አርሰናል ከ20 ዓመታት በኋላ ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ደረሰ
#ethiopia | መድፈኞቹ በታሪካዊ ጉዟቸው ታላቁን የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ መድረክ ዳግም ተቀላቅለዋል።
በሰሜን ለንደኑ ክለብ ቤት ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ አዲስ ታሪክ ተፅፏል።
አርሰናል በአሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ መሪነት በደርሶ መልስ ጨዋታዎች የተሻለ ብቃት በማሳየት ለአውሮፓ የክብር መድረክ ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል።
በኤምሬትስ ስታዲየም በተደረገው ወሳኝ ጨዋታ ቡካዮ ሳካ ያስቆጠራት ብቸኛ ጎል ለንደነኞቹን ወደ ቡዳፔስቱ የፍፃሜ ጨዋታ የምታሸጋግር የድል ትኬት ሆናለች።
መድፈኞቹ በዘንድሮው የውድድር ዘመን እስካሁን አንድም ጨዋታ ሳይሸነፉ ለፍፃሜ መድረሳቸው ስኬቱን ልዩ ያደርገዋል።
እንደ ቪክቶር ዮኬሬስ እና ዴክላን ራይስ ያሉ ተጫዋቾች በሜዳው ላይ የነበራቸው አስደናቂ ትግልና ብቃት ለክለቡ ስኬት ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
የአርሰናል የኋላ ክፍል እንደ ብረት የጠነከረ መሆኑን ያስመሰከረበት ይህ ጨዋታ የአትሌቲኮ ማድሪድን የአጥቂ መስመር ክፉኛ ፈትኖታል።
አንቶኒዮ ግሪዝማን እና ዩሊያን አልቫሬዝ የመድፈኞቹን የመከላከል ግድግዳ ሰብረው መግባት ሳይችሉ ቀርተዋል።
ይህም አርሰናል በ2006 ዓመተ ምህረት ከአርሴን ቬንገር ጋር የደረሰበትን የፍፃሜ ታሪክ በአርቴታ ዘመን እንዲደግም አስችሎታል።
አሁን ላይ መድፈኞቹ ሁለት ታላላቅ ዋንጫዎችን የማንሳት ህልማቸው ከጫፍ ደርሷል።
በሊጉም ሆነ በአውሮፓ መድረክ ውጤታማ የሆነው አርሰናል የረዥም ጊዜ የደጋፊዎቹን የዋንጫ ጥም ለመቁረጥ ተቃርቧል።
#arsenal #championsleague #football #ucl #final #sports #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago