4 hours ago
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ800 በላይ አዳዲስ የቱሪስት መስህቦች ተለይተዋል - የቱሪዝም ሚኒስትር
#ethiopia | በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ሩብ ዓመታት ኢትዮጵያ በቱሪዝም መስክ የላቀ ገጽታ የገነባችበት እና በርካታ ዓለም አቀፍ መድረኮችን በውጤታማነት ያስተናገደችበት ወቅት መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ገለጹ።
ሚኒስትሯ ይህንን ያመለከቱት ተቋማቸው በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ለመገምገም እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ለመወያየት ዛሬ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከሠራተኞች ጋር ባደረጉት ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ነው።
በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት በዓመቱ አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ መጽደቁ ለዘርፉ ዕድገት ትልቅ መሠረት ጥሏል።
ከግሉ ዘርፍ እና ከክልል መስተዳድሮች ጋር ጠንካራ የሥራ ግንኙነት እንደነበር የገለጹት ሚኒስትሯ፣ አገሪቱን የስብሰባ፣ የጉዞ እና የዝግጅቶች ወይም የማክ ቱሪዝም መዳረሻ አድርጎ ለማስተዋወቅ ሰፊ ጥረት መደረጉንና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ800 በላይ አዳዲስ የቱሪስት መስህቦች መለየታቸውን አብራርተዋል።
በቀጣዩ አንድ ወር ውስጥ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በውጤታማነት ማጠናቀቅ እንደሚገባ የጠቆሙት ሰላማዊት ካሳ፣ የፈጠራ አቀራረብ ያላቸውን የፕሮሞሽን ሥራዎች ማጠናከር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማሳደግ እና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍን ማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሠራበት አስገንዝበዋል።
የቱሪዝም መዳረሻዎችና መሠረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው፣ ከተለመዱት የቱሪዝም ዓይነቶች በተጨማሪ አዳዲስ አማራጮችን ለይቶ በፖሊሲ ደረጃ ትኩረት እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉ የዓመቱ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል።
የማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እንደገና አበበ በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ መልካም ተሞክሮዎችን በማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በማረም የዘርፉን ተወዳዳሪነት ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
#tourismethiopia #ethiopiatourism #micetourism #ethiopianheritage #tourismpolicy #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments