Logo
SeledaPost
ድህነት የአእምሮን መጠን ያሳንሳል፤ እርጅናንም ያፋጥናል ተባለ

​የረዥም ጊዜ ሳይንሳዊ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ዝቅተኛ ገቢና ስር የሰደደ የገንዘብ እጥረት የአእምሮን መጠን ለማሳነስና የአስተሳሰብ ብቃትን ለመቀነስ ምክንያት ይሆናሉ።

​በለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ (UCL) ተመራማሪዎች የተካሄደ አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው፣ በወጣትነት እና በጎልማሳነት እድሜ የሚከሰት ዘላቂ የገንዘብ እጥረት ወይም ዝቅተኛ ገቢ በዕድሜ መግፋት ወቅት የአእምሮ ህመም እና የማስታወስ ችሎታ መቀነስ አደጋን ያፋጥናል።

​በኢኖቬሽን ኢን ኤጅንግ ጆርናል ላይ የታተመው ይህ ጥናት በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ 2,759 ሰዎችን መረጃ መሠረት ያደረገ ነው።

ተመራማሪዎቹ የረጅም ጊዜ የገንዘብ ችግር ያጋጠማቸው ሰዎች በ53 ዓመታቸው ባደረጉት የአእምሮ ብቃት ምርመራ ዝቅተኛ ውጤት ማምጣታቸውን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም ከ69 እስከ 71 ባለው እድሜ ውስጥ በኤምአርአይ (MRI) ስካን ከተመረመሩት መካከል፣ ለረጅም ጊዜ ዝቅተኛ ገቢ የነበራቸው ሰዎች ከፍተኛ የአእምሮ መንጠፋጠፍ  ታይቶባቸዋል።

​ችግሩ በተለይም በወንዶች፣ በልጅነታቸው ችግር ውስጥ ባደጉ እና በአልዛይመር በሽታ የመያዝ አደጋን በሚጨምረው 'APOE-ε4' ጄን ተሸካሚዎች ላይ የጎላ ሆኖ ተገኝቷል።

በገንዘብ ጭንቀት የሚፈጠር የረጅም ጊዜ ውጥረት (chronic stress) ለአእምሮ እርጅና መፋጠን ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።

​በጥናቱ የተሳተፉ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች፣ ምንም እንኳ የትምህርት ደረጃቸውና የአእምሮ ብልህነት (IQ) ምጣኔያቸው ግምት ውስጥ ቢገባም፣ በትውስታና መረጃ የመተንተን ፍጥነት ፈተናዎች ላይ ዝቅተኛ ውጤት አስመዝግበዋል።

​የኤም.አር.አይ ምስል ምርመራዎች ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአእምሮ ሴሎች መኮማተር (Brain Atrophy) ታይቶባቸዋል።

​ስለ ገንዘብ ሁልጊዜ መጨነቅ በሰውነት ውስጥ እብጠትን (Inflammation) በመጨመር የሰውነትን የእርጅና ሂደት እንደሚያፋጥነው በጥናቱ ተገልፇል።

Seledadotio
Seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.