በልማት ሥራዎች 'ቅርሶች ይጠፋሉ' የሚለው ወቀሳ የፖለቲካ ፍጆታ እንጂ እውነተኛ የሕዝብ ስጋት አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግሥት እያከናወናቸው ባሉ ሰፊ የልማትና የእድሳት ሥራዎች “ቅርሶች ይጠፋሉ” በሚል የሚነሳው ወቀሳ የፖለቲካ ፍጆታ እንጂ እውነተኛ የሕዝብ ስጋት አለመሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት የሀገራችንን ቅርሶች በከፍተኛ ጥራትና ጥንቃቄ የሚጠብቅ፣ የሚያስውብ እና ለቀጣዩ ትውልድ የሚያሻግር እንጂ የሚያፈርስ አለመሆኑን በተግባር የተሠሩ ሥራዎችን በማንሳት አብራርተዋል።
በፖለቲካ ልምምድ ድክመት ምክንያት የሚሰሩ ሥራዎችን ሁሉ የመቃወም አዝማሚያ መኖሩን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በጎንደር የፋሲል ግንብ ላይ የነበረውን እውነታ በምሳሌነት አንስተዋል።
የፋሲል ግንብ ለመቶ ዓመታት ያህል ምንም ዓይነት እድሳት ሳይደረግለት በቁሙ እየፈረሰ እንደነበር አስታውሰው፣ መንግሥት ይህንን ታሪካዊ ቅርስ ለማዳን ሥራ ሲጀምር የተሳሳተ ቅስቀሳ ቢፈጠርም፣ ዛሬ ላይ በተሠራው የእድሳት ሥራ ግን ሕዝቡን ጨምሮ ማንም ኢትዮጵያዊና የውጭ ዜጋ የሚኮራበት ማራኪ ቅርስ መሆን መቻሉን ተናግረዋል።
በተመሳሳይ በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ በጅማ የአባ ጅፋር ቤተመንግሥት፣ በሐረር ጀጎል ግንብ እና በሶፍ ዑመር ዋሻ የተከናወኑት የጥገና እና የመሠረተ ልማት ሥራዎች ቅርሶቹን በከፍተኛ ጥንቃቄ የጠበቁ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና አባቶች ጭምር የሚመሰክሩት ሀቅ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ከዚህ ቀደም እንክብካቤ ተነፍጓቸው ፈርሰውና ተበላሽተው የነበሩት እንደ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ያሉ ስፍራዎችም፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት አግባብ ታድሰው ዛሬ ላይ በሚሊዮኖች የሚጎበኙ ውብ የቱሪዝም መዳረሻዎች መሆናቸውን ለአብነት አንስተዋል።
መንግሥት ያሉትን ታሪካዊ ቅርሶች ከማስዋብና ከመጠበቅ ባለፈ፣ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ዘመናት ከሀገር የተዘረፉና የጠፉ ከ35 በላይ ታሪካዊ ቅርሶችን ማስመለስ መቻሉንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስረድተዋል።
አሁንም በድርድር ሂደት ላይ ያሉ በርካታ ቅርሶች እንዳሉ ጠቁመው፣ እጅግ ማራኪ የሆነው የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ዙፋን (የመቀመጫ ወንበር) በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለስም ተናግረዋል።
መንግሥት የሁሉንም አካባቢዎችና ሃይማኖቶች ታሪክ ባካተተ እንዲሁም የኢትዮጵያን አጠቃላይ ገጽታ በሚያሳይ መልኩ የቅርሶችን ትክክለኛነትና ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃ በጠበቀ አግባብ እየሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በስሜትና በፖለቲካ ፍላጎት ብቻ የሚነሱ መሠረተ ቢስ ትችቶች መንግሥትን ወደ ኋላ እንደማይጎትቱት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ መንግሥት የኢትዮጵያን እምቅ የቱሪዝም አቅም ለዓለም አውጥቶ በማሳየት የቅርስ ጠባቂነትና አሻጋሪነት ታሪካዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
#heritageconservation #tourismethiopia #pmabiyahmed #preservinghistory #ethiopianbroadcastingcorporation

1 month ago