የተገለጠው እውነታ
በ ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ
በምሥራቃዊው ኢትዮጵያ ይልቁንም በሐረር፣ አርሲና ባሌ አካባቢዎች ላይ ትኩረት አድርጎና አቅዶ ክርስቲያኖችን የሚገድል፣ የሚያፈናቅል እና የሚያሳድድ የአክራሪ ክንፍ መኖሩ ተደጋግሞ ሲነገር ኖሯል። ይህ አካል ደርግ ወድቆ ኢህአዴግ ከተተካበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛዋንም የለውጥ፣ የምርጫ እና የመሳሰሉትን የጫና ወቅቶች ጠብቆ አደጋ ያላደረሰበት ጊዜ የለም።
ከተቻለ የመንግሥት መዋቅርን በመጠቀምና በየዘመኑ ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም እና ለሚገድላቸው አካላት ከወቅቱ ፖለቲካ አንጻር የሚስማማ ታርጋ በመስጠት የሚቻለውን ያህል ይገድላል፣ ያፈናቅላል፣ ያሳድዳል።
ይህ የተገለጠ እውነት ነው። ተደጋግሞም ተነግሯል፣ ተገልጿል። ሆኖም እንደዚህ ዘመን እንደ ልቡ ክርስቲያኖችን የሚያጸዳበት ስለመኖሩ ግን አላውቅም። በእኔ እምነት ኢህአዴግ ከመጣበት ጀምሮ የተፈጸሙት ተደምረው በዚህ ዓመት ብቻ የፈጸመውን የመግደልና የማሳደድ ተግባር የሚያክሉ አይመስለኝም። ይህ ሁሉ ሲሆን አንድም መንግሥታዊ ተቋም ሐዘኔታ ሲያሳዩ፣ አንድም አካል ተጠያቂ ሲደረግ ዓይተንም ሰምተንም አናውቅም።
ይህም የተገለጠ እውነት ነው።
ምንም ቢሆን፣ ማንም ቢሆኑ ይህ ሁሉ መከራ የሚደርስባቸው ሰዎች ደግሞም ዜጎች ነበሩ። በደቡብ አፍሪካ ላለው ከሀገራችን ውጡ የሚል ዐመጽ ዜጎቹን ለመከላከል መንግሥት በኢንባሲው በኩል እየሠራ እንደሆነ የሚገልጽ ዜና ከሰማንና ለዚህኛው መንግሥት በዝምታ የሚያልፍ ከሆነ ድርጊቱን የሚፈጽመው እርሱም ጭምር ነው የሚለውን ወቀሳ እውነት ነው ብሎ በአዎንታ እንደተቀበለው ለመረዳት ግዴታችን ጭምር ይሆናል። ይህ በእውነት ከልብ ያሳዝናል።
አንድ የተረጋገጠና የትገለጠ እውነት ደግሞ አለ። የሰው ደም በከንቱ ፈስሶ አይቀርም። እግዚአብሔር የሚባል ተበቃይ አምላክ አለና። ለንስሐ ጊዜ ቢሰጥም "በቀል የእኔ ነው" ያለውና "ከኦሪትና ከነቢያት አንዲት ቃል ከምታልፍ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል" ያለው አምላክ ቃሉ የታመነ ነውና አይቀርም። እርሱ ሁላችንንም ይቅር ይበለን፣ የመከራውንም ወቅት አሳልፎ ለሰላምና ለፍቅር ያብቃን።

2 months ago