1 month ago
“ኢትዮጵያ አንድ ቪዛ ብቻ ወስደው መላውን ዓለም የሚያዩባት ድንቅ ሀገር ናት” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ቪዛ ብቻ ተጉዘው ከተፈጥሮ፣ ከሥነ-ምሕዳር፣ ከቅዝቃዜና ከሙቀት እንዲሁም ከጥንታዊ ታሪክና ባህል ባለብዙ መልክነትን በአንድ ላይ የሚያዩባት በዓለም ላይ ድንቅ ሀገር ኢትዮጵያ መሆኗን ገልጸዋል።
ወደ ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሚጓዝ ሰው ከአፍሪካ ሁለተኛ ከፍተኛ ቦታ የሆነውን የሰሜን ተራሮች ብርድና አስደናቂ መልክዓ ምድር አጣጥሞ፣ በጥቂት ሰዓታት ጉዞ ደግሞ በታሪክና በቅርስ የተሞላችውን የጎንደር ፋሲል ግንብን መጎብኘት እንደሚችል ጠቅሰዋል።
ከዚያም አልፎ ውብ መዳረሻ ወደሆነችው ጎርጎራ፣ የረጅሙ የዓባይ ወንዝ መነሻ ወደሆነው ጣና ገዳማትና የዛሬ 800 እና 900 ዓመታት የቆዩ የክርስትና የብራና ጽሑፎችና ቅርሶችን ተመልክቶ፣ በውቧ ባሕር ዳር ጉዞውን እንደሚያጠናቅቅ ጠቁመው፣ በዚህ መስመር ላወጣው ወጪ የሚቆጭ ማንም እንደማይኖር አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በዓለም ላይ በአንድ አቅጣጫ ሁሉንም ዓይነት ተፈጥሮ በጥምረት የያዘ እንደ ባሌ ዓይነት ቦታ ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ከባሕር ጠለል በላይ ከ4 ሺህ 300 ሜትር በላይ ከፍታ ባለው የቱሉ ዲምቱ ተራራ ላይ አስደናቂ ሐይቆችን፣ ብርቅዬዋን ቀይ ቀበሮና የሎቤሊያ ዕፅዋትን ተመልክቶ፣ በደቂቃዎች ልዩነት ወደ ሀረና ዝቅተኛ ጫካ ሲወርድ ለማመን የሚከብድ ጥቁር አንበሳ፣ ማራኪ ፏፏቴዎችና ብርቅዬ ወፎች ያሉበትን ጥቅጥቅ ያለ ደን ያገኛል ብለዋል።
በዲንሾ ብሔራዊ ፓርክ ከተላመዱ የዱር እንስሳት ጋር ከተገናኘ በኋላ፣ ወደ ሶፍ ዑመር ዋሻ ሲያመራ ደግሞ ከሕንድ ውቅያኖስ ጋር በቀጥታ ይገናኝ የነበረና የዛሬ 800 ዓመት የነበረ መስጊድ፣ አርቲፊሻል ሐይቅ እንዲሁም ከ60 በላይ ቋንቋዎች የሚማሩበት ታሪካዊ መድረሳ ያለበትንና ጥንታውያን ስልጡን ኢትዮጵያውያን የገነቡትን ገና ያልተደረሰበትን ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ በዓይኑ እንደሚመለከት ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ አስደናቂ ባለብዙ መልክነት በዚህ ብቻ እንደማያበቃ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ወደ አፋር ክልል የሚጓዝ ሰው የሰው ልጅ መገኛ ታሪክን ሰምቶ፣ በምድር ላይ መሆኑን የሚያጠራጥረውን የኤርታሌ የሚፈላ እሳተ ጎመራ እቶንና ማራኪውን የዳሎልን የሰልፈር ከለሮችና የጨው መስኮች እንደሚመለከት አብራርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእነዚህ በተጨማሪ ወደ ሐረር፣ ጅማ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ቢኬድ ሙቀትና ቅዝቃዜ፣ ከፍተኛና ዝቅተኛ መልክዓ ምድር፣ አስደናቂ የዱር እንስሳትና ጥንታዊ ታሪኮች የተሰናሰሉባት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት ብለዋል።
ይህንን ሁሉ ድንቅ የተፈጥሮና የታሪክ ጸጋ የያዘችውን ኢትዮጵያን ማንኛውም ዜጋ ሊያውቃትና ሊጎበኛት እንደሚገባ በማሳሰብ፣ ሀገራችን ተዘርዝረው በማያልቁና በእውነት “ይህ ስፍራ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ወይ?” በሚያሰኙ ማራኪ መዳረሻዎች የተሞላች መሆኗን ገልጸዋል።
#visitethiopia #onevisamultidestinations #pmabiyahmed #landoforigins #ethiopianbroadcastingcorporation

Comments