2 days ago
የሐረማያ ሐይቅ ማንሰራራት፦ የአረንጓዴ ዐሻራ ትሩፋት ማሳያ
********************
በተፈጥሯዊ እና በሰው ሰራሽ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ደርቆ ወደ አቧራማ ሜዳነት ተቀይሮ የነበረው ታሪካዊው ሐረማያ ሐይቅ አሁን ላይ በዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አማካኝነት ወደ ቀድሞ ይዘቱ ተመልሷል።
የሐረማያ ሐይቅ በዚህ መልኩ ማገገሙ በዕቅድ እና በጋራ ጥረት የተራቆቱ ሌሎች ተፋሰሶችንም ወደነበሩበት ሁኔታ መመለስ እንደሚቻል የሚያሳይ ሕያው ማረጋገጫ ሆኗል።
ሐረማያ ሐይቅ ለሐረማያ እና ለሐረር ከተሞች፣ ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ለአካባቢው ነዋሪዎች ዋነኛ የንጹህ መጠጥ ውኃና የግብርና መሠረት የነበረ ቢሆንም፣ በከፍተኛ የደን መጨፍጨፍ እና በደለል መሞላት ምክንያት ውኃ የመያዝ አቅሙን አጥቶ ተስፋ ተቆርጦበት የነበረ ነው።
ሆኖም ባለፉት ዓመታት በሐይቁ የላይኛው ተፋሰስ አካባቢዎች በተከናወነ የችግኝ ተከላ እና የእርከን ሥራ ወደ ሐይቁ ይገባ የነበረውን ከፍተኛ ደለል ከምንጩ መግታት ተችሏል።
በሌላ በኩል በሐይቁ ዙሪያ በተሠሩ የውኃ ማሳረፊያዎች አማካኝነት የዝናብ ውኃ ወደ መሬት እንዲሰርግ በማድረግ የሐይቁን ከርሰ ምድር ውኃ ክምችት እንዲጨምር ሆኗል።
በዚህም ሐይቁ ዳግም ውኃ መያዝ በመጀመሩ ቀደም ሲል አካባቢውን ለቀው የተሰደዱ በርካታ አእዋፍ፣ የጠፉ ዓሳዎች እና ሌሎች የውኃ ሕይወቶች እየተመለሱ ይገኛሉ።
የሐረማያ ሐይቅ ተሞክሮ ነገ የሚካሄደው የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ተራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ሳይሆን የታመመ ተፈጥሮን አክሞ የማዳን ሀገራዊ ጥረት መሆኑን የሚያስረግጥ ነው።
ይህ ተሞክሮ እያንዳንዱ ችግኝ የተራቆቱ አካባቢዎችን መልሶ የማቋቋም፣ የውኃ አካላትን የመታደግ እና የተጎዳ ተፈጥሮን የማከም ወሳኝ ድርሻ ይጫወታል።
ነገ በአንድ ጀምበር በጋራ የምናኖረው አረንጓዴ ዐሻራ የዛሬን የተፈጥሮ ቁስል እያከመ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ በውኃ ሀብት እና በልምላሜ ሙሉ የሚያደርግ ታሪካዊ ተግባር ነው።
በሐና ምንዳሁን
#ethiopia #climateaction #greenlegacy #800milliontrees #lakeharamaya #ebc #ebcdotstream

Comments