ወደ ትምህርት ገበታ ይመለሳሉ!!
📌በአማራ እና ትግራይ ክልሎች ለሚገኙ ተማሪዎች የ9 ሚሊዮን 980 ሺህ ዶላር ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ
#ethiopia | በጦርነት እና ግጭት ምክንያት ትምህርት ቤቶች በፈረሱባቸው የአማራ እና ትግራይ ክልሎች፣ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ ያለመ ግዙፍ ፕሮጀክት በይፋ ተጀምሯል።
"ፕሌይፉል ኢዱኬሽን ፓዝዌይስ ኢን ኢትዮጵያ" (PEPE) የተሰኘው ይህ ፕሮጀክት 9 ሚሊዮን 980 ሺህ ዶላር በጀት የተያዘለት ሲሆን፣ በኢንተርናሽናል ሬስኪው ኮሚቴ (IRC) መሪነት ከሉሚኖስ ፈንድ እና ከኢማኑኤል ደቨሎፕመንት አሶሴሽን (EDA) ጋር በመተባበር የሚተገበር ነው።
የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ትኩረቶች፡
* ተደራሽነት፡ በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በሁለቱ ክልሎች ለችግር የተጋለጡ 150,620 ተማሪዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ ለማድረግ አልሟል።
* የትኩረት አካባቢዎች፡ የመፈናቀል መጠን በበዛባቸው እና ትምህርት ቤቶች በብዛት በፈረሱባቸው ወረዳዎች ላይ ልዩ ትኩረት ያደርጋል።
ከባለድርሻ አካላት የተሰጡ አስተያየቶች፡
* አማራ ክልል፡ የትምህርት ቢሮ ኃላፊው አቶ ጥላሁን ወርቅነህ፤ በክልሉ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ይህ ፕሮጀክት ተማሪዎችን ለመመለስ ለሚደረገው ጥረት አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል።
* ትግራይ ክልል፡ የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኢስማኤል አብዱራህማን በበኩላቸው፤ በሰሜኑ ጦርነት የወደሙና እስካሁን አገልግሎት መስጠት ያልጀመሩ ትምህርት ቤቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ፕሮጀክቱ እንደ መልካም እድል እንደሚቆጠር ተናግረዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ ዶ/ር ዮሴፍ አበራ፣ ለፕሮጀክቱ ስኬት ሚኒስቴሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ያረጋገጡ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በጦርነት የጎዳውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማገዝ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል ብለዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #education #amhara #tigray #irc #pepe #students #humanitarianaid #eda #luminosfund

8 months ago