28 days ago
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሪያል ማድሪድ ኢንተር ሚላንን 2 ለ 1 አሸነፈ
********************
በ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ቀን ሪያል ማድሪድን ከኢንተር ሚላን ያገናኘው ተጠባቂው የሳንቲያጎ በርናባዎ ጨዋታ በሪያል ማድሪድ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ለሪያል ማድሪድ ግቦቹን በመጀመሪው አጋማሽ 14ኛው ደቂቃ ላይ ኪሊያን ምባፔ እንዲሁም 23ኛው ደቂቃ ላይ ፌደሪኮ ቬልቫርዴ አስቆጥረዋል።
ለኢንተር ሚላን ብቸኛዋን ግብ በሁለተኛው አጋማሽ 77ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው ካርሎስ አውጉስቶ ነው።
ከጨዋታው መጀመር አስቀድሞ በቀደመው የውድድር ዓመት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 15 ግቦች በማስቆጠር ኮከብ ግብ አግቢ የሆነው ኪሊያን ምባፔ የወርቅ ጫማ ሽልማቱን ከቀድሞ ፖርቹጋላዊ ኮከብ ሉዊስ ፊጎ እጅ ተቀብሏል።
በሌላ ጨዋታ ማንቸሰተር ሲቲ ወደ ፖርቹጋል ተጉዞ በኤርሊንግ ሀላንድ ግቦች ፖርቶን 2 ለ 0 አሸንፏል። ግቦቹ ለሃላንድ በ59 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ያስቆጠራቸው 58ኛ እና 59ኛ ሆነው ተመዝግበዋል።
ሪያል ቤቲስ ሊልን 3 ለ 2 ያሸነፈበት እንዲሁም ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ቪያሪያልን 3 ለ 1 የረታበት ሌሎች የ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ቀን መርሐ ግብሮች ናቸው።
#ucl #uefachampionsleague #uefa #realmadrid #intermilanfc #manchestercityfc #porto #matchday #football #sports #ebc

1 month ago
ድህነት የአእምሮን መጠን ያሳንሳል፤ እርጅናንም ያፋጥናል ተባለ
የረዥም ጊዜ ሳይንሳዊ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ዝቅተኛ ገቢና ስር የሰደደ የገንዘብ እጥረት የአእምሮን መጠን ለማሳነስና የአስተሳሰብ ብቃትን ለመቀነስ ምክንያት ይሆናሉ።
በለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ (UCL) ተመራማሪዎች የተካሄደ አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው፣ በወጣትነት እና በጎልማሳነት እድሜ የሚከሰት ዘላቂ የገንዘብ እጥረት ወይም ዝቅተኛ ገቢ በዕድሜ መግፋት ወቅት የአእምሮ ህመም እና የማስታወስ ችሎታ መቀነስ አደጋን ያፋጥናል።
በኢኖቬሽን ኢን ኤጅንግ ጆርናል ላይ የታተመው ይህ ጥናት በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ 2,759 ሰዎችን መረጃ መሠረት ያደረገ ነው።
ተመራማሪዎቹ የረጅም ጊዜ የገንዘብ ችግር ያጋጠማቸው ሰዎች በ53 ዓመታቸው ባደረጉት የአእምሮ ብቃት ምርመራ ዝቅተኛ ውጤት ማምጣታቸውን አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም ከ69 እስከ 71 ባለው እድሜ ውስጥ በኤምአርአይ (MRI) ስካን ከተመረመሩት መካከል፣ ለረጅም ጊዜ ዝቅተኛ ገቢ የነበራቸው ሰዎች ከፍተኛ የአእምሮ መንጠፋጠፍ ታይቶባቸዋል።
ችግሩ በተለይም በወንዶች፣ በልጅነታቸው ችግር ውስጥ ባደጉ እና በአልዛይመር በሽታ የመያዝ አደጋን በሚጨምረው 'APOE-ε4' ጄን ተሸካሚዎች ላይ የጎላ ሆኖ ተገኝቷል።
በገንዘብ ጭንቀት የሚፈጠር የረጅም ጊዜ ውጥረት (chronic stress) ለአእምሮ እርጅና መፋጠን ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።
በጥናቱ የተሳተፉ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች፣ ምንም እንኳ የትምህርት ደረጃቸውና የአእምሮ ብልህነት (IQ) ምጣኔያቸው ግምት ውስጥ ቢገባም፣ በትውስታና መረጃ የመተንተን ፍጥነት ፈተናዎች ላይ ዝቅተኛ ውጤት አስመዝግበዋል።
የኤም.አር.አይ ምስል ምርመራዎች ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአእምሮ ሴሎች መኮማተር (Brain Atrophy) ታይቶባቸዋል።
ስለ ገንዘብ ሁልጊዜ መጨነቅ በሰውነት ውስጥ እብጠትን (Inflammation) በመጨመር የሰውነትን የእርጅና ሂደት እንደሚያፋጥነው በጥናቱ ተገልፇል።
Seledadotio

From a vibrant buffet selection to a relaxing atmosphere, every detail at Ethiopian CIP Lounge is designed to make your journey more comfortable, enjoyable, and memorable.
https://www.ethiopianairli...
https://www.ethiopianairli...
1 month ago
የ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጨዋታ ድልድል ይፋ ተደረገ
#ethiopia | የ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር የጨዋታ ድልድል በዛሬው ዕለት በሞናኮ ይፋ ሆኗል። እንደ መርሃ ግብሩ ገለጻ ውድድሩ በጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም የሚጀመር ይሆናል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ከ2016 ዓ.ም የውድድር ዘመን ጀምሮ የቀደመውን የምድብ ድልድል አሰራር በመቀየር 36 ክለቦች በ 4 ቋቶች ተከፋፍለው የሚወዳደሩበትን የሊግ ደረጃ አዲስ ፎርማት መተግበሩ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት በዘመነኛው ውድድር የተካተቱት 36 ክለቦች በእያንዳንዱ ቋት 9 ቡድኖች እንዲይዙ ተደርገው ተከፋፍለዋል።
በቋት አንድ ውስጥ የወቅቱ ሻምፒዮን ፒኤስጂን ጨምሮ ሪያል ማድሪድ፣ ባየር ሙኒክ፣ ማንችስተር ሲቲ፣ አርሰናል፣ ባርሴሎና፣ ኢንተር ሚላን፣ ሊቨርፑል እና አትሌቲኮ ማድሪድ ተካተዋል።
በቋት ሁለት ደግሞ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ፣ ሮማ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን፣ አስቶንቪላ፣ ፖርቶ፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ክለብ ብሩዥ፣ ሪያል ቤቲስ እና ፒኤስቪ አይንድሆቨን ይገኛሉ።
በቋት ሶስት ላይፕዚግ፣ ቪያሪያል፣ ናፖሊ፣ ሊል፣ ፌይኖርድ ሮተርዳም፣ ቦዶ ግሊምት፣ ፊነርባቼ፣ ሻክታር ዶኔስክ እና ጋላታሳራይ ተደልድለዋል።
በቋት አራት ስቱትጋርት፣ ሌንስ፣ ስላቪያ ፕራግ፣ ስሎቫን ብራቲስላቫ፣ ኤኢኬ አቴንስ፣ ላስክ፣ ኮሞ፣ ቫይኪንግ እና ሳባህ ተመድበዋል።
በአዲሱ አሰራር መሰረት አንድ ክለብ ከራሱ ቋት ከተካተቱ ሁለት ቡድኖች እንዲሁም ከቀሪዎቹ ሶስት ቋቶች ከእያንዳንዳቸው ከሁለት ክለቦች ጋር የሚጫወት በመሆኑ በጠቅላላው 8 ጨዋታዎችን ያደርጋል።
በሊግ ደረጃ ከሚወዳደሩት 36 ክለቦች መካከል በ 8 ጨዋታዎች ከፍተኛ ነጥብ የሚያስመዘግቡ የመጀመሪያዎቹ 8 ቡድኖች በቀጥታ ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ ዙር ያልፋሉ።
ከ 9ኛ እስከ 24ኛ ደረጃ የሚይዙት ደግሞ በሁለት ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች ተወዳድረው ቀሪዎቹን 8 የጥሎ ማለፍ ቦታዎች ይይዛሉ። ከጥሎ ማለፉ ዙር ጀምሮ ያለው የጨዋታ ፎርማት ከዚህ ቀደም ይተገበር ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ነው።
በመጀመሪያው ሳምንት ከሚጠበቁ Select Item ጨዋታዎች መካከል ሪያል ማድሪድ ከአርሰናል፣ ማንቸስተር ሲቲ ከባርሴሎና፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ከባየር ሙኒክ፣ ባርሴሎና ከፒኤስጂ እና ሊቨርፑል ከአትሌቲኮ ማድሪድ የሚያደርጓቸው ተጠቃሽ ናቸው።
የጣሊያኑ ኮሞ እና የአዘርባጃኑ ሳባህ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊጉ የሚሳተፉ ይሆናል።
#championsleague #ucl #uefa #football #sports #soccer #europe #realmadrid #barcelona #manchesterunited #arsenal #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ሲነሳ ስማቸው ከፊት ከሚሰለፉት ታላላቅ ከዋክብት መካከል፣ እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽንን (ESFNA) በመመስረትና በማሳደግ ወደር የለሽ አሻራ ካኖሩት የቁርጥ ቀን ልጆች አንዱ የሆኑት ጋሽ ፍስሐ ወልደአማኑኤል ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። "በጎ ስራ የሕይወት ስንቅ ነው" በሚለው የዘወትር መሪ ቃላቸው የሚታወቁት ጋሽ ፍስሐ፣ በኖሩበት አሜሪካ ሎስ አንጀለስ ከተማ ማረፋቸው ተሰምቷል።
ከሐረር ከተማ ወጣ ካለች አንዲት ትንሽ ቀበሌ ተወልደው በኳስ ፍቅር ያደጉት ጋሽ ፍስሐ፣ ቤተሰቦቻቸው ወደ አዲስ አበባ ሲዛወሩ ዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት እየተማሩ ሳለ ነበር በታላቁ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ዓይን ውስጥ የገቡት። በቅዱስ ጊዮርጊስ ማልያ የኢትዮጵያን እና የአዲስ አበባን ሻምፒዮና ደጋግመው በማንሳት የነገሱ ሲሆን፣ ለብሔራዊ ቡድንም በ5ኛ፣ 6ኛ እና 7ኛ የአፍሪካ ዋንጫዎች ላይ ሀገራቸውን ወክለው በድንቅ ብቃት ተጫውተዋል። ከረር ባሉት የሩቅ ምቶቻቸው "መድፈኛው"፣ በጥበበኛ አጨዋወታቸው ደግሞ "ኳስ ፊደሉ" የሚሉ የክብር ስሞችን አትርፈው ነበር።
እ.ኤ.አ. በ1969 በእግር ኳስ የትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) ወደ አሜሪካ ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ (UCLA) በማቅናት የኳስ ህይወታቸውን በባህር ማዶ ቀጠሉ። ፕሮፌሽናል ተጫዋች በመሆንም የሜጀር ሊግ ሶከር (MLS) ቀዳሚ በነበረው ሊግ ውስጥ ለ'ሎስ አንጀለስ አዝቴካ' ክለብ ፈርመው፣ ከታዋቂው እንግሊዛዊ ጆርጅ ቤስት ጋር በአንድ ቡድን ተጫውተዋል። ጋሽ ፍስሐ በሜዳ ላይ ከዓለማችን ታላላቅ የእግር ኳስ ነገስታት ጋር ፊት ለፊት ተፋልመዋል፤ ከእነዚህም መካከል ብራዚላዊው ፔሌ፣ ጀርመኖቹ ሄንዝ ቤክንባወር እና ጌርድ ሙለር፣ ፖርቹጋላዊው ዩሴቢዮ፣ እንዲሁም ኔዘርላንዳዊው ዮሃን ክራይፍ ይገኙበታል። ይህም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ እጅግ ብርቅዬ ከሚባሉ ገጠመኞች አንዱ ያደርገዋል።
ከእግር ኳሱ ጎን ለጎን ትምህርታቸውን በመከታተል ሁለት የተለያዩ የማስተርስ ዲግሪዎችን የጫኑት ጋሽ ፍስሐ፣ በ1978 እ.ኤ.አ. 'ሎስ አንጀለስ ስታርስ' የተባለውን ቡድን ከመሰረቱት አንዱ ነበሩ። ከሁሉ በላይ ግን በ1985 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ (ESFNA) የድርጅት ቅርጹን ሲይዝ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት በመሆን ታሪካዊ ኃላፊነትን ተወጥተዋል።
ፕሬዚዳንትነቱን ካጠናቀቁ በኋላም ከፌዴሬሽኑ አልራቁም። በእግር ኳስ ውድድር ክፍል ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት ለ35 ዓመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አገልግለዋል። ፌዴሬሽኑ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ለ42 ተከታታይ ዓመታት በየዓመቱ በሚካሄደው ስፖርታዊ በዓል ላይ ያልተለዩ ሲሆን፣ በቅርቡ በተካሄደው የ2026ቱ በዓል ላይ ብቻ በህመማቸው ምክንያት መገኘት ሳይችሉ ቀርተው ነበር።
የጋሽ ፍስሐ በጎነት በስፖርቱ ሜዳ ብቻ የተወሰነ አልነበረም። "አጋር" የተሰኘ የረድኤት ድርጅት ከ27 ዓመታት በፊት በማቋቋም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ረዳት የሌላቸውን ተማሪዎች እስከ ዶክተርነት እና የከፍተኛ ትምህርት እርከን ድረስ አስተምረዋል።
ለ50 ዓመታት በትዳር አብረዋቸው ከኖሩት ባለቤታቸው ወይዘሮ አልማዝ ጋር ሁለት ሴት ልጆችን (ጽዮን እና ናኦሚን) ያፈሩትና አራት የልጅ ልጆችን ያዩት ጋሽ ፍስሐ፣ በኖሩበት ማኅበረሰብ ዘንድ እጅግ የተከበሩና አገር ወዳድ ዜጋ ነበሩ። የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ በህልፈታቸው የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ፣ "በጎ ስራ የህይወት ስንቅ ነው" የሚለው መርሆቸው እና ግርማ ሞገሳቸው በየዓመቱ በሚደረገው የፌዴሬሽኑ ዝግጅት ላይ በመንፈስ አብሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

Sponsored by
Surafel
3 months ago
How MICE Tourism is Changing Addis Ababa Forever
u27a1https://youtu.be/5UyyrcjM8...
#ethiopia #micetourism #pmabiyahmed #addisababa ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"ExternalUrl","__isEntity":"ExternalUrl","url":"https://l.facebook.com/l.p...
How MICE Tourism is Changing Addis Ababa Forever
➡https://youtu.be/5UyyrcjM8...
#ethiopia #micetourism #pmabiyahmed #addisababa
5 months ago
ለሻምፒዮንስ ሊግ፤ ለታላቁ ክብር ይፋለማሉ
#ethiopia | በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ወሳኝ የመልስ ጨዋታ ፒኤስጂ ከባየር ሙኒክ ጋር አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
በአሊያንዝ አሬና በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ኡስማን ዴምቤሌ ለፒኤስጂ ቀዳሚዋን ግብ ሲያስቆጥር የባየር ሙኒኩ ሃሪ ኬን በጭማሪ ሰዓት የቡድኑን የአቻነት ግብ አስቆጥሯል።
ሆኖም ፓሪስ ላይ በተደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ 5 ለ 4 አሸንፎ የነበረው ፒኤስጂ በድምር ውጤት 6 ለ 5 በመርታት ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።
የአምናው የሻምፒዮንስ ሊግ ባለክብር ፒኤስጂ በሉዊስ ኤንሪኬ መሪነት በቡዳፔስት በሚደረገው የፍጻሜ ፍልሚያ ከአርሰናል ጋር ለዋንጫ የሚፋለም ይሆናል።
በጨዋታው ላይ የፒኤስጂው ኡስማን ዴምቤሌ ገና በ3ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ለፓሪዚያኑ ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረች ሲሆን የባየር ሙኒኩ ተከላካይ ኡፓሜካኖ በፈጣን የፒኤስጂ አጥቂዎች ሲፈተን አምሽቷል።
ባየር ሙኒክ ጨዋታውን ለመቀልበስ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም የፒኤስጂው ግብ ጠባቂ ድንቅ ብቃት እና የተደራጀው የተከላካይ መስመር የባቫሪያኑን ጉዞ ሊያግዱ ችለዋል።
ግንቦት 22 በሃንጋሪ ፑሽካሽ አሬና በሚካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ፒኤስጂ ዋንጫውን ለማስጠበቅ ሲጫወት አርሰናል ደግሞ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦችን ወክሎ ለበቀልና ለታላቁ ክብር ይፋለማል።
#psg #bayernmunich #championsleague #football #ucl #arsenal #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

አርሰናል ከ20 ዓመታት በኋላ ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ደረሰ
#ethiopia | መድፈኞቹ በታሪካዊ ጉዟቸው ታላቁን የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ መድረክ ዳግም ተቀላቅለዋል።
በሰሜን ለንደኑ ክለብ ቤት ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ አዲስ ታሪክ ተፅፏል።
አርሰናል በአሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ መሪነት በደርሶ መልስ ጨዋታዎች የተሻለ ብቃት በማሳየት ለአውሮፓ የክብር መድረክ ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል።
በኤምሬትስ ስታዲየም በተደረገው ወሳኝ ጨዋታ ቡካዮ ሳካ ያስቆጠራት ብቸኛ ጎል ለንደነኞቹን ወደ ቡዳፔስቱ የፍፃሜ ጨዋታ የምታሸጋግር የድል ትኬት ሆናለች።
መድፈኞቹ በዘንድሮው የውድድር ዘመን እስካሁን አንድም ጨዋታ ሳይሸነፉ ለፍፃሜ መድረሳቸው ስኬቱን ልዩ ያደርገዋል።
እንደ ቪክቶር ዮኬሬስ እና ዴክላን ራይስ ያሉ ተጫዋቾች በሜዳው ላይ የነበራቸው አስደናቂ ትግልና ብቃት ለክለቡ ስኬት ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
የአርሰናል የኋላ ክፍል እንደ ብረት የጠነከረ መሆኑን ያስመሰከረበት ይህ ጨዋታ የአትሌቲኮ ማድሪድን የአጥቂ መስመር ክፉኛ ፈትኖታል።
አንቶኒዮ ግሪዝማን እና ዩሊያን አልቫሬዝ የመድፈኞቹን የመከላከል ግድግዳ ሰብረው መግባት ሳይችሉ ቀርተዋል።
ይህም አርሰናል በ2006 ዓመተ ምህረት ከአርሴን ቬንገር ጋር የደረሰበትን የፍፃሜ ታሪክ በአርቴታ ዘመን እንዲደግም አስችሎታል።
አሁን ላይ መድፈኞቹ ሁለት ታላላቅ ዋንጫዎችን የማንሳት ህልማቸው ከጫፍ ደርሷል።
በሊጉም ሆነ በአውሮፓ መድረክ ውጤታማ የሆነው አርሰናል የረዥም ጊዜ የደጋፊዎቹን የዋንጫ ጥም ለመቁረጥ ተቃርቧል።
#arsenal #championsleague #football #ucl #final #sports #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

''አርሰናል ዋንጫውን ማንሳት ይገባዋል" — አርሴን ቬንገር
#ethiopia | የቀድሞው የአርሰናል ዝነኛ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር ክለቡ በሻምፒዮንስ ሊግ መድረክ አዲስ ታሪክ መፃፍ እንደሚችል ያላቸውን ፅኑ እምነት ገልጸዋል።
ቬንገር ለአርሰናል ደጋፊዎች ወሳኝ ምሽት መሆኑን በመጠቆም፣ አሁን ያለው ስብስብ ታላቅ ታሪክ የመስራት አቅም እንዳለው ተናግረዋል። ክለቡ በውድድሩ ካለው የቆየና በህመም የተሞላ ታሪክ አንፃር፣ "ዋንጫው ወደ አርሰናል መሄድ አለበት" ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።
አሰልጣኙ አክለውም "ዋንጫው ለአርሰናል ይገባዋል" በማለት ለቀድሞ ክለባቸው ያላቸውን ድጋፍና ለቡድኑ ያላቸውን ከፍተኛ ግምት በይፋ አጋርተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #tikvah #arsenal #championsleague #arsenewenger #footballnews #gunners #ucl #አርሰናል #ስፖርት #አርሴንቬንገር

አርሰናል ከሁለ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ይፋለማል
#ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ ከኤቨርተን ጋር ነጥብ መጣሉን ተከትሎ የሊጉን ዋንጫ ከ22 ዓመታት በኋላ የማንሳት አጋጣሚው ሰፊ የሆነለት አርሰናል ዛሬ ደግሞ በታላቁ የአውሮፓ መድረክ ታሪክ ለመስራት ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
መድፈኞቹ በሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ጨዋታ በስፔን 1 ለ 1 ተለያይተው የተመለሱ ሲሆን ዛሬ ምሽት ወሳኝ የሆነውን የመልስ ጨዋታ በገዛ ሜዳቸው ያከናውናሉ፡፡
ሁለቱ ክለቦች በሃንጋሪ ቡዳፔስት ለሚካሄደው የዘንድሮው የሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ፍልሚያ ለማለፍ ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡
አርሰናል በምድብ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፉ ቢታወስም በዛሬው ጨዋታ ግን ከዲዬጎ ሲሚዮኒ ተጫዋቾች ከባድ ፈተና እንደሚገጥመው ይጠበቃል፡፡
መድፈኞቹ በአውሮፓ መድረክ ከስፔን ክለቦች ጋር ባደረጓቸው ያለፉት ስምንት ጨዋታዎች ሽንፈት አልገጠማቸውም፡፡
በሌላ በኩል አትሌቲኮ ማድሪድ ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር ከሜዳው ውጭ ባደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች የስድስቱን ሽንፈት ቀምሷል፡፡
አትሌቲኮ በሲሚዮኒ መሪነት ለሁለት ጊዜያት ለፍጻሜ ደርሶ በሪያል ማድሪድ ዋንጫውን መነጠቁ የሚታወስ ሲሆን ለሦስተኛ ጊዜ ለፍጻሜ ለመድረስ በሚያደርገው ጉዞ በውድድሩ እስካሁን ያልተሸነፈው አርሰናል ከፊቱ ተደቅኗል፡፡
አርሰናል የዛሬውን ጨዋታ አሸንፎ ለፍጻሜ የሚያልፍ ከሆነ በአዲሱ የሻምፒዮንስ ሊግ አወቃቀር አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ ለዋንጫ ጨዋታ በመድረስ የመጀመሪያው ክለብ በመሆን አዲስ ታሪክ ይጽፋል፡፡
የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ እንደተናገሩት ማርቲን ኦዴጋርድ እና ካይ ሃቨርትዝ ከጉዳታቸው በማገገም ለዛሬው ጨዋታ ዝግጁ ሲሆኑ ዩሪየን ቲምበር ግን አሁንም ከቡድኑ ጋር አይሆንም፡፡
በአትሌቲኮ ማድሪድ በኩል መጠነኛ ጉዳት የነበረባቸው ሁሊያን አልቫሬዝ፣ አሌክሳንደር ሶርሎዝ እና ጂሊያኖ ሲሚዮኒ ለጨዋታው ዝግጁ መሆናቸውን አሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሚዮኒ አረጋግጠዋል፡፡
በአርሰናል በኩል በሳምንቱ መጨረሻ በሊጉ ጨዋታ በፉልሃም ላይ ድንቅ ብቃት ያሳየው ወጣቱ ሉዊስ ስኬሊ ማርቲን ዙቢሜንዲን ተክቶ የመጀመር ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡
#arsenal #atleticomadrid #championsleague #football #ucl #gunners #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ፒኤስጂ ባየርን ሙኒክን በጎል ናዳ አሸነፈ
#ethiopia | በፓሪስ ፓርክ ዴ ፕሪንስ ስታዲየም የተካሄደው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ እጅግ አስደናቂ እና በጎሎች የታጀበ ምሽት ነበር።
ዘጠኝ ጎሎች የተቆጠሩበት ይህ ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪዎችን ቀልብ የገዛ ሲሆን ፒኤስጂ ባየርን ሙኒክን 5 ለ 4 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ለሁለተኛው ዙር ጨዋታ መጠነኛ ብልጫ መያዝ ችሏል።
ጨዋታው እንደተጀመረ ሃሪ ኬን በፍፁም ቅጣት ምት ባየርን ሙኒክን ቀዳሚ ቢያደርግም ፓሪሶች በክቫራትስኬሊያ እና በጆአኦ ኔቬስ አማካኝነት ተከታታይ ጎሎችን በማስቆጠር መሪነቱን ተረክበዋል።
ባየርኖች በሚካኤል ኦሊሴ ጎል አቻ መሆን ቢችሉም በመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ ኡስማን ዴምቤሌ በቪዲዮ ረዳት ዳኛ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ወደ ጎል በመቀየር ፒኤስጂን 3 ለ 2 መሪ አድርጎ ወደ እረፍት አምርተዋል።
ከእረፍት መልስ ፒኤስጂዎች ብልጫቸውን በማስፋት በክቫራትስኬሊያ እና በዴምቤሌ አማካኝነት ተጨማሪ ጎሎችን አስቆጥረው ልዩነቱን ወደ ሶስት አሳድገው ነበር።
ሆኖም የጀርመኑ ሀያል ክለብ ባየርን ሙኒክ ተስፋ ሳይቆርጥ በመታገል በኡፓሜካኖ እና በሉዊስ ዲያዝ አማካኝነት ሁለት ጎሎችን በማከታተል የጎል ልዩነቱን ወደ አንድ ማጥበብ ችሏል።
ፒኤስጂ በዚህ ጨዋታ ያስመዘገበው ውጤት በታሪኩ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን በተለይም ክቫራትስኬሊያ ክለቡን ከተቀላቀለ በኋላ እያሳየ ያለው ድንቅ ብቃት ለቡድኑ ስኬት ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል።
ባየርን ሙኒክ ምንም እንኳን በሜዳው ቢሸነፍም ያስቆጠራቸው አራት ጎሎች ለሁለተኛው ዙር ጨዋታ ትልቅ ተስፋ የሚሰጡት ናቸው።
የሁለቱ ቡድኖች ወሳኝ የሁለተኛ ዙር ፍልሚያ ረቡዕ ግንቦት 6 ቀን በሙኒክ አሊያንዝ አሬና የሚካሄድ ይሆናል።
#ucl #psg #bayernmunich #championsleague #football #sports #goal #paris #munich #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
የአሜሪካ ኤንባሲ ፕ/ር ኃይሌ ገሪማን አደነቀ
#ethiopia | ታዋቂውና ዝነኛው ኢትዮ-አሜሪካዊ የፊልም ባለሙያ ኃይሌ ገሪማ ለዓለም የሲኒማ ጥበብ ላበረከቱት ከፍተኛና ተፅዕኖ ፈጣሪ አስተዋፅኦ፣ በ76ኛው የበርሊን ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል (Berlinale) ላይ የተከበረውን "የበርሊን ካሜራ" (Berlinale Camera) ሽልማት ተረክበዋል።
ኃይሌ ገሪማ በፊልም ጥበብ ጉዞው በቺካጎ የቲያትር ጥበብን በማጥናት የጀመሩ ሲሆን፣ በኋላም በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ (UCLA) በፊልም ጥበብ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝቷል።
በዘርፉ በነበራቸው ጠንካራ ተሳትፎም "የሎስ አንጀለስ የጥቁር ፊልም ባለሙያዎች ትምህርት ቤት " (L.A. School of Black Filmmakers) ፈር ቀዳጅና ግንባር ቀደም አባል ለመሆን በቅተዋል።
ይህ ሽልማት ለታሪክ ዘጋቢነታቸው፣ ለኪነ-ጥበብ ጥራቱና ለብዙዎች አርአያ ለሆነው የረጅም ዘመን የፊልም ሥራዎቿቸው የተሰጠ ታላቅ እውቅና ነው። በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲም ለባለሙያው ያለውን አድናቆት ገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ
#getutemesgen #getu #hailegerima #berlinale76 #ethiopiancinema #filmmaking #legend #berlinfilmfestival #ethiopia #usainethiopia #ኃይሌገሪማ #በርሊን #ሲኒማ

አትሌቲኮና ፒኤስጂ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ተቃረቡ! 

#ethiopia | የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ያልተጠበቁ ውጤቶችን አስተናግደዋል። የ
ሊቨርፑልና የባርሴሎና ደጋፊዎች ምሽቱን በሀዘን ሲያሳልፉ፣ አትሌቲኮና ፒኤስጂ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለመጓዝ ትልቅ በር ከፍተዋል።
ፒኤስጂ 2-0 ሊቨርፑል
ዲዘር ዱዌ እና ኪቪቻ ካቫርስኬሊያ ባስቆጠሯቸው ግቦች ፒኤስጂ ድል ቀንቶታል።
መርሲሳይዶቹ በጨዋታው አንድም ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ (0 shots on target) ሳያደርጉ ወጥተዋል።
ሊቨርፑል ከሜዳው ውጭ በአራት ተከታታይ ጨዋታዎች ሲሸነፍ ከ14 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኖ ተመዝግቧል።
ባርሴሎና 0-2 አትሌቲኮ ማድሪድ 
የሲሚዮኒ ታሪክ፦ አሰልጣኝ ዲየጎ ሲሚዮኒ ባርሴሎናን በሜዳው (ካምፕ ኑ) ለመጀመሪያ ጊዜ ማሸነፍ ችሏል።
ባርሴሎና በሜዳው በአትሌቲኮ ማድሪድ የተሸነፈው ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ፓዎ ኩባርሲ በቀይ ካርድ መውጣቱ ለባርሳ ሽንፈት ትልቅ አስተዋጽኦ ሲያደርግ፣ ሁሊያን አልቫሬዝ እና አሌክሳንደር ሶርሎዝ ድሉን አረጋግጠዋል።
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #championsleague #ucl #psg #liverpool #barcelona #atleticomadrid #simeone #footballnews #ethiopia #የአውሮፓሻምፒዮንስሊግ #ስፖርት #ባርሴሎና #ሊቨርፑል

7 months ago
"በእግርኳስ የማይቻል ነገር የለም፤ አዳዲስ ሀሳቦች አሉኝ!" ፔፕ ጋርዲዮላ
#ethiopia | የማንችስተር ሲቲው ስትራቴጂስት ፔፕ ጋርዲዮላ፣ ነገ ከሪያል ማድሪድ ጋር ለሚጠበቀው ወሳኝ ፍልሚያ ቡድናቸው ዝግጁ መሆኑን ገለጹ። አሰልጣኙ ውጤቱን ለመቀልበስ "ፍጹም" የሆነ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
የፔፕ ጋርዲዮላ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* ተስፋ አልቆረጥንም፦ "በእግርኳስ ሁሉም ነገር ሊፈጠር ይችላል፤ እኛም ውጤቱን ለመቀልበስ እንሞክራለን። ነገር ግን ይህ እንዲሆን ፍፁም የሆነ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ያስፈልገናል።"
* የማጥቃት ፈተና፦ በሪያል ማድሪድ ላይ ከሶስት ጎሎች በላይ ማስቆጠር ቀላል እንዳልሆነ የገለጹት ፔፕ፣ ቡድናቸው በርትቶ መከላከልና ሳይሰለች መሞከር እንዳለበት ተናግረዋል።
* አዳዲስ ታክቲኮች፦ "ለነገው ጨዋታ የተወሰኑ ሀሳቦች አሉኝ፤ እነሱን በሜዳ ላይ ለመተግበር ጥሩ እድል አለን" በማለት በታክቲክ ረገድ ለውጦች ሊኖሩ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል።
* የደጋፊዎች ሚና፦ በኢቲሃድ ስታዲየም የሚኖረው ድባብ ለቡድኑ ተጨማሪ ጉልበት እንደሚሰጥ ሙሉ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ማንችስተር ሲቲ ለጨዋታው ዝግጅት
እንዲረዳው ለተጫዋቾቹ የዛሬውን ቀን እረፍት የሰጠ ሲሆን፣ ነገ ከጨዋታው በፊት የመጨረሻ ልምምዳቸውን እንደሚያደርጉ ታውቋል። "ቢሳካም ባይሳካም ያለንን ሁሉ እንደምንሰጥ አውቃለሁ" ሲሉ ጋርዲዮላ ለደጋፊዎቻቸው ቃል ገብተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #mancity #realmadrid #ucl #pepguardiola #championsleague #footballnews #ethiopia

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ፦
ሪያል ማድሪድ ሲቲን፣ ፒኤስጂ ቼልሲን አሸነፉ
#ethiopia | በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች አስገራሚ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በሳንቲያጎ ቤርናባው የተደረገው ታላቅ ፍልሚያ በሪያል ማድሪድ የበላይነት ተጠናቋል።
ሪያል ማድሪድ 3 - 0 ማንችስተር ሲቲ
የጨዋታው ኮከብ፦
ኡራጓያዊው አማካይ ፌደሪኮ ቫልቨርዴ በመጀመሪያው 45 ደቂቃ ውስጥ ብቻ ሀትሪክ በመስራት ማድሪድን ለድል አብቅቷል።
ያመለከተ ዕድል፦
ቪኒሺየስ ጁኒየር ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት የቀረ ቢሆንም፣ ማድሪድ ለሩብ ፍጻሜው ያለውን ዕድል በሰፊው አስፍቷል።
የመልስ ጨዋታ፦
ማንችስተር ሲቲ በቀጣይ ሳምንት በሜዳው ኢቲሃድ ስታዲየም ማድሪድን በድምር ውጤት ለማሸነፍ ቢያንስ 4 ግቦችን አስቆጥሮ ማሸነፍ ይኖርበታል።
ፒኤስጂ 5 - 2 ቼልሲ
የፒኤስጂ ግቦች፦ ኪቪቻ ካቫርስኬሊያ (2 ግቦች)፣ ኡስማን ደምቤሌ፣ ብራድሊ ባርኮላ እና ቪቲንሃ አስቆጥረዋል።
የቼልሲ ግቦች፦ ማሎ ጉስቶ እና ኢንዞ ፈርናንዴዝ ለለንደኑ ክለብ መጽናኛ ግቦችን አስገኝተዋል።
ፒኤስጂ በፓርክ ዴስ ፕሪንስ ያሳየው የማጥቃት ብቃት ለቼልሲ የመልስ ጨዋታ ከባድ የቤት ስራ ጥሎባቸዋል።
የዓመቱ ክስተት፦ ቦዶ ግሊምት
ኖርዌያዊው ክለብ ቦዶ ግሊምት ስፖርቲንግ ሊዝበንን 3 ለ 0 በማሸነፍ በውድድሩ እያስመዘገበ ያለውን አስገራሚ ጉዞ ቀጥሏል።
ጎል አግቢዎች፦
ሶንደር ፊት፣ ኦሌ ብሉምበርግ እና ካስፐር ሆጅ።
የዘንድሮው ሻምፒዮንስ ሊግ ባልተጠበቁ ውጤቶችና በግል ብቃቶች የታጀበ ሆኗል። በተለይ የቫልቨርዴ ሀትሪክ እና የቦዶ ግሊምት ጥንካሬ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
#ucl #realmadrid #mancity #psg #chelsea #bodoglimt #championsleague #football #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

"የዘንድሮው የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ የአርሰናል ነው" ጄሚ ካራጋር
#ethiopia | የቀድሞው የሊቨርፑል ተከላካይ እና የአሁኑ እውቅ የስፖርት ተንታኝ ጄሚ ካራጋር፣ የአርሰናልን የሻምፒዮንስ ሊግ ጉዞ በተመለከተ አስደናቂ ግምት ሰጥቷል።
ካራጋር ከባልደረባው ሚካ ሪቻርድስ ጋር በመሆን በሰጡት ትንታኔ፣ መድፈኞቹ በዘንድሮው ውድድር እስከ ፍፃሜው እንደሚዘልቁ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በተለይም ካራጋር አርሰናል ለፍፃሜ መድረስ ብቻ ሳይሆን፣ የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ታሪካዊውን የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ወደ ሰሜን ለንደን እንደሚወስዱ በልበ ሙሉነት ተናግሯል።
በተቃራኒው ካራጋር ስለ ቀድሞ ክለቡ ሊቨርፑል ሲጠየቅ፣ ቡድኑ ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋል የሚል ምንም አይነት ተስፋ እንደሌለው በግልጽ አስታውቋል።
ይህም ብዙዎችን ያስገረመ ሲሆን፣ ተንታኙ በአሁኑ ሰዓት ከአርሰናል ስብስብ በስተጀርባ ያለውን ጥንካሬ በከፍተኛ ሁኔታ እያደነቀ መሆኑን አመላካች ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #arsenal #championsleague #jamiecarragher #footballnews #gunners #ucl #የስፖርትዜና

8 months ago
የክብር ሰልፈኛው የመጨረሻ ጉዞ፦ ሬቨረንድ ጄሲ ጃክሰን እና የማይጠፋው የተስፋ ቋያ
ዛሬ የአሜሪካ ሰማይ በሀዘን ደመና ተሸፍኗል። በቺካጎ ከተማ በሚገኘው ኖርዘስተርን ሜሞሪያል ሆስፒታል ውስጥ፣ ላለፉት ስድስት አስርተ ዓመታት የአለምን ህሊና ሲቀሰቅስ የነበረው ያ ድምፅ ለዘላለም ዝም ብሏል።
ሬቨረንድ ጄሲ ሉዊስ ጃክሰን ሲኒየር፣ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ይህ ዜና ለቤተሰቦቻቸው ብቻ ሳይሆን፣ ፍትህ ለተራበውና ሰብአዊነት ለጎደለው ዓለም ትልቅ ድንጋጤ ነበር።
የመጨረሻው ተጋድሎ፦ የጤና እና የፅናት ፍልሚያ
የሬቨረንድ ጄሲ ጃክሰን ህይወት እስከ መጨረሻው ሰከንድ ድረስ ትግል ነበር። እ.ኤ.አ. በ2017 የፓርኪንሰን በሽታ እንዳለባቸው በይፋ ቢያሳውቁም፣ ትግላቸውን ግን አላቆሙም ነበር። ሆኖም እ.ኤ.አ. በ2025 አጋማሽ ላይ Progressive Supranuclear Palsy (PSP) የተባለና እጅግ አልፎ አልፎ የሚከሰት፣ የሰውነትን እንቅስቃሴ፣ ንግግርንና ሚዛንን የሚገታ የነርቭ በሽታ እንደተገኘባቸው ተገለጸ።
ይህ በሽታ ከፓርኪንሰን እጅግ የከፋና የሰውነትን የነርቭ ስርአት ቀስ በቀስ የሚበላሽ ነው። ጃክሰን በመጨረሻዎቹ ወራት በዊልቸር ለመንቀሳቀስ ተገደው ነበር። ህዳር 12 ቀን 2025 በሆስፒታል በገቡበት ወቅት፣ የልብ ምታቸው መጨመር እና በሳምባ አቅራቢያ የሚሰማ የ"መንቀጥቀጥ" ድምፅ (Rattle) የፍፃሜያቸው መቃረብ ምልክት ነበር።
ባለቤታቸው ጃኩሊን ላቪኒያ ብራውን እና አምስቱ ልጆቻቸው—ሳንቲታ፣ ጄሲ ጁኒየር፣ ጆናታን ሉተር፣ ዩሱፍ እና አሽሊ—በዙሪያቸው ሆነው ጸሎት ያደርጉ ነበር። የታሪክ ምሁራን እንደሚሉት፣ ያ በድፍረት መድረክ ላይ አንበሳ ሆኖ የሚያገሳው መሪ፣ በመጨረሻው ሰዓት በአይኖቹ ብቻ ነበር የሚናገረው።
"ከጥላ ስር የወጣ ብርሃን"
ታሪክ ጸሐፊዎች ጄሲ ጃክሰንን የሚመለከቷቸው እንደ ተራ የሲቪል መብቶች ተሟጋች ሳይሆን፣ እንደ "የድልድይ ሰሪ" (Bridge Builder) ነው። የደቡብ ካሮላይና ተወላጅ የሆኑት ጃክሰን፣ በደቡብ አሜሪካ የዘረኝነት ቀንበር በከበደበት ወቅት ከአባት አልባ (out-of-wedlock) ቤተሰብ መገኘታቸው ለትግል ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዳጠናከረው ምሁራን ይተነትናሉ።
ጃክሰን የተወለዱት ከሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እና ጎረቤታቸው ከነበሩ ባለትዳር ሰው ነበር። በልጅነታቸው "ዲቃላ" እየተባሉ ሲሰደቡ፣ ያ ስድብ በውስጣቸው "እኔ ሰው ነኝ" የሚለውን እልህ ፈጥሮባቸዋል። ታሪክ ጸሐፊው ማርሻል ፍራዲ እንዳሉት፣ "ጃክሰን በታሪክ ውስጥ የነበረው ሚና በዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ እና በባራክ ኦባማ መካከል ያለውን ክፍተት መሙላት ነበር።"
እ.ኤ.አ በ1968 ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ በሜምፊስ ሆቴል በጠመንጃ ጥይት ሲገደሉ ጃክሰን ከጎናቸው ነበሩ። ያ በደም የተጨማለቀው ሸሚዝ የትግሉን አደራ የመረከብ ምልክት ሆኖ ታይቷል። ምንም እንኳን በወቅቱ በነበሩት የሲቪል መብቶች መሪዎች መካከል "አደራውን ማን ይረከብ?" በሚል መጠነኛ ፉክክር ቢኖርም፣ ጃክሰን የኪንግን "ኢኮኖሚያዊ ፍትህ" ራዕይ በማንገብ 'Operation Breadbasket' የተባለውን ንቅናቄ ወደ ላቀ ደረጃ አድርሰዋል።
የ"ቀስተ ደመና" ጥምረት ተዓምር
በፖለቲካ ሳይንቲስቶች እይታ፣ የጃክሰን ትልቁ ስኬት እ.ኤ.አ. በ1984 እና 1988 ያደረጓቸው የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳዎች ናቸው። በወቅቱ ጥቁር አሜሪካዊ ፕሬዝዳንት ይሆናል ብሎ ማሰብ እንደ ቅዠት በሚቆጠርበት ዘመን፣ ጃክሰን በሚሊዮን የሚቆጠሩ አዳዲስ መራጮችን አስመዝግበዋል።
የ1984 ዘመቻ፦ 3.2 ሚሊዮን ድምፅ በማግኘት፣ ጥቁር እጩ በከፍተኛ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የ1988 ዘመቻ፦ ከ6.9 ሚሊዮን በላይ ድምፅ በማግኘት እና በ11 ግዛቶች አሸናፊ በመሆን፣ የዴሞክራቲክ ፓርቲን አቅጣጫ ቀይረዋል።
ፖለቲካ ሳይንቲስቱ ኤዲ ዊሊያምስ እንደሚሉት፣ "ጃክሰን 'ቀስተ ደመና ጥምረት' (Rainbow Coalition) በሚለው ፅንሰ ሃሳብ፣ ጥቁሮችን፣ ነጮችን፣ ሂስፓኒኮችን፣ ሴቶችን እና ድሆችን በአንድ ጥላ ስር በማምጣት የአሜሪካን ፖለቲካ መዋቅር ለውጠዋል።
" ዛሬ የምናየው የባራክ ኦባማም ሆነ የካማላ ሃሪስ ስኬት መሰረቱ የጄሲ ጃክሰን "Run, Jesse, Run!" የሚለው የትላንት ጩኸት ነው። ጃክሰን ፖለቲካን ከላይኛው መደብ አውርደው ወደ ተራው ህዝብ ጎጆ ያስገቡ መሪ ነበሩ።
"እኔ ሰው ነኝ!"
ለፈላስፎች ደግሞ የጄሲ ጃክሰን ትልቁ ውርስ የሰው ልጅን ክብር የመመለስ ጥበባቸው ነው። እ.ኤ.አ. በ1971 በሰሊጥ ጎዳና ላይ ህፃናትን ሰብስበው ያስደገሙት ግጥም ዛሬም ድረስ በነፍስ ውስጥ ያስተጋባል፦
"ጭንቅላቴ ባዶ ሊሆን ይችላል፣ ግን እኔ ሰው ነኝ! ... ድሃ ልሆን እችላለሁ፣ ግን እኔ ሰው ነኝ! ... እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ!"
ይህ ፍልስፍና "Ontological Affirmation" ወይም "የመኖር ማረጋገጫ" ይባላል። በዘረኝነት ሰንሰለት የታሰረን ህዝብ መንፈስ ነፃ ለማውጣት መጀመሪያ "ማንነቱን" ማሳመን እንዳለበት ጃክሰን ተረድተው ነበር።
ፈላስፋው ዴቪድ ማስቺዮትራ እንደሚለው፣ "ጃክሰን ለተናቁት ድምፅ ብቻ ሳይሆን፣ ለራሳቸው ያላቸውን ግምት የገነባ የነፍስ መሃንዲስ ነው።" ጃክሰን ለጥቁር አሜሪካውያን "ጥቁርነት ውበት ነው" (Black is Beautiful) የሚለውን ብቻ ሳይሆን "ጥቁርነት አቅም ነው" የሚለውን አስተምረዋል።
ዲፕሎማሲያዊ ብቃታቸው፦ "የሰላም መልእክተኛው"
ጄሲ ጃክሰን በአገር ውስጥ ትግል ብቻ አልተወሰኑም። በዓለም አቀፍ ደረጃም የታገቱ ሰዎችን በማስፈታት ረገድ አስደናቂ ተሰጥኦ ነበራቸው። እ.ኤ.አ. በ1983 ወደ ሶሪያ በመጓዝ የባህር ሃይል አብራሪው ሮበርት ጉድማንን አስፈትተዋል። በ1999 ወደ ዩጎዝላቪያ በመሄድ ሶስት የአሜሪካ ወታደሮችን ከምርኮ ነፃ አውጥተዋል። የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት፣ ጃክሰን በይፋዊ ዲፕሎማሲ የማይፈቱ ችግሮችን በ"ሞራል ዲፕሎማሲ" (Moral Diplomacy) የመፍታት ተአምራዊ ችሎታ ነበራቸው።
ትዝታዎች እና የመጨረሻው እንባ
የጄሲ ጃክሰን ህይወት በደስታ እና በሀዘን የተሞላ ነበር። በፈረንጆቹ ህዳር 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ባራክ ኦባማ ምርጫውን ሲያሸንፉ፣ ጄሲ ጃክሰን በቺካጎ ግራንት ፓርክ ውስጥ ቆመው በካሜራ የታየው የመሪር እንባ ዘነብ፣ የአንድ ትውልድ ትግል ፍሬ ያየበት ቅፅበት ነበር። ያ እንባ ለባራክ ኦባማ ብቻ ሳይሆን፣ በሴልማ አብረዋቸው ለቆሰሉት፣ በሜምፊስ ለወደቁት ዶክተር ኪንግ እና በባርነት ለተሰቃዩ አባቶቻቸው የፈሰሰ ነበር። ያን እለት "ተስፋ ህያው ሆነ" ብለው ነበር።
ሬቨረንድ ጃክሰን በህይወት ዘመናቸው ስህተቶችን ሰርተዋል—የ1984ቱ የአይሁድ ማህበረሰብን ያስቆጣ ንግግራቸው እና ከጋብቻ ውጭ የወለዱት ልጅ መኖሩ በወቅቱ ስማቸውን ቢያጎድፍም፣ በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ እና ለኃላፊነት በመገዛት ዳግም ተነስተዋል።
ይህ ደግሞ "ሰው መሆን" ስህተትንም ድልንም እንደሚጨምር የሚያሳይ የህይወት ትምህርት ሆኖ ተመዝግቧል።
የዓለም መሪዎች ምስክርነት

ታዋቂው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሬቨረንድ ጄሲ ጃክሰን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ለስድስት አስርት ዓመታት ያህል ለአፍሪካ-አሜሪካውያን መብትና ለማህበራዊ ፍትህ የታገሉት ታዋቂው የባፕቲስት ፓስተር እና የፖለቲካ ሰው ጄሲ ጃክሰን፣ በዛሬው ዕለት የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም.በ84 ዓመታቸው አርፈዋል።
ስለ ጄሲ ጃክሰን ዋና ዋና ነጥቦች፡
የትግል አጋርነት፡ ከዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ጋር በቅርበት በመስራትና በታዋቂው የሴልማ ሰልፍ ላይ በመሳተፍ የሲቪል መብቶች ንቅናቄ ግንባር ቀደም መሪ ነበሩ።
ታሪካዊ ምርጫ፡ በ1984 እና 1988 ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንትነት በእጩነት የቀረቡ ሲሆን፣ በ1988ቱ ውድድር 7 ሚሊዮን ድምፅ በማግኘት ለአፍሪካ-አሜሪካውያን ፖለቲከኞች አዲስ መንገድ ቀድደዋል።
ተቋማዊ ትግል፡ "Operation PUSH" እና "Rainbow/PUSH Coalition" የተባሉ ድርጅቶችን በመመስረት፣ ጥቁር አሜሪካውያን በኢኮኖሚና በፖለቲካው ዘርፍ እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሰርተዋል።
ዲፕሎማሲያዊ ስኬት፡ በሶሪያ፣ በኩባ እና በዩጎዝላቪያ ታስረው የነበሩ አሜሪካውያን እስረኞች እንዲፈቱ በማድረግ ዓለም አቀፍ እውቅናን አትርፈዋል።
የጤና ሁኔታና ሕልፈት፡
ሬቨረንድ ጄሲ ጃክሰን ከ2017 ጀምሮ ከፓርኪንሰን በሽታ ጋር ሲታገሉ የቆዩ ሲሆን፣ በቅርቡ ደግሞ በከባድ የነርቭ በሽታ (Progressive Supranuclear Palsy) ሲታከሙ ቆይተው ዛሬ በቤተሰቦቻቸው መካከል በሰላም ማረፋቸው ተገልጿል።
ቤተሰቦቻቸው ባወጡት መግለጫ፦ "አባታችን ለቤተሰባችን ብቻ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ ለተጨቆኑና ድምፅ ለሌላቸው ህዝቦች አገልጋይ መሪ ነበር" ብለዋል።
የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ዝርዝር ወደፊት እንደሚገለጽ ታውቋል።

"በቀል ሳይሆን ዋንጫው ነው የሚያስጨንቀን" — አርቤሎኣ
#ethiopia ||የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ አልቫሮ አርቤሎኣ ቡድናቸው ዛሬ ምሽት ከቤኔፊካ ጋር ለሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። አሰልጣኙ በተለይ ስለ ተጋጣሚው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ሲናገሩ፥ "ሞሪንሆ በፍፁም ሊያስገርመኝ አይችልም፤ ምን ማድረግ እንደሚችል ጠንቅቄ አውቃለሁ" በማለት ለቀድሞ አሰልጣኛቸው ያላቸውን ትውውቅና ንቃት ገልጸዋል።
የአርቤሎኣ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* ስለ ቤኔፊካ ጥንካሬ፦ ቤኔፊካ ካለፈው ጨዋታ በበለጠ ተጠናክሮና ተሻሽሎ ሊቀርብ እንደሚችል በመጠቆም፣ ተጫዋቾቻቸው ለከባድ ፈተና እንዲዘጋጁ አሳስበዋል።
* ስለ በቀል፦ ቡድኑ ቤኔፊካን ለመበቀል እያሰበ ስለመሆኑ ለቀረበለት ጥያቄ፥ "ሀሳባችን በቀል ሳይሆን ማሸነፍና ጥሩ መጫወት ነው" ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
* ትልቁ ግብ፦ ማድሪድ ትኩረቱን በነጠላ ጨዋታዎች ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ዋና አላማው የሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ወደ ቤርናባው መመለስ እንደሆነ በድፍረት ተናግሯል።
ማድሪድ በሞሪንሆ የሚመራውን ቤኔፊካን አስተናግዶ የሚያደርገው የዛሬ ምሽት ጨዋታ፣ በአሰልጣኞች የታክቲክ ብልጫ የታጀበ እንደሚሆን ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #realmadrid #arbeloa #mourinho #benfica #ucl #championsleague #halamadrid #footballnews

በግንኙነት ውስጥ የታማኝነት መጉደል እና የዕድሜ ምስጢር፡ ሳይንሳዊ ትንታኔ
በትዳር ወይም በማንኛውም የፍቅር ግንኙነት ውስጥ "ታማኝነት" ትልቁ የጥንካሬ ምሰሶ ነው። ሆኖም ግን፣ "ሰዎች ለምን ይከዳሉ?" የሚለው ጥያቄ ለዘመናት የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። በቅርብ ጊዜ የወጡ ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ ክህደት በዘፈቀደ የሚከሰት ሳይሆን፣ ከሰው ልጅ የዕድሜ እድገት እና የስነ-ልቦና ለውጥ ጋር የተያያዘ መሆኑን ያሳያሉ።
በተለይም የአንድን አስርተ ዓመት ማብቂያ የሚጠቁሙ የእድሜ ክልሎች ለዚህ ከፍተኛ ተጋላጭነት አላቸው።
1. የ"9" ቁጥር ምስጢር፡ ለምን 29፣ 39 እና 49?
በኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ (NYU) እና በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ (UCLA) ተመራማሪዎች የተደረገ ጥናት እንደሚጠቁመው፣ ሰዎች እድሜያቸው በ "9" ቁጥር በሚያልቅበት ወቅት ለየት ያለ ስነ-ልቦናዊ ለውጥ ውስጥ ያልፋሉ። ይህ ወቅት "The 9-enders" ተብሎ ይጠራል።
እድሜ 29 (የወጣትነት ስንብት)፦ አንድ ሰው ወደ 30 ዓመት ሊገባ ሲል "በወጣትነቴ ማሳካት ያለብኝን አሳክቻለሁ? ህይወቴን በትክክል እየመራሁ ነው?" የሚሉ ጥያቄዎችን ይጠይቃል። በዚህ ወቅት ያለው ግንኙነት አሰልቺ መስሎ ከታየው፣ አዲስ ደስታን ፍለጋ ወደ ሌላ ግንኙነት የመሄድ እድሉ ይጨምራል።
እድሜ 39 (ከፍተኛው የክህደት ወቅት)፦
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት 39 ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛው የትዳር ክህደት የሚፈጸምበት እድሜ ነው። ይህ ወቅት "የመካከለኛ እድሜ ቀውስ" (Midlife Crisis) መጀመሪያ ተደርጎ ይወሰዳል። ሰዎች "ውበቴ እየቀነሰ ነው? አሁንም ተፈላጊ ነኝ?" የሚለውን ለማረጋገጥ አዳዲስ ግንኙነቶችን ይሞክራሉ።
እድሜ 49 (የህይወት ግምገማ)፦ ወደ 50 ዓመት ሊሸጋገሩ ጥቂት ሲቀራቸው፣ ሰዎች የደረሱበትን ስኬትና ያጡትን ነገር ያመዛዝናሉ። "በህይወቴ የፈለኩትን አላገኘሁም" የሚል ስሜት ካላቸው፣ ያንን ክፍተት በሌላ ሰው ለመሙላት ይሞክራሉ።
2. በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለው ልዩነት
ክህደት በሁለቱም ጾታዎች ዘንድ ቢከሰትም፣ ምክንያቶቹና የሚከሰቱባቸው ወቅቶች ግን ይለያያሉ።
የሴቶች ሁኔታ
ሴቶች አብዛኛውን ጊዜ በ30ዎቹ መጀመሪያ ላይ ለክህደት የመጋለጥ እድላቸው ይጨምራል። ይህ የሚሆነው ከወሊድ በኋላ ወይም የትዳር ህይወት "መለመድ" (Routine) ሲጀምር ነው። ሴቶች በግንኙነት ውስጥ ስሜታዊ ትኩረት ካጡ፣ ያንን ስሜት የሚሰጣቸውን ሌላ ሰው የመፈለግ ዝንባሌ አላቸው። በ50ዎቹ እና 60ዎቹ እድሜያቸው ደግሞ ልጆች አድገው ቤት ሲለቁ (Empty Nest Syndrome) የሚፈጠረውን ባዶነት ለመሙላት ለክህደት ሊጋለጡ ይችላሉ።
የወንዶች ሁኔታ
ወንዶች በበኩላቸው በ40ዎቹ መገባደጃ እና በ50ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከፍተኛ ተጋላጭነት ይታይባቸዋል። የወንዶች ክህደት አብዛኛውን ጊዜ ከ"ወንድነት ብቃት" እና "ተፈላጊነት" ጋር የተያያዘ ነው። እድሜ እየገፋ ሲሄድ የሚመጣውን የተፈጥሮ ለውጥ ለመቀበል ከመቸገር የተነሳ፣ ወጣት ከሆኑ ሴቶች ጋር ግንኙነት በመመሥረት እንደገና ወጣት እንደሆኑ ለማሰብ ይሞክራሉ።
3. ለክህደት የሚገፋፉ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ምክንያቶች
ጥናቱ እንደሚያሳየው እድሜ ብቻውን ምክንያት አይደለም፤ ይልቁንም ከእድሜ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ሁኔታዎች ናቸው፦
የመሰላቸት ስሜት (Boredom)፦ የረጅም ጊዜ ግንኙነቶች ውስጥ የሚፈጠር መደጋገም እና አዳዲስ ነገሮች ማጣት ሰዎችን ለሌላ አማራጭ ያጋልጣል።
ስሜታዊ ርቀት (Emotional Disconnect)፦ በትዳር አጋሮች መካከል ግልጽ ውይይት ሲጠፋና አንዱ ሌላውን እንደማይረዳው ሲሰማው ክፍተት ይፈጠራል።
የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ፦ እንደ አሽሊ ማዲሰን ያሉ ድረ-ገጾች እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ክህደትን ቀላልና ሚስጥራዊ እንዲሆን አድርገውታል።
የስራ አካባቢ ተጋላጭነት፦ ብዙ ሰዓት በስራ ቦታ ማሳለፍና ከስራ ባልደረቦች ጋር የሚፈጠር ጥልቅ መቀራረብ ለተሳሳተ ግንኙነት በር ይከፍታል።
4. ግንኙነትን እንዴት መጠበቅ ይቻላል? (የባለሙያዎች ምክር)
ምንም እንኳን እድሜያችን "9" ላይ ቢደርስም፣ የግድ እንከዳለን ማለት አይደለም። ግንኙነትን በጤናማ መንገድ ለመቀጠል የሚከተሉት ነጥቦች ወሳኝ ናቸው፦
ኢንቨስት ማድረግ፦ ግንኙነት ልክ እንደ ተክል ነው፤ ካልተኮተኮተ ይደርቃል። አዳዲስ ትዝታዎችን መፍጠር፣ አብሮ መዝናናት እና የፍቅር ህይወትን ማደስ ያስፈልጋል።
ግልጽ ውይይት፦ በውስጣችን የሚፈጠሩትን ፍራቻዎች፣ የፍላጎት መቀነስ ወይም የመሰላቸት ስሜቶች ለትዳር አጋራችን በግልጽ መንገር። "ክህደት የሚጀምረው ሚስጥር ሲኖር ነው" ይላሉ ባለሙያዎች።
ራስን ማሳደግ፦ በግንኙነት ውስጥ ራስን መርሳት ለድብርትና ለሌላ ፍላጎት ይዳርጋል። የራስ ስራ፣ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያና ጓደኞች መኖር ግንኙነቱ ጤናማ እንዲሆን ይረዳል።
አድናቆት መግለጽ፦ የትዳር አጋርን ማድነቅና አሁንም ተፈላጊ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ማድረግ ለሌላ ፍለጋ እንዳይሄዱ ትልቅ መከላከያ ነው።
ማጠቃለያ
በ39 ወይም በ49 ዓመት እድሜ ላይ መሆን የግድ ክህደትን አያመጣም። ይሁን እንጂ በእነዚህ የእድሜ ክልሎች ውስጥ የሚፈጠሩትን ስነ-ልቦናዊ ጫናዎች ቀድሞ መረዳት ለግንኙነቱ ጥንቃቄ ለማድረግ ይረዳል። ዋናው ቁልፍ ያለው እርስ በእርስ በመደማመጥ እና ሁልጊዜም ግንኙነቱን አዲስ ለማድረግ በሚደረግ ጥረት ላይ ነው።

10 months ago
ማስታወቂያ አይነቱን ቀይሮ መጥቷል መጥቷል
#ethiopia | ቴክኖ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን በዓይነቱ ለየት ያለ ማስታወቂያ በታህሳስ 1 ዕትም ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ይፋ አድርጓል ።
ይኽ ማስታወቂያ በRed Communication እና HahuCloud አማካኝነት የተሰራ ሲሆን ። ማስታወቂያን በዘመናዊ መልክ ከ ጋዜጣ ጋር አጣምሮ በመምጣት ቀዳሚ ሁኗል ።
QR ኮዱን ስካን በማድረግ የሚመጣውን ተንቀሳቃሽ ምስል እንድታዩ ተጋብዛችኋል ።
10 months ago
ማስታወቂያ አይነቱን ቀይሮ መጥቷል መጥቷል ።
ቴክኖ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን በዓይነቱ ለየት ያለ ማስታወቂያ በታህሳስ 1 ዕትም ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ይፋ አድርጓል ።
ይኽ ማስታወቂያ በRed Communication እና HahuCloud አማካኝነት የተሰራ ሲሆን ። ማስታወቂያን በዘመናዊ መልክ ከ ጋዜጣ ጋር አጣምሮ በመምጣት ቀዳሚ ሁኗል ።
QR ኮዱን ስካን በማድረግ የሚመጣውን ተንቀሳቃሽ ምስል እንድታዩ ተጋብዛችኋል ።
Sponsored by
Surafel
10 months ago
ኢትዮጵያ እንኳን ደስ ያለሽ
#ethiopia | የኢትዮጵያ የኑክሌር መርሐ-ግብር ሂደት በይፋ መጀመሩን ተከትሎ ዓለምአቀፉ ተቋም ያስተላለፈው መልዕክት
| IAEA | Ethiopia | Nuclear |
1 year ago
#ግዕዝ እንደ ቋንቋ ትምህርት ትምህርት የሚሰጥባቸው የዓለማችን ቦታዎች:–
North America
============
1. Harvard University (USA):
2. Princeton University (USA):
3. University of Toronto (Canada)
4. University of Pennsylvania (USA)
5. Catholic University of America (USA)
6. UCLA (University of California, Los Angeles)
Europe
======
1. Hamburg University (Germany)
2. University of Oxford (UK)
3. University of Cambridge (UK)
4. University of Leiden (Netherlands)
5. Sapienza University of Rome (Italy)
6. University of Paris (France)
7. University of Warsaw (Poland)

Comments