የ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጨዋታ ድልድል ይፋ ተደረገ
#ethiopia | የ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር የጨዋታ ድልድል በዛሬው ዕለት በሞናኮ ይፋ ሆኗል። እንደ መርሃ ግብሩ ገለጻ ውድድሩ በጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም የሚጀመር ይሆናል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ከ2016 ዓ.ም የውድድር ዘመን ጀምሮ የቀደመውን የምድብ ድልድል አሰራር በመቀየር 36 ክለቦች በ 4 ቋቶች ተከፋፍለው የሚወዳደሩበትን የሊግ ደረጃ አዲስ ፎርማት መተግበሩ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት በዘመነኛው ውድድር የተካተቱት 36 ክለቦች በእያንዳንዱ ቋት 9 ቡድኖች እንዲይዙ ተደርገው ተከፋፍለዋል።
በቋት አንድ ውስጥ የወቅቱ ሻምፒዮን ፒኤስጂን ጨምሮ ሪያል ማድሪድ፣ ባየር ሙኒክ፣ ማንችስተር ሲቲ፣ አርሰናል፣ ባርሴሎና፣ ኢንተር ሚላን፣ ሊቨርፑል እና አትሌቲኮ ማድሪድ ተካተዋል።
በቋት ሁለት ደግሞ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ፣ ሮማ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን፣ አስቶንቪላ፣ ፖርቶ፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ክለብ ብሩዥ፣ ሪያል ቤቲስ እና ፒኤስቪ አይንድሆቨን ይገኛሉ።
በቋት ሶስት ላይፕዚግ፣ ቪያሪያል፣ ናፖሊ፣ ሊል፣ ፌይኖርድ ሮተርዳም፣ ቦዶ ግሊምት፣ ፊነርባቼ፣ ሻክታር ዶኔስክ እና ጋላታሳራይ ተደልድለዋል።
በቋት አራት ስቱትጋርት፣ ሌንስ፣ ስላቪያ ፕራግ፣ ስሎቫን ብራቲስላቫ፣ ኤኢኬ አቴንስ፣ ላስክ፣ ኮሞ፣ ቫይኪንግ እና ሳባህ ተመድበዋል።
በአዲሱ አሰራር መሰረት አንድ ክለብ ከራሱ ቋት ከተካተቱ ሁለት ቡድኖች እንዲሁም ከቀሪዎቹ ሶስት ቋቶች ከእያንዳንዳቸው ከሁለት ክለቦች ጋር የሚጫወት በመሆኑ በጠቅላላው 8 ጨዋታዎችን ያደርጋል።
በሊግ ደረጃ ከሚወዳደሩት 36 ክለቦች መካከል በ 8 ጨዋታዎች ከፍተኛ ነጥብ የሚያስመዘግቡ የመጀመሪያዎቹ 8 ቡድኖች በቀጥታ ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ ዙር ያልፋሉ።
ከ 9ኛ እስከ 24ኛ ደረጃ የሚይዙት ደግሞ በሁለት ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች ተወዳድረው ቀሪዎቹን 8 የጥሎ ማለፍ ቦታዎች ይይዛሉ። ከጥሎ ማለፉ ዙር ጀምሮ ያለው የጨዋታ ፎርማት ከዚህ ቀደም ይተገበር ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ነው።
በመጀመሪያው ሳምንት ከሚጠበቁ Select Item ጨዋታዎች መካከል ሪያል ማድሪድ ከአርሰናል፣ ማንቸስተር ሲቲ ከባርሴሎና፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ከባየር ሙኒክ፣ ባርሴሎና ከፒኤስጂ እና ሊቨርፑል ከአትሌቲኮ ማድሪድ የሚያደርጓቸው ተጠቃሽ ናቸው።
የጣሊያኑ ኮሞ እና የአዘርባጃኑ ሳባህ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊጉ የሚሳተፉ ይሆናል።
#championsleague #ucl #uefa #football #sports #soccer #europe #realmadrid #barcelona #manchesterunited #arsenal #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago