6 months ago
የአሜሪካ ኤንባሲ ፕ/ር ኃይሌ ገሪማን አደነቀ
#ethiopia | ታዋቂውና ዝነኛው ኢትዮ-አሜሪካዊ የፊልም ባለሙያ ኃይሌ ገሪማ ለዓለም የሲኒማ ጥበብ ላበረከቱት ከፍተኛና ተፅዕኖ ፈጣሪ አስተዋፅኦ፣ በ76ኛው የበርሊን ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል (Berlinale) ላይ የተከበረውን "የበርሊን ካሜራ" (Berlinale Camera) ሽልማት ተረክበዋል።
ኃይሌ ገሪማ በፊልም ጥበብ ጉዞው በቺካጎ የቲያትር ጥበብን በማጥናት የጀመሩ ሲሆን፣ በኋላም በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ (UCLA) በፊልም ጥበብ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝቷል።
በዘርፉ በነበራቸው ጠንካራ ተሳትፎም "የሎስ አንጀለስ የጥቁር ፊልም ባለሙያዎች ትምህርት ቤት " (L.A. School of Black Filmmakers) ፈር ቀዳጅና ግንባር ቀደም አባል ለመሆን በቅተዋል።
ይህ ሽልማት ለታሪክ ዘጋቢነታቸው፣ ለኪነ-ጥበብ ጥራቱና ለብዙዎች አርአያ ለሆነው የረጅም ዘመን የፊልም ሥራዎቿቸው የተሰጠ ታላቅ እውቅና ነው። በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲም ለባለሙያው ያለውን አድናቆት ገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ
#getutemesgen #getu #hailegerima #berlinale76 #ethiopiancinema #filmmaking #legend #berlinfilmfestival #ethiopia #usainethiopia #ኃይሌገሪማ #በርሊን #ሲኒማ

7 months ago
መሪር ሐዘን በኢትዮጵያ ሲኒማ
የ"አሸንጌ" ፊልም ዳይሬክተር ጳውሎስ ረጋሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
#ethiopia | የኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ አንዱን ድንቅ ባለሙያውን አጥቷል።
በፊልም ዳይሬክተርነቱ፣ በሙዚቃ ቀማሪነቱና በፖስት ፕሮዳክሽን (Post-production) ሊቅነቱ የሚታወቀው ጳውሎስ ረጋሳ ዛሬ፣ ቅዳሜ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ጳውሎስ በተለይ "አሸንጌ" የተሰኘውን ድንቅ ፊልም ለታዳሚ በማቅረብ የሚታወስ ባለሙያ ነው።
ለብዙ የዘርፉ ባለሙያዎች የሲኒማ ጥበብ መምህር፣ በተግሳጽና በምክር ያሳደገ ታላቅ ወንድም እንዲሁም ነገሩ ሁሉ ፊት ለፊት የሆነ እውነተኛ ባለሙያ ነበር።
ከዳይሬክተርነት ባለፈ በሙዚቃ ቅንብርና በፊልም ቴክኒክ ሥራዎች ላይ የነበረው ተሰጥኦ ለኢትዮጵያ ሲኒማ ዕድገት ትልቅ አሻራ ጥሎ አልፏል።
ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹና ለመላው የኪነጥበብ ቤተሰብ መጽናናትን እንመኛለን።
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ፦
መቼ እንደሚከናወን አስከሬኑ ከሕንድ ሲመጣ የምናሳውቅ ይሆናል።
የጥበብ ሰው ጳውሎስ ረጋሳ ነፍስ ይማር!
#getu #ethiopia #cinema #filmmaking #ashengefilm #paulosregassa #art #tribute #ኢትዮጵያ #ሲኒማ #ጳውሎስረጋሳ #አሸንጌ #ሐዘን #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments