Logo
FastMereja
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሐምሌ 7/1940 ዓ.ም በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጨለንቆ አቅራቢያ በምትገኝ ፈንዲዴ በተባለች መንደር ተወለዱ።

እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በትውልድ መንደራቸው ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን በሐረር በሚገኘው የላዛሪስት አባቶች የዘርዐ ክህነት ትምህርት ቤት በመግባት መንፈሳዊ ጥሪያቸውን ጀመሩ።

ከዚያም በአዲስ አበባ በሚገኘው የካፑቺን ፍራንቸስካውያን የፍልስፍናና ቲዎሎጂ ኮሌጅ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ወደ እንግሊዝ ሀገር በማምራት በለንደን ዩኒቨርሲቲ በሶሺዎሎጂ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
እ.አ.አ ሰኔ 1976 ምስጢረ ክህነትን የተቀበሉ ሲሆን
የማኅበረ ልዑካን አባቶች ላዛሪስት ገዳም ያፈራቸው ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ጥር 17/1990 ዓ.ም ጵጵስናን ፤ የካቲት 7/2007 ዓ.ም በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አማካኝነት የካርዲናልነት ማዕረግን ያገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ታሪክ ከብፁዕ ጳውሎስ አድዋ ቀጥሎ ካርዲናል የሆኑ ሁለተኛው ጳጳስ ናቸው።
ብፁዕ ካርዲናል በኢትዮጵያ በሰላም ሚኒስቴር ስር ተቋቁሞ የነበረው የብሔራዊ እርቅና ሰላም ኮሚሽን ውስጥ በሊቀመንበርነት አገልግለዋል።

ብፁዕነታቸው ለቅድስት መንበር ባቀረቡት የጡረታ ጥያቄ መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ ጥያቄያቸውን መቀበላቸውን በቅድስት መንበር ልዪ መልዕክተኛ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ጉጀሮቲ አማካይነት ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል።

ለብፁዕ አባታችን እንኳን ለ50ኛ ዓመት የክህነት በዓልዎ በሰላም አደረስዎት።

27 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.