15 days ago
ታሪካዊ ድል ለኢትዮጵያ ሲኒማ
#ethiopia | በሌጎስ በተካሄደው የAMVCA ሽልማት ላይ ሁለት ዋንጫዎችን ወሰደ
የኢትዮጵያ የፈጠራና የፊልም ኢንዱስትሪ በአፍሪካ ትልቁና ተደራሽ በሆነው 12ኛው የ"Africa Magic Viewers’ Choice Awards (AMVCA)" መድረክ ላይ ታሪካዊ ስኬት በማስመዝገብ የአህጉሪቱን ትኩረት ስቧል!
የኩራት መዝገብ የተባሉት አሸናፊዎቻችን
አዲስ ፍቅር" (Addis Fikir)
በወጣቱና ጎበዙ ዳይሬክተር ልዑል ሸዋፈራው የተመራውና የአዲስ አበባን ዘመናዊ ህይወትና መንፈስ በድንቅ አቀራረብ ያስመለከተው ተከታታይ ድራማ ምርጥ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር በቀል ቋንቋ ፊልም" (Best Indigenous Language Film - East Africa) በመሆን አሸንፏል።
Out N' About" (Harar)
በብሩክ ይብራህ ፕሮዲውስ የተደረገውና የታሪካዊቷን የሐረር ከተማን ባህላዊና ታሪካዊ ገጽታ እውነተኛ በሆነ መልኩ ያቀረበው ይህ ጥልቅ ዘጋቢ ፊልም ምርጥ ያልተቀነባበረ ተከታታይ ፊልም" (Best Series - Unscripted) ዋንጫን በክብር ተቀብሏል።
ክብረ-ወሰን የሰበረው የኢትዮጵያ ልዑክ
በሽልማት ምሽቱ ላይ "ግዛት" (Gizat) የተባለው ተከታታይ ድራማን ጨምሮ ሦስት የሀገር ውስጥ ስራዎቻችን በ6 የተለያዩ ዘርፎች (የምርጥ ደራሲነትን ጨምሮ) ለመጨረሻው ሽልማት መታጨታቸው፣ የኢትዮጵያ ፊልም ስራዎች አሁን ላይ ዓለም አቀፍ ደረጃንና የሙያ ብቃትን ማሟላታቸውን ማሳያ ሆኗል።
ዛሬ በአትሌቶቻችንና በኳስ ስኬታችን ላይ ሌላ ትልቅ የጥበብ ድል ተጨምሮልናል። ያኔ በምናውቀው የውጭ ፊልሞችን ተርጉሞና ደብ አድርጎ (Dubbing) የማቅረብ ዘመን አልፎ፣ ዛሬ 100% ሀገር በቀልና ኦሪጅናል የሆኑ የራሳችንን ታሪኮች ይዘን አፍሪካን ማሸነፍ መቻላችን ትልቅ ኩራት ነው።
አቦል ቲቪ (Abol TV) እና መሰል የሀገር ውስጥ ይዘት የሚያሳድጉ ተቋማት ለፈጠራ ሰዎቻችን፣ ለዳይሬክተሮችና ለተዋንያን ትልቅ መድረክ እየሆኑ ነው።
ለአሸናፊዎቹና ለመላው የኪነ-ጥበብ ቤተሰብ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ!
#getu #amvca2026 #ethiopiancinema #addisfikir #outnaboutharar #aboltv #dstv #africanfilm #lagos #historicwin #የኢትዮጵያፊልም #አዲስፍቅር #አቦልቲቪ #ታሪካዊድል #ጌጡተመስገን #getutemesgen

16 days ago
u1210u1228u122du1293 u12a0u121du1235u1271 u12e8u1300u130eu120d u1218u130du1262u12eb u1260u122eu127d u1260u12aeu122au12f0u122d u120du121bu1275 u12cdu1265 u1308u1345u1273u1295 u12e8u121bu120bu1260u1235 u1270u130du1263u1229 u1270u1320u1293u12adu122e u1240u1325u120fu120du1362 u1260u121du123du1275 u12e8u12a5u130du122d u1309u12de u12e8u120du121bu1271u1295 u12cdu1324u1275 u12e8u1270u1218u1208u12a8u1275u1295 u1232u1206u1295 u1260u1300u130eu120d u1260u122eu127d u1201u1209 u12f0u121bu1245 u12a0u1240u1263u1260u120d u120bu12f0u1228u1309u120du1295 u12e8u1210u1228u122d u1290u12cbu122au12ceu127d u12a8u120du1265 u12a0u1218u1220u130du1293u1208u1201u1366 u121du12adu1275u120d u1320u1245u120bu12ed u121au1292u1235u1275u122d u1270u1218u1235u1308u1295 u1325u1229u1290u1205 #harari #mosob #ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ሐረርና አምስቱ የጀጎል መግቢያ በሮች በኮሪደር ልማት ውብ ገፅታን የማላበስ ተግባሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በምሽት የእግር ጉዞ የልማቱን ውጤት የተመለከትን ሲሆን በጀጎል በሮች ሁሉ ደማቅ አቀባበል ላደረጉልን የሐረር ነዋሪዎች ከልብ አመሠግናለሁ፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ #harari #mosob #ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation
25 days ago
የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር የሰውነት እሴትን የሚያጎለብት ታላቅ ኃይል ነው፡- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ
****************
"የሕዝቦች ሰላምና አብሮነት ለጋራ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል የሕዝብ ለሕዝብ የሰላምና የአብሮነት ኮንፈረንስ በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ በድምቀት ተካሂዷል።
የሐረሪ እና የኦሮሞ ሕዝቦችን ለዘመናት የዘለቀ ጠንካራ የአብሮነት እሴት ይበልጥ ለማጎልበት ያለመው ይህ መድረክ፣ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ወንድማማችነት የሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጓል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ ሰላም ለአንድ ሀገር ዕድገት፣ ለዜጎች ደህንነትና ለነገ ተስፋ መሠረት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ፣ ሰላም ማለት የጦርነትና የግጭት አለመኖር ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ መከባበር፣ መደማመጥ እና ልዩነቶችን በውይይት መፍታት መቻል ጭምር ነው።
ልዩነቶቻችን የመከፋፈል ምክንያት ሳይሆኑ ይልቁንም የመቀራረብ ኃይል መሆን እንዳለባቸው የጠቆሙት አቶ ኦርዲን፣ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር የሰውነት እሴትን የሚያጎለብት ታላቅ ኃይል መሆኑን አስገንዝበዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም የሐረሪ እና የኦሮሞ ሕዝቦች ለዘመናት በአንድ ገበያ የተገበያዩ፣ በአንድ ሰፈር የኖሩ፣ በደስታ ተሳስበው በችግርም የተደጋገፉ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ግንኙነታቸው በታሪክ፣ በደም እና በላብ የተገነባ ጠንካራ መሠረት እንዳለው አብራርተዋል።
በመድረኩ ከሐረሪ ክልል፣ ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን እና ማያ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ
#ethiopianbroadcastingcorporation #publicrelations #peaceandunity #harar #ethiopia

1 month ago
የሀረሩ ጃፓን!
የአገር ኩራት!
ያንዳንድ ሰው እድል ደሞ ይገርማል፡፡
የሀረሩ ጃፓን እንድል አሰኝቶኛል፡፡
ይህ የእውቁ ቢሊየነር የሮክፌለር መነሻ፤ መናገሻ ነው ኢስት ክሊቭላንድ ከተማ።
ሰውየው ደግሞ እስኪገርመኝ የነካኸው ይስፋ የተባለለት አይነት ነው።
“የአንዳንድ ሰው እድል ደግሞ ጉደኛ ነው፣” ከማለት ውጭ ሌላ ምን ይባላል።
ግራ ቢገባኝ ነው የሀረሩ #ጃፓን ማለቴ።
በአሜሪካ አገር ከፊት ከሚቆሙ በጣት የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊ ባለሃብቶች አንዱ ነው፡፡
የአለም ቀን መጀመሪያ የምስራቁ ክፍል መነሻ አገር ጥንቁቅ ወግ እና ባህል ለሚረዱ ነገሩ ይገባል፡፡
የጃፓኖች አመጋገብ ሆነ የምግብ ዝግጅት የተለየ ግምት የሚወስድ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ።
ለዚህም ነው በጃፓን ምግብ ስራ ለመሰማራት እንኳን ሌላ ጃፓናዊ እራሱ ሁለት ሶስቴ ማሰብ ይጠበቅበታል የሚባለው፡፡
ቢዝነስ እና ድፍረት ግን ያወጣል! እንዲል መርሁ
በምስራቅ አፍሪካ ከምስራቋ ታሪካዊ ከተማ ሀረር የፈለቀው ሰው ወደዚህ ቢዝነስ ሲገባ ውሳኔው የቢዝነስ ድፍረት ነበር፡፡
ጀመረው፤ እናም ብዙዎች ይሆንልኛል ብለው የማያስቡትን የጃፓን ጣእም አመጣው!
ተሳካለት!
የምወደውን ምግብ ለመመገብ ከባልደረቦቼ ጋር ጃፓን ሬስቶራንት ሄድኩኝ አለ ጨዋታው ሲነሳ፡፡
በምኖርበት ክሊቭላንድ ከተማ ወደሚገኝ የጃፓን ቴርያኪ ሬስቶራንት አቀናሁ የተመኘሁትን ለማግኘት ግን እንዳሰብኩት አልቀናኝም ይላል ለማ ጌታቸው፡፡
“ምግብ ልበላ ሄጄ ወረፋ አላስደርስ አለኝ፡፡ ያኔ ወሰንኩ።” የሚለው የተለያዩ ግዙፍ ቢዝነሶች ባለቤት፤ አስቦት በማያውቀው ነገር ግን ገንዘብ እንደሚያመጣ ቀልቡ በነገረው የምግብ ቢዝነስ ለዛውም ትልቅ ግምት በሚሰጠው የጃፓን ማእድ ስራ ሊሰማራ ወሰነ፡፡
እውነቱን ነው!
የሞላ ገበያ መገለጫዋ በሆነችው አገረ አሜሪካ ‘የምን ወረፋ ነው? የምን እጥረት?’
ቀልቡ ነገረው፡፡ እሱም አመነው፡፡ “ቢዝነሱ ተጨማሪ ዘዋሪ ይፈልጋል፣” ሲል ወሰነ በቀዝቃዛማዋ ኦሃዮ ግዛት የሞቀ የንግድ ህይወት የሚዘውረው ለማ፡፡
ቀልጣፋው የሃረር ልጅ ዘየደ። አንድ ወዳጁ ጋር ደወለ።
“ስማ ወዳጄ የፈጀውን ይፍጅ እስቲ ሁነኛ የጃፓን ሼፍ ፈልግልኝ፣” አለ፡፡ ተገኘ፡፡
መኖር ደጉ ጨላውን አወጣ! በሮክፌለር የቢዝነስ መነሻ ሰፈር፤ ኢስት ክሊቭላንድ ሬስቶራንቱ የሚከፈትበትን ቦታ ገዛው፡፡
አቦ ይመቸው!
ቢዝነሱ ተጀመረ። ተከፈተ፡፡ ተሳካ! መሳካት ብቻ አይደለም ሞቀ። በቅርንጫፎች ሰፋ፤ ደመቀ።
እንደ መደበኛ ተመጋቢ ምናልባት በወራት አንዴ ይሄድ እንደሆን እንጂ ዛሬ ቢዝነሱ እሱን አይፈልግም፡፡ ጥሩ ገንዘብ ግን ያመጣል፡፡
“ተመጋቢዎች ለምን እንዳማረን ይቅር?” በሚል የተጀመረው ቢዝነስ ዛሬ የካናዳ ድንበር በምትጋራው የኦሃዮ ክሊቭ ላንድ እና ኮሎምበስ ከተሞች ስራው ሞቋል፡፡
በሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶች ጫና፤ የራስ ሰው በማጣት እና በአንዳንድ አካባቢዎች የስራ ቦታ አመቺነት ችግር ቢዝነሱ እጅግ ማደግ የሚችልበትን እድል አልተጠቀምም እንጂ በጣም ሊሰፋ ይችል ነበር ይላል ለማ፡፡
ስለ እትዮጵያ ዲያስፖራ እንዲህ አለ፡፡ “እኛ ትንሽ ነን፡፡ የሆነ 10 ሺ ኢትዮጵያዊ ባለበት ከተማ ለምን መቶ የሀበሻ ምግብ ቤት ትከፍታለህ? ሁሉም ላይሰሩ ነው፡፡ ማን ውጤታማ ሊሆን ነው? ስንት ሰው በአንድ የሀበሻ ምግብ ቤት ሊመገብ ነው?” ሲል ይጠይቃል ለማ፡፡
“ሀበሾች መንቃት አለባቸው እርስ በእር ከመነጣጠቅ ይልቅ በርካታ ተመጋቢ ባለባቸው የሌላ አገር የሬስቶራንት ቢዝነሶች ጭምር ስለመሰማራት ማሰብ ይኖርባቸዋል፣” ሲል ሃሳቡን ያጋራል፡፡
ይህ ከለማ በርካታ ተስፈንጣሪ የቢዝነስ መገለጫዎጭ መካከል አንዱ ብቻ ነው፡፡
በርግጥ ሰውየው ብዙ ስራ አለው፡፡ ይህ የጃፓን ቴርያኪ ምግብ አቅራቢ እሱ ከደረሰበት የሀብት ማማ አንፃር እጅግ በጣም ትንሽ ነው፡፡ የትርፍ ጊዜ ስራ (ሆቢ እንደማለት)፡፡
የብዙ ክህሎት ባለቤት!
በግዛቱ አለ የተባለ የሪል እስቴት ኢንቨስተር ነው ለማ፡፡
በኦሀዮ ክሊቭላንድ እና ኮሎምበስ ከተሞች የሚያከራያቸው በርከታ የንግድ ህንፃ እና ቦታዎች አሉት፡፡
የተለያዩ ቢዝነሶች ጀምሮ ያሳካ፡፡
ለስደተኛ አይታለፍ የሚባሉ መከራዎችን የተሻገረ ጀግና፡፡
አይደለም ተወልዶ ላደገባት ኢትዮጵያ የህዝብ ወገን እና ደራሽ ነው ለማ በሰሜን አሜሪካ፡፡
ሀረር ከተማ አደሬ ጢቆ ነው ተወልዶ ያደገው፡፡
ጨዋታ አዋቂ፣ ወሬ የሚያምርለት፣ ተዝናንቶ የሚያዝናና ነው ይሉታል፡፡
ያደገበትን ያካባቢውን ወግ አልረሳም፡፡ ወደ አገሩ ሲመጣ አብሮ አደግ የሀረር ልጆችን ይዞ ይዞራል፡፡
ወርቃማ የህይወቱን ክፍል ውጭ ነው ያሳለፈው ከማለት ይልቅ እዛው ሀረር ነው የሚኖረው ያስብላል ነገረ ስራው፡፡
ቸርነቱስ ቢባል አሉ። ሰውየው በዚህ ጉዳይ ብዙ መናገር ባይፈቅድም እጁ የደረሰበት ልቡ ያውቀዋል።
መጪው ትውልድ ላይ ደግሞ ወጥሮ መስራት ነው መርሁ፡፡ ትምህርት ላይ ያምናል፡፡
የአገር ኩራት!
ኢትዮጵያውያኖች በደረሳችሁበት ይሁንላችሁ!
መሉቀን የወንደወሰን
ከአሜሪካ 🇺🇸
#harar #ጃፓን #ሀረር #teriyaki #clevelandohio #cleveland #teriyaki_express #lemmagetachew #lemma_getachew #ohio #japanesefood #ጃፓን #ethiopianfood #ethiopia #realestate #addisababarealestate #clevelandclinic #clevelandclinicabudhabi #clevelandsddisview #addisview #harar #japan #teriyaki #cleveland #ohio #success #business #diaspora #realestate #entrepreneur #ethiopian #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
📢 የምሥራች ከወደ ምሥራቅ ኢትዮጵያ!
* የመምህር መክብብ ዐሥራት (የሐረሩ) "ጌርሳም" የግጥም መጽሐፍ ሊታተም ነው 📚
#ethiopia | የአንጋፋው የሐረር ራስ መኮንን ት/ቤት ሚኒ ሚዲያ ዓርማ፣ የብዙዎቻችን የሞያ አባት እና መካሪ፣ በ"ንስር ዓይን" የሬዲዮ ዝግጅቶቹ የምናውቀው መምህር መክብብ ዐሥራት፤ ከ30 ዓመታት በላይ ያካበተውን የሥነ-ጽሑፍ ልምድ "ጌርሳም" በተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ከትቦ ይዞልን መጥቷል።
በዶ/ር እንዳለጌታ ከበደ፣ በገጣሚ አበባው መላኩ እና በመምህር ገዛኸኝ ፀጋው (ዶ/ር) የተገመገመ ድንቅ ሥራ ነው!
ስለ መጽሐፉ ሊቃውንት ምን አሉ?
"ጌርሳም መክብቤን መመልከቻ አንዷ መነጽራችን ናት፡፡ ገጣሚው በልቡ ውስጥ የታተመውን አሻራ ነው ያስጎበኘን፡፡ አሻራዎቹ ደግሞ አገር ወዳድነቱን፣ ቀናኢ ስሜቱን፣ ማኅበራዊ ሃያሲነቱን አምነን እንድንቀበል የሚያስገድዱ ናቸው፡፡"
— ዶ/ር እንዳለጌታ ከበደ (ደራሲ)
"በግጥሞቹ ሕይወትን፣ አካባቢን፣ ሰውነትን ሞግቷል፡፡ በጥሩ የአገጣጠም ስልት ባልጠነነ የቋንቋ ለዛ አስውቦ የሰደራቸውን ስንኞች እነሆ ብሎናል።"
— ገጣሚ አበባው መላኩ
💰 የመጽሐፉ ዋጋ: 400 ብር
በኦንላይን ለሚገዙ ዋጋ 350 ብር ነው
🏦 ገቢ የሚደረግበት ሂሳብ ቁጥር:
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000302286489
ስም: Tsedey Melaku Tesfaye
(ፀደይ መላኩ ተስፋዬ)
⚠️ ማሳሰቢያ:
ገቢ ሲያደርጉ ደረሰኙን እና የመጽሐፍ ተረካቢውን ስልክ በቴሌግራም/ሜሴንጀር ለ +251-915-740291 መላክዎን አይርሱ።
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ #ሼር ያድርጉት!
ለበለጠ መረጃ (አስተባባሪ): 0915 46 46 46 (ታሪኩ ለሜሳ)
ወዳጆች ሆይ፤ እንረባረብ!
ለጋሽ መክብብ ያለንን ክብርና ፍቅር ለመግለጽ፤ መጽሐፉን አስቀድመን በመግዛት ድጋፋችንን እናሳይ።
#gersam #mekbibasrat #harar #poetry #newbook #ethiopianliterature

“ሸንተም ሹቢሳ”- ትዝተኛው አንበሳ
------
ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ
-----------
#ethiopia | ከአንጋፋ አርቲስቶቻችን መካከል አንዱ ሙሐመድ ኢብራሂም ወዳይ ነው፡፡ ሆኖም ሰውዬውን በዚህ ስም የሚያውቀው ሰው ብዙም አይደለም፡፡ እኔም ይህንን ስም የጠቀስኩት እናትና አባቱ ያወጡለት መጠሪያው መሆኑን ልነግራችሁ በመፈለጌ ነው እንጂ እናንተ በምታውቁት ስም “ሸንተም ሹቢሳ” ብዬ ልጠራው እችል ነበር፡፡
አዎን! ሸንተም ሹቢሳ አንጋፋ አርቲስት ነው፡፡ ይህ ኮከብ የተወለደው በድሬ ዳዋ ከተማ ነው፡፡ የወጣትነት ዕድሜውንም እዚያው ነው ያሳለፈው፡፡ ቀልቡ በሙዚቃ የተሳበው ገና ወጣት ሳለ በ1940ዎቹ ነው።
የአፍረን ቀሎ ቡድን አንጋፋ አባልም ነበር፡፡ ሸንተም ሹቢሳ ገጣሚ፣ ዜማ ቀማሪና የስነ-ቃል ሊቅም ነው፡፡ አርቲስት ሸንተም ከሌሎች አርቲስቶች የሚለየው ከዘፈኖቹ መካከል ለሚበዙት ዜማና ግጥም የደረሰው እርሱ ራሱ በመሆኑ ነው፡፡ ሌሎች ዘፋኞችም የርሱን ዘፈኖች እየወሰዱ ተጫውተዋቸዋል፡፡
ለምሳሌ ሐመልማል አባተ የሸንተምን ዘፈኖች በመዝፈን ትታወቃለች፡፡ ከነርሱም መካከል በጣም ዝነኛው “ኪያ ኪያ” የተሰኘው ነው፡፡ ሌላው ደግሞ “ቦና ሀረርጌ” የተሰኘው ነው፡፡ እስቲ “ቦና ሀረርጌ”ን ላስታውሳችሁ (ዘፈኑን ሸንተም የተወጫተው “ቦንቱ ሀረርጌ” በማለት ነበር፤ በመሆኑም “ቦንቱ ሀረርጌ” ወደሚለው ቀይሬዋለሁ)፡፡
Gamnomni khee ajabaa
Arjoomni khee jaalalaa
Miidhagni keetis daran dhaabbatni khee waatola
Khabajaa fi arjoomummaa hundaatu sirrati wal-gaha
----
Miidhagni kee honga hinqabu
Boontuun Harargee naaf lubbuu
Bareedni kee hammanaa hammasi
Je’ee himuu hindandayu
----
በአማርኛ ለመፍታት ብንሞክረው እንዲህ ሊሆን ይችላል (ቃል በቃል አልተረጎምኩትም)፡፡
አርቆ ማሰብሽ አጃዒብ ነው፤ ችሮታሽም ፍቅር ነው
ውበትሽ ከዚያም ይበልጣል፣ ቁመናሽማ ልዩ ነው
ክብርና ለጋስነት ሁሌ ባንቺ ላይ ነው የሚሰባሰበው፡፡
---
ውበትሽ እንከን የለውም
የሀረርጌ ጉብል ነፍሴ ናት
ቁንጅናሽ እንዲያ ነው እንዲህ ነው
ብሎ መናገር ለምላሴ ተሳናት
---
በ1960 ገደማ ሸንተም ሹቢሳ ከጥቂት ጓደኞቹ ጋር ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተሰደደ፡፡ በኋላም ከጓደኞቹ ጋር የኃይለ ሥላሴን መንግሥት በትጥቅ ትግል የመጣል እቅድ ወጥኖ በሰሜን ሶማሊያ በኩል ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ላይ ሳለ በሶማሊያ ወታደሮች ተያዘ፡፡ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ዚያድ ባሬ በነበረው የመስፋፋት ምኞት የሀረርጌ ኦሮሞ “ሶማሌ አቦ” ነው በማለት ሲያካሄደው የነበረውን ፕሮፓጋንዳ እንዲቀበሉና በሶማሊያ ስም እንዲታገሉ ጠየቃቸው፡፡ ሸንተም ሹቢሳ እና ጓደኞቹ ግን ተቃውሞአቸውን ፊት ለፊት ገለጹለት፡፡ በዚህም ምክንያት ሸንተምና ጓደኞቹ ለአምስት ዓመታት በስመ-መጥፎው የማንዼራ እስር ቤት ታስረዋል (ይህ እስር ቤት በአሁኑ የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ውስጥ ነው የሚገኘው)፡፡
ሸንተም ሹቢሳ ከእስር ከወጣ በኋላ ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ የዚያድ ባሬን ፕሮፓጋንዳ “ገዋን ሂንዸለቲን” በተሰኘው ዘፈኑ አምርሮ ተችቶታል፡፡ ይሁንና በሀገር ቤትም በሰላም ለመኖር አልታደለም፡፡ የደርግ የአፈና አገዛዝ የፈጠራ ስራውን በነጻነት እንዲሰራ ስላልፈቀደለት በቅድሚያ ወደ ጅቡቲ ተሰደደ፡፡ በ1980ዎቹ ደግሞ ወደ አውስትራሊያ ተሻገረ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሀገረ አውስትራሊያ ነው የሚኖረው።
------
ከሸንተም ሹቢሳ ዘፈኖች መካከል ዘወትር የማልረሳው አንድ ዘፈን አለ፡፡ ይህ ዘፈን በዜማና ግጥሙ ውህደት በጣም ውብ የሚባል ነው፡፡ እስቲ ግጥሙን አንዴ ልጻፍላችሁ!
Naaf si uume siif na uume nu lachuu wal-duraa
Hamdi gooytaa nu ciqqaawe Rabbi foon tokkorraa
-----
Ani aaree dallansuudhaan yoon dufee gama khee
Kokofleetin of wallaala agarraan fuula khee
-----
Ani si qofan jiruu tiyyaaf filadhe
Ani simalee ani simalee
Ani simalee je’ee durin khakhade
---
የዚህ ማራኪ ጣዕመ ዜማ ደራሲ በሸንተም ሹቢሳ ራሱ፡፡ ትርጉሙም እንዲህ ነው፡፡
---
ለኔ ነው የፈጠረሽ ላንቺው ነው የፈጠረኝ
ሁለታችንም አንድ አምሳያ፡፡
ካንድ ስጋ ቆርሶ የሰራን አንድዬ ይመስገን
የሌለው እኩያ፡፡
---
በጣም ተናድጄ ወዳንቺ ብመጣ መልኬን አጠልሽቼ
ወዲያው ስቄ እረሳዋለሁ ፊትሽን አይቼ
---
አንቺን ብቻ ነው ለህይወቴ የመረጥኩት
ድሮ ነው “ካንቺ በቀር” ካላንቺ በቀር
ብዬ የማልኩት፡፡
---
ይህንን ዜማ በጣም ነው የምወደው። በጣም ነው የማስታውሰው። ለለምን መሰላችሁ? የልጅነት ትዝታ አለኝ፡፡ የደጉ ዘመን ማስታወሻ!!
የከተማችን (ገለምሶ) ዋነኛ የገበያ ቀን ማክሰኞ ነው፡፡ በዚህ ቀን በመላው የሀብሮ አውራጃ የሚኖሩ ገበያተኞች ለግብይት ይመጣሉ፡፡ እቃ የሚሸጠው፣ ቡና የሚገዛው፣ ከብት የሚሸጠው ወዘተ.. ሁሉም ይመጣል፡፡ ከዚህ ለየት የሚሉ ሰዎች ደግሞ አሉ፡፡ የስፌት መኪናቸውን በመኪና አስጭነው የሚመጡ! እነዚህ ልብስ ሰፊዎች የከተማዋ ነዋሪ ከሆኑ ሌሎች ልብስ ሰፊዎች የሚለዩት ለዚያች አንድ ቀን ብቻ ወደ ገለምሶ የሚመጡ በመሆናቸው ነው፡፡ በማክሰኞ ቀን በጠዋቱ ላይ የስፌት መኪናቸውን አስጭነው ከች ይላሉ፡፡ ከገጠር አካባቢዎች የሚመጡት ወገኖቻችንን ልብሶች ሲሰፉ ይውላሉ፡፡ በአስራ ሁለት ሰዓት ሰዓት ገደማ ያገኙትን ሲሳይ ይቋጥሩና ወደ መጡበት ይመለሳሉ፡፡
ከነዚያ ልብስ ሰፊዎች አንዱ “አደሜ” ይባላል፡፡ አደሜ ወደ ገለምሶ የሚመጣው ከመቻራ ከተማ ነው፡፡ ጧት የስፌት መኪናውን ያስጭንና ከች ይላል፡፡ በከተማችን መሀል ላይ ከሚገኘው የአቶ ማማ ዩሱፌ መደብር ስር ገበያተኞችን ይጠብቃል፡፡ ገበያተኞቹ ሲመጡለት የተለያዩ ብትን ጨርቆችን ይቀበላቸውና ሲሰፋላቸው ይውላል፡፡ ምሽት ላይ ስራውን አጠናቅቆ ወደ መቻራ ይመለሳል፡፡
ታዲያ አደሜ ልብሱን ሲሰፋ በአፉ ዝም አይልም፡፡ ቀኑን ሙሉ ሲዘፍን ነው የሚውለው፡፡ ዘፈኑ ደግሞ አንድ ብቻ ነው፡፡ እርሱኑ ነው የሚደጋግመው፡፡ ደግሞም በከፍተኛ ተመስጦ እየጮኸ ነው የሚዘፍነው፡፡ ሆኖም እኛ ታዳጊዎቹ የዘፈኑን ግጥም ስለማናውቀው “ወጀላቴ….ወጀላቴ…” የሚል ቃል የሚደጋግም ይመስለን ነበር፡፡ በመሆኑም “ወጀላቴ” የሚል ቅጽል አወጣንለት፡፡
በዚያ ወርቃማ ዘመናችን ማክሰኞ ዕለት በጣም ነበር የሚናፍቀን፡፡ ማክሰኞ እንዲናፍቀን ከሚያደርጉት ምክንያቶችም አንዱ ማራኪው የአደሜ “ወጀላቴ” ጨዋታ ነው፡፡ እናም በማክሰኞ ዕለት ከእኩለ ቀን በኋላ የአንድ ሰፈር ልጆች ተሳበስበን ወደ ማማ ዩሱፌ መደብር መሄድ የዘወትር ተግባራችን ነበር፡፡ በመጀመሪያው ላይ የአደሜን ዘፈን ከመስማት በስተቀር ሌላ ተንኮል አልነበረብንም፡፡ በሂደት ግን ተንኮል ለመድን፡፡ ከአደሜ ፊት እንቆምና ከፍ ባለ ድምጽ
“ወጀላቴ… ወጀላቴ…
ወጀላን… ወለጃቴ…
አለለ ለላ!…አለለ..ለላ”
እያልን እንዘፍናለን፡፡ አደሜ ይናደድና ስፌቱን ትቶ እኛን ያባርራል፡፡ ከዚያም የስፌት መኪናው ወደ ተቀመጠበት ይመለሳል፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግን እንደገና ተሰባስበን እንመጣና ከፊቱ ቆመን “ወጀላቴ… ወጀላቴ…” እያልን እንዘፍናለን፡፡ አደሜም እንደፈረደበት ከመቀመጫው ተነስቶ ያባርረናል፡፡ እንዲህ እያደረግን ቀኑን ሙሉ በንዴት እንዲቃጠል እናደርገዋለን (አላህ ይቅር ይበለን መቼስ!… ልጅነት የማያደርገው ነገር የለም!)፡፡
በኋላ ጎረመስኩ፡፡ በ1989 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆንኩ፡፡ በዚያው ዓመት ሻፊ አብዱላሂ በዳሶ የሚባል አማቻችን (የአክስቴ ባል) ከሳዑዲ ዐረቢያ መጣ፡፡ እናም አንድ ቀን ከርሱ ጋር ቁጭ ብለን ሳለ ያንን የአደሜን ዘፈን ከነሙሉ ግጥሙ ለቀቀው፡፡ “አጃዒብ!” ብዬ አደመጥኩት፡፡ “ይህ አሁን የዘፈንከው የእውነት ዘፈን ነው? ወይንስ አንተ ራስህ ፈጥረኸው ነው?” ብዬ ጠየቅኩት፡፡ የሸንተም ሹቢሳ ዘፈን መሆኑን ነገረኝና ሙሉ ግጥሙን አስጨበጠኝ፡፡ በዚያች ቅጽበት አደሜ ትውስ አለኝ፡፡ ልጅነታችን በከንቱ እንደሸወደን ተገለጸልኝ፡፡
አንዳንዴ ትንንሽ ነገሮች ያስገርሟችኋል አይደል? እኔን ካስገረሙኝ ትንሽዬ ነገሮች መካከል አንዱ ያ አደሜን “እንደውክበት” የነበረው የልጅነት ጨዋታችን ነው፡፡ ለኛ የአደሜ የግል ፈጠራ ይመስለን የነበረው ዘፈን የታላቅ ሰው ውድ ስራ በመሆኑ በጣም ነበር የተደነቅኩት፡፡ ሸንተም ሹቢሳን ከልጅነቴ ጀምሮ ባውቀውም ሻፊ እስኪያስረዳኝ ድረስ ያ ዘፈን የአደሜ የግል ጨዋታ ይመስለኝ ነበር፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ ቀመር ዩሱፍ ዘፈኑን ባማረ ሁኔታ ተጫውቶት ሰማሁት፡፡ በ1997 ደግሞ ሸንተም ሹቢሳ ራሱ በድጋሚ ተጫወተው፡፡
እንግዲህ ይህንን የልጅነት ትዝታ ጥሎብኝ ያለፈ ስራ የሰራልን ሸንተም ሹቢሳ ነው፡፡ ሸንተም ሹቢሳን ያስገኘችው ደግሞ ውዲቷ ድሬ ዳዋ ናት፡፡ ከዋክብት መፍጠር የማያልቅባት ቀሽቲ ከተማ!
----
አፈንዲ ሙተቂ
ኡመተ ፈናን ኡመተ ቀሽቲ ዲሬዳዋ ከተሰኘው መጽሐፌ የተወሰደ

Sponsored by
Surafel
11 months ago
ክረምት መውጫ
#ethiopia | ክረምት እንደመሆኑና ብዙ ሰው ምን ላንብብ ጠቁመኝ ባለኝ መሰረት ቀለል ያሉ ሁሉም ሰው ሳያነባቸው መሞት የለበትም ብዬ የማስባቸውን ከእንግሊዘኛ 20 ከሀገር ውስጥ 20 እንዲሁም ከትርጉም 20 በርግጥ ቁጥሩ አንሷል ቢሆንም በቀላሉ የሚገኙት ብዬ ካሰብኩት ነው።
ሌሎች መጽሀፍቶቼን በየ ስርቻው ደብቄ እነኚህን ግን ፊት ለፊት አስቀምጬ በየ ሆነ ግዜው የምደግማቸውና በፍጹም ለሰው የማላውሳቸው አንብቤ የወደድኳቸው መጽሀፍቶች ናቸው እያየን ደሞ እንጨምራለን አሰልቺ እንዳይሆን ብዬ ነው 🙌
#ከ_እንግሊዘኛ_መነበብ_አለባቸው_ብዬ_ከማስበው_ውስጥ :-
📌 the brother Karamazov by Dostoyevsky
📌 crime and punishment by Dostoyevsky
📌 notes from underground by Dostoyevsky
📌 The Trial by Franz Kafka
📌metamorphosis by Franz Kafka
📌Animal Farm by George Orwell
📌 Nineteen Eighty-Four by George Orwell
📌Thus Spoke Zarathustra by Nietzsche
📌Beyond Good and Evil by Nietzsche
📌The Birth of Tragedy
📌The Stranger by albert Camus
📌The Plague by albert camus
📌The Myth of Sisyphus
📌Being and Nothingness by Jean-Paul Sartre
📌The World as Will and Representation by Schopenhauer
📌The Interpretation of Dreams by Sigmund Freud
📌Man and His Symbols by Carl Jung
📌Man's Search for Meaning by Viktor Frankl
📌Night by Elie Wiesel
📌the old man and the sea by Hemingway
📌sapiens by yuval harari
ቀለል ያለውን ለመጥቀስ ያክል እና እንደልብ ስለሚገኙ እንጂ ሌላ ብዙ የምለው ነበረኝ 😃
#ከ_አማርኛ_መነበብ_አለባቸው_ብዬ_ከማስበው_ውስጥ
📌 እግረመንገድ በ ስብአት ገ/እግዚአብሔር
📌አምስት ስድስት ሰባት በ ስብአት ገ/እግዚአብሄር
📌እነሆ ጀግና ስብአት ገ/እግዚአብሔር
📌ማስታወሻ በ ዘነበ ወላ
📌ኦሮማይ በ በአሉ ግርማ
📌ሀዲስ በ በአሉ ግርማ
📌ጥበብ በ ሀይለጊዮርጊስ
📌የፍልስፍና አጽናፍ በ አለማየሁ ገላጋይ
📌ቅበላ በ አለማየሁ ገላጋይ
📌ዋሪሳ በአለማየሁ ገላጋይ
📌 ማእበል ጠሪ ወፍ በአለማየሁ ገላጋይ
📌የስንብት ቀለማት በ አዳም ረታ
📌ግራጫ ቃጭሎች በ አዳም ረታ
📌ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ በአዳም ረታ
📌መረቅ በአዳም ረታ
📌የቅኔ ውበት በ ከበደ ሚካኤል
📌 እሳት ወይ አበባ በ ጸጋዬ ገብረመድህን
📌አደፍርስ በዳኛቸወ ወርቁ
📌የባስሊቆስ እንባ በ ትእግስት ታፈረ
📌በፍልስፍና መደመም በ ዋለልኝ
📌ጠመንጃና ሙዚቃ በ ይነገር ጌታቸው
📌ፊታውራሪ ተክለሀዋሪያት በ ግርማቸው (ልጃቸው ነው ኦቶባዮግራፊ)
📌ልኡል እራስ እምሩ (ኦቶባዮግራፊ)
ከ ሀያ እንዳይበልጥብኝ እንጂ ብዙ የምለው ነበረኝ 😅
ከ_ትርጉም_መነበብ_አለባቸው_ብዬ_ከማስበው_ውስጥ
📌ካፖርቱ ተርጓሚው ጠፍቶኛል
📌እፎይታ ትርጉም ተሾመ ዳምጠው
📌ፓፒዮ ተርጓሚው ጠፋኝ
📌የመጨረሻው ፈተና በ ማይነግረው
📌እምዮ ሳህለስላሴ
📌እናት ተርጓሚው ተረስቶኛል
📌ምጽአተ እስራኤል በማሞ ውድነህ
📌መከረኞቹ ሳህለስላሴ
📌ብርቅርቅታ አብይ ደምሴ
📌ሆሞዲየስ በ ዳግም
📌ግራጋቢው ዘመን በ ተስፋጽዮን
📌ቡቃያው በ ሙሉብርሀን ታሪኩ
📌 የሀገር ልጅ ሳህለስላሴ
📌ቼሆቭ አጫጭር በበላይነህ አሰጉና በ ጌታቸው
📌ሁለት አጫጭር ታሪኮች (ቱርጌኒቭ) በ ደስታ ታደሰ
📌ያንገት ጌጡ በ አውግቸው ተረፈ
📌ታራስ ቡልባ በበካፋ ሀይለ
📌ሌቭ ቶሎስቶይ ካሳይ ገብሬ
📌ሽማግሌውና ባህሩ ተርጓሚው ተዘነጋኝ
📌የሩሲያ ልቦለድ ታሪኮች በ መኩሪያ
በያሬድ ግርማ