6ኛው “ጣፋጭ ሕይወት” የምስጋና ፕሮግራም በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ
#fastmereja I ዜጎች በሕይወታቸው መልካም የዋሉላቸውን ባለውለታዎች የሚያመሰግኑበትና ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ የተዘጋጀው “ጣፋጭ ሕይወት የምስጋና ፕሮግራም” በአዲስ አበባ፣ በሐዋሳ እና በሐረር ከተሞች ሙሉ ቀን የቆዩ ልዩ ልዩ የክብር መርሃ ግብሮችን በማካተት በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ።
የዘንድሮው የምስጋና ቀን መርሃ ግብር ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሦስቱም ከተሞች ለአካባቢ ጥበቃና ውበት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ የፅዳት ባለሙያዎችን በማህበረሰቡ ዘንድ ታላቅ ምስጋና እና ክብር በመስጠት ተጀምሯል። በመቀጠልም ከረፋዱ 2:00 ሰዓት ላይ መምህራን ከተማሪዎቻቸው ደማቅ የእውቅና ስነ-ስርዓት የተበረከተላቸው ሲሆን፣ በምሳ ሰዓት ደግሞ በየሆስፒታሎቹና በሕክምና ተቋማቱ የሚገኙ ታካሚዎች የሕክምና ባለሙያዎችን በአካል በመገኘት አመስግነዋል።
ከምሽቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ ከአምስት መቶ በላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም ታዋቂና በጎ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በታደሙበት ስድስተኛው ጣፋጭ ሕይወት ምስጋና መርሃ ግብር በአምስት ዘርፍ የሚመሰገኑ አካላት እውቅና አግኝተዋል ።
ከ15 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ጋር ይደርሳል ተብሎ የታቀደው የዚህ መርሃ ግብር አዘጋጆች ቲኤች ሚድያ ግሩፕ እና ስዊት ላይፍ ፎር ኦል ሲሆኑ፣ ዋና ዓላማቸውም በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ውስጥ ግንቦት 30 ቀን በኢትዮጵያ ብሔራዊ “የምስጋና ቀን“ ሆኖ እንዲሰየም ማድረግ እንደሆነ አስታውቀዋል።

5 days ago