ወር መጨረሻ ጀምሮ እስከ ዛሬ ጁላይ 5 ድረስ በሜምፊስ በሚገኘው ኮርዶቫ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአንድነት እና በደስታ ሲካሄድ ቆይቷል።

ከኢትዮጵያዊያን ወላጆች የተገኘው የካናዳ 20 ቁጥር ተጨዋች አሊ አህመድ
#fastmereja I በትውልድ ኢትዮጵያዊ ከሆኑት ቤተሰብ የተገኘው በአሁኑ ወቅት በካናዳ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ሊግ ውስጥ አስደናቂ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው ወጣቱ አማካይ አሊ አህመድ። ሁለቱም ወላጆቹ ከኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል ሐረርጌ በዴሳ የተገኙት አሊ፣ በሰሜን አሜሪካ እግር ኳስ መድረክ ተስፋ ሰጪ ተጫዋች መሆኑን እያስመሰከረ ይገኛል።
በእግር ኳስ ስፖርት ታላቅ ተስፋ የተጣለበትና በአሁኑ ወቅት በሜዳ ላይ በሚያሳየው ቀልጣፋ እንቅስቃሴ ስሙ እየገነነ የመጣው አሊ አህመድ፣ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ገና በስድስት ዓመት ዕድሜው በሰሜን ቶሮንቶ የስፖርት ክለብ (North Toronto SC) እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ። ከወላጆቹ ከአቶ አፈንዲ እና ከወይዘሮ ሙና የተወለደው አሊ፣ እንግሊዝኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎችን አቀናጅቶ መናገር የሚችል ሲሆን፣ ከእግር ኳስ በተጨማሪ የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ከፍተኛ ፍላጎት አለው።
አሊ አህመድ በታዋቂዎቹ የእግር ኳስ ኮከቦች ሊዮኔል ሜሲ እና ኤደን ሀዛርድ እንዲሁም በእንግሊዙ ቼልሲ ክለብ አጫዋች ዘይቤ ተጽዕኖ አድሮበታል። በቅርጫት ኳስ በኩል ደግሞ እንደ ኮቢ ብራያንት፣ ዴማር ዴሮዛን እና ስቴፍ ካሪ ያሉ የኤንቢኤ (NBA) ታላላቅ ተጫዋቾችን በአርአያነት እንደሚከተል ይነገራል። ይህ የተለያየ የስፖርት ፍቅርና ክህሎት በሜዳ ላይ ላለው የአስተሳሰብ ብስለትና የአካል ብቃት ጥንካሬ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳበረከተለት የስፖርት ተንታኞች ይገልጻሉ።
#ስፖርት ዘገባ

እኛ ቅርስ የምንጠብቅና የምናስመልስ እንጂ የምናፈርስ አይደለንም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እኛ ቅርስ የምንጠብቅና የምናስመልስ ነን እንጂ የምናፈርስ አይደለንም አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “አዲሱ የኢኮኖሚ ሞተር" በሚል በቱሪዝም ዙሪያ ባደረጉት ልዩ ቃለምልልስ ላይ እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ ውስጥ በየአካባቢው በቱሪዝም ዘርፍ የተሰሩት ስራዎች አስደናቂ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚሰሩ ስራዎች ቅርስ ይጠፋብኛል የሚል ስጋት አለው ብዬ አላምንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ልምምድ ደካማ በመሆኑ በሁሉም ነገር ላይ ተቃውሞ የሚያነሱ አካላት መኖራቸውን አመልክተዋል፡፡
ከኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የተወሰዱ
ከ35 በላይ ቅርሶች እንዲመለሱ መደረጉን ገልጸው፥ እኛ ቅርስ የምንጠብቅና የምናስመልስ እንጂ የምናፈረረስ አይደለንም ነው ያሉት፡፡
በተለያዩ ጊዜያት ከኢትዮጵያ የተወሰዱ ቅርሶችን ለማስመለስ አሁንም ንግግር እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ብሔራዊ ቤተ መንግሥት፣ የጎንደር አብያተ መንግሥታት፣ ጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግሥት፣ የሐረር ጁገል ግንብና የሶፍ ኡመር ዋሻን ጨምሮ በርካታ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶች ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ ታድሰው የቱሪዝም ገቢን እያሳደጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
በዚህም የሚያኮራ ሥራ መሰራቱን ጠቅሰው፥ የተሰራው ሥራ ለልጆቻችን የሚሻገር ነው ብለዋል፡፡
እኛ የተከተልነው መርህ ጥራትና ትክክለኝነት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ሁሉንም ታሪኮች በእኩል የሚያሳይ እንዲሁም የኢትዮጵያን አጠቃላይ መልክ የሚያሳይ መሆን አለበት በሚል አግባብ መሰራቱን ተናግረዋል።
ብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ መተግበር ከተጀመረ ወዲህ በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው፥ በዚህ ዓመት 10 ነጥብ 2 በመቶ ዕድገት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡
ይህ ዕድገት በድፍን አፍሪካ የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ይህ የሆነው ምክንያት ሁሉም ዘርፎች በደንብ የሚታይ ለውጥ በማምጣታቸው ነው ብለዋል፡፡
በዚህ ዓመት ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ጉብኚዎች ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን ጠቅሰው፥ በቱሪዝም ፍሰት ከ5 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ተገኝቷል ነው ያሉት፡፡
በዚህ ዓመት 50 ነጥብ 16 ሚሊየን የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች የኢትዮጵያን የተለያዩ ቦታዎች መጎብኘታቸውን ገልጸዋል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

ሐረርን ለናፈቃችሁ በሙሉ... ሚኒሶታ ውስጥ ሐረርን አገኘኋት!
በሚኒሶታ ወደሚገኘው 'ጀጎል ሬስቶራንት' ጎራ ብዬ ነበር። እስኪ ስለ ምግቦቻቸው ልዩ ጣዕም፣ ስለ አስገራሚ መስተንግዷቸው እና ቦታው ስላለው ልዩ ድባብ ላካፍላችሁ...
ምግቦቹ የሐረርን ማዕድ በቀጥታ እዚህ ያመጡልዎታል፤ ጣዕማቸው የሀገር ቤትን እና የእናትን እጅ ያስታውሳል። መስተንግዶው ደግሞ ልክ እንደ ሐረር ህዝብ ሞቅ ያለ፣ ትሁት እና ቤተሰባዊ ነው! ባህላዊ ምግቦችን እየተመገቡ የጀጎልን ሞቅ ያለ ድባብ ሚኒሶታ ውስጥ ማግኘት በእውነት ልዩ ስሜት ነው። #jegolrestaurant #minnesotaeats #hararifood #ethiopianfood #tasteofharar
1 month ago
በልማት ሥራዎች 'ቅርሶች ይጠፋሉ' የሚለው ወቀሳ የፖለቲካ ፍጆታ እንጂ እውነተኛ የሕዝብ ስጋት አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግሥት እያከናወናቸው ባሉ ሰፊ የልማትና የእድሳት ሥራዎች “ቅርሶች ይጠፋሉ” በሚል የሚነሳው ወቀሳ የፖለቲካ ፍጆታ እንጂ እውነተኛ የሕዝብ ስጋት አለመሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት የሀገራችንን ቅርሶች በከፍተኛ ጥራትና ጥንቃቄ የሚጠብቅ፣ የሚያስውብ እና ለቀጣዩ ትውልድ የሚያሻግር እንጂ የሚያፈርስ አለመሆኑን በተግባር የተሠሩ ሥራዎችን በማንሳት አብራርተዋል።
በፖለቲካ ልምምድ ድክመት ምክንያት የሚሰሩ ሥራዎችን ሁሉ የመቃወም አዝማሚያ መኖሩን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በጎንደር የፋሲል ግንብ ላይ የነበረውን እውነታ በምሳሌነት አንስተዋል።
የፋሲል ግንብ ለመቶ ዓመታት ያህል ምንም ዓይነት እድሳት ሳይደረግለት በቁሙ እየፈረሰ እንደነበር አስታውሰው፣ መንግሥት ይህንን ታሪካዊ ቅርስ ለማዳን ሥራ ሲጀምር የተሳሳተ ቅስቀሳ ቢፈጠርም፣ ዛሬ ላይ በተሠራው የእድሳት ሥራ ግን ሕዝቡን ጨምሮ ማንም ኢትዮጵያዊና የውጭ ዜጋ የሚኮራበት ማራኪ ቅርስ መሆን መቻሉን ተናግረዋል።
በተመሳሳይ በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ በጅማ የአባ ጅፋር ቤተመንግሥት፣ በሐረር ጀጎል ግንብ እና በሶፍ ዑመር ዋሻ የተከናወኑት የጥገና እና የመሠረተ ልማት ሥራዎች ቅርሶቹን በከፍተኛ ጥንቃቄ የጠበቁ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና አባቶች ጭምር የሚመሰክሩት ሀቅ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ከዚህ ቀደም እንክብካቤ ተነፍጓቸው ፈርሰውና ተበላሽተው የነበሩት እንደ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ያሉ ስፍራዎችም፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት አግባብ ታድሰው ዛሬ ላይ በሚሊዮኖች የሚጎበኙ ውብ የቱሪዝም መዳረሻዎች መሆናቸውን ለአብነት አንስተዋል።
መንግሥት ያሉትን ታሪካዊ ቅርሶች ከማስዋብና ከመጠበቅ ባለፈ፣ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ዘመናት ከሀገር የተዘረፉና የጠፉ ከ35 በላይ ታሪካዊ ቅርሶችን ማስመለስ መቻሉንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስረድተዋል።
አሁንም በድርድር ሂደት ላይ ያሉ በርካታ ቅርሶች እንዳሉ ጠቁመው፣ እጅግ ማራኪ የሆነው የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ዙፋን (የመቀመጫ ወንበር) በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለስም ተናግረዋል።
መንግሥት የሁሉንም አካባቢዎችና ሃይማኖቶች ታሪክ ባካተተ እንዲሁም የኢትዮጵያን አጠቃላይ ገጽታ በሚያሳይ መልኩ የቅርሶችን ትክክለኛነትና ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃ በጠበቀ አግባብ እየሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በስሜትና በፖለቲካ ፍላጎት ብቻ የሚነሱ መሠረተ ቢስ ትችቶች መንግሥትን ወደ ኋላ እንደማይጎትቱት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ መንግሥት የኢትዮጵያን እምቅ የቱሪዝም አቅም ለዓለም አውጥቶ በማሳየት የቅርስ ጠባቂነትና አሻጋሪነት ታሪካዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
#heritageconservation #tourismethiopia #pmabiyahmed #preservinghistory #ethiopianbroadcastingcorporation

“ኢትዮጵያ አንድ ቪዛ ብቻ ወስደው መላውን ዓለም የሚያዩባት ድንቅ ሀገር ናት” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ቪዛ ብቻ ተጉዘው ከተፈጥሮ፣ ከሥነ-ምሕዳር፣ ከቅዝቃዜና ከሙቀት እንዲሁም ከጥንታዊ ታሪክና ባህል ባለብዙ መልክነትን በአንድ ላይ የሚያዩባት በዓለም ላይ ድንቅ ሀገር ኢትዮጵያ መሆኗን ገልጸዋል።
ወደ ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሚጓዝ ሰው ከአፍሪካ ሁለተኛ ከፍተኛ ቦታ የሆነውን የሰሜን ተራሮች ብርድና አስደናቂ መልክዓ ምድር አጣጥሞ፣ በጥቂት ሰዓታት ጉዞ ደግሞ በታሪክና በቅርስ የተሞላችውን የጎንደር ፋሲል ግንብን መጎብኘት እንደሚችል ጠቅሰዋል።
ከዚያም አልፎ ውብ መዳረሻ ወደሆነችው ጎርጎራ፣ የረጅሙ የዓባይ ወንዝ መነሻ ወደሆነው ጣና ገዳማትና የዛሬ 800 እና 900 ዓመታት የቆዩ የክርስትና የብራና ጽሑፎችና ቅርሶችን ተመልክቶ፣ በውቧ ባሕር ዳር ጉዞውን እንደሚያጠናቅቅ ጠቁመው፣ በዚህ መስመር ላወጣው ወጪ የሚቆጭ ማንም እንደማይኖር አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በዓለም ላይ በአንድ አቅጣጫ ሁሉንም ዓይነት ተፈጥሮ በጥምረት የያዘ እንደ ባሌ ዓይነት ቦታ ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ከባሕር ጠለል በላይ ከ4 ሺህ 300 ሜትር በላይ ከፍታ ባለው የቱሉ ዲምቱ ተራራ ላይ አስደናቂ ሐይቆችን፣ ብርቅዬዋን ቀይ ቀበሮና የሎቤሊያ ዕፅዋትን ተመልክቶ፣ በደቂቃዎች ልዩነት ወደ ሀረና ዝቅተኛ ጫካ ሲወርድ ለማመን የሚከብድ ጥቁር አንበሳ፣ ማራኪ ፏፏቴዎችና ብርቅዬ ወፎች ያሉበትን ጥቅጥቅ ያለ ደን ያገኛል ብለዋል።
በዲንሾ ብሔራዊ ፓርክ ከተላመዱ የዱር እንስሳት ጋር ከተገናኘ በኋላ፣ ወደ ሶፍ ዑመር ዋሻ ሲያመራ ደግሞ ከሕንድ ውቅያኖስ ጋር በቀጥታ ይገናኝ የነበረና የዛሬ 800 ዓመት የነበረ መስጊድ፣ አርቲፊሻል ሐይቅ እንዲሁም ከ60 በላይ ቋንቋዎች የሚማሩበት ታሪካዊ መድረሳ ያለበትንና ጥንታውያን ስልጡን ኢትዮጵያውያን የገነቡትን ገና ያልተደረሰበትን ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ በዓይኑ እንደሚመለከት ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ አስደናቂ ባለብዙ መልክነት በዚህ ብቻ እንደማያበቃ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ወደ አፋር ክልል የሚጓዝ ሰው የሰው ልጅ መገኛ ታሪክን ሰምቶ፣ በምድር ላይ መሆኑን የሚያጠራጥረውን የኤርታሌ የሚፈላ እሳተ ጎመራ እቶንና ማራኪውን የዳሎልን የሰልፈር ከለሮችና የጨው መስኮች እንደሚመለከት አብራርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእነዚህ በተጨማሪ ወደ ሐረር፣ ጅማ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ቢኬድ ሙቀትና ቅዝቃዜ፣ ከፍተኛና ዝቅተኛ መልክዓ ምድር፣ አስደናቂ የዱር እንስሳትና ጥንታዊ ታሪኮች የተሰናሰሉባት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት ብለዋል።
ይህንን ሁሉ ድንቅ የተፈጥሮና የታሪክ ጸጋ የያዘችውን ኢትዮጵያን ማንኛውም ዜጋ ሊያውቃትና ሊጎበኛት እንደሚገባ በማሳሰብ፣ ሀገራችን ተዘርዝረው በማያልቁና በእውነት “ይህ ስፍራ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ወይ?” በሚያሰኙ ማራኪ መዳረሻዎች የተሞላች መሆኗን ገልጸዋል።
#visitethiopia #onevisamultidestinations #pmabiyahmed #landoforigins #ethiopianbroadcastingcorporation

ቱሪዝምን ሕይወት የዘራበት የመደመር መንግሥት
***********
ኢትዮጵያ የበርካታ ታሪካዊ ተፈጥሯዊና የባህል ቅርሶች ማህደር ብትሆንም ይህን ዕምቅ ፀጋ ወደ ሀገር ከፍታና ብልፅግና ቀይራ መጠቀም ሳትችል ዘመናት ተቆጥረዋል።
ሆኖም በምናብ ከፍታ ነገን አሻግሮ በመመልከት ቃልን በተግባር የመኖር ባህልን በተቋማዊ መሰረት የገነባው የመደመር እሳቤ የቱሪዝም ዘርፉን የሀገር ምሰሶ አድርጎ ተነስቷል።
የመደመር ፍልስፍና ዳራው ትናንትን ከነክብሩ ጠብቆ፣ የተበታተኑ ሀገራዊ ፀጋዎቻችንን በማሰባሰብና እሴትን በመጨመር ወደ ላቀ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅም መቀየር ነው።
በዚህም መነሻነት የመደመር መንግሥት አዲስ አበባን ከጥልቅ ጉስቁልና በማውጣት ወደ ሚመጥናት የውበት ከፍታ እያሸጋገራት ይገኛል።
ይህ ጥረት በዋና ከተማዋ ብቻ ሳይገደብ ላለፉት አምስት ዓመታት በመላ የሀገራችን ክፍሎች የተመዘገቡት ስኬቶች የዚህን ዕሳቤ ጥልቀትና ተግባራዊነት ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ ናቸው።
ሀገራችን ለዘመናት ተዘንግተውና አቧራ ጠጥተው የቆዩ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶቿን ደረጃቸውን በጠበቀና በጥናት ላይ በመመስረት በማደስና በመንከባከብ በቱሪዝም ዘርፍ አስደናቂ ውጤት አስመዝግባለች።
ታሪካዊ ገፅታቸውን ሳያጡ በዘመናዊ አቀራረብ ሕይወት ዘርተው ከተነሱት ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል ብሔራዊ ቤተ መንግሥትን፣ የሐረር ጀጎል ግንብን፣ የጎንደር አብያተ መንግሥታትን፣ የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግሥትንና የሶፍ ኡመር ዋሻን ጨምሮ በርካታ ድንቅ ቅርሶች ይገኙበታል።
የእነዚህ የቅርስ ዕድሳት ፕሮጀክቶች ፋይዳ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ከማስፋትና ማራኪ ከማድረግም በእጅጉ የዘለለ ነው።
በዘርፉ አዲስ መነቃቃትን በመፍጠር የግሉ ዘርፍ በኢንቨስትመንት በስፋት እንዲሳተፍና ተወዳዳሪነቱ እንዲጠናከር ምቹ መደላድል ፈጥረዋል።
አዳዲስ የቱሪዝም ማዕከላት መበራከታቸው የጎብኚዎችን የቆይታ ጊዜ ከማራዘሙም ባሻገር ከዘርፉ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬና አጠቃላይ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ እንዲያድግ አስችሏል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነትና የቅርብ ክትትል የተተገበሩት እነዚህ የቅርስ ልማትና ጥበቃ ስራዎች የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን ቁጥር በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር አድርገዋል።
መንግሥት በቅርስ ጥበቃና ልማት ላይ የፈጠረው ይህ አዲስ ዕይታ የሀገራችንን የካበተ የታሪክ ሃብት በአግባቡ ጠብቆ ወደ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም መቀየር እንደሚቻል አረጋግጧል።
በአዶኒያስ ወ/አረጋይ
#ethiopianbroadcastingcorporation #medemergovernment #tourismethiopia #visitethiopia #landoforigins #abiyahmed

“በሳቅዎ ይክፈሉ”
ሐረር ቢራ፣ ሳቃችንን እየመነዘረ ከጓደኞቻችንና ከምንወዳቸው ጋር የሚያገናኘንን አዲስ «ሳቅፔ» (SAQPay) የተሰኘ መተግበሪያ ይዞልን ከች ብሏል!
ለመሆኑ የማህበራዊ ህይወታችን እውነተኛ ዋጋ በገንዘብ ልውውጥ ብቻ ይለካል እንዴ? ከወዳጆቻችን ጋር የምናሳልፈው ያ ደስ የሚል ጊዜ እንጂ! ይህንን እውነት መነሻ በማድረግ፣ ሐረር ሳቃችንን በቀጥታ
ልንመነዝረው ወደምንችለው ጥቅም የሚቀይር አዲስ ፈጠራ ይዞ መጥቷል። ትኩረቱንም ሰዎች ከኪሳቸው ከሚያወጡት ወጪ ይልቅ፣ በጋራ ወደሚጋሩት ሳቅ እና ጨዋታ አዙሮልናል!
ነገሩ እንዲህ ነው፤ «በሳቅዎ ይክፈሉ» በሚለው አዲስ ሃሳብ፣ የሳቅፔ (SAQPay) መተግበሪያ እውነተኛ ሳቅን በመለየት ለሳቃችን ነጥብ ይሰጠናል። ተንቀሳቃሽ ስልካችን ላይ ነጥቡን እያጠራቀምን ደግሞ ሐረር ቢራን በተመረጡ ቦታዎች በቅናሽ እንድንናኝ ያስችለናል!
ሐረር ቢራ የሀገራችንን የፈጠራና የኪነጥበብ ዘርፍ የሚደግፍ ከመሆኑም በላይ፣ ሰዎች በአንድነት ተገናኝተው የሚዝናኑበት ሰፊ እድል በመፍጠር ላለፉት 40 ዓመታት ማህበረሰባችንን በሳቅና በጨዋታ ሲያገናኝ ቆይቷል። ይሄ አዲስ ሃሳብም የዚሁ የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነታችን አንዱ ማሳያ ነው!
"ለእኛ ለሐረሮች፣ ከገንዘብ ልውውጥ ይልቅ እጅግ ትርጉም ያለው ነገር አብረን የምንጋራው ደስታ እና በእውነተኛ ሳቅ ውስጥ የሚፈጠረው አብሮነት እንደሆነ እናምናለን። «በሳቅዎ ይክፈሉ» ይሄንኑ እውነት በተግባር የምናሳይበት መንገዳችን ነው። ምክንያቱም መዝናናት ለሁሉም ክፍት ሲሆን፣ ሰዎች በአንድ ላይ ከመሰባሰብ አልፈው የእርስ በርስ ትስስራቸው ይበልጥ ይጠነክራልና!" ካሳሁን ፈለቀ፣ የሃይኒከን ኢትዮጵያ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር
ሁሉም «በሳቅዎ ይክፈሉ» ላይ የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በተመረጡ ቦታዎች ብቻ የሚካሄዱ ሲሆን፤ ህጋዊ የእድሜ ገደብን እና ኃላፊነት የተሞላበት መጠጥ አጠቃቀም መመሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ያከበሩ ናቸው።

የመዳረሻ ልማት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ
#ethiopia | ባሌ፣ ሮቤ - የኢትዮጵያ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ የመዳረሻ ልማት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሽግግር፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ማሳደግ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገለጹ።
በመዳ ዋላቡ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው 2ኛው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ “The Responsible AI Revolution: Building Ethiopia's Institutional Edge in Tourism and Hospitality by 2030” በሚል አበይት ርዕስ ሚኒስትሩ “የመዳረሻ ልማት ብሔራዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ንግግር፣ መዳረሻዎች የቱሪዝም መስህቦች ብቻ ሳይሆኑ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የኢንቨስትመንት ማዕከላት፣ የማህበራዊ ለውጥ መድረኮች እና የብሔራዊ ማንነት መገለጫዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል።
እንደ ዶ/ር አብርሃም ገለጻ፣ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሞቿ ውስጥ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ፣ ኢንቨስትመንት ለመሳብ፣ መሠረተ ልማትን ለማዘመን እና ዘላቂ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እየሰራች ሲሆን፣ የመዳረሻ ልማት እነዚህን ግቦች በተግባር የሚያሳካ ስትራቴጂ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሶፍ ኦማር ዋሻዎች፣ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ ዋንጪ፣ ሐረር፣ ሐዋሳ ሐይቅ፣ ጣና ሐይቅ፣ ገራልታ እና አርባምንጭን ጨምሮ የኢትዮጵያ መዳረሻዎች ጎብኚዎችን፣ ባለሀብቶችን፣ ተመራማሪዎችን እና ፈጣሪዎችን ከዓለም ዙሪያ ለመሳብ ትልቅ አቅም እንዳላቸውም ተናግረዋል።
ዶ/ር አብርሃም የመዳረሻ ልማት በትራንስፖርት፣ ሎጂስቲክስ፣ ግብርና፣ ሪል እስቴት፣ መስተንግዶ እና አገልግሎት ዘርፎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን እንደሚያነቃቃ ገልጸው፣ በተለይም ለወጣቶችና ለሴቶች ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ጨምሮ በትስስር እና መሠረተ ልማት ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች የቱሪዝም፣ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የሪል እስቴት ዕድሎችን እንደሚያሰፉ ገልጸዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍ ባለሀብቶች እና የአካባቢ ማህበረሰቦች በመዳረሻ ልማት ዘርፍ በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበው፣ የኢትዮጵያ መዳረሻዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የኢንቨስትመንትና የፈጠራ ማዕከላት ማድረግ እንደሚቻል አስገንዝበዋል።
#ethiopia #destinationdevelopment #tourism #investment #economicgrowth #getutemesgen #ethiopia #bale #tourism #getutemesgen #ጌጡተመስገን #artificialintelligence #digitalethiopia2030 #mwu

2 months ago
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የክልል ምክር ቤት ውጤት
👉ሀረሪ ክልል - የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት 36
ብልጽግና ፓርቲ - 32 መቀመጫዎች
የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ - 1 መቀመጫ
ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ - 1 መቀመጫ
የሐረር ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - 1 መቀመጫ
የግል ተወዳዳሪው ጀማል አባገሮ አሕመድ - 1 መቀመጫ
👉ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል - የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት 170
ብልጽግና ፓርቲ - 143 መቀመጫዎች
ኢዜማ - 12 መቀመጫዎች
ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ - 7 መቀመጫዎች
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - 3 መቀመጫዎች
ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ ፓርቲ - 3 መቀመጫዎች
የወሎ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - 1 መቀመጫ
የወለኔ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - 1 መቀመጫ
👉ሲዳማ ክልል - የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት 190
ብልጽግና ፓርቲ - 175 መቀመጫዎች
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ - 8 መቀመጫዎች
ሲዳማ አንድነት ፓርቲ - 3 መቀመጫዎች
የሲዳማ ሕዝብ አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት - 1 መቀመጫ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ - 1 መቀመጫ
የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ሕብረት - 1 መቀመጫ
የመላው ሲዳማ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ - 1 መቀመጫ

u121du12adu1275u120d u1320u1245u120bu12ed u121au1292u1235u1275u122d u1270u1218u1235u1308u1295 u1325u1229u1290u1205 u1260u121du1235u122bu1245 u1210u1228u122du130c u130bu122b u1219u1208u1273 u12ebu12f0u1228u1309u1275 u1309u1265u129du1275
#ebc #ethiopia #reconciliationu200b #historylessons #medemer #nationaldialogue #u1210u1228u122du130c ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በምስራቅ ሐረርጌ ጋራ ሙለታ ያደረጉት ጉብኝት
#ebc #ethiopia #reconciliation #historylessons #medemer #nationaldialogue #ሐረርጌ
2 months ago
በቆጂ : አትሌት ማሞ ሐጫሉ እና ማህሌት ካሳሁን የድል አክሊል ደፉ
#ethiopia | ለአምስተኛ ጊዜ መነሻና መድረሻውን በቆጂ ስታዲየም ባደረገው የ12 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በወንዶች ዘርፍ የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ክለብ ተወካይ የሆነው ማሞ ሐጫሉ አንደኛ በመሆን አሸንፏል።
በዚሁ ምድብ አማን ቃዲ እና አልዬ ቃሲም ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በሴቶች ምድብ በተደረገው ፉክክር የአሰላ አትሌቲክስ ክለብ አትሌት ማህሌት ካሳሁን ቀዳሚነቱን ስትይዝ፤ ኪያ ፍስሃ እና ድርቤ ኢርኮ በቅደም ተከተል ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል።
የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተከታታይ ውድድር አካል በሆነው በዚህ ዝግጅት ላይ ዕድሜያቸው ከ11 እና ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በሁለቱም ጾታ ያደረጉት ተሳትፎ ለውድድሩ የተለየ ድምቀት ሰጥቶት አርፍዷል።
በስፍራው ተገኝተው የክብር እንግዳ የነበሩት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ መኪዩ ሙሐመድ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ ዶክተር፣ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ቢያ እና የበቆጂ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ ብርሃኔ ነገሰ ሲሆኑ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችም ታድመውታል።
በስድስት ከተሞች ላይ የሚካሄደው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ውድድር ቀጣይ መርሃ ግብሩን ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በአርባምንጭ ከተማ የሚያደርግ ሲሆን የፍጻሜው ውድድር ደግሞ ሐምሌ 12 ቀን በታሪካዊቷ ሐረር ከተማ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።
#bekoji #athletics #ethiotelecom #greatethiopianrun #sportnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6ኛው “ጣፋጭ ሕይወት” የምስጋና ፕሮግራም በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ
#fastmereja I ዜጎች በሕይወታቸው መልካም የዋሉላቸውን ባለውለታዎች የሚያመሰግኑበትና ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ የተዘጋጀው “ጣፋጭ ሕይወት የምስጋና ፕሮግራም” በአዲስ አበባ፣ በሐዋሳ እና በሐረር ከተሞች ሙሉ ቀን የቆዩ ልዩ ልዩ የክብር መርሃ ግብሮችን በማካተት በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ።
የዘንድሮው የምስጋና ቀን መርሃ ግብር ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሦስቱም ከተሞች ለአካባቢ ጥበቃና ውበት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ የፅዳት ባለሙያዎችን በማህበረሰቡ ዘንድ ታላቅ ምስጋና እና ክብር በመስጠት ተጀምሯል። በመቀጠልም ከረፋዱ 2:00 ሰዓት ላይ መምህራን ከተማሪዎቻቸው ደማቅ የእውቅና ስነ-ስርዓት የተበረከተላቸው ሲሆን፣ በምሳ ሰዓት ደግሞ በየሆስፒታሎቹና በሕክምና ተቋማቱ የሚገኙ ታካሚዎች የሕክምና ባለሙያዎችን በአካል በመገኘት አመስግነዋል።
ከምሽቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ ከአምስት መቶ በላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም ታዋቂና በጎ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በታደሙበት ስድስተኛው ጣፋጭ ሕይወት ምስጋና መርሃ ግብር በአምስት ዘርፍ የሚመሰገኑ አካላት እውቅና አግኝተዋል ።
ከ15 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ጋር ይደርሳል ተብሎ የታቀደው የዚህ መርሃ ግብር አዘጋጆች ቲኤች ሚድያ ግሩፕ እና ስዊት ላይፍ ፎር ኦል ሲሆኑ፣ ዋና ዓላማቸውም በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ውስጥ ግንቦት 30 ቀን በኢትዮጵያ ብሔራዊ “የምስጋና ቀን“ ሆኖ እንዲሰየም ማድረግ እንደሆነ አስታውቀዋል።

የተገለጠው እውነታ
በ ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ
በምሥራቃዊው ኢትዮጵያ ይልቁንም በሐረር፣ አርሲና ባሌ አካባቢዎች ላይ ትኩረት አድርጎና አቅዶ ክርስቲያኖችን የሚገድል፣ የሚያፈናቅል እና የሚያሳድድ የአክራሪ ክንፍ መኖሩ ተደጋግሞ ሲነገር ኖሯል። ይህ አካል ደርግ ወድቆ ኢህአዴግ ከተተካበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛዋንም የለውጥ፣ የምርጫ እና የመሳሰሉትን የጫና ወቅቶች ጠብቆ አደጋ ያላደረሰበት ጊዜ የለም።
ከተቻለ የመንግሥት መዋቅርን በመጠቀምና በየዘመኑ ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም እና ለሚገድላቸው አካላት ከወቅቱ ፖለቲካ አንጻር የሚስማማ ታርጋ በመስጠት የሚቻለውን ያህል ይገድላል፣ ያፈናቅላል፣ ያሳድዳል።
ይህ የተገለጠ እውነት ነው። ተደጋግሞም ተነግሯል፣ ተገልጿል። ሆኖም እንደዚህ ዘመን እንደ ልቡ ክርስቲያኖችን የሚያጸዳበት ስለመኖሩ ግን አላውቅም። በእኔ እምነት ኢህአዴግ ከመጣበት ጀምሮ የተፈጸሙት ተደምረው በዚህ ዓመት ብቻ የፈጸመውን የመግደልና የማሳደድ ተግባር የሚያክሉ አይመስለኝም። ይህ ሁሉ ሲሆን አንድም መንግሥታዊ ተቋም ሐዘኔታ ሲያሳዩ፣ አንድም አካል ተጠያቂ ሲደረግ ዓይተንም ሰምተንም አናውቅም።
ይህም የተገለጠ እውነት ነው።
ምንም ቢሆን፣ ማንም ቢሆኑ ይህ ሁሉ መከራ የሚደርስባቸው ሰዎች ደግሞም ዜጎች ነበሩ። በደቡብ አፍሪካ ላለው ከሀገራችን ውጡ የሚል ዐመጽ ዜጎቹን ለመከላከል መንግሥት በኢንባሲው በኩል እየሠራ እንደሆነ የሚገልጽ ዜና ከሰማንና ለዚህኛው መንግሥት በዝምታ የሚያልፍ ከሆነ ድርጊቱን የሚፈጽመው እርሱም ጭምር ነው የሚለውን ወቀሳ እውነት ነው ብሎ በአዎንታ እንደተቀበለው ለመረዳት ግዴታችን ጭምር ይሆናል። ይህ በእውነት ከልብ ያሳዝናል።
አንድ የተረጋገጠና የትገለጠ እውነት ደግሞ አለ። የሰው ደም በከንቱ ፈስሶ አይቀርም። እግዚአብሔር የሚባል ተበቃይ አምላክ አለና። ለንስሐ ጊዜ ቢሰጥም "በቀል የእኔ ነው" ያለውና "ከኦሪትና ከነቢያት አንዲት ቃል ከምታልፍ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል" ያለው አምላክ ቃሉ የታመነ ነውና አይቀርም። እርሱ ሁላችንንም ይቅር ይበለን፣ የመከራውንም ወቅት አሳልፎ ለሰላምና ለፍቅር ያብቃን።

1ሺ 4መቶ 47ኛው የዒድ ኣል - አድሃ (አረፋ) በዓል በሐረር እየተከበረ ይገኛል
*************************
1ሺ 4መቶ 47ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የሃይማኖት አባቶች እና ምዕመናን በተገኙበት በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በሐረር ኢማም አህመድ ስታዲየም በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉን ሕዝበ ሙስሊሙ ለተከታታይ 10 ቀናት በጾም እና በምስጋና ካሳለፈ በኋላ በጋራ ሶላት እያከበሩ የሚገኝ ሲሆን፣ የፈጣሪን ትዕዛዝ መሰረት በማድረግ በመረዳዳት እና በመተጋገዝ የሚከበር በዓል ነው።
የሐረሪ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ሼክ አብዱሰላም ጂብሪል በአሉን አቅመ ደካሞችን በመደገፍ በመረዳዳት እና በመጠያየቅ ማክበር እንደሚገባ ገልፀዋል።
መጪው 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሕዝበ ሙስሊሙ የበኩሉን እንዲወጣ ያነሱት ሼክ አብዱሰላም ለሀገር እና ለሕዝብ የሚበጀውን በመምረጥ የወሰዱትን ካርድ ዋጋ እንዲሰጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ

Comments