Logo
Ethio telecom
🏃‍♀️🏃‍♂️ የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በሐረር በድምቀት ተካሔደ!!

መነሻና መድረሻውን ሐረር በር ላይ በማድረግ ፕሮፌሽናል አትሌቶችና ከአዲስ አባባ ተጓዥ ተሳታፊዎችን ያካተተ ልዩ የ10ኪ.ሜ ውድድር በወንዶችና በሴቶች ደስ በሚል ድባብ ተካሒዷል።

በተጨማሪም ተተኪዎችን ለማፍራት ከ16 ዓመት በታች ታዳጊ አትሌቶች የተሳተፉበት የ1.5 ኪ.ሜ ውድድርና ከ11 ዓመት በታች ልጆች የተሳተፉበት የ1 ኪ.ሜ.ውድድር ሌላው የዕለቱ ድምቀት ነበር፡፡

የአገራችን አትሌቲክስ ለማሳደግና ተተኪዎች ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮም በስያሜና የቴክኖሎጂ አጋርነት ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር እየሠራ የሚገኝ ሲሆን ወደ ፊትም በአትሌቲክሱ ዘርፍ የምናደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክረን እንቀጥላለን።
#ethiotelecomgreathararrun #greatethiopianrun #harar #telebirr #ethiotelecom

19 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.